Quantcast
Channel: Kalkidan Amharic – Kal Tube
Viewing all 212 articles
Browse latest View live
↧

ሰማያዊ እና ኦፌኮ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

≫ Next: (ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ)የሕዝቦችን ሕገመንግሥታዊ መብቶች በመጣስ የሚከናወኑ የኢህአዴግ ሕገወጥ እርምጃዎች ሕዝባችንን ለከፍተኛ ችግር፣ ሀገራችንንም ለአሳሳቢ ሁኔታ እየዳረጉ ስለሆነ በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል!!
$
0
0

lkjh
ሰማያዊ ፓርቲና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች ዛሬ ታህሳስ 5/2008 ዓ.ም ባደረጉት ስብሰባ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ በመስጠት፣ መንግስት የሚፈፅመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመከታተል ለማጋለጥ እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባዎችን በጋራ ለማካሄድ እንደተስማሙ ምክትል ሊቀመንበሩ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ከመድረክ ጋር እንዲሰራ በወሰነው መሰረት ዛሬ ከኦፌኮ ጋር በተደረገው ውይይት በሰማያዊ ፓርቲ በኩል ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ፣ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ጋሻው መርሻና የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ መሃመድ ተገኝተዋል፡፡ በኦፌኮ በኩልም ሊቀመንበሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ሙላቱ ገመቹ እና ፀኃፊው አቶ በቀለ ነገአ ተገኝተዋል፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች በቅርቡ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ እንደሚሰጡና የጋራ ግብረ ኃይል አቋቁመው የፖለቲካ ትግል እንደሚያደርጉም አቶ ነገሰ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

↧

(ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ)የሕዝቦችን ሕገመንግሥታዊ መብቶች በመጣስ የሚከናወኑ የኢህአዴግ ሕገወጥ እርምጃዎች ሕዝባችንን ለከፍተኛ ችግር፣ ሀገራችንንም ለአሳሳቢ ሁኔታ እየዳረጉ ስለሆነ በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል!!

$
0
0

The spark that lit the flame of Oromo students protest 10 days ago!(ALEMNEH WASSE NEWS)
የኢህአዴግ አገዛዝ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በተግባር ሊያውላቸው ያልተዘጋጀባቸውን ድንጋጌዎች ከሀገሪቱ ሕገመንግሥት ጀምሮ ሲያውጅ ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ያወጃቸውን ድንጋጌዎች በማፍረስና በተግባር እንዳይውሉ በማድረግ የዜጎችንና የሕዝቡን መብቶች የሚጥሱ ተግባራትን እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ይህ ሁኔታ ከአንድ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት በጉልበትና በማጭበርበር ቀምቶ መንግሥት ነኝ ከሚል አምባገነን ቡድን የሚጠበቅ ቢሆንም፣ መዘዙ የሀገራችንን ደህንነትና የሕዝቦቻችንን እኩልነትና አንድነት ለማይሹ ኃይሎች አፍራሽ እንቅስቃሴ ቀዳዳ እየሰጣቸው መሆኑ መድረክን በእጅጉ ያሳስበዋል፡፡
ከእነዚህ ሕገመንገሥታዊ ድንጋጌዎች ጥሰት መነሻነት ከተፈጠሩት ውስብስብ ችግሮች ውስጥ አንዱ የአዲስ አበባ ከተማንና የኦሮሚያን ክልላዊ መንግሥት ግንኙነት በሚመለከት፣ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 5 “የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሐል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል” የሚለውን በማንአለብኝነት ከመጣስ የመነጨ ችግር ነው፡፡ በዚህ ረገድ የኢህአዴግ ሥርዓተ-አልበኝነት መገለጫ ሆኖ የቆየው በሕገመንግሥቱ የሰፈረው ዝርዝር የአፈጻጸም ሕግ ሳይወጣ ከ21 ዓመታት በላይ መቆየቱ ተጠቃሽ ነው፡፡ እንዲሁም በአዲስ አበባ አከበቢ የሚሠሩ የልማት ሥራዎችንም በሚመለከት ሕዝቡን በአግባቡ ሳያወያዩ ጥቂት እበላ ባይ ካድሬዎችን በአስፈጻሚነት በማሰማራት የእርሻ መሬታቸውን እየነጠቁ ወደ አዲስ አበባ ከተማ የማካለል እንቅስቃሴ ላይ መሠማራቱ በተከታታይ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችንና ውዝግቦችን ከማስነሳቱም በላይ ለብዙ ዜጎች ሕይወት በኢህአዴግ መንግሥት አርመኔአዊ እርምጃ መቀጠፍ ምክንያት ሆኖአል፡፡
ባለፉት ሁለት ሳምንታት የአዲስ አበባ ከተማን ከሕግ አግባብ ውጪ ማማስፋት ጋር በተያያዘ በሕዝቡ ዘንድ ካደረው ስጋት በመነሳት የተቀሰቀሰውን ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞን በኃይል ለማስቆም የኢህአዴግ መንግሥት በወሰደው እርምጃም በርካታ ተማሪዎችና ሌሎች ዜጎች መገደላቸውን መድረክ በእጀጉ ይኮንነዋል፡፡ የተገደሉት ዜጎችም 1ኛ፡- ተማሪ ካረሳ ጫላ ምዕራብ ወለጋ ጉልሶ ወረዳ፣ 2ኛ፡- ተማሪ ጉቱ አበራ ምዕራብ ወለጋ ጉልሶ ወረዳ፣ 3ኛ፡- ተማሪ ሚፍታህ ጁንዲ በምዕራብ ሐረርጌ በደኖ ወረዳ፣ 4ኛ፡- ተማሪ ገዘሃኝ ኦልሂቃ የሀራማያ ዩንቨርሲቲ ተማሪ፣ 5ኛ፡- ተማሪ ደጀኔ ሰርቤሳ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ቶሌ ወረዳ፣ 6ኛ፡- ተማሪ በቀለ ሰቦቃ አዳበርጋ ወረዳ ሙገር፣ 7ኛ፡- ተማሪ በቀለ ሰይፉ አዳበርጋ ወረዳ ሙገር፣ 8ኛ፡- ተማሪ ሙራዲ አብዱ የሀራማያ 2ኛ ደረጃ ተማሪ፣ 9ኛ፡- አቶ ጫላ ተሾሜ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ባቢቻ ከተማ፣ 10ኛ፡- ተማሪ አብደታ ባይሳ ምዕራብ ሸዋ ጫለያ ወረዳ ባብቻ ከተማ፣ 11ኛ፡- ተማሪ ዱሌ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣ 12ኛ፡- አቶ ታመነ ጸጋዬ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣ 13ኛ፡-ተማሪ ደረጀ ጋዲሰ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣ 14ኛ፡- ተማሪ ፈቃዱ ግርማ ምዕራብ ሸዋ ጨለያ ወረዳ ጌዶ ከተማ፣ 15ኛ፡-ተማሪ ሉጫ ገማቹ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ፣ 16ኛ ተማሪ አያና ባንቲ ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ፣ 17ኛ፡- ተማሪ አላዛር ምዕራብ ወለጋ ኢናንጎ ወረዳ ነዋሪ 18ኛ አቶ ኤብሰ ቱጆ ሆሮ ጉዱሩ ፍንጫ፣ 19ኛ፡- አቶ ደበላ ጣፋ ጫንጮ ላይ ተገድሎ ተጥሎ የተገኘ፣ 20ኛ ወ/ሮ ዲሶ ሚሊኬሳ ሕልፈታ ወረዳ 21ኛ፡- አቶ አበበ ቡሎ ወሊሶ ከተማ፣ 22ኛ፡- አቶ ታዴ ሰፈራ አመያ ከተማ፣ 23ኛ፡- አቶ ሌንጮ ሁንዴራ ወሊሶ ከተማ፣ 24ኛ፡- አቶ ሰለሞን ሞገስ አማያ ከተማ፣25ኛ፡- አቶ ታዴ አንዲሳ ወንጪ ከተማ፣ 26ኛ፡- አቶ እናውጋው ኃይሉ ግንደበረት ወረዳ፣ 27ኛ፡- ተማሪ አብደታ ለታ ግንደበረት ወረዳ 28ኛ፡-አቶ ባይኢሳ ገደፋ አቡና ግንደበረት ወረዳ 29ኛ፡- ተማሪ አስቻለው ወርቁ ግንጪ ወረዳ፣ 30ኛ፡- ተማሪ ሰይፉ ቱራ ግንጪ ወረዳ፣ 31ኛ፡- ተማሪ አሸናፊ ግንጪ ወረዳ፣ 32ኛ፡- አቶ ገላና ባቃና ጪቱ ከተማ ነዋሪ የነበሩ ስለመሆናቸው የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ከዚህም ሌላ ከመቶ ባለይ ዜጎች ቆስለዋል፣ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእስራት ተዳርገዋል፡፡ ሰላማዊና ሕጋዊ ተቃውሞን ለማፈን በመንግሥት እየተወሰደ ያለው የኃይል እርምጃ እስከ አሁንም እንደቀጠለ በመሆኑ፣ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት መድረክን በእጅጉ እያሳሰበው ይገኛል፡፡ እንደዚሁም በቅርቡ በጎንደር ከተማ በሚገኘው ወሕኒ ቤት በእስረኞች ላይ የተፈጸመው ግዲያ መድረክን አሳስቦታል፡፡
ከዚህም ሌላ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 4 ላይ “የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኘትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው” የሚለውንና በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ለግጦሽም ሆነ ለእርሻ የሚጠቀሙበት መሬት በነፃ የማግኘት፣ የመጠቀምና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት አላቸው” ተብሎ የተደነገገውን በመተላለፍ፣ በከተሞችና በእንቨስትመንት ማስፋፋት ስም የአርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን መሬት እየቀሙ በማፈናቀል ለከፍተኛ የኑሮ ችግሮች እየዳረጉዋቸው ይገኛሉ፡፡ መድረክ ይህንን የኢህአዴግ መንግሥት የመሬት ቅሚያ እርምጃ ደጋግሞ ሲያጋልጥ የቆየ ሲሆን በእርምጃው ምክንያት በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለው የጉዳት መጠን ከጊዜ ወደጊዜ በአሁኑ ወቅት እየሰፋ ስለመገኘቱ መረጃዎች ያሳያሉ፡፤
በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አገዛዙ በርካታ የሀገሪቱን ከተሞች ለማስፋፋትና መሬቱንም በፌዴራል መንግሥት ቁጥጥር ሥር በመሬት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ለማስተዳደር፣ የማስተር ፕላንና የሪፎርም ከተሞች ብሎ በመሰየም፣ በየከተሞቹ አከባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች ይዞታዎች አርሶ አደሩን ሳያማክሩና ተገቢውን ካሳ ሳይከፍሉ ወደ ከተማ ለማካለል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ነዋሪውን ሕዝብ ለከፍተኛ ስጋትና ጭንቀት እየዳረጋቸው ይገኛል፡፡ ስለሆነም የኢህአዴግ አገዛዝ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በማንአለብኝነት አምባገነናዊ ስሜት እየተመራ ፌዴራላዊ ሥርዓቱንና የዜጎችን ሕገመንግሥታዊ መብቶች በመጣስ እየፈጸመ ከሚገኘው ሕገወጥ ተግባር እንዲቆጠብ እንጠይቃለን፡፡ በተለይም፡-
1ኛ፡- ከአዲስ አበባ ከተማና ከኦሮሚያ ክልል ግንኙነት ጋር በተያያዘ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮች ሕገመንግሥቱን ተግባራዊ ባለማድረግ ምክንያት እየተከሰቱ ስለሆኑ የሕገመንግሥቱን አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ 5 ተግባራዊ የሚያድርግ ሕግ በአስቸኳይ ወጥቶ ተግባራዊ እንዲደረግና ለችግሩ ዘላቂ እልባት እንዲሰጥ፣ ለከተማዋ ልማት የሚወጡ እቅዶችም የሕገመንገሥቱን ድንጋጌ የሚያከብሩ ሆነው የአከባቢውን አርሶ አደሮች መብትና ጥቅም በሚገባ የሚያስጠብቅ እንዲሆኑ፣
2ኛ፡- በቅርቡም መንግሥት ሕገወጥ እርምጃ ለመውሰድ በተንቀሳቀሰበት ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችን ባደረጉና በሌሎችም ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው የኃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም፣
3ኛ፡- እስከአሁን የዜጎችን ሕይወት በሕገወጥነት ያጠፉና ሌሎች ጉዳቶችን ያደረሱ የመንግሥት አካላትም ለሕግ እንዲቀርቡና ለሟቾቹ ቤተሰቦችም ተገቢው ካሳ እነዲከፈላቸው እንዲደረግ፣
4ኛ፡- በመላ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች ሕገመንግሥቱ ያረጋገጠላቸው ከመሬታቸው የያለመፈናቀል መብታቸው ተከብሮ፣ በየአከባቢያቸው በልማት ሥራዎች ሰበብ ኑሮአቸው እየተናጋ ለችግር የሚዳረጉበት ሁኔታ በአስቸኳይ ተወግዶ፣ የሚከናወኑት የልማት ሥራዎችም ቢሆኑ የአከባቢውን ሕዝብ ይሁንታ ያገኘና መብታቸውን የጠበቀ እንዲሆን እንዲደረግ፤
5ኛ፡- በተለይም በአሁኑ ወቅት ከተሞችን በማስፋፋት ስም የአርሶ አደሩን መሬቶች ወደ ከተማ ለማካለልና በከፍተኛ ዋጋ በሊዝ ለመሸጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ፣ አርሶ አደሩን በስጋት ውስጥ እየከተተው ስለሚገኝ፣ ኑሮአቸውን ለማሻሻል የሚበቃ በቂ ካሳ ሳይከፈል ይዞታቸውን ለመንጠቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዲቆም እንዲደረግ፣
6ኛ፡- በቅርቡ በጎንደር ከተማ በሚገኘው ወሕኒ ቤት የተገደሉ በርካታ ዜጎች ጉዳይ በአስቸኳይ ተጣርቶ የሰላማዊ ዜጎችን ሕይወት ያጠፉና ጉዳት ያደረሱ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡና ለሟቾቹ ቤተሰቦችም ተገቢው ካሳ እንዲከፈላቸው እንዲደረግ አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡
በመጨረሻም መድረክ በንጽሐን ዜጎቻችን ላይ በኢህአዴግ መንግሥት የተወሰደውንና እየተወሰደ ያለውን ኢሰብአዊ ግዲያ በጥበቅ እያወገዘ ለሟቾቹ ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፡፡ መላው ሕዝባችንም በኢህአዴግ በጉልበትና በማጭበርበር በተካሄዱት ምርጫዎች የተቀማውን ሕገመንግሥታዊ መብቶቹን ለማስከበር ሰላማዊ ትግሉን እንዲያጠናክር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ጥሪ ያቀርባል፡፡
ድል ለሕዝባዊ ትግላችን !!
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ
ታህሳስ 5 ቀን 2008 ዓ ም
አዲስ አበባ

↧
↧

ማፈናቀል እንደገንዘብ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

≪ Previous: (ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ)የሕዝቦችን ሕገመንግሥታዊ መብቶች በመጣስ የሚከናወኑ የኢህአዴግ ሕገወጥ እርምጃዎች ሕዝባችንን ለከፍተኛ ችግር፣ ሀገራችንንም ለአሳሳቢ ሁኔታ እየዳረጉ ስለሆነ በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል!!
$
0
0

kalkidantube.jpg46
ከ1966 ዓ.ም. በፊት መሬት አገር ነበር፤ ከዚያ በኋላ እስከ1983 መሬት የጋራ ሀብት ሆነ፤ ከ183 ወዲህ መሬት ገንዘብ ሆነ፤ ጡንቻ ገንዘብ ሆነ፤ መሬት ጡንቻና ገንዘብ ሆነ፤ አገር የት ደረሰ?
በጡንቻ ሀብታም መሆን ይቻላል፤ በጡንቻ ገበያውን መቆጣጠር ይቻላል፤ በጡንቻ ሻጩን መቆጣጠር ይቻላል፤ በጡንቻ ገዢውን መቆጣጠር ይቻላል፤ ገበያውን፣ ገዢውንና ሻጩን መቆጣጠር ከተቻለ ዋጋውን መቆጣጠር ይቻላል፤ እዚህ ደረጃ ላይ ከተደረሰ ምሥጢሩ ግልጽ ይሆናል፤ ምሥጢሩ ምንድን ነው? ዋናው ነገር ጡንቻ ነው፤ ጡንቻ የሀብት ምንጭ ነው፡፡
ጤንቻ ካለ ተማሪ ቤት ወይም ሀኪም ቤት፣ ወይም አንድ መሥሪያ ቤት ለመሥራት በሚል ሰበብ አንድ መቶ ቤተሰቦችን ከኑሮአቸው ማፈናቀል ሕጋዊ ያሆናል፤ አንድ መቶ ቤተሰቦች ሰፍረውበት የነበረው በአማካይ በነፍስ ወከፍ 100 ሜ.ካ. መሬት ነው እንበል፤ አንድ መቶ ቤተሰቦችን በማፈናቀል የተገኘው መሬት 100×100=10,000 ሜ.ካ. ይሆናል፤ በሊዝ ገበያ ላይ 10,000 ሜ.ካ. መሬት እንደሚከተለው ካሬ ሜትሩ በ20,000 ብር ይቸበቸባል፤ 10,000×20,000=200,000,000 ብር! ሳይሠሩ፣ ሳይለፉ፣ ሰዎችን በጡንቻ ትእዛዝ በማፈናቀል ብቻ የሚገኝ የጡንቻ ትርፍ!
አንድ ሺህ ቤተሰቦችን ማፈናቀሉ የበለጠ ትርፍን ያስገኛል፤ — 1,000x100x20,000=2,000,000,000 ብር! ምን የመሰለ ዘመናዊ ሰማይ-ጠቀስ ሕንጻ ይሠራል! ገንዘብ ካነሰም ማፈናቀል ነው!

ታኅሣሥ 2008

↧

አገር ህዝብ እንጂ መንግስት አይደለም (የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዓለም ዓቀፍ ህብረት)

$
0
0

pow
የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት የተጫነበትን የጭቆና ቀንበር ሲታገልና እራሱን ነፃ እያወጣ የኖረ ህዝብ ነው ። በፊውዳሉ የዘውድ ስርዓትም ሆነ በማርክሲሳዊው ወታደራዊ አገዛዝ ለዴሞክራሲና ለህግ የበላይነት በብዙ ታግሏል ። የሚገጥሙትን የአስተዳደር በደሎች ጐዳና ላይ በመውጣት ብሶቱን ሲያሰማ የኖረ ቢሆንም እንደዚህ ዘመን ግን የመከላከያ ሰራዊቱ በአልታጠቀ ሰላማዊ ህዝብ ላይ አልሞ ሲተኩስና የጅምላ ፍጅት ሲፈፅም ታይቶ አይታወቅም ።
በመሰረቱ የአገር መከላከያ ሰራዊት ከህዝቡ አብራክ ውስጥ የተገኘ እንደ መሆኑ መጠን የህዝቡ ብሶትና በደል የእራሱም በደል ሊሆን ይገባዋል ። የተመሰረተበት ዋና ዓላማም የአገርን ዳር ድንበር ማስከበርና የህዝብን ሰላምና ደህንነት መጠበቅ ነው ። ይሁን እንጂ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የህውሃት/ኢህአዴግ ስርዓት ህዝቡን በዘር በመከፋፈል አገራችንን ወደ አደገኛ ብጥብጥና ፍጅት እየወሰደ ሲሆን ሰራዊቱም ብሶቱን ለማሰማት ወደ ጐዳና በወጣ ያልታጠቀ ሰላማዊ ህዝብና ገና አድገው ያልጨረሱ ወጣት ተማሪዎች ላይ ዓልሞ በመተኰስ አሰቃቂ ፍጅት እየፈፀመ ነው ።
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዓለም ዓቀፍ ህብረት የህውሃት/ኢህአዴግ ስርዓት ከህዝብ ፈቃድ ውጪ ከሱዳን ጋር የሚያደርገውን የድንበር መካለል ፣ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ በህዝባችን ላይ እየፈፀሙ ያሉትን የጐዳና ላይ አሰቃቂ የጅምላ ፍጅት አጥብቆ ያወግዛል ።
በመሆኑም የመከላከያ ሰራዊቱም ሆነ የፌደራል ፖሊስ መንግስት አላፊ ፣ አገርና ህዝብ ግን ሁልጊዜም ቋሚ መሆናቸውን በማስታወስ በገዛ ወገናቸው ላይ የሚያደርሱትን የጅምላ ፍጅት በማቆም ከህዝቡ የነፃነት ትግል ጐን በመሰለፍ ህዝባቸውን ከማንኛውም ጥቃትና አደጋ እንዲታደጉ ጥሪ ያቀርባል ።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
United Former Ethiopian Air Force Association
(የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዓለም ዓቀፍ ህብረት)
www.formerethiopianairforce.com

↧

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በዛሬው ዕለት መተማ አካባቢ በህወሓት የመከላከያ ኃይል ላይ ድንገተኛ የሽምቅ ውጊያ ጥቃት ከፍተ

$
0
0

poqa
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ሰሞኑን በዋል ድባ እና በአድ-እርቃይ ተከታታይ የሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴዎችን አድርጎ የህወሓትን መከላከያ፣ ፌደራል ፖሊስና ሚሊሻ ኃይል በገፍ በመግደልና በማቁሰል ክፉኛ አሽመድምዶታል፡፡
ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈፀመው ለሚገኘው ጭፍጨፋ የአፀፋ እርምጃ መተማ አካባቢ ተከማችቶ በሚገኘው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ኃይል ላይ ዛሬ ከሰዓት በኋላ መጠነ ሰፊና የተቀናጀ የሽምቅ ውጊያ ጥቃት ከፍቶ በሰው ኃይል፣ በትጥቅና ስንቅ ላይ እጅግ በጣም የከፋ ጉዳትና ኪሳራ አድርሷል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በዛሬው ዕለት በህወሓት አገዛዝ ላይ በወሰደው ከባድ እርምጃ ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ለሁለት ተከታታይ ሰዓታት በመተማ አካባቢ ሰፍሮ የቆየውን የመከላከያ ኃይል እያራወጠ በእሳት በትር ገርፎታል፡፡
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በመተማ ወረዳ በዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ መከላከያ ኃይል ላይ በወሰደው እርምጃ የህዝብ ወገን መሆኑን እንዳስመሰከረ የአካባቢው ነዋሪዎች በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡

ምንጭ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ

↧
↧

መንግስት ከባድ ማስጠንቀቂያ በሰጠ ማግስት በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች መንግስትን የሚቃወሙ ህዝባዊ አመጾች ተካሂደዋል።

$
0
0

The spark that lit the flame of Oromo students protest 10 days ago!(ALEMNEH WASSE NEWS)
መንግስት ከባድ ማስጠንቀቂያ በሰጠ ማግስት በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች መንግስትን የሚቃወሙ ህዝባዊ አመጾች ተካሂደዋል። ህዝባዊ አመጾቹ በሃረርጌ አሰቦት፣ በምእራብ ወለጋ ባቡ ገምበሌና ነጆ፣ በሆድሮጉድሩ በጋጨቲ እንዲሁም በአሰላ የተካሄዱ ሲሆን፣ በቡራዩ ፣ አምቦና አወዳይ ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከፍተኛ ሁኔታ ተሰማርተው ቅኝት እያደረጉና የሚጠረጥሩት ወጣት እየያዙ እያሰሩ ነው። ታህሳስ 5 በአወዳይ የነበረውን ተቃውሞ በማስመልከት ዘጋቢያችን ከቦታው ያጠነከረው ዘገባ እንደሚያመለክተው፣የጫት እና ሌሎች ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ ይዘው የመጡ አርሶደአሮች በወታደሮች ተደብድበው ታስረዋል። ህዝቡ በተቃውሞው ወቅት ተይዘው በአወዳይ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ እስረኞች እንዲፈቱ ያደረገ ሲሆን፣ ከእስር ቤት ጠባቂ በተተኮሰ ጥይት ሶስት እስረኞች ቆስለዋል።ህዝቡ ቁስለኞችን ይዞ ወደ አብዲ በሽር መካከለኛ ክሊኒክ ሲወስዱዋቸው፣የክሊኒኩ ባለቤት ከመንግስት የሚደርሰውን ጥቃት በመፍራት አላክምም በማለታቸው የክሊኒካቸው መስታውት በተበሳጩ ወጣቶች ተሰብሯል። ግለሰቡ ለህብረት ባንክ ያከራዩት ፎቅ መስታውትም የተሰበረ ሲሆን፣ ባለሀብቱም ግንባራቸው በድንጋይ ተፈንክተዋል። ህዝቡ መንግስትን ከመቃወም ውጭ እርስ በርስ የነበረው መከባበር አስገራሚ እንደነበር ዘጋቢያችን አክሎ ገልጿል። በኦሮሚያ ከተሞች እየተቀጣጠለ ያለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በአዲስአበባም ሊቀጥል ይችላል በሚል ስጋት የጸጥታ ቁጥጥሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠብቋል፡፡ ወረዳዎችም ሕዝቡን እየሰበሰቡ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንዲመካከሩም ከአ/አ አስተዳደር ትዕዛዝ ተላልፎላቸዋል፡፡ በአዲስአበባ ጎዳናዎች ከወትሮው በተለየ መልኩ ዱላ እና ክላሽ የያዙ ፖሊሶች በብዛት የተሰማሩ ሲሆን በከተማዋ የሚገኙ ዓለምአቀፍና አህጉራዊ ደርጅቶች ጥበቃቸው ተጠናክሮአል፡፡ በብዙ የከተማዋ አካባቢዎች የሚገኙ ጫማ የሚጠርጉ ሊስትሮወች ሳይቀሩ አንዳች የተለየ እንቅስቃሴ ሲያዩ ለፖሊስ ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዘዋል፡፡ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የኦሮሚያን ተቃውሞ በጠመንጃ ሃይል ለመቆጣጠር ባለፈው አንድ ሳምንት ሙከራ ያደረገ ቢሆንም ተቃውሞን ከመቆጣጠር ይልቅ በተቃራኒው እየተባባሰ መምጣቱ የአገዛዙን መሪዎች አስደንግጦአል፡፡ የመብራት እና ኢንትርኔት መስመር መቆራረጥ እጅግ ተባብሶ ቀጥሎአል።ከአዲስአበባ በተለያዩ ወረዳዎች አመራሮች በስብሰባ የተወጠሩ ሲሆን ሕዝቡንም በየአዳራሹ እየሰበሰቡ እንዲያወያዩ በታዘዙት መሰረት ስራቸውን ማከናወን ጀምረዋል፡፡ መንግስት ተቃውሞው ወደ ህዝባዊ አመጽ መሸጋጋሩን
አስታውቋል።
ኢሳት ዜና

↧

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በምስክርነት እንደማያቀርብ አሳወቀ

$
0
0

as
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሰውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በምስክርነት እንደማያቀርበው ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ማረሚያ ቤቱ ታህሳስ 4/2008 ዓ.ም ለልደታ ፍርድ ቤት በላከው ደብዳቤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ‹‹የ18 አመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት በመሆኑና ከአሁን ቀደም ምስክር ሆኖ ከማረሚያ ቤቱ ወጥቶ መስክሮ ስለማያውቅ ለመስክርነት ለማቅረብ እንቸገራለን›› ብሏል፡፡
እስክንድር ነጋ ለእነ ዘላለም ወርቃገኘው በመከላከያ ምስክርነት ከተቆጠረ በኋላ ከህዳር 13 /2008 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ቀጠሮዎች በምስክርነት ሳይቀር የቀረ ሲሆን ዛሬ ታህሳስ 6/2008 ዓ.ም ማረሚያ ቤቱ በላከው ደብዳቤ መሰረት ሳይቀርብ ቀርቷል፡፡ ከአንድ አመት በፊት ከ6 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ተኩል ለ30 ደቂቃ ሲጠየቅ የነበረው እስክንድር ነጋ በአሁኑ ወቅት እንዳይጠየቅ ተከልክሏል፡፡ በተጨማሪም ማረሚያ ቤቱ በተደጋጋሚ እስክንድር ነጋ የታሰረበትን ክፍል በመፈተሽ መፅሃፍ ቅዱስን ሳይቀር መነጠቁም ይታወሳል፡፡
ምንጭነገረ ኢትዮጵያ

↧

ተቃውሞው በአዲስ አበባ ዙሪያ ደርሷል ሱሉልታ ላይ መንገድ ተዘግቷል::

$
0
0

0p9
የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ተቀጣጥሏል: መንግስት በመላው ኦሮሚያ ጦርነት ቢያውጅም በባለስልጣኖቹ የህዝብን ክብር የሚነካ ንግግር በመናገር ሊያሸማቅቅ ቢሞክርም፤ ህዝቡ ለመሞት ቆርጦ ፊት ለፊት እየተጋፈጠ ነው።ትላንት ከአዲስ አበባ 60 ኪ/ሜ ወለንኮሚ ተባብሶ መቀጠሉን ብሉምበርግ ዘግቧል።
የብሉምበርግ ዘጋቢ ዊሊያም ዴቪድሰን ከስፍራው እንደዘገበው መንገድ ተዘግቷል፣ የመንግስት ሃይሎችን ጥቃት በማውገዝ፣ በሺ የሚቆጠሩ ፈረሰኞች ወደሆለታ ከተማ ተንቀሳቅሰዋል።
የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን አርሶአደሮችን ያፈናቅላል፣ ህገመንገስቱን ጭምር ይጻረራል በሚል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጀመሩትና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል እያካተተ የቀጠለው ተቃውሞ፣ በተለይ በአዲስ አበባ አቅራቢያ እየተጠናከረ መገኘቱ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ትኩረት ስቧል።
በአዲስ አበባና በአምቦ መካከል የምትገኘውና ከአዲስ አበባ በ60 ኪሎሜትር ላይ የምትገኘው ወለንኮሚ ከተማ 4 ሰላማዊ ሰዎች ትናንት መገደላቸውን ከስፍራው የዘገበው የብሎምበርግ ዊሊያም ዴቪድሰን፣ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት መያዟን ገልጿል።
ሰው ተደብቆ እንደሚገኝና በየሰከንዱ የማያቋርጥ ተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ የገለጸው ዊሊያም ዴቪድሰን፣ ከጤና ጣቢያና ትምህርት ቤት በስተቀር ሁሉም ተቋማት ላለፉት 4 ቀናት በሰልፈኞቹ ተይዘው መቆየታቸውን ጽፏል።
የቶታል ነዳጅ ማደያ ተሳቢ መኪናን እንዲሁም የዳሸን ቢራ ፋብሪካ የጭነት መኪና በመጠቀም ወደ አምቦ የሚወስደውንና ወደ አዲስ አበባ የሚወስደውን መንገድ የዘጉት ሰልፈኞች የቀበሌ ፅ/ቤት ጠረጴዛዎችንና መደርደሪያዎችን ጭምር ለመንገድ መዝጊያነት እንደተጠቀሙ ከስፍራው ተዘግቧል።
የህዝቡ መገደል ያስቆጣቸው ፈረሰኞች ትላንት ወደ ሆለታ ተንቀሳቅሰው ተቋውሟቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ወደ አዲስ አበባ ለመንቀሳቀስ ሞክረው እልቂት ይከሰታል በሚል ማግባቢያ መመለሳቸው ታውቋል።
ዛሬም በኦሮሚያ ክልል በተቀጣጠለው ህዝባዊ ቁጣ የመንግስት ሃይላት የአጸፋ ጥቃት የቀጠለ ሲሆን፣ ህዝባዊ እምቢተኝነትቱም ጨምሯል። ሱልልታ ላይ በሚደረገው ተቃውሞ የጎጃም በር በመዘጋቱ ወደ ባህርዳር የሚጓዙ የጭነት መኪኖች ይሁን የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ከሱሉልታ ሲመለሱ ውለዋል::ሱሉልታ ላይ ሕዝቡ መንገዱን በመዝጋት ተቃውሞውን እያሰማ የሚገኝ ሲሆን ቀበሌዎችን ወሮ ይዟል::

ተቃውሞው ቀጥሎ በወለጋ ኦብዲ በምእራብ ሸዋ ሜታ ሮቢ እጅግ ከፍተኛ ተቃውሞ በመሰማት ላይ ይገኛል::

↧

የኢትዮጵያዉያን አንድነት – ለወያኔ ግብዐተ መሬት (ይገረም አለሙ)

$
0
0

et2
በኢትዮጵያ የነበሩት መንግስታት ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ማስፈን ባይሆንላቸው ለሀገራቸው ቀናኢ ነበሩና ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትመኘውን መሬት ለመወሰድ የነበራት የዘመናት ህልም ሳይሳካ ኖሯል፡፡ አሁን ግን በስም እንጂ በተግባር ኢትዮጵያ መንግሥት አልባ የሆነችበትን ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የዘመናት ምኞቷን ለማሳካት ከወያኔ ጋር እየተሞዳመደች ነው፡፡ ይህን ድብቅ የአቶ መለስ ዜናዊ ሴራ የወያኔ ባለሥልጣኖች ለመደበቅ ቢጣጣሩም የሱዳን ጋዜጦች በደስታና በአሸናፊነት ስሜት እየዘገቡት ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ የድብቅ ስምምነት ተግባራዊ ሆኖ ከኢትዮጵያ ሕዝብ እውቅናና ፍላጎት ውጪ ሱዳን መሬት ለመውሰድ ብትችል ሰላም የማታገኝበት ለትውልድም ግዜ እየጠበቀ የሚፈነዳ ፈንጂ ማቆየት መሆኑን በዋሽንግቶን ዲሲ በሚገኘው የሱዳን ኤንባሲ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ኢትዮጵያውያን አስገንዝበዋል፡፡ የዚህ ሰልፍ ተካፋይ ለመሆን ከሌላ ከተማ የተገኙ የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን በቦታው ሲደርሱ መጣን ተቀበሉን ማለታቸውን ስሰማ የወያኔ የመቶ አመት የቤት ሴራ አበቃለት ይሆን! በማለት ሳላውቀው አይኔ በእንባ ተሞላ፡፡ ለካስ ከሀዘን ባላተናነሰ ደስታም ያስለቅሳል፡፡የአመታት ምኞት እውን ሲሆን ማየት አይንን አንባ ያስረግዛል!!
በዚሁ ስብሰባ ላይ የተገኙት አቶ ገመቹ የተባሉ ሰው እኛ የኦሮሞ ተወላጆች የወያኔን የከፋፍለህ ግዛ አጥር ሰብረን ስንመጣ እናንተ አማራና ቅማንት ተባብላችሁ ተከፋፍላችሁ ጠበቃችሁን፤በጣም አዝነናል ይህን የወያኔን ሴራ በጥሳችሁ በአንድ ኢትጵያዊነት መንፈስ እንድትቆሙ ጥሪ እናስተላልፋለን በማለት የገለጹት ወቅታዊ መልእክትም ልብ የሚነካ ነበር፡፡ መለያየት በቃ እንበል!
ተደጋግሞ እንደተገለጸው ወያኔ በስልጣን መቆየት የሚችለው ኢትዮጵያውያንን ሰበብ እየፈጠረ ማለያየት፤ እሳት እየጫረ ማገዳደል የሀሰት ወሬ እየነዛ በጥርጣሬ እንዲተያዩ ማድረግ እስከቻለ ብቻ ነው፡፡ የኢትዮጵያውያን አንድነት የወያኔ ግብአተ መሬት መሆኑን ከማንም በላይ ቁንጮዎቹ ወያኔዎች በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ሰለሆነም እንቅልፍ አጥተው የሚያልሙትና የሚሰሩት እንዴት በምን መንገድና ስልት እንዲሁም መቼና የት ኢትዮጵያዉያንን በተለይ አማራና ኦሮሞን ርስ በርስ እንደሚያበጣብጡ ነው፡፡
ሀያ አራት አመት ሙሉ በጽሁፍ፤ በንግግር ፤ በዘፈን ወዘተ የተላለፉ መልእክቶች የወያኔን የመከፋፈል ሴራ አክሽፈው አንድነትን ሊያመጡ አልቻሉም ነበር፡፡ ሎሬት ጸጋየ ገብረ መድህን በአንድ ግጥሙ የሰው ልጅ ሀ ብሎ ከፊደል ወይንም ዋ ብሎ ከመከራ ይማራል እንዳለው እነሆ ዛሬ ህዝቡ ከመከራ ተምሮ ከፖለቲከኞቹም ቀድሞ ወደ አንድነት እየመጣ ነው፡፡
ከህዝቡ ቀድመው የወያኔን ሴራ ሊያከሽፉ፣አርአያ ሆነው አንድነትን ሊያጠናክሩ፣ግንባር ቀደም ሆነው ትግሉን ሊመሩ ይገባቸው የነበሩ ብዙዎቹ ፖለቲከኞች ከገቡበት ህልም ሳይነቁ ሕዝቡ ቀደማቸው፡፡ መምራቱ ባይሆንላቸውም የህዝቡ ተነሳሽነት እያናቃቸው፤ እየተከፈለ ያለው መስዋዕትነትም ከየግል ጠባብ አመለካከትና የሥልጣን ጥም ተላቀው ለህዝብ ትግል ቅድሚያ እንዲሰጡና ስለ አንድነት እንዲያስቡ እያደረጋቸው መሆኑን እያን እየሰማ ነው፡፡ እሰየው፣ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡
ሎሬት ጸጋየ ገብረ መድህን የአባቶቻችንን ጥረት ሳስታውሰው ትዝ ሲለኝ ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው የሚቆጨኝ እንዳለው ትናንት፣ ትናንት በስትያ በሆነው ባደረግነው የምናዝን የምንቆጭና በዚሁም የምንወቃቀስ ሳይሆን ልናደርገው ሲቻለን ያላደረግነውን ልናውቀውና ልንሄድበት ሲገባን ያላወቅነውንና ያልሄድንበትን መንገድ ለይተን (ይህም አንድነት ነው) የተጀመረው ትግል ከውጤቱ መስዋእትነቱ የማይከፋበትንና ለድል የሚበቃበትን ስራ መስራት ወቅታዊና አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡
ለዚህ ደግሞ ቀዳሚውና ዋናው በየግል ከምትሰጡት መግለጫና ከምታደርጉት እንቅስቃሴ አልፋችሁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ገና በ 97 ምርጫ ዋዜማ ጃ ያስተሰርያል ብሎ ባዜመው ዘፈኑ እስቲ ተባበሩ ይያዝ እጃችሁ አለበለዚያማ በምን ያስታውቃል እኛን መውደዳችሁ ያለውን ዛሬ ከአስር አመት በኋላ ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ የትናንት ልዩነቶችን ወደ ጎን ብሎ እጅ ለእጅ ተያይዞ መታየትና በተግባርም በጋራ መንቀሳቀስ ነው፡፡ ፖለቲከኞቻችን በዚህ መልክ ብትታዩ ከምንም በላይ የወያኔን የከፋፋይነት ሴራና ስራ ታከሽፋላችሁ ብቻ ሳይሆን የመቶ አመት የቤት ስራ የሚለውን ከምንጩ ታደርቃላችሁ፡፡ ለተጀመረው ትግልም ብርታትና ቀጣይነት ሀይል ትሰጣላችሁ፤ በተግባር ደግሞ ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርኣት የምታመራበትን ስልትና መንገድ በጋራ ትቀይሳላችሁ፤ድል ያለመስዋዕትነት ባይገኝም ከድሉ መስዋዕትነቱ እንዳይከፋ ማድረግ ትችላላችሁ፣ በጥቅሉ ድሉን ታቃርባላችሁ፡፡
በታላቁ መጽኃፍ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ ተብሎ እንደተጻፈው ይህ ወቅት ኢትዮጵያ ከወያኔ አገዛዝ ተላቃ ዴሞክራሲያዊት ሀገር እንድትሆን የሚሹና የሚታገሉ፣ በተቃራኒው በስመ ተቀዋሚ እያጭበረበሩ የኖሩና አሁንም በዚሁ መንገድ መቀጠል ዓላማቸው የሆኑ ፖለቲከኞችና ፓርቲዎች የሚለዩበት ነው፡፡ እስካሁንም መለየት እየተቻለ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት ለሀገሪቱም ዴሞክራሲያዊነት ነው የምንታለው የምትሉ ወገኖች ህዝቡ እያሳየ ያለውን አንድነት እናንተ ተግባራዊ ማድረግ ተስኖአችሁ ይህ ህዝብ ከባድ መስዋዕትነት እየከፈለበት የሚገኘው ትግል በዚሁ መልኩ ብቻ ቀጥሎ በወያኔ ቢጨፈለቅ ከወያኔ ባልተናነሰ በታሪክና በትውልድ ትጠየቃላችሁ፡፡
መስዋእትነቱ ሊከብድ የድሉ ወቅት ሊረዝም ይችል ይሆናል እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ የትእግስቱን ያህል ሲያመር የሚያደርገውን ማወቅ የፈለገ ያውቀዋል፡፡ ሰሞኑን የሚታየውም ከበቂ በላይ ገላጭ ነው፡፡ ሕዝቡ ካመረረ መሪ ማጣት ለግዞት እንደማያንበረክከው የአምስት አመቱ የአርበኝነት ታሪኩም ያስረዳል፡፡ ዘር ሳይመነዝር የቋንቋም ሆነ የሀይማኖት ልዩነት ሳይፈጥር በአርበኞች እየተመራ እንዲያም ሲል ከመካከሉ የጎበዝ አለቆችን እየመረጠ በዱር በገደሉ ተዋግቶ ከፊሉም ከጣሊያን ጋር መስሎና ተመሳስሎ በውስጥ አርበኝነት ታግሎ ነው ለነጻነት የበቃው፡፡
በርካታ ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ድርጅቶች ባሉበት በዚህ ዘመን ግን የህዝብ ትግል መሪ አጥቶ ወደ ጎበዝ አለቃ ምርጫ ሊደረስ አይታሰብም፡፡ እናም ለሥልጣኑ መቆየት ሲል ሕዝብ ቢያልቅ ሀገር ቢጠፋ ደንታ የሌለው ወያኔ ራሱም እየገደለ ርስ በርስም እያገዳደለ ዜጎች በየቀኑ እየሞቱ በመሆኑ ፖለቲከኞቻችን ሀላፊነታችሁ ከባድና ውስብስብ ነውና ፍጠኑ፤ እስከዛሬ የለበሳችሁትን ሱፍም ሆነ ገበርዲን አስቀምጡና ኢትዮጵያዊ ኩታ ለብሳችሁ ስለ ዴሞክራሲ እያዜማችሁ እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ እናያችሁ፡፡ ፈጠናችሁ ሸንጎ ተቀመጡና ትግሉ ተጠናክሮና ሰፍቶ ስለሚቀጥልበት፤ መስዋእትነቱ ስለሚቀንስበትና ድሉ ስለሚቃረብበት ዘዴና መንገድ ተነጋገሩ አቅዱ ተንቀሳቀሱ፡፡
የኢትዮጵያውያን አንድነት ለወያኔ ግብዐተ መሬት ነው፡፡ በመሆኑም አንዱ የሌላውን ግብዣና ጥሪ መጠበቅና ይህን ላለመገናኘት ምክንያት ማድረግ አሁን ግዜው አልፎበታል፡፡ በዲሲው ሰልፍ ላይ ተገኝተው መጣን ተቀበሉን እንዳሉት የኦሮሞ ተወላጆች ሁሉም መጣን ተቀበሉን ማለት አንዱ ወደ ሌላው መሄድ ይኖርበታል፡፡ ርስ በርስ እየተጠራሩና አንዱ የሌላውን በር እያንኳኳ በአንድ መድረክ መገናኘትና መምከር ግዜ የሚሰጠው አይደለም፣ እናም ፍጠኑ፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ ህዝቡ እየከፈለው ካለው መስዋዕትነት አንጻር ሚዛን የሚደፋ አይደለም፡፡ታሪክ ለክብር ያጫቸው ኢትዮጵያዉያን የሚታዩበትም የሚፈተኑበትም ወቅት አሁን ነው፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ.

↧
↧

“ህዝቡን ስሙት…. መግለጫ ይቁም…. ውጥረቱን አርግቡት” (አፈንዲ ሙተቂ)

$
0
0

j3
አንደኛ፡
በቀላልና በማያሻማ መንገድ “ማስተር ፕላኑ ተሰርዟል” ማለት አይቻልንምን…? በደንብ ይቻላል፡፡ ነገሮች እንዲህ ከመወጣጠራቸው በፊት መንግሥት ይህንኑ ቃል ቢናገር ህዝቡ “በጄ” ይለው ነበር፡፡ መንግሥትም ዘወትር የሚወቀስበትን “ህዝብን ያለማዳመጥ ችግር” ለመቅረፍ ጥርጊያ ጎዳናውን ያመቻችለት ነበር፡፡ ይሁንና ይህንን ለማድረግ አልተፈቀደም፡፡ በዚህ ፋንታ ልዩ ልዩ ባለስልጣኖች ወደ ሚዲያ እየቀረቡ “ማስተር ፕላኑ ህዝብ ሳይመክርበትና ሳይነጋገርበት ወደ ትግበራ ደረጃ አይገባም” ማለትን ነው የመረጡት፡፡ ይህንን ማለቱ ለምን አስፈለገ?..… ይህ እኮ በሌላ ቋንቋ “ማስተር ፕላኑ ይተገበራል” የማለትን ያህል ነው፡፡ ምክንያቱም “ህዝብ ይነጋገርበታል” ማለት በኛ ሀገር በተለመደው ቋንቋ መሰረት “በማስተር ፕላኑ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች ይካሄዳሉ” እንደማለት ነው እንጂ “በረቂቁ ላይ ህዝቡ ድምጹን ሰጥቶ ውድቅ ለማድረግ ይችላል” ማለት አይደለም፡፡ ላለፉት ሃያ አራት ዓመታት የለመድነው አሰራር ያስተማረን ይህንኑ ነው፡፡
ስለዚህ አሁንም ኳሱ ያለው በመንግሥት እጅ ውስጥ ነው፡፡ ውጥረቱን ለማርገብ ሲባል መንግሥት “ማስተር ፕላኑ ተሰርዟል” ማለት ይገባዋል፡፡
—–
ሁለተኛ
የመግለጫው ጋጋታ ይገርማል፡፡ ተቃውሞውን እያባባሰ የሚገኘው ዋነኛው “እርሾ” ልዩ ልዩ ባለስልጣናትና ተቋማት የሚሰጡት መግለጫ ነው፡፡ መንግሥት በየደረጃው በሚሰጠው መግለጫ ውስጥ “የማያዳግም እርምጃ፤ አስፈላጊውን እርምጃ ” የመሳሰሉ ቃላትን መጠቀሙ ተቃውሞውን ያዳክመዋል ወይንስ ያባብሰዋል…? በብዙ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ለተቃውሞ መውጣቱን እያየንና እየሰማን “ጥቂት ነውጠኞች፣. … አንዳንድ ጸረ-ልማት ሃይሎች” እያሉ ማናናቅስ ተቃውሞውን ያስቀረዋል?…. በአብዛኛው ገበሬዎች የታቀፉበትን የተቃውሞ ንቅናቄ በሽብርተኝነት መፈረጁስ ለመንግሥት ይጠቅማል….?
መንግሥት የሃገሪቱን ሰላምና የህዝብ ደህንነት የሚሻ ከሆነ በሚዲያ የሚንፈቀፈቀውን የመግለጫ ጋጋታ መግታትና ችግሩን ከመሰረቱ ማጥናት አለበት፡፡
—–
ሶስተኛ
ይበልጥ የሚገርመው ነገር የአንዳንድ ባለስልጣናት ያልተገባ አነጋገር ነው፡፡ እኔ አፈንዲ በግል ስራዬ ላይ የተሰማራሁ ሰው ነኝ፡ በመንግሥት ስም የያዝኩት ስልጣንና ወንበር የለኝም፡፡ ከመንግሥት ቢሮክራሲ ውጪ በመሆኔ እንዳሻሁት ብናገርና ብጽፍ “የመናገር መብቱን ተጠቀመ” ነው የምባለው፡፡ ከዚህ አልፎ ለክስና ለህዝባዊ ችሎት የምቀርብበት የህግ አንቀጽ የለም (ህዝብን በይፋ እስካልተሳደብኩ ማለቴ ነው)፡፡ የኔ ንግግርና ጽሑፍ ህዝብን አስቆጥቶ ሀገር የማናወጥ አቅምም የለውም፡፡ የመንግሥት ባለስልጣናት ግን ሲናገሩም ሆነ ሲንቀሳቀሱ የህዝቡን ክብርና ልዕልና ዝቅ ከሚያደርጉ ድርጊቶችና ንግግሮች መቆጠብ አለባቸው፡፡ እነርሱ የሚናገሩት አንድ ቃል ሺዎን አስቆጥቶ ሀገሪቱን የበለጠ ሊያተራምሳት ይችላል፡
ይሁንና ባለስልጣናቶቻችን ሹመት ሲሰጣቸው የንግግርና የእንቅስቃሴ ፕሮቶኮሎችን የሚያስገነዝብ “ኦሬንቴሽን” የሚሰጣቸው አይመስልም፡፡ ጥቂት የማይባሉ ባለስልጣናት ስብሰባ ሲመሩም ሆነ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ የሚናገሩባቸውን ቃላት አይመርጡም፡፡ ብዙዎቹ በትህትና ከመናገር ይልቅ መደንፋትና ማስፈራራት ይቀናቸዋል፡፡ እርግጥ ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለዘብ ባለው አነጋገራቸው ይታወቃሉ፡፡ ሌሎቹስ?… በጣም ያሳዝናል
የአሁኑ ተቃውሞ በአንድ ጊዜ የመጣ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ተቃውሞው ውስጥ ለውስጥ ሲቀጣጠል የቆየ ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ አቶ አባይ ፀሐዬ የሚባሉት የቀድሞ ባለስልጣን ሃዋሳ ላይ የኦህዴድ ካድሬዎችን በመሰብሰብ ተናገሩት የተባለው ቃል ነው፡፡ እኚያ ባለስልጣን ለካድሬዎች “ማስተር ፕላኑን የሚቃወሙትን ልክ እናስገባቸዋለን” ማለታቸው ነው የተነገረው፡፡ ኦህዴድ የራሳቸው ድርጅት ስለሆነ “የኛ ካድሬዎችን እንደፈለግነው ነው የምናናግራቸው” ልንባል እንችላለን፡፡
በትናትናው ዕለት የኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው “ልክ እናስገባቸዋለን” የሚለውን ቃል መደጋገማቸውስ ምን ይባላል…? ይህ አነጋገር ለተቃውሞው መፈንዳት ዐቢይ ሚና መጫወቱን አያውቁትም ማለት ነውን…? ተቃውሞ አድራጊዎቹን “ጋኔል… ጋንግስተር፣ ጠንቋይ…” ወዘተ እያሉ መዝለፍስ ጥቅሙ ምንድነው… የታላቋ ሶሻሊስት ሊቢያ ዐረብ ጀመሃሪያ አብዮታዊ መሪ የነበሩት ወንድም ሙአመር አል-ቀዛፊ (ጋዳፊ) በመጨረሻው ሰዓት የተነሳባቸውን ህዝባዊ ተቃውሞ እንደማብረድ በሚዲያ ቀርበው ተቃዋሚዎችን “የሐሺሽ ተጠቃሚዎች፣ የአል-ቃኢዳ ምንደኞች፣ አሸባሪዎች” እያሉ ዘለፏቸውና በእሳት ላይ ቤንዚን ጨመሩ፡፡ ሊቢያንም ወደ ባሰ ብጥብጥና ሁከት ከተቷት፡፡ እኛ በጭንቅ ዘመናት የበለጠ የምንዋደድና የምንፋቀር ህዝቦች በመሆናችን ያንን የመሰለ ብጥብጥና ሁከት በሀገራችን ይከሰታል ብዬ አላስብም፡፡ ባለስልጣኖቻችን በሚወረውሯቸው ቃላት ላይ ጥንቃቄ ካላደረጉ ግን ነገሮች ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ሊያመሩ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት አነጋገራቸውን ያላረሙ ባለስልጣናትን ወደ ህዝብ ሚዲያ ባያቀርብ ይሻለዋል፡፡
—–
አጭር የመፍትሔ ሓሳብ
መንግሥት ከርሱ የሚጠበቀውን ያድርግ፡፡ ጆሮዎቹን ክፍት አድርጎ ህዝቡን ያዳምጥ፡፡ ማስተር ፕላኑ በብዙሃኑ የኦሮሞ ህዝብ የተወገዘ ስለሆነ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን በይፋ ይናገር፡፡ የታፈኑ የህዝብ ተቃውሞ ያለባቸውን ርዕሶች በአግባቡ ይፈትሽ!! ዜጎችን በእኩል ዐይን ይመልከት፡፡ ከኢንቨስተሮች የዶላር ጋጋታ በፊት የድሃ ገበሬዎችን ህልውናና እና ማንነት ያስቀድም፡፡ ኢንቨስተር በዶላር ላይ ዶላር የሚቆልልበትን ስርዓት ከመዘርጋት ይልቅ ደሃው ገበሬ በመሬቱ በአግባቡ ተጠቅሞ ወደ አግሮ ኢንዱስትሪ የሚሸጋገርበትን በከተሞች አካባቢ የሰፈነውን የኖሮ ውድነትና ስራ አጥነት ለማስተንፈስ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ይቅረጽ፡፡ አዲስ አበባ ብቻ የምትለጠጥበትን የከተሞች ልማት ስትራቴጂ ሙሉ በሙሉ በማስወገድ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ከተማ የልማት አምባ የሚሆንበትን አዲስ የከተሞች ልማት ስትራቴጂ ይቅረጽ፡፡
ተቃውሞውን ለመቆጣጠር በሚል በብዙ ከተሞች ውስጥ የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት ዳር ድንበር ወደ ማስከበር መደበኛ ስራው ይመለስ፡፡ በምትኩ የፖሊስ ሃይሉ ጸጥታውን የመቆጣጠር ስራውን ይቀጥል፡፡ በተቃውሞው ሳቢያ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ነጻ ኮሚሽን በአስቸኳይ ይቋቋም፡፡ በተቃውሞው ሳቢያ የታሰሩ ወገኖች በአስቸኳይ ይፈቱ፡፡ ህይወታቸውን ላጡት ተገቢውን ካሳ ይክፈል፡፡ የሀገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ዝምታቸውን በመስበር ለችግሩ እልባት የማፈላለግ ሃላፊነታቸውን ይወጡ፡፡
——
ታሕሳስ 17/2008
(በተረፈ “አፈንዲ ፈርቷል” እያላችሁ የምታሙኝ ኮልኮሌዎች እንዳላችሁ አውቃለሁ፡፡ ፍርሃት በኛ ዘንድ የለም፡፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ከመናገር የተቆጠብነው ነገሮችን በአትኩሮት ለማጥናት ካለን ፍላጎት አኳያ ነው፡፡ ደግሞም ፌስቡክ ላይ የምንታወቀው ወቅታዊ ርዕሶችን በመጻፍ ሳይሆን የቆዩ ጉዳዮችን በማሰናኘት ነው፡፡ እናንተ ግን በሰው ፍላጎትና ምርጫ ላይ በግድ ልወስን ባይ ስለሆናችሁ በሃሜትና በውረፋ ልትጨርሱን ተቃርባችሁ ነበር፡፡ ሁላችሁም እንዳትረሷት!!…. ጊዜው ሲደርስ ልክ እናስገባችኋለን፡፡ ቂቂቂቂቂቂቂ… )

↧

ጄኔራል መንግስቱ ንዋይን እንደ ግሪካዊው ፈላስፋ ሶቅራጥስ (የመንግስቱ ዲስኩር ለዛሬዋ ኢትዮጵያ) -ቻላቸው ታደሰ

$
0
0

gf1
ወሩ ታህሳስ ነው… ጄኔራል መንግስቱ ንዋይ፣ ግርማሜ ንዋይ (የመንዜው የአለቃ ንዋይ ልጆች)፣ ኮሎኔል ወርቅነህ ገበየሁ፣ ጄኔራል ፅጌ ዲቡ ወዘተ በንጉሰ ነገስቱ ዙፋን ላይ መፈንቅለ-መንግስት ያደረጉበት ታሪካዊ ወር… መፈንቅለ-መንግስቱ ከከሸፈ በኋላ ጄኔራል መንግስቱ በፍርድ ቤት ችሎት ላይ ቆሞ የተናገረውን ታሪካዊ ንግግር እንደገና አነበብኩት… ሆኖም ከሁልጊዜውም የተለየ ስሜት ተሰማኝ፡፡

መንግስቱ ያንን ታሪካዊ ዲስኩር ያደረገው በአሜሪካው ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ፖለቲካል ሳይንስ ተምሮ የተመለሰው ታናሽ ወንድሙ ግርማሜ ንዋይ ፅፎ ስለሰጠው አይደለም፡፡ ግርማሜ ከአዲስ አበባ ሲያመልጥ በተደረው የተኩስ ልውውጥ ቀደም ቀድሞ ተገሏል፡፡ ጎንደሬው ኮሎኔል ወርቅነህም እጄን አልሰጥም ብሎ በታላቅ ጀግንነት ለሰዓታት ከተዋጋ በኋላ በመጨረሻው ሰዓት እንደ አፄ ቴዎድሮስ ራሱን ገሏል፡፡ መንገስቱ ያንን ታካዊ ንግግር ያደረገው እንደወረደ ነበር… በወረቀት ፅፎም አላነበበውም፡፡ በአደባባይ በወረቀት ላይ ሳይፅፉ ንግግር ማድረግ በማይችሉ ፖለቲከኞች እየተመራች ባለችው ሀገር መንግስቱ ንዋይ ከሃምሳ ዓመት በፊት በሞት ፊት ቆሞ እንኳ እንደወረደ የተናገረው ንግግር ትናንትም፣ ዛሬም፣ ወደፊትም ዘመን ሊሽረው አይቻለውም፡፡

በነገራችን ላይ ብዙ ፀሃፍት መንግስቱን መፈንቅለ-መንግስት ወደማድረግ የገፋፋው ግርማሜ እንደሆነ ፅፈዋል… በትክክልም የግርማሜ ተፅዕኖ ሊኖር መቻሉ እንደተጠበቀ ሆኖ መንግስቱ በችሎት ላይ ያደረገው ንግግር የሚመሰክረው ግን ከድሮም የተፈጥሮ ዕውቀትና ያገናዘብና የመረዳት ልዩ ችሎታ (native intelligence) የነበረው ሰው መሆኑን ነው፡፡

አንድ ሰው ሞት እንደሚፈረድበት ቀድሞ እያወቀ በፍርድ ቤቱ ችሎት (የያኔዎቹ ፍርድ ቤቶች ከአሁኖቹ እጅጉን ይሻሉ እንደነበር ልብ ይሏል!) ፊት ቆሞ ሦስት ትውልድ የሚሻገር ንግግር ለማድረግ ጥልቅ ዕውቀት (knowledge) ወይም የንግግር ክህሎት (the art of oratory) ብቻ በቂው አይደለም፡፡ በፈረንጆች ቋንቋ ለመግለፅ “wisdom” ያስፈልገዋል… መንግስቱ ንዋይ አስደማሚ wisdom የነበረው ሰው መሆኑን ለማወቅ ንግግሩን ብቻ በጥሞና ማንበብ በቂ ነው፡፡ እያዳንዷን ቃል፣ እያንዳንዷን ዓረፍተ ነገር… በጥንቃቄ ብንመረምር የመንግስቱ ልዕልና ወለል ብሎ ይታየናል…

እኔ መንግስቱን በዋነኛነት የምመመዝነው መፈንቅለ-መንግስቱ ሲከሽፍ በውዥንብር (“በውዥንብር” የሚለውን ቃል አፅንዖት መስጠት እፈልጋለሁ) ባስወሰደው የጅምላ ግድያ እርምጃ አይደለም፡፡ ይልቁንስ አንግቦት በተነሳው ዓላማ እንጂ፡፡ (ለነገሩ ከዝነኛው አርበኛ ራስ አበበ አረጋይ እና ሌሎች ጥቂት ሰዎች ውጭ ሌሎቹ በኋላ በደርግ ከስልሳዎቹ ባለስልጣናት ጋር መረሸናቸው አይቀርም ነበር!)

በዚህ ጉዳይ ላይ ነገሮችን በተለየ አቅጣጫ የሚያየው ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ከያዘው አቋም እለያሁ፡፡ ዶክተር ዳኛቸው “የ1953ቱ መፈንቅለ መንግስት ጠንሳሾች የፈፀሙት ጅምላ ግድያ በኋላ ላይ ደርግ ለፈፀመው ቀይ ሽብር በር ከፋች ሆኗል” በማለት ይከራከራል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን የተለየ አቋም በአደባባይ በማንፀባረቅ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ምሁር ሳይሆን አይቀርም፤ በሀገራችን የትምህርት ስርዓት፣ በታሪክ ፀሃፍትም ይሁን በአፈ ታሪክ የ1953ቱ መፈንቅለ መንግስት ለ1966ቱ ህዝባዊ አብዮት ፈር ቀዳጅ (a pioneer landmark event) እና አወንታዊ ድርጊት መሆኑ ብቻ ነው ሲወሳ የኖረው…

እኔ እንዲህ እያልኩ እጠይቃለሁ፤ እውነት ደርግ በስልሳዎቹ ባለስልጣናት በኋላም በኢህአፓ ላይ ቀይ ሽብርን ለማፋፋም፤ ኢህአፓም በፊናው በደርግ ላይ ነጭ ሽብርን ለማፋፋም የመንግስቱ ንዋይን ድርጊት ማስታወስ አስፍልጓቸው ነበርን? ለመሆኑ ተፃራሪ የአብዮቱ ኃይሎች ወደ ኢትዮጵያ ታሪክ ተመልክተው ያውቃሉን? ኢትዮጵያዊ ስነ-ልቦናስ ነበራቸውን?

ሁሉም የአብዮቱ ኃይላት እኮ አሻግረው ያዩት ወደ ሌኒንና ትሮትስኪ ሀገር ሶቪዬት ህብረት እንጂ ወደ ኢትዮጵያ ታሪክና ነባራዊ ሁኔታ አልነበረም… ከኢትዮጵያ ጋር ተመሳሳይ ታሪክ ወደ ነበራት ጃፓንም አላዩም… ወደ ማኦ ዜዶንግ ሀገር ቻይናም ቢሆን አብዝተው አላዩም… ሆቺሚኒህ ሀገር ቬትናም እንኳ አላዩም (ስሙን ለመፈክር ቢጠቀሙበትም ቅሉ)፡፡ ሆቺሚኒህ የቬትናምን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ ስርዓት ለማቆም የታገለ ብሄርተኛ እንጂ ኮሚኒስት አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ ከሌኒንና ስታሊን ለየት ያለ ሃሳብ ከነበረው ትሮትስኪ እንኳ የተማሩት ነገር ያለ አይመስልም… የሀገራችን አብዮተኞች የእነ ካርል ማርክስ፣ የእነ ሌኒን፣ የእነ ማኦን (በመጠኑም ቢሆን) ቀይ መፅሃፍ እንደ ቅዱስ መፅሃፍ አነበቡት እንጂ የመንግስቱ ንዋይን የችሎት ላይ ንግግር አባዝተው፣ አሳትመው ሲያሰራጩ አልታዩም፡፡ የመንግስቱን ታሪካዊ ዲስኩር በማንበብ ርዕዮተ-ዓለማዊ ገፅታ በማላበስ (ርዕዮተዓለም ግን የግድ አይደለም) አላዳበሩትም፡፡ በአብዮቱ ዘመን እንዲህ ዓይነት ነገር ስለመደረጉ የሚነግረኘ ካለ ለመማር ዝግጁ ነኝ… በጠቅላላው ተማሪዎቹ መንግስቱ ንዋይን አርዓያ አላደረጉትም፤ በ1953ቱ መፈንቅለ-መንግስት ጊዜም ተማሪዎቹ አስተዋፅዖ አልነበራቸውም፡፡ ምናልባት ያኔ ፖለቲካዊ ግንዛቢያቸው ገና አልዳበረም ይሆናል… እምብዛም ያልተማረው ወታደሩ መንግስቱ ግን ቀድሞ ገብቶት ነበር…

ያም ሆኖ ዶክተር ዳኛቸው የሚያቀርበው የተለየ አተያይ እውቀትን ለማዳበር፣ ታሪክን እንደገና ለመፈተሸ ስለሚረዳ እጅጉን ሊመሰገን እንጂ ሊወቀስ አይገባውም…

በተነሳለት ዓላማ እና ዓላማውን ለመፈፀም በተከተለው ስልት ስንመዝነው መንግስቱ በጊዜው በጣም ተራማጅ ሰው እንደነበር መገንዘብ ይቻላል፡፡ መንግስቱ ወታደር ሆኖም እንኳ በውጭም በሀገር ውስጥም ከፍተኛ ትምህርት ይማሩ ከነበሩ ተማሪዎች ሁሉ ቀድሞ የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ፣ መፃዒ እጣ ፋንታዋን ብሎም መደረግ የነበረበት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ቀድሞ የተገለጠለትና የተገለጠለትን እውቀትም ለመተግበር ያላወላዳ ሰው ነው፡፡ መንግስቱ በግርማ ሞገሳቸውና በሳል አነጋገራቸው ማንንም ማሳመን ከሚችሉት አፄ ኃይለ ስላሴ ጋር እያዋለ… ከእርሳቸው ጋር ወደተለያዩ ጠቅላይ ግዛቶች እየተጓዘም እንኳ ዓይኑንና ህሊናውን ክፍት በማድረግ የሀገሩን ነባራዊ ሁኔታ ለመገንዘብ የቻለ ሰው ነበር…

የመንግስቱን ልዕልና ለመረዳት (እና ለማድነቅ ወይም ለመተቸት) የማንም አስረጅነት ወይም ምስክርነት የሚስፈልግ አይመስለኝም፡፡ በችሎት ላይ የተናገረው ሳይበረዝ ለታሪክ ተቀምጧል፡፡ (በነገራችን ላይ የያኔው ገዥዎች መንግስቱ ንግግር እንዲያደርግ ብቻ ሳይሆን ንግግሩ በጥንቃቄ ተጠብቆ እንዲቆይ ማድረጋቸው በኋላ ከመጡት ሁለት ገዥዎቻችን ምን ያህል የተሻሉ እንደነበሩ ያሳየናል… ለመሆኑ የ1981ዱ መፈንቅለ-መንግስት ጠንሳሽ ጄኔራል ፋንታ በላይ ከመረሸኑ በፊት በደረግ ችሎት ላይ እንዲናገር ተፈቅዶለት ነበርን? ከተፈቀደለትስ ምን ዓይነት ዲስኩር አሰምቶ ይሆን? በእስር ላይ እያለ ለቴሌቪዥን ከተናገራት ቁንፅል ነገር ውጪ መንግስቱ ንዋይ ያገኘውን ዕድል እንኳ ያገኘ አይመስለኝም፡፡ ካገኘም እስካሁን የሰማነው ምንም ነገር የለም፡፡) ለማንኛውም የመንግስቱን ዲስኩር በጥንቃቄ ከመረመርነው ዲስኩሩ የራሱን ትውልድ ነባራዊ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሦስት ትውልዶች ዕጣ ፋንታ አስቀድሞ የተነበየበት ግዙፍ መፅሃፍ ነው…

መንግስቱ የህግ የበላይነት ውድቀትን፣ ማህበራዊ ፍትህ መንኮታኮትን፣ የፍፁማዊ አገዛዝ መበስበስን (degeneration of absolute power)፣ የሞራል ድቀትን፣ የህግና ፍትህ ፍልስፍናን (jurisprudence)፣ የፍርሃትና ስልጣን መስተጋብርን (nexus between power and fear)፣ የሞትና ነፃነት ትስስርን፣ የህዝባዊ አብዮት አይቀሬነትን ወዘተ በማስተሳሰር በፍልስፍና የታጨቀ ዲስኩር ማሰማት ችሏል…

በፍርድ ቤት ችሎት ላይ የሚደረጉ ዲስኩሮች ታሪካዊ ተመሳሳይነት አላቸው… መንግስቱም በዲስኩሩ “የዛሬ ወንጀለኛ የነገ ባለታሪክ ነኝ” ብሏል፡፡ ይህ ትንቢት ነው… ፊደል ካስትሮና አዶልፍ ሂትለር አብዮታቸውን ከማቀጣጠላቸው በፊት በወንጀል ተፈርዶባቸው ወደ እስር ቤት ተወርውረው ነበር፡፡ ሂትለር በችሎት ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፤ “History will absolve me” (ታሪክ ነገ ነፃ ያወጣኛል!) እንዳለውም አልቀረም፤ በዘጠኝ ወሩ የእስር ቤት ቆይታው “Mein Kampf” (የእኔ ትግል) የተሰኘውን ታሪካዊ መፅሃፍ ፅፎ እንደጨረሰ ከእስር ተለቀቀ፡፡ ዓለምን ከስር መሰረቷ የሚቀይር ስርዓትም አሰፈነ… መቼም ሁሌም ታሪክ የአሸናፊዎች መሳሪያ ናትና ሂትለርም አረመኔ (evil)፣ ዕብድ (psychopath)… ተባለ…ተባለ… ተባለ… (በነገራችን ላይ በጀርመን ሀገር የተከለከለው መፅሃፉ ከብዙ ዓመታት በኋላ ሰሞኑን እንደገና ታትሟል)፡፡

እኤአ በ1950ዎቹ መጨረሻ አይበገሬ የነበረው የህግ ምሩቅ ፊደል ካስትሮ በችሎት ፊት ቀርቦ እስር ሲፈረድበት “History will absolve me” ብሎ በመናገሩ ሲወሳ ይኖራል፡፡ እንዳለውም አልቀረ፤ ከሁለት ዓመት በኋላ ኩባን በአብዮት አጥለቀለቃት፡፡ የኩባውን ልዩ አብዮት እንተወውና በአፍሪካዊያን ጫንቃ ላይ ተንሰራፍቶ የነበረውን ቅኝ አገዛዝ ወደ መጨረሻ ግብዓተ-መሬት የሸኘው ፊደል ካስትሮ ነው፡፡ እውነትም “history absolved him very well!”

የመንግስቱ የፍርድ ቤት ዲስኩር ታላቁ ግሪካዊ ፈላስፋ ሶቅራጥስ ሞት በበየነበት ፍርድ ቤት ፊት ቆሞ ካሰማው ዲስኩር ጋርም ቢሆን መሳ ለመሳ መቆም ይችላል… መንግስቱ ለሞት ያለውን ንቀት በችሎቱ ፊት ሲገልፅ “እኔ ግን በደስታ ወደ ሞት እሄዳለሁ” አላለምን? “ይግባኝ በመጠየቅ የአፄ ኃይለስላሴን ፊት አላይም” አላለምን? በደንብ ብሏል እንጂ! ይህንን አባባል ቃል በቃል ሶቅራጥስ ከሁለት ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በፊት በዳኞች ፊት ተናግሮታል፡፡ “I am going to die; you are going to live. Which one is better? Only God knows” በማለት ይግባኝ እንደማይልና ይልቁንስ የሞት ፍርዱ እንዲፀናበት ተማፅኗል፡፡ ሶቅራጥስ እንዲህ አለ፤ “እኔ ወደ እውቀት… ወደ እውነት (Truth… “T” capital letter መሆኑ ግንዛቤ ውስጥ ይግባ) እየሄድኩ ነው…ለእናንተ ይብላኝ!” መንግስቱም ያለው ተመሳሳይ ነው… ምድራዊ ሞትን ልፍትህ… ለእውነት ሲሉ የናቁ የሁለት ዓለም ሰዎች!

ሶቅራጥስ የበሰበሰው የግሪክ መሪዎች አገዛዝ ውድቀት አይቀሬነትን ተናግሯል፡፡ ራሱን እንደ “ተናዳፊ ዝንብ” (gadfly) ያየው ሶቅራጥስ በቅንጦት፣ በመታበይና ድንቁርና የሚታወቁት የግሪክ ገዥዎች የዝንቧ ንክሻ ሲሰማቸው እንዲነቁ መክሯል፤ አልሰሙትም እንጂ፡፡ መንግስቱንም የሰማው የለም፡፡ “ዋ! ዋ! ዋ! ለእናንተ እና ለገዢያችሁ… የኢትዮጵያ ህዝብ ሃሳቤ በዝርዝር ገብቶት በአንድነት በሚነሳበት ጊዜ የሚወርድባችሁ መዓት አሰቃቂ ይሆናል፡፡”

እኤአ በ1780ዎቹ መጨረሻ ላይ ታዋቂው የፈረንሳይ አብዮት መሪ ሮብስፔርም ለፈረንሳይ ንጉሳዊያን ገዥዎች ይህንኑ ነግሯቸው ነበር፡፡ አልሰሙም እንጂ… በነገራችን ላይ “ቀይ ሽብር” እና “ነጭ ሽብር” ምንጫቸው ከዚህ አብዮት ነው…

በእውነቱ ያልታደልን ትውልዶች ስለሆንን እንጂ ገላጭ ጥቅሶች ፍለጋ ወደ ግሪክና ፈረንሳይ አሻግሮ ማየት ባላስፈለገን ነበር… የመንግስቱ ዲስኩር እንኳን ለእኛ ለሌላ የሚተርፍ ነበር…

መንግስቱ በዲስኩሩ የተነበየው ነገር በአፄ ኃይለ ስላሴ ላይ በደረሰው ነገር ብቻ አልቆመም፤ በደርግ ላይም ደርሷል… ለአሁኖቹ ገዥዎችም የሰራል! ሀገራችን ዴሞክራሲያዊና ፍትሃዊ ስርዓት እስኪሰፍንባት ድረስ የመንግስቱ ዲስኩር ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ሆኖ ይኖራል… የመንግስቱ ደወል ከሃምሳ ዓመታት በኋላም እንኳ ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ጎልቶ ይሰማል… አድማጭ ግን የለም፤ እንደ ግሪክ መሪዎች፣ እንደ ኩባው አምባገነን ባቲስታ፣ እንደ ሩሲያው ዛር፣ እንደ ፈረንሳዩ ንጉስ ሉይ አስራ ስድስተኛ… ኃይል (ስልጣን ላለማለት ነው!)፣ ሃብት፣ ቅንጦት (extravagance)፣ መታበይ (arrogance)፣ ድንቁርና (ignorance) ተባብረው አውረዋቸዋል…

ኢትዮጵያ ሆይ! የመንግስቱ ንዋይ ዲስኩር በርሽን እያንኳኳ ነው…

↧

እነ ሀብታሙ አያሌው የጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ጠየቁ

$
0
0

11053372_826118777474147_1371325407605832008_n
• አቶ ዳንኤል ሺበሽ በእስር ቤት በደል እየተፈጸመበት መሆኑን ተናግሯል

በፌደራል አቃቤ ህግ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩና በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ተወስኖላቸው ሳለ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ጉዳያቸው በፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት እየተከታተሉ የሚገኙት እነ ሀብታሙ አያሌው የይግባኝ ሰሚ ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ ከችሎት እንዲነሱላቸው ጠይቀዋል፡፡
በዚህ መዝገብ ይግባኝ የተጠየቀባቸውና ሰብሳቢ ዳኛው፣ ዳኛ ዳኜ መላኩ ከችሎት እንዲነሱ የጠየቁት ተከሳሾች አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሽ እና አቶ አብርሃም ሰለሞን ናቸው፡፡
የይግባኝ መልስ ሰጭዎቹ ሰብሳቢ ዳኛው ከችሎት እንዲነሱላቸው ለመጠየቃቸው ምክንያታቸውን ዘርዝረው በጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በዋናነት ዳኛው ‹‹…ችሎቱን እየመሩበት ካለው አግባብ አንጻርም ሆነ በህግ ከሚጠበቅባቸው ገለልተኝነት አንጻር እርሳቸው እንደ አንድ ዳኛም ሆነ እንደ ሰብሳቢ በሚሳተፉበት ችሎት ትክክለኛ ፍትህ እናገኛለን ብለን ስለማናምን›› የሚል ነው፡፡
እነ ሀብታሙ አያሌው ነሀሴ 15/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በጻፈው እግድ ምክንያት እስካሁን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
በሌላ በኩል ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘውና በዚሁ መዝገብ የተካተተው የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ በእስር በሚገኝበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በደል እየተፈጸመበት እንደሆነ ለችሎቱ ገልጾዋል፡፡ አቶ ዳንኤል ለፍርድ ቤት ክርክር ያዘጋጀው ወረቀት ተቀምቶ እንደተቀዳደደበትና በአስተዳደሩ ከፍተኛ ዛቻም እየተፈጸመበት መሆኑን ለችሎቱ ተናግሯል፡፡ ‹‹እዚህ ቤት አስክሬንህ ነው የሚወጣው›› እያሉ ይዝቱብኛል ያለው አቶ ዳንኤል፣ ‹‹ከሌላው እስረኛ እኩል የማልታየው ለምንድነው? እኔስ ዜጋ አይደለሁምን?›› ሲል ጠይቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ መልስ ሰጭዎቹ ባቀረቡት የሰብሳቢው ዳኛ ይነሳልን አቤቱታ ላይ ብይን ለመስጠት ለታህሳስ 15/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

↧

አመፀኛው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲያስነጥስ…? (ቻላቸው ታደሰ )

$
0
0

oil1
መላ ምት አንድ፡ “በሰለማዊ አመፅ ጊዜ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን መቆጣጠር የቻለ ኃይል ከሞላ ጎደል መላ ሀገሪቱን መቆጣጠር ይችላል፡፡” (One who controls AAU controls the soul of Ethiopia እንደማለት ነው)፡፡ ለዓመታት እንደታዘብኩት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲያስነጥስ የመላ ሀገሪቱ ዓይኖች ያነባሉ፡፡ ስለሆነም በሃምሳ ዓመታት ታሪካችን የሦስቱም ገዥዎች ሩጫ ዩኒቨርስቲው እንዳያስነጥስ ማፈን ሆኖ ቆይቷል፡፡
በመርህ ደረጃ በየትኛውም ዓለም የገጠርና ትናንሽ ከተማዎች ሰላማዊ አመፅ ብዙ ርቀት ለመጓዝ አይቻለውም፡፡ የተማሪ ሰላማዊ አመፅም በራሱ (in and of itself ይሉታል በእንግሊዝኛው) መሰረታዊ ለውጥ አያመጣም፡፡ እንዲያውም በአሳዛኝ ሁኔታ የመክሸፍ ዕድሉ ይበዛል፡፡ ሆኖም በዓለም ታሪክ በተለይም በታዳጊ ሀገሮች በተደጋጋሚ እንደታየው የትናንሽ ከተሞችና ከዋና ከተማ ወጣ ያሉ ዩኒቨርስቲዎች አመፅ በዋና ከተማ ወደሚገኙ ተማሪዎቸ ከተዛመተ በዋና ከተማ ወደሚገኘው ህዝብ (በዋነኛነት መካከለኛው መደብ ህብረተሰብ ክፍል) በፍጥነት የመዛመት ኃይል ያገኛል፡፡ በዋና ከተማ የሚነሳ አመፅ symbolicም ሆነ practical ትሩፋቶች አሉት፡፡ የሰላማዊ አመፅ ታሪክ ቀማሪ ሁሉ ገና ብዕሩን ከማንሳቱ በኢራንና ቻይና ተማሪዎች አመፅ የሚጀምረው ወዶ አይደለም፡፡ አመፆቹ በገዥዎች ላይ bombshell ያወረዱ ስለነበሩ ነው…
በአጭሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና የትላልቅ ከተማዎች መነሳሳት (uprising) ለገዥዎች ራስ ምታት ከመሆን ያለፈ አርማጌዶንን የማምጣት ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ አዲስ አበባ ላይ ጠረጴዛው ላይ ያቀረቀረ የሮይተርስ ወይም የአሶሼትድ ፕሬስ ዘጋቢ፤ ወይም የአውሮፓ ህብረት፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ ዲፕሎማት ጆሮውን እንደ ሚዳቋ የሚቀስረው ያኔ ነው፡፡ በሀገራችን ፌደራሊዝም ስርዓት ተዘርግቶም እንኳ የሀገሪቱ ልብ ትርታ የሚለካው አዲስ አበባ ላይ በሚሆነው ነገር ነው፡፡ በተለይ በአመፅ ጊዜ አዲስ አበባ የሀገሪቱ ልብ ነች፡፡ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሳንባ ጭምር ነች… ስድስት ኪሎና አራት ኪሎ ዩኒቨርስቲዎችም የሀገሪቱ ጥንድ ኩላሊቶች ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሀገሪቱ ሙቀት መለኪያ thermometer ነው፡፡ በሌላ ምንም ምክንያት ሳይሆን በሀገራችን ኋላ ቀርነት ምክንያት ሌላው ዩኒቨርስቲ ሁሉ ከጣፊያ ያለፈ ሚና ላይኖረው ይችላል፡፡ ለጭፍለቃም የተጋለጠ ነው…
እስካሁንም ማንም ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወቅታዊ እንቅስቃሴ ምንም ሲል አልሰማሁም፡፡ በ1989 ዓ.ም ከጓደኞቼ ጋር በስንት ትግል ያቋቋምነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት ድምፅም አይሰማም፡፡ ፈሩን ስቶ ተንገራግጮ ከቆመ በጣም ቆይቷል፡፡

↧
↧

ሁለት ዝነኛ የአትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞች ራሳቸውን ከአሰልጣኝነት አገለሉ።

$
0
0

fd1
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በቅርቡ ለ2016ቱ የብራዚል ኦሎምፒክ ለሚያደርገው ዝግጅት በሚል በቅርብ የስፖርት ኮሚሽን ሆነው በመጡት አቶ ሬድዋን ሁሴን የተላለፈውን መመርያ አልቀበልም በማለት ውጤታማዎቹ አሰልጣኞች ዶክተር ይልማ በርታ እና አሰልጣኝ ቶሎሳ ቆቱ ከብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነት ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ።
አሰልጣኝ ዶክተር ይልማ በርታ ከብሄራዊ ቡድኑ የ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ዋና አሰልጣኝነት ወርደው የወጣቶች ብሄራዊ በድኑን እንዲያሰለጥኑ መመደባቸው ሆን ተብሎ ሞራሌን ለመንካት የተደረገ በሚል ራሳቸውን ከብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነት ያገለሉ ሲሆን
የአዋቂ 5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ዋና እና ረዳት አሰልጣኞች እንዲሆኑ ሁሴን ሺቦ እና ቶሎሳ ቆቱ የተመረጡ ቢሆንም
ምክትል አሰልጣኝ ሆነው እንዲሰሩ የተመረጡት ቶሎሳ ቆቱ ለአገሬ እስካሁን ያበረከትኩት ብቃት በምንም መመዘኛ በረዳትነት የሚያሰራ ባለመሆኑ ከብሄራዊ ቡደኑ ራሴን አግልያለሁ ብለዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብሄራዊ ቡድን ሁለቱን አሰልጣኞች ማጣቱ ከባድ እንደሆነ ባለሞያዎች አስተያየት ይሰጣሉ።

↧

ሁለት ሴት የ6ኪሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታፍነው ተወሰዱ

$
0
0

ew

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6ኪሎ ካምፓስ ሴት ተማሪዎች የሆኑት ተማሪ ሎሚቱ ዋቅቡልቻ የ3ተኛ አመት የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተማሪ እና ተማሪ ሂሩት ቱሌ የ2ተኛ አመት ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ናቸው። ትላንት ምሽቱን በደህንነቶች ከዶርማቸው ታፍነው መወሰዳቸውና የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ስለተማሪዎቹ መሰወር ተጠይቀው “አያገባኝም “የሚል ምላሽ መስጠታቸው በግቢው ውስጥ ተቃውሞውን እንዳስነሳው ምንጮች ገልጸውልናል ።
ሁለቱ ተማሪዎች ሲቪል በለበሱ ሰዎች በተወሰዱበት ወቅት ከለሊት ልብስ በቀር ምንም አለመልበሳቸው ተነግሯል ።

↧

ጎዳናው የት ያደርሳል? _(ከተስፋዬ ገብረአብ (Gadaa)

$
0
0

0p9
አባይ ፀሃዬ ስልጣኑን ከመለስ ዜናዊ ከተረከበ ወዲህ የመጀመሪያው ከባድ ፈተና ገጥሞታል። ከሰላሳ ቀናት በፊት ጀልዱ በተባለች ትንሽ መንደር ላይ የተለኮሰው ቁጣ እና አመፅ መላ ኦሮሚያን አጥለቅልቆታል። ይህን ፅሁፍ ከማተሜ በፊትም አመፁ ከኦሮሚያ አልፎ ወደ ምእራብ ጎንደር የተስፋፋ ሲሆን፤ የወያኔ ቡድን የገጠመውን ፈተና በምን አይነት ዘዴ ማፈን እንደሚችል ሲመክር መሰንበቱም እውነት ነው። ይቻላቸው ይሆን? የሚቻልበትም ሆነ የማይቻልበት እድል አለ።

በምርጫ 97 ወያኔ ከመውደቅ ለጥቂት አምልጦአል። መለስ ዜናዊ አዲስአበባን ለቆ ቢሾፍቱ ላይ የማዘዣ ጣቢያውን ተክሎ ነበር። ይዛው ለመሸሽ ሄሊኮፕተር ሞተሯን ሳታጠፋ ትጠብቀው ነበር። ያ እድል በአንዳንድ ሰንካላ ምክንያቶች ከመሳካት ተደናቅፏል። የወያኔ ስርአት ከሽፍታነት ጠባዩ እንዲላቀቅ ለማስገደድ ይህ የሰሞኑ ህዝባዊ አመፅ ሌላው እድልና ወርቃማ ጊዜ ነው። በርግጥ እንዳጀማመሩ በኦሮሞ ህዝብ መስዋእትነት ብቻ ወያኔ ከስልጣኑ ቢወገድ ለኢትዮጵያ በጎ አይሆንም። የኦሮሞ ህዝብ ያለማንም ድጋፍ የከፈለውን ያህል ከፍሎ ለመብት ጥያቄው ምላሽ ሊያገኝ ይችላል። ሂደቱ በዚህ መንገድ ከተጠናቀቀ ከዚያ በሁዋላ ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቆም እድሏ አጠያያቂ ይሆናል። በዚህ አጋጣሚ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለመጪው ዘመን የሚጠቅም በጎ አስተዋፅኦ ማድረግ ከቻለ ግን ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን አካባቢያችንም ከታላቅ ቀውስ ይድናል።

ይህችን እየፃፍኩ ሳለ 71ኛው ኦሮሞ የመገደሉን ዜና ሰምቻለሁ። እና አዝኛለሁ። በጣም አዝኛለሁ። ያዘንኩት 71 ኦሮሞዎች በመገደላቸው ብቻ አይደለም። በተያያዘ የብዙ ሺህ የሰው ህይወት ሊጠፋ ይችላል ብዬ በመስጋቴ ጭምር ነው። መቸም ቢሆን በከንቱ ፈሶ የሚቀር የሰው ልጅ ደም የለም። የህወሃት ጓደኛሞች በረጋ ህሊና ቆም ብለው እንዲያስቡ እመኛለሁ። ጊዜ አለው ለሁሉም። ጊዜ በራሱ ቀመር የራሱ ተገላቢጦሽ አለው። እየተገደሉ ያሉት ወጣቶች የሰው ልጆች እንጂ ከጭቃ የተሰሩ ጡቦች አይደሉም። እና የማንመኘው ዘመን እንዳይመጣ መስጋት ይገባል።

በርግጥ ጊዜው ደርሶአል። ‘ጊዜው የደረሰን አሳብ ማቆም አይቻልም።’ ይባላል። በአመፅ ላይ ያለውን የኦሮሞን ህዝብ ወይም በጥቅሉ የመብት ጥያቄ እያነሳ ያለውን ኢትዮጵያዊ ማፈንም ሆነ ገድሎ መጨረስ አይቻልም። ወያኔ ጊዜ በማራዘም፣ በማሰላቸት፣ ድብደባውን በማጠንከር፣ በገፍ በማሰር፣ ግድያውን በመጨመር አመፁን አዳክሞ የማቀዝቀዝን ስልት እየተጠቀመ ነው። የኦሮሞን ህዝብ የመብት ጥያቄ ወደ ብሄር ግጭት በመጠምዘዝ ለሚወስደው ርምጃ ምክንያት ለማግኘት እየሞከረ ነው። “ኦነግ ከመጣ ይፈጀሃል” በሚል የተለመደ ማስፈራሪያ በተለይ የአማራውን የህብረተሰብ ክፍል ከጎኑ ለማሰለፍ እየሞከረ ነው። ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ ታህሳስ 15 2015 “Oromo Uprising: Danger and Opportunity” በሚል ርእስ ባስነበበው ፅሁፍ የኦሮሞን አመፅ መደገፍ ለኢትዮጵያ አንድነት አደጋ እንዳይኖረው ስጋቱን ገልፆአል። ይህን የመሰለ መሰረት አልባ ጥርጣሬ በአንድነት ሃይሎች ዘንድ ይደመጣል። ለመጥቀስ ያህል መሳይ ከበደ እንዲህ ብሏል፣

Oromo political leaders and activists, including those of the OLF, should openly state that the uprising is not only about Oromo land, Oromo peasants, and Oromia, but that it is also a democratic movement that includes and speaks for other ethnic groups as well. With few exceptions, the word “Ethiopia” is not mentioned even once in the numerous declarations made by Oromo leaders and activists. The Oromo leadership must understand that there is no point for other ethnic groups to rise and support the uprising if the whole concept of a common country is removed from the political horizon. Without unity, the removal presages chaos, which is enough to stifle the will to show solidarity with the Oromo revolt.

መሳይ ከበደ ስጋቱን ከማስነበቡ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ግን OLF በለቀቀው መግለጫ እንዲህ ብሎ ነበር፣

This cruel regime is able to commit all these crimes by dividing the people of Ethiopia. Now, time is an essence for all peoples in Ethiopia to stand firm with Oromo people who have been fighting the TPLF regime for freedom, democracy, justice and human rights. The Oromo struggle is a struggle for freedom, justice, equality and human rights. When Oromo people are free from TPLF regime, all people in Ethiopia will be free. We are also encouraged by the support and solidarity of different Ethiopian political & Civil Organizations against the massacre of Oromo students and farmers by the TPLF regime. Now!
The OLF calls upon all Ethiopian to join the Oromo people struggle for freedom, democracy, justice & human rights, and once for all to dismantle the genocidal regime of TPLF. To that effect , the OLF calls for all inclusive struggle that include all political parties and civil organizations that will enable the Peoples in Ethiopia to decide their destiny by establishing government of people , for people and by people in Ethiopia.

We also warn everybody to be vigilant against possible evil actions of the TPLF to instigate animosity in the country by destroying property and killing none Oromo’s and blaming on Oromo’s. The TPLF will do this to disrupt this genuine movement towards freedom, democracy, human rights and justice. The Ethiopian people should be aware of the motives of the TPLF as it has been doing for the last 24 years since it seized political power in Ethiopia. It is widely known that the Oromo people have no problem with other people of Ethiopian, except with the TPLF and the systems that have been killing them, disposing them from their lands, arresting them & torturing them.

“OLF 40 አመታት ታግሎ አንድ ወረዳ እንኳ አልያዘም” የሚለው የአንዳንድ ወገኖች ሽሙጥ እውነት አዘል ትረባ አልነበረም። የኦሮሞ ህዝብ ትግል ልብና አእምሮን ከጨቋኙ ስርአት ነፃ እያወጣ በመጨረሻ ይህን ህብረ ትግል፤ ይህን ማመን የማይቻል ሰላማዊ አመፅ ለማየት አስችሎናል። ከአባዱላ እና ከባጫ ደበሌ በቀር የOPDO አባላት ልባቸው ውስጥ ከማንኛውም ኦሮሞ ያልተለየ ተመሳሳይ ጥያቄ አለ። መጫና ቱለማ ማህበር የለኮሰው ጥያቄ በቦታው አለ። የኦሮሞ ህዝብ ነባር ጥያቄዎች ገና ምላሽ አላገኙም። ከአሊ ቢራ እስከ ሃጫሉ ሁንዴሳ፣ ከመረራ ጉዲና እስከ ዱጋሳ በከኮ የኦሮሞ ህዝብ መንፈስ አንድ መሆኑ እየታየ ነው። እነ አቦማ ምትኩ፣ እነ መገርሳ በሪ፣ እነ አባጢቂ ኢንሰርሞ፣ እነ ዶሪ በሪ ሃሞ፣ እነ ይገዙ በንቲ፣ እነ ጨጨብሳ፣ እነ ፋፋም ዶዮ፣ እነ ኢረና ቀጨሌ ህይወታቸውን የሰጡለት ትግል በመጨረሻ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሶአል። እነ ባሮ ቱምሳ፣ እነ ማሞ መዘምር፣ የዚህ አመፅ መነሻ የሆነችው ጀልዱ ያፈራቻቸው እነ አለሙ ቂጤሳ ያነሱት ጥያቄ ዛሬ በሚሊዮኖች ተደግፎ ድምፃቸው እየተሰማ ነው። ማፈን አይቻልም። የመብት ጥያቄ ነው። የኦሮሞ ህዝብ በፖለቲካና በሃይማኖት ሳይለያይ በአንድ ድምፅ እየጠየቀ ያለውን የመብት ጥያቄ ማቃለል ለአካባቢያችን አደጋ አለው። ርግጥ ነው፤ የኦሮሞ ህዝብ ሲወለድ ጀምሮ አብሮት የመጣ መብቱን በጉልበቱ መንጭቆ የራሱ እስኪያደርገው ድረስ ማንም ቢሆን በችሮታ አይሰጠውም። የከፈለውን ያህል ከፍሎም መብትና ክብሩን ማስጠበቁ የማይቀር ነው።

የዘመናችን ኦሮሞ ወጣት አንዲት ጥይት ሳይተኩስ ምን ማድረግ እንደሚችል ልምድ እና እውቀት አጊኝቷል። ያገኘው ልምድና እውቀት ሃያል መሳሪያ ነው። አመያ ላይ የአግአዚን ሬጅመንት ከበው ያርበደበዱት ወጣት ፈረሰኞችን አይተናል። ቆርጦ በገነፈለ ህዝብ ፊት የታጠቀ ወታደር እንደ አሪቲ ጉዝጓዝ ከመሆን በቀር ሊያደርግ የሚችለው ነገር የለም። አኖሌ ዋቆ እንዳለው፣ የህዝብን የቁጣ አይኖች የመቋቋም አቅም ያለው ባለጠመንጃ የለም። በዚህ በሶስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ የ71 ውድ ልጆቹን ህይወት ቢከፍልም ገዳዮቹ ላይ አፀፋዊ እርምጃ አልወሰደም። ስላልቻለ አይመስለኝም። ከገደሉበት በላይ መግደል እየቻለ እስካሁን ነፍስ አላጠፋም። መሞትን ያልፈራ መግደል እንደማይቸግረው ግልፅ ነው። እና በዚህ በሰሞኑ አመፅ ኦሮሞ ሲሞት እንጂ ሲገድል አልታየም። ይህ ታጋሽነት፣ ይህ ሰላማዊነት ወደ መራራ በቀልና ቁጣ ሊቀየር የሚችልበት እድል ግን አለ። ማስተዋል ይገባል። አለማስተዋል ለፀፀት ሊዳርግ ይችላል።

ብርሃኑ ነጋ እና ንአምን ዘለቀ ሲናገሩ የሰነበቱትን ተከታትያለሁ። ባርኔጣዬን አንስቼላቸዋለሁ። አርበኞች ግንቦት7 ከኦሮሞ ህዝብ ትግል ጎን ለመቆም ያሳየውን ቁርጠኛነት ማክበር እና ማወቅ የሚገባ ይመስለኛል። ኢሳት ቴሌቪዠን የኦሮሞን ህዝብ አመፅና መስዋእትነት የራሱ ጉዳይ አድርጎ በመውሰዱ ሊመሰገን ይገባዋል። ሰማያዊ ፓርቲና መኢአድ ታክቲካዊ ሳይሆን ስታራቴጂያዊ ርምጃ መውሰድ መቻል አለባቸው። የኦሮሞን ህዝብ አመፅ ከልብ ደግፈው ማበር ከቻሉ ለአካባቢያችን መረጋጋት ጠቃሚ ውጤት ያመጣል። የተከፋፈለ ቤት ሲቆም አላየንም። በመጪው ዘመን በአንድ ጎጆም ሆነ በጉርብትና አብሮ መኖር የማይቀር ስለሆነ ስለነገ አጥብቆ ማሰብ ይገባል። በዚህ ወቅት ከኦሮሞ ህዝብ ጎን አለመቆም የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያዊነት ማእቀፍ ስር ለመኖር ያለውን ጥቂት ተስፋ መግደል መሆኑን የማይገነዘብ ፖለቲከኛ ኢትዮጵያን ወደ ገሃነመ እሳት ለመጨመር እንደተባበረ ማወቅ አለበት። የማንመኘው አደጋ ከደረሰ ችግሩ የእያንዳንዱን ዜጋ ጎጆ ሊያንኳኳ ይችላል። የኦሮሞ ህዝብ የመብት ጥያቄዎች በሌሎች ኢትዮጵያውያንም ሲነሱ የቆዩ ናቸው። ወያኔ እንደ ኢሰፓ ስርአት ተግባራዊ ያማያደርገውን አዋጅ፣ ፖሊሲና ድንጋጌ ሲያረቅና ሲያፀድቅ የኖረ ቡድን እንደመሆኑ ስርአቱን የመቀየር ጥያቄ ትግራይን ጨምሮ የመላ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል።

ሶስተኛ ሳምንቱን የያዘው የኦሮሞ ህዝብ አመፅ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ብቻ የተያያዘ አይደለም። በርግጥ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን መቃወም የአመፁ ቀዳሚ መፈክር ነው። ተያያዥ ጥያቄዎችም ግን በኦሮሞ ህዝብ ተቃውሞ ውስጥ እየተደመጡ ነው። “የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ!!” የሚለው ጥያቄም ዋና ነው። “በመሃመድ አላሙዲ ስም የሚካሄድ ዝርፊያ ያብቃ!!” ሌላው ጥያቄ ነው። የኦሮሞ ህዝብ ክልሉን ያለሞግዚት በራሱ ማስተዳደር ይፈልጋል። ይህም ቀዳሚ ጥያቄ ነው። Oromiyaan Haadursitu!! የሚል መፈክር መስማታችን ያለምክንያት አይደለም። ሲታፈንና ሲዳፈን ዘመናት ያስቆጠረው የመብት ጥያቄ ስርነቀል መፍትሄ ካላገኘ በጥገናዊ ለውጥ ጥያቄዎችን አፍኖ ማስቀረት የሚቻል አይደለም። የሚቻል የነበረበት ዘመን አልፎአል። እድሉም አምልጦአል።

ርግጥ ነው፤ የኦሮሞ ህዝብ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች የመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄዎች ናቸው። በቤኒሻንጉል እና በጋምቤላ ጭቆናና አፈና አለ። በደቡብ ኢትዮጵያም እንዲሁ ጭቆናውን እየተቃወመ የሚሰዋ ዜጋ አለ። በትግራይ ህወሃትን የሚቃወሙ አማፅያን አሉ። እየታገሉ እየተሰው ነው። የወልቃይትና የአርማጭሆ ሚሊሻ የወያኔን አፋኝ ስርአት በመቃወም ጠመንጃውን እንዳነገበ ሰልፍ ወጥቶአል። በሰራዊቱ ውስጥ ጭምር የአመፅ እንቅስቃሴዎች አሉ። በጥቅሉ ዛሬ የኦሮሞ ህዝብ ህይወቱን እየከፈለላቸው ያሉ ጥያቄዎች የመላ ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ናቸው። ተመስገን ደሳለኝ፣ እስክንድር ነጋ፣ አንዱአለም አራጌ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ እና አብርሃ ደስታ ወደ ወያኔ ማጎሪያ የተወረወሩት መሰረታዊ የሆኑ የሰው ልጆች ዴሞክራሲያዊ እና ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ በመጠየቃቸው ነው። “የአመለካከት ልዩነት አንድን ዜጋ እንዲሞት ወይም እንዲታሰር ሊያደርገው አይገባም” በማለታቸው በእስር ቤት ተቆልፎባቸዋል። አሊያም በተለያየ መንገድ እንዲሞቱ ተደርገዋል። ደበላ ጣፋ የገብረጉራቻ ልጅ ነው። ከዩንቬርሲቲ ትምህርቱ ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ፣ አስር አመታት ታስሮ፣ ከሁለት አመታት በፊት ተፈትቶ ነበር። መንፈሱ ባለመሰበሩና ተቃውሞውን በመቀጠሉ ገድለው ሬሳውን መንገድ ላይ ጣሉት። በኦነግ አባልነታቸው በደርግ ጊዜ ታስረው የነበሩት ኦቦ ሰኚ ዛሬም ቃሊቲ እስር ቤት ሲሆኑ፣ በጥቅሉ የእስር ቤት ህይወታቸው ወደ ሰላሳ አመታት ተጠግቶአል። በመላ ኦሮሚያ የተቀሰቀሰው አመፅ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ከመቃወም በላይ የመረረ ብሶት አምቆ የያዘ ነው። ከአቅሙ በላይ ተለጥጦ ሲያበቃ የፈነዳ አመፅ ነው። ሞት ወይም የመብቶች መከበርን በምሬት የሚጠይቅ ህዝባዊ አመፅ ነው።
መታወቅ ያለበት እውነት አለ። ገንፍሎ ያመፀው ህዝብ መንፈሱን አዳክሞ ለጨቋኙ ስርአት የመረጋጋት እድል ከሰጠ አንገቱን ለወያኔ የበቀል ካራ አዘጋጀ ማለት ነው። ስርአት እየተለዋወጠ ሲበዘበዝ የኖረው ህዝብ የሙሉ መብቶቹን መከበር እስከያረጋግጥ በፅናት ከመታገል የተሻለ አማራጭ የለውም። በዚህ ወቅት ማፈግፈግ መሞት ማለት ነው። ትግሉ በቅንጅትና በፅናት መቀጠል ከቻለ የሽግግር መንግስት ማቋቋም ያስፈልግ ይሆናል። ብሄራዊ የእርቅ ጥያቄ ወቅታዊ ሊሆን ይችላል። ጥላቻን ከሚያራግቡ ንግግሮችና ፅሁፎች መታቀብ ይገባ ይሆናል። የትግራይ ህዝብ እንደማንኛውም ሌላው ኢትዮጵያዊ የስርአቱ ሰለባ መሆኑን ከልብ ማመንም ይገባል።

በመጨረሻ – ልጆቹን ለሰዋ ቤተሰብ እግዚአብሄር አምላክ መፅናናቱን ይስጥ። አላህ ይርዳን!!

↧

የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላንተቃውሞ እና የመንግሥት ምላሽ፤አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ከሕግ አኳያ ትንታኔ-VOA Amharic

$
0
0

አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምሕርት ክፍል የቀድሞ መምሕር ነበሩ። በአውስትራሊያ ሜልበርን ከተማ፤ በሜልበርን የሕግ ትምሕርት ቤት “በሕገ-መንግሥት ሕግ” የዶክሬት ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል።የሕግ አስተማሪና ተመራማሪም ናቸው። በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ መደረግን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በድጋሚ ስላገርሸው ተቃውሞ እና የመንግሥት ምላሽ፤ ከሕግ አኳያ ትንታኔ ሰጥተዋል፡፡

↧
↧

“…ማን አለ እንዳንተ፣ ታማኝ?” -(በፍቃዱ ዘ ኃይሉ)

$
0
0

cvw1
የሆነ ጊዜ የሰማኋት ቀልድ ትዝ አለችኝ፤ አንዳንድ የተቃዋሚ ተወካዮች ፓርላማ ውስጥ በነበሩበት በዚያ በደጉ ጊዜ ነው አሉ፡፡ አንድ ተወካይ የሻዕቢያ መንግሥት ላይ ሊደረግ ስለሚገባው እርምጃ ሲናገሩ እንዲህ አሉ፤ “አሁኑኑ ገብተን ድምጥማጣቸውን ማጥፋት አለብን፡፡ አለበለዚያ ካደሩ አይቆረጠሙም፤ እነዚያ ወያኔዎችም ያኔ ሲመሠረቱ ሳንጨፈልቃቸው ዝም ብለናቸው ነው ዛሬ አናታችን ላይ…” አሉና ያሉበት ቦታ ትዝ ሲላቸው ድንግጥ ብለው ወደአቶ መለስ መቀመጫ አማተሩ፡፡ አቶ መለስ በጥሞና ያዳምጣሉ፤ ተወካዩ እንደደነገጡ “…ልጨርሰው ወይስ ትጨርሰኛለህ?” አሉ ይባላል፡፡
የሕወሓት/ኢሕአዴግ ወታደሮች አዲስ አበባ ደርሰው “ሲቪል” መንግሥት ከመመሥረታቸው አስቀድሞ “እኩይ” ናቸው በሚል ሲቃወማቸው የነበረ እና እስካሁንም ስክነቱ ያልተለየው አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው፡፡ የታማኝ የአክቲቪስትነት ሪከርድ ከኮሜዲያንነቱ የሚመዘዝ ነው፡፡ በቀልዶቹ ቢጀምርም አሁን ግን በጣም ‹ሲሪዬስ› ነው፡፡ አሁን እነቪኦኤ፣ ዶቸ ቬሊ፣ ኢሳት በየቤቱ እንደሚደመጡት ከደርግ ማክተሚያ ቀደም ብሎ ብዙ ሰው በየቤቱ ‹ድምፂ ወያነ›ን በድብቅ ያደምጥ ነበር፡፡ የፕሮፓጋንዳ ሚዲያዎች አመል ነውና ያው ውሸታቸው አይጣል ነው፡፡ ታዲያ ታማኝ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቀርቦ የምሩን ሲቀልድ ‹እዚህ ቦታ ይሄን ያክል ሻለቃ ጦር፣ እዚያ ቦታ ደግሞ ይሄን ያክል ሻለቃ ጦር ደመሰስን ይላሉ፡፡ ሲደመር ግን ይሄን ያክላል፡፡ ቆይ እኔ የምለው ወያኔዎቹ የሚደመስሱት ጦር ከጠቅላላ ጦሩ በለጠ እኮ፤ ከየት እያመጡ ነው የሚደመስሱት?› ዓይነት ቀልድ ተናግሮ አላገጠባቸው፡፡ ከዚያ በድምፂ ወያነ መልስ ተሰጠው፤ “ቁጥሩን አዲስ አበባ ስንደርስ እናወራርዳለን” የሚል፡፡ ዛቻ የሽፍትነት ዘመንም አመል ነበረች፡፡
ግንቦት 20/1983 – ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ሲረግጥ፣ ሲ ኤን ኤን ካነጋገራቸው ሰዎች አንዱ ታማኝ በየነ ነበር፡፡ “በመሣሪያ ተከበናል፣ ምንም ሠላም የለም…” የሚል ነገር ለጋዜጠኛው ሲነግረው ይታያል፡፡ ታዲያ ታማኝ ሁኔታውን በቀልድ ሲያስታውስ “ጓደኞቼ ከውጪ ደውለው ‹ሲ ኤን ኤን› ላይ አየንህ ሲሉኝ፣ ወዲያውኑ እንግሊዝኛዬ እንዴት ነበር?” አልኳቸው ይላል፡፡
ታማኝ ከአዲሱ ስርዓት ጋር አብሮ መኖር በማይችልበት ሁኔታ የተቀያየመው፣ ካልተሳሳትኩ የወቅቱ ባለሥልጣናት፣ እነታምራት ላይኔ በተገኙበት ስታዲዬም ውስጥ በቀለደው ቀልድ ነው፡፡ እንደማስታውሰው ቀልዱ በማንነት ላይ የተመሠረተ እና ለኢሕአዴግ የማንነት ብያኔ የማይበገር ዓይነት ቀልድ ነው፡፡
ፍቃዱ ማሕተመወርቅ፣ የቀድሞዋ ዕንቁ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ነበር፡፡ በመጽሔትና ጋዜጦች አከፋፋይነትም ይታወቃል፡፡ አሁን መጽሔቱ ተዘግቶ “በታክስ ስም” ፍርድ ቤት እየተመላለሰ ይገኛል፡፡ ፍቃዱ ነጻው ፕሬስ ሲጀመር ጀምሮ ምኅዳሩን ያውቀዋል፤ እናም “እናንተ በደጉ ጊዜ ነው የመጣችሁት” እያለ ይቀልድብኛል፡፡ ያኔ (ማለትም የመጀመሪያው አንቀጼ ላይ ‹ደግ› ባልኩት፣ ለፍቃዱ ግን ‹ክፉ› ግዜ) አንድ ሰው ስርዓቱን የሚያስቀይም ንግግር ሲናገር፣ እንዳሁኑ በሕግ ሥም ፍርድ ቤት አይመላለስም፣ የደረሰበት ይጠፋና ከአራት አምስት ወር በኋላ ተመልሶ ይመጣል፡፡ እንዳይሞት እንዳይሽር ተቀጥቅጦ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ከዚያ ወዲህ ያሻሻልነው ነገር ቢኖር ፍርድ ቤት የመቅረብ ዕድል መፈጠሩ ነው ማለት ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ ይህን ያነሳሁት ታማኝ ላይ የደረሰውም እንዲህ ያለው ነገር ነው ለማለት ነው፡፡
ታማኝ ተሰደደ፡፡ ብዙዎች ሲሰደዱ አቅላቸውን ያጣሉ፡፡ የሀገር ቤት ናፍቆት መመለስ ካለመቻሉ ጋር ተደማምሮ ይሁን፣ የሄዱበት አገር ኢሕአዴግ የማይደርስባቸው ከመሆኑ በተጨማሪ የሚያዩት ነጻነት ስለሚያስቀናቸው አላውቅም ብቻ ጠርዝ ይይዛሉ፡፡ ጥቂቶች ብቻ ሚዛናቸውን በጥፍራቸው ቆንጥጠው ይቆማሉ፡፡ ታማኝ ለኔ ከጥቂቶቹ አንዱ ነው፤ ያውም በረዥም ቆይታ ይህንን ማስመስከር የቻለ፡፡ ታማኝ አሁን አክቲቪዝሙን የሚሠራው ብዙ ጊዜ የቪዲዮ ማስረጃዎችን እያቀረበ ነው፡፡ ቪዲዮዎቹን ዩቱዩብ ላይ ሳያቸው በክምችቱ እቀናለሁ፡፡ ለረዥም ጊዜ የአገር ቤት ጉዳይን እየተከታተሉ፣ ማስረጃዎችን እየሰበሰቡ የመቆየት ፅናት የገቡበትን ጉዳይ ርዝመት እና ክብደት ከመረዳት ይመነጫል፡፡
የማስረጃ ነገር ከተነሳ አይቀር፣ አሁን እነ ታማኝ ማስረጃ ዶት ኮም (masreja.com) የተባለ ድረአምባ ፈጥረዋል፡፡ ድረአምባው በአሁኒቷ ኢትዮጵያ ውስጥ በሕግ የበላይነት ፈንታ ራሳቸው ከሕግ የበላይ ሆነው ወንጀል የሚፈጽሙ ሰዎች ላይ ማስረጃ የሚሰበሰብበት ነው፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ እኔ በይቅርታ አምናለሁ፤ እስከዛሬ አዲሱ ያለፈውን እየቀጣ የመጣበት ዑደት ቢያንስ የእኛ ትውልድ ላይ ቢቆም እያልኩ እመኛለሁ፡፡
ይህንን በተመለከተ ጓደኛዬ ሶሊያና “ይቅርታ ከፍትሕ ጋር መጋጨት የለበትም” ብላ ሞግታኛለች፡፡ ልክ ነች፤ በወቅቱ የሰጠችኝን ምሳሌ ከወቅታዊው ሁኔታ ጋር አዋህጄ ልናገር፤ “‪#‎OromoProtests‬ ላይ ልጇ የተገደለባት እናት የስርዓት ለውጥ ቢመጣ እና ለገዳዩ ወታደር ይቅርታ አድርጊለት ብትባል ፍትሕ ተደረገልኝ ብላ ታምናለች?” በወቅቱ፣ ሶሊም እኔም ጥያቄውን ከመጠየቅ በቀር መልስ መስጠት አልቻልንም፡፡ እርግጥ ነው ልጁ የሞተው የመጣው ለውጥ እንዲመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በምሳሌያችን መሠረት አወዛጋቢው ማስተር ፕላን ቢሰረዝ እንኳን ልጁ የለውጡ እሸት ተጋሪ ላይሆን አልፏል፡፡ ይቅርታ ለአገሪቱ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ያስፈልግ ይሆናል፤ የቤተሰቡን አባል ወይም ወዳጁን ላጣው ግለሰብ ግን ፍትሕ ሆኖ ይሰማዋል ማለት አይቻልም፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ለይቅርታውም ቢሆን ማስረጃውን መሰብሰብ አስፈላጊ ነው፡፡ አጥፊው ጥፋቱን እንዳይክድ፣ ይቅርታ ጠይቁኝ ባዩም በማስረጃ እንዲሞግት፡፡
ማስረጃ መሰብሰብ ሕገ-ወጥ መስሏችሁ የምትፈሩ ካላችሁ አትሳሳቱ፡፡ ሕጋዊ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግሥት ራሱ በፀረ-ሙስና ኮሚሽን በኩል አላግባብ የተገኘ ሀብት ካለ በሚል የባለሥልጣናቱን ሀብት ምንጭ ሳይቀር የማጣራት ማንዴት አለው፡፡ ቁርጠኝነቱ ስለሌለ አልተሳካላቸውም፤ እኛ ግን ይሳካልናል፡፡ በየቀኑ ከታችኛው እርከን (ወረዳ) እስከ ላይ ድረስ የምንጠየቃቸውን ጉቦዎች፣ ባለሀብቱና ባለሥልጣናቱ (ሁለቱም አንድ ናቸው) ኢ-ርትዓዊ በሆነ መንገድ የሚያካብቱትን ሀብት፤ ከትላልቆቹ እስከ ትናንሾቹ ሹመኞች በሕዝብ ላይ የሚፈፅሙትን ግፍ፤ ትንንሽሽም፣ ትልልቅም ሠላማዊ ተቃውሞዎች በተነሱ ቁጥር በንፁሐን ዜጎች ነፍስ ላይ የሚሰነዘሩትን የኃይል እርምጃዎች የሚያጋልጡ ማስረጃዎች ባገኘን ቁጥር ለማስረጃ ዶት ኮም በመላክ ለኢትዮጵያችን የወደፊት መልካም ዕጣ ፈንታ ሲባል እንዲከማቹ የበኩላችንን እናድርግ፡፡ ማስረጃዎቹን መሰብሰቡ ሌላው ቢቀር አጥፊዎቹን ስለሚያስፈራቸው በደላቸውን ሊያላሉልን ይችላሉ፡፡
ቪቫ ላ ታማኝ!!!

↧

‹‹ሦስት መቶ ሺሕ ሔክታር መሬት እንዲሰጡኝ አልጠየቅሁም ፤ የጋምቤላ ክልል ኃላፊዎች ግን ሦስት መቶ ሺሕ ሔክታር መሬት እንሰጥሃለን ቢሉኝም እኔ ማልማት የምችለው አሥር ሺውን እንደሆነ ገልጬ ነበር፤››የካሩቱሪ መሥራች ሳይ ራማክሪሽና ካሩቱሪ

$
0
0

wk
ካሩቱሪ ለሁለተኛ ጊዜ ሐራጅ ወጣበት
የህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ በእህት ኩባንያው ካሩቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በኩል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረውን 55.8 ሚሊዮን ብር ሊከፍል ባለመቻሉ ሐራጅ ተባለ፡፡

ባለፈው ዓመትም በ65 ሚሊዮን ብር ዕዳ ባንኩ ሐራጅ አውጥቶበት እንደነበር ሪፖርተር መዘመገቡ አይዘነጋም፡፡

ኩባንያው ካለበት 65 ሚሊዮን ብር ውስጥ 10 ሚሊዮን ብር ብቻ በአንድ ዓመት ውስጥ ለባንኩ ከፍሏል፡፡ በመሆኑም ንግድ ባንክ ለ55.8 ሚሊዮን ብር የብድር ዕዳ ያወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ እንደሚያመለክተው፣ ካሩቱሪ በጋምቤላ ክልል ለብድር ማስያዣነት ያስመዘገበው 100 ሺሕ ሔክታር መሬትና ሌሎች ንብረቶች በሐራጅ ተሽጠው ብድሩን ለማስመለስ ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ በመጪው ማክሰኞ ታኅሳስ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ጨረታው እንደሚከፈት የሚጠበቀው ሐራጅ፣ 100 ሺሕ ሔክታሩን ጨምሮ በዚያው መሬት ላይ የለማ 7,645 ሔክታር እርሻ፣ መጋዘን፣ የሠራተኞች መኝታ ቤትና ተገጣጣሚ ቤትን ለጨረታ አቅርቧል፡፡

ሪፖርተር ከንግድ ባንክ ባገኘው መረጃ መሠረት፣ ባንኩ የካሩቱሪ ንብረት የነበሩ ሁለት ተጨማሪ የውኃ መቆፈሪያ ማሽነሪዎችን ሸጦ ለዕዳ ማገገሚያነት አውሏል፡፡ የንግድ ባንክ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣ ሁለቱ ማሽነሪዎች በጠቅላላው 2.6 ሚሊዮን ብር አካባቢ ተሸጠው ገንዘቡ ለባንኩ ገቢ ተደርጓል፡፡

የካሩቱሪ መሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳይ ራማክሪሽና ካሩቱሪ በበኩላቸው ንግድ ባንክ፣ ‹‹የአገሪቱን ሕጎች የሚጥስ፣ ተገቢነት የጎደለውና እዚህ ግባ ለማይባል ጉዳይ…›› በማለት የገለጹትንና ባንኩ ያወጣውን የሐራጅ ማስታወቂያ እንዳሳገዱ በኢሜል ለሪፖርተር ቢገልጹም፣ ንግድ ባንክ በበኩሉ እስካለፈው ዓርብ የሥራ ሰዓት ማብቂያ ድረስ እንዲህ ያለው የሐራጅ ማሳገጃ ሰነድ እንዳልደረሰው አቶ ኤፍሬም ገልጸዋል፡፡ ይህም ሆኖ ካሩቱሪ ጨረታው ከሚያበቃበት ከመጪው ማክሰኞ በፊት ከሚጠበቅበት ዕዳ ውስጥ 25 በመቶውን በመክፈል ጨረታውን የማሳገድና የመደራደር መብት ሕጉ እንደሚፈቅለት አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር ካሩቱሪ ከዘመን ባንክ ጋርም በብድር ዕዳ ምክንያት እስከ ፍርድ ቤት የደረሰ መካረር ውስጥ ገብቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይህንን ያመኑት ራም ካሩቱሪ፣ በፍርድ ቤት የነበረው ሒደት በስምምነት ተቋጭቶ በአሁኑ ወቅት ለዘመን ባንክ የሚከፈል 26 ሚሊዮን ብር ዕዳ ኩባንያቸው እንዳለበት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ለሃምሳ ዓመታት በሚቆይ የሊዝ ስምምነት መንግሥት ለካሩቱሪ የሰጠው መሬት እጅግ ዝቅተኛ በሚባል ዋጋ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ኩባንያው ከስድስት ዓመት በላይ በተሰጠው እርሻ ቦታ ላይ ተገቢውን ልማት ማከናወን ሳይችል ቆይቷል፡፡ በእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የግብርና ኢንቨስትመንትና መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ሙላት ዓምና በጉዳዩ ላይ ተጠይቀው ለሪፖርተር በሰጡት ማብራሪያ፣ ኩባንያው ይጠበቅበት የነበረውን ሥራ ማከናወን ሳይችል ቀርቷል፡፡

ካሩቱሪ በገባበት አስተዳደራዊ ቀውስ ምክንያት ለኪሳራ ከመዳረጉም በላይ፣ ወደ መዘጋቱ እያዘገመ ያለ ኩባንያ ለመሆን እንደበቃ አቶ አበራ መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡ ኩባንያውን በቦርድ የሚመሩት 19 ግለሰቦች ሲሆኑ፣ በመካከላቸው በተፈጠረ የአመራር ችግር ኩባንያው ለኪሳራ ተዳርጎ እያለ፣ በአንፃሩ መንግሥት ለኢንቨስትመንት የሚመች ዕድል እንዳልፈጠረለት በመግለጽ ስም ማጥፋቱን አቶ አበራ ኮንነው ነበር፡፡ በዝቅተኛ ገንዘብ ከተሰጠው የሊዝ መሬት ባሻገር በርካታ ማሽነሪዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገባ እንደተፈቀደለትም ጠቅሰው ነበር፡፡ የፋይናንስ ችግሮች አጋጥመውትም፣ ለአገር ውስጥ ኩባንያዎች ብቻ የፈተቀደውን የማሽነሪ ማከራየት ሥራ ለካሩቱሪ ብቻ ተፈቅዶለት ሲሠራ እንደነበር አቶ አበራ አስታውሰዋል፡፡ ኩባንያውም ይህንን እውነታ በዓመታዊ ሪፖርቱ መጥቀሱን ሪፖርተር አረጋግጧል፡፡
ይሁንና ሰሞኑን ስለሚገኝበት ሁኔታና ስለታዩ ለውጦች ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁት አቶ አበራ፣ ሚኒስቴሩ ባለው የሚዲያ ግንኙነትና አሠራር ቢሮክራሲ ሳቢያ በቀጥታ መግለጫ ከመስጠት እንደሚቆጠቡ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ይሁንና ከዚህ በፊት ሪፖርተር በዘገበው ዜና ላይ ኩባንያቸው ከእንግዲህ እምነት የሚጣልበት እንዳልሆነ፣ ቀውስ ውስጥ የሚገኝና ኪሳራ ውስጥ የወደቀ ኩባንያ ሆኗል ተብሎ የቀረበበትን ትችት ክፉኛ ያጣጣሉት ራም ካሩቱሪ፣ ምንም እንኳ የእርሻ አፈጻጸማቸው የሚያበሳጭ መሆኑን ቢያምኑም በዚህ ደረጃ ስለኩባንያቸው መገለጹ ግን እንደ ወንጀለኛ መቆጠራቸውን የሚጠቁም አድርገው እንደሚወስዱት ተናግረዋል፡፡ ንግድ ባንክን ጨምሮ የመንግሥት ባለሥልጣናትንና የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴርን የኮነኑት ካሩቱሪ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘመቻ እንደተከፈተባቸው፣ ሪፖርተርን ጨምሮ ሚዲያው እሳቸውንና ኩባንያቸውን ለማሳቀል እንደተነሱ በመጥቀስ ለመብታቸው የትኛውንም ሕጋዊ መንገድ እንደሚጠቀሙ በመግለጽ ለማስጠንቀቅም፣ ለማስፈራራትም ሞክረዋል፡፡

ካሩቱሪ ከጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 300 ሺሕ ሔክታር መሬት በሊዝ ወስዶ ነበር፡፡ ኋላ ላይ ከፌደራል መንግሥት ጋር በተደረገ ድርድር ኩባንያው የወሰደው የመሬት መጠን ወደ አንድ መቶ ሺሕ ሔክታር እንዲቀንስ መደረጉን አስታውሰዋል፡፡ ካሩቱሪ በሊዝ ለወሰደው መሬት በሔክታር ሃያ ብር ያህል መክፈሉም ይታወቃል፡፡
ይሁንና ካሩቱሪ 300 ሺሕ ሔክታር መሬት እንዲሰጠው እንዳልጠየቀ፣ ይልቁንም የማልማት አቅሙ 10 ሺሕ ሔክታር መሬት እንደነበር ካሩቱሪ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሦስት መቶ ሺሕ ሔክታር መሬት እንዲሰጡኝ አልጠየቅሁም፡፡ የጋምቤላ ክልል ኃላፊዎች ግን ሦስት መቶ ሺሕ ሔክታር መሬት እንሰጥሃለን ቢሉኝም እኔ ማልማት የምችለው አሥር ሺውን እንደሆነ ገልጬ ነበር፤›› በማለት የገለጹት ካሩቱሪ፣ ይሁንና የክልሉ ባለሥልጣናት ከ300 ሺሕ ሔክታር በታች እንደማይሰጧቸው ገልጸው እሳቸው በሚስማሙበት ዋጋ በሊዝ እንዲገዙ ባለሥልጣናቱ እንዳግባቧቸው ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የንግድ ባንክን ዕዳ አከፋፈል በተመለከተ ተጠይቀው፣ ያለባቸውን ዕዳ የሚከፍሉት በሌላ ትልቅ ኩባንያ ላይ ያላቸውን 100 ሚሊዮን ብር ማግኘት ሲችሉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ኩባንያቸው ከንግድ ባንክና ዕዳ አለበት ካሉት ኩባንያ ጋር የሦስትዮሽ ስምምነት በመፈረም ዕዳውን ለመክፈል እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይሁንና አቶ ኤፍሬም ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣ ባንኩ እንዲህ ያለውን ነገር የማያውቀውና በጽሑፍም የደረሰው ምንም ነገር የለም፡፡

ባለፈው ዓመት የእርሻ መሣሪዎችና ቁሳቁሶች ሽያጭ ለማካሔድ ማስታወቂያ ማውጣቱን ተከትሎ ካሩቱሪ ትኩረት ስቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ራም ካሩቱሪ በወቅቱ ከሪፖርተር ስልክ ሲደወልላቸው፣ ከህንድ ባንጋሎር ከተማ ሆነው አስተያየት መስጠታቸውም ይታወሳል፡፡ ኩባንያቸው በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ለሽያጭ ያቀረባቸው ማሽነሪዎች ግን ከአገር ለመውጣት በማሰብ ሳይሆን፣ ኩባንያው አገር ውስጥ ያለበትን የባንክ ዕዳ ለመክፈል ያደረገው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ኩባንያቸው ከንግድ ባንክ፣ ከዘመን ባንክና ከዳሸን ባንክ ብድር ወስዷል፡፡ ጠቅላላ ያለበት የብድር ዕዳ 170 ሚሊዮን ብር ያህል መሆኑን የጠቀሱት ራም ካሩቱሪ፣ ይህንን ዕዳ ባለፈው ዓመት እንደሚዘጉ ገልጸው ነበር፡፡ ይሁንና አሁንም ድረስ በባንክ ዕዳ ጥያቄ እየቀረበባቸው ይገኛሉ፡፡ ለሽያጭ ቀርበው የነበሩት ማሽነሪዎች ዋጋ 15 ሚሊዮን ብር እንደነበርና አገልግሎት ሰጥተው በትርፍ ንብረትነት የተመዘገቡ ንብረቶች ላይ የሽያጭ ማስታወቂያ በማውጣት ሽያጭ መከናወኑን በወቅቱ ተናግረዋል፡፡
ካሩቱሪ በኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ቶን በቆሎ፣ ሩዝ፣ የፓልም ተክልና ሌሎች የግብርና ውጤቶችን ለማምረት አልሞ መነሳቱ ይታወሳል፡፡ ራም ካሩቱሪ ይህንን ህልማቸውን ለማሳካት አሁንም ቁርጠኛ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስለኩባንያው ለመነጋገር በጠሩት ስብሰባም የኩባንያው ችግሮች ላይ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ኩባንያው ማስተካከል አለበት ያላቸውን ችግሮች ማስተካከሉን፣ በአሁኑ ወቅት በአራት ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ ከ30 ሺሕ ቶን በላይ በማልማቱ ለጎረቤት አገሮች ለመሸጥ እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡ ሆኖም ከጋምቤላ አዲስ አበባ ምርቱን ማጓጓዝ የሚጠይቀው የትራንስፖርት ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ፣ በደቡብ ሱዳን በኩል ምርቱን ለማውጣት ብቸኛው አማራጭ እንደነበር ራም ካሩቱሪ ገልጸው ነበር፡፡
ካሩቱሪ ገና ከመምጣቱ ጀምሮ ነቀፋ ሲሰነዘርበት ቆይቷል፡፡ የተሰጠውን መሬት መነሻ በማድረግ በዓለም የስቶክ ገበያ ሽያጭ ማካሄዱ የኩባንያውን የካፒታል አቅም ጥርጣሬ ላይ እንደጣለው የሚገልጹ አልታጡም፡፡ የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ካሩቱሪን ጨምሮ ሌሎች ሰፋፊ እርሻ ለማልማት መሬት በወሰዱና ባላለሙት ላይ ጀርባቸውን ማዞራቸው ተሰምቷል፡፡ አቶ አበራ በቅርቡ በተካሄደ የሚኒስቴሩ ስብሰባ ወቅት እንዳስታወቁት፣ ከእንግዲህ ውጤታማ ባልሆኑ ባለሀብቶች ላይ የካሩቱሪ ዓይነት ዕርምጃ ይወሰዳል፡፡
ካሩቱሪ ግሎባል ሊሚትድ ኢትዮጵያን ሜዶውስ፣ ሱሪያ ብሎሶምስ፣ ሺቫ ፓክስ የተባሉትን ጨምሮ ካሩቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ የተባሉትን ኩባንያዎች በአባልነት ያስተዳድራል፡፡

↧

ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ

$
0
0

kadd
ሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አዲስ አበባ ላይ በጋራ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸው የሚታወስ ሲሆን እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም በጋራ ሰልፍ መጥራታቸውን አቶ ነገሰ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲና መድረክ የጠሩት ሰልፍ በዋነኛነት ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ መንግስት እየወሰደው ያለውን እርምጃ፤ እንዲሁም መንግስት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ያቀደውን መሬቱ እንዳይሰጥ ለመቃወም ያለመ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰልፉ ላይ በሰብአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ መንግስት እየወሰደው ያለውን እፈና እና እርጃዎቸ እንደሚያወግዙ ምክትል ሊቀመንበሩ ተገልፆአል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ እና መድረክ በጋራ የሚያደርጉት ሰልፍ መነሻውን ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ አድርጎ፣ በቸርቺል አደባባይ የሚያልፍ ሲሆን መዳረሻው ኢትዮ-ኩባ አደባባይ መሆኑን ታውቋል፡፡ መንግስት እየወሰዳቸው ባሉ የተሳሳቱ እርምጃዎች ሀገራችን አጣብቂኝ ውስጥ መሆኗን የገለፁት አቶ ነገሰ ተፋረደኝ ሀገራችን ካለችበት ችግር ለማውጣት ኢትዮጵያውያን በጋራ እንዲቆሙና በሰልፉም እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ሰልፉ እሁድ ታህሳስ 17/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ ላይ እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል፡፡

↧
Viewing all 212 articles
Browse latest View live