Quantcast
Channel: Kalkidan Amharic – Kal Tube
Viewing all 212 articles
Browse latest View live

ሕገ መንግስታዊነት እንዲሰፍን የሚፈሰው ተጨማሪ ደም ይገደብ! ( ዞን 9)

$
0
0

cv
የአዲስ አበባ ከተማና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላንን ተቃውመው ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል በርካታ ወረዳዎችና ከተሞች እያቀረቡት ያለው ሠላማዊ ጥያቄ በሰከነ መንገድ መልስ ለመስጠት ከመሞከር ይልቅ ተመጣጣኝ ያልሆነ ሀይል በመጠቀም ጥያቄውን ለማፈን እየተሞከረ ነው፡፡ በዚህ ሂደትም ብዙዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፣ ለቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ እስካሁን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎችም ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ሰሞኑን ከሚወጡት መግለጫዎችና የመንግስት ባለስልጣናት ቃለመጠይቆች እንደተረዳነው ጥያቄዎቻቸውን በሃይል ለመመከት ከመዛትና ዜጎችን ከሰው በታች አውርዶ ቁጣን በሚጋብዝ መልኩ ከመጥራት በዘለለ ሀላፊነት እንደሚሰማው አካል ለችግሩ መፍትሔ ለመፈለግ ዝግጁነት እንደሌለ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሁሌም እንዲከበር የምንጠይቀውን የሀገሪቱ ሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነውን ሕገ-መንግስት የሚጻረር ነው፡፡
በዚህ ሂደት በጥቂቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የሕገ-መንግስቱ አንቀጾች ተጥሰዋል
1. የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 15 የሕይወት መብት
‹‹ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› ቢልም ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር በተያያዘ ከ8 ዓመት ልጅ አንስቶ እስከ የ80 ዓመት አዛውንት ድረስ ሕይወት እየተቀጠፈ ነው፤ እስከዛሬ የሞቱት ሰዎች ቁጥር በሶስተኛ ወገን ማረጋገጥ ባይቻልም ጉዳዬን በቅርበት የሚከታሉ ሰዎች እንደዘግቡት ወደ መቶ እየተጠጋ ይገኛል፡፡
2. የሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 15 የአካል ደኅንነት መብት
‹‹ማንኛውም ሰው በአካሉ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የመጠበቅ መብት አለው፡፡ ›› አሁንም ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር በተያያዘ በጥይት የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ቁጥራቸው በርካታ ነው፡፡ ድብደባ እና አላግባብ አንግልት የደረሰባቸውንም ቤት ይቁጠራቸው፡፡
3. አንቀጽ 24.1 የክብርና የመልካም ስም መብት
‹‹ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው፡፡ ›› እየሆነ ያለው ዜጎችን አጋንንት እያሉ መጥራት፣ ጥፋተኛ ተብለው በሕግ ያልተፈረደባቸውን አሸባሪ እያሉ ክብራቸውን በሚዲያ መግፈፍ ነው፡፡
4. አንቀጽ 30.1 የመሰብሰብ፤ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት
‹‹ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ከቤት ውጭ የሚደረጉ ስብሰባዎችና ሰላማዊ ሰልፎች በሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች በሕዝብ እንቅስቃሴ ላይ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ ወይም በመካሔድ ላይ ያለ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ሰላምን፣ ዴሞክራሲያዊ መብቶችንና የሕዝብን የሞራል ሁኔታ እንዳይጥሱ ለማስጠበቅ አግባብ ያላቸው ሥርዓቶች ሊደነገጉ ይችላሉ፡፡ ›› ቢልም መንግስት ይህን የህገ መንግሰቱን አንቀጽ በመጣስ ብዙ ሰብዓዊ ጉዳቶችን አድርሷል፡፡

ዜጎች ለመረጃ ቅርብ በሆኑበት በዚህ ጊዜ መንግስት እያደረጋቸው ያሉትን ተግባራት መካድ፣ እንዲሁም እንደሌሉ አደርጎ ለማስተባበል መሞከር ብዙ ኃላፊነት የሚጠበቅበት መንግስት የሚያሰገምትና ትዝብት ላይ የሚጥል ነው፡፡ ይህ የመንግስት ግዴለሽነት ብዙኃን ዜጎችን እየገፋ ከመስመር እያስወጣ ነው፡፡ ሰላማዊውን የሕዝብ እንቅስቃሴ ወደ አመጽ እና ወደአልተፈለገ ዕልቂት ከመግፋት ይልቅ የተቀናጀ የጋር ማስተር ፕላኑን መሰረዝ፣ በዚህ ሒደት ጥፋት የፈጸሙ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አስፈጻሚ አካላትን ለፍርድ ማቅረብ፣ የግል ተበዳዮችን መካስና ሌሎች አስፈላጊ የመፍትሔ እርምጃዎችን ሁሉ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡ ሁልጊዜም እንደምንለው በሰላማዊ መንገድ የመብት ጥያቄ ማቅረብ ወንጀል አይደለም፡፡ መንግሰት በሰላማዊ መንገድ መብታቸውን ከሚጠይቁ ዜጎች ጋር እልህ አይጋባ ፣ ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸው ይከበሩ ፣ የመብት ጥሰት ድብደባ እና ግድያው ይቁም፡፡ ሕገ-መንግስታዊነት የታሰርንለት፣ ከሀገር የተሰደድንለት፣ ብዙ ዋጋ የከፈልንበትና አሁንም እየከፈልንበት ያለ ዐሳብ ነውና በሀገሪቱ ህጋዊነት እንዲሰፍን ህይወታቸውን እስከመስጠት ድረስ ዋጋ ለከፈሉ ዜጎች ክብር እንሰጣለን፡፡ ለሕገ መንግስታዊ ስርዓት መስፈን ዜጎች የከፈሉት ዋጋ እጅግ ብዙ እና ከበቂ በላይ ነውና ተጨማሪ ሰብዓዊ ዋጋ መክፈል ሳያፈልገን ሕገ መንግስቱ እንዲከበር አንጠይቃለን፡፡
ሕገ-መንግስቱ ይከበር!


በኦሮሚያ ክልል የሟቾች ቁጥር ከ85 በላይ መድረሱ ተሰማ-VOA Amharic

$
0
0

በኦሮሚያ ክልል የሟቾች ቁጥር ከ85 በላይ መድረሱ ታወቀ። እናትና ልጅ ተገድለው ለሦስት ቀናት እሬሳው እንዳይነሳ ተደርጓል ያሉት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኰንግሬስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ እስራቱ በመቀጠሉ በርካቶች ቤታቸውን ጥለው ጫካ መግባታቸውን የፓርቲውም አባላት እየታሰሩ መሆናቸውንና እሳቸውም በግል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል።ያዳምጡት።

“ሰብዓዊ መብቶች ገደብ የላቸውም”ከሕግ ባለሞያ አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ጋር የተደረገ ቃል ምልልስ (ክፍል ሁለት)-VOA Amharic

$
0
0

አቶ ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምሕርት ክፍል የቀድሞ መምሕር ነበሩ። በተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት የሰብዓዊ መብትና መልካም አስተዳደር ዴስክ ኃላፊ ኾነው ሠርተዋል።አሁን ደግሞ በአውስትራሊያ ሜልበርን ከተማ፤ በሜልበርን የሕግ ትምሕርት ቤት “በሕገ-መንግሥት ሕግ” የዶክሬት ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል።
ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ሰሞኑን እየታየ ያለውን ያለመረጋጋት የቀሰቀሰው ተቃውሞ የሽብር አድራጎት ሳይሆን በሃገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ሕግጋት የተፈቀደ፣ መዘዞቹ ደግሞ በሕግ አግባብ ሊታዩ የሚችል የተቃውሞ አቀራረብና መብትም ነው ሲሉ የሕግ አስተማሪና ተመራማሪው አቶ ፀጋዬ ረጋሳ አራርሳ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡

በማዕከላዊ እጁን ታስሮና ተሰቅሎ በተገረፈበት ወቅት የግራ እጁ አጥንት የተሰበረበት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር ህክምና እንዳያገኝ ተደረገ

$
0
0

xa
የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝደንት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር የህክምና አገልግሎት እንዳያገኝ መደረጉን ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር በማዕከላዊ በደረሰበት ድብደባ እጁ፣ እግሩና ጆሮው ላይ ጉዳት የደረሰበት ቢሆንም ህክምና እንዳያገኝ መደረጉን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን በማዕከላዊ እጁን ታስሮና ተሰቅሎ በተገረፈበት ወቅት የግራ እጁ አጥንት የተሰበረ ሲሆን የእግር ጥፍሮቹም ተነቅለዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ጆሮው ላይ ጉዳት ደርሶበታል፡፡
በተለይ እጁ ላይ ቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልገው ተነግሮት የነበር ቢሆንም ከክኒን ውጭ ሌላ ህክምና እንዳልተሰጠው ቤተሰቦቹ ገልፀዋል፡፡ የ17 አመት ፍርደኛ የሆነውና በዝዋይ እስር ቤት የታሰረው አቶ ዘሪሁን በአሁኑ ወቅት ለህክምና ቃሊቲ የሚገኝ ቢሆንም አሁንም ህክምና እንዳላገኘ ቤተቦቹ ገልፀዋል፡፡ የዝዋይ እስር ቤትን ህክምና እንዲያገኝ በጠየቀበት ወቅት ‹‹ከቃሊቲ እስር ቤት ጋር እየተነጋገርን ነው፣ መኪና የለም›› በሚሉ ሰበቦች ህክምና ሳያገኝ ቆይቷል ያሉት ቤተሰቦቹ ወደ ቃሊቲ ከመጣ በኋላም ፖሊስ ሆስፒታል ተመርምሮ መድሃኒት ቢታዘዝለትም የታዘዘለትን መድሃኒት ‹‹ሀኪም አላየውም፡፡ ሀኪም ያረጋግጠው›› እየተባለ ህክምና እንዳያገኝ ተደርጓል ብለዋል፡፡ አቶ ዘሪሁን የፀረ ሽብር አዋጁ በወጣ በወራት ውስጥ ከታሰሩት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ረዳት መምህራን ቅሬታ አሰሙ-VOA Amharic

$
0
0

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባልደረቦች የሆኑ ከመቶ በላይ ረዳት መምህራን ከሁለት ዓመታት በፊት ለጠየቁት የሥራ ዕድገት መልስ እስካሁን እንዳልተሰጣቸው እየተናገሩ ነው፡፡
ቅሬታ አቅራቢዎቹ “ለከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ዕድገት እንዳንወዳደር ተደርገናል፤ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠውን የቤት ኪራይ አበልና ሌሎችም ጥቅማጥቅሞችን ተከልክለናል” ብለዋል፡፡
የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ-ትምህርት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱልቃድር ከድር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “ረዳት መምህራኑ የትምህርት ደረጃ ዕድገት በውድድር እንዲሆን ሕግ ስለሚያዝ እንጂ መብታቸውን አልተከለከሉም” ብለዋል፡፡

የቤት ኪራይ አበል መከልከላቸውን አስመልክቶ መምህራኑ ላነሱት ጥያቄ ሲመልሱ “ማግኘት እንደማይችሉ በሕግ ስለተደነገገ ነው” ብለዋል፡፡

ከትምህርታቸው በመባረር ላይ ያሉትን ተማሪዎች አስቧቸው!(ቻላቸው ታደሰ)

$
0
0

በ1990 ዓ.ም ነበር፡፡ ከ18 ዓመታት በፊት፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረት አመራሮች የነበርነው እኔ፣ አሰግድ ወርቃለማሁ እና ጌታነህ ይስማው ወደ ጎንደር፣ ዓለማያ፣ ባህር ዳር እና መቀሌ ዩኒቨርስቲዎች በመሄድ ነፃ የተማሪዎች መማክርቶች እንዲቋቋሙ በማድረግ የመላ ኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህብረትን ለማቋቋም መሰረት በመጣል ላይ ነበርን፡፡ መቼም ያኔ በመላ ሀገሪቱ የነበረው ተማሪዎች አንድነትና ራዕይ ልዩ ነበር፡፡ የዩኒቨርስቲው አመራር ጉዟችንን ቢቃወምም የተጓዝነው በራሳችን ህብረት ባጀት ነበር…
lkj32
ከተልዕኳችን ስንመለስ በሳምንታት ውስጥ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች አመፅ ተቀስቅሶ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ወደ ግቢው ገብተው በተማሪዎች ላይ ከባድ ድብደባ ፈፀሙ፡፡ እኛው በታዛቢነት ቁመን በመላ ተማሪው ያስመረጥናቸው አምስት የተማሪው አመራሮች በአመፁ እጃቸው እንዳለበት ተጠርጥረው በአያሌው ጎበዜ ፊርማ (በወቅቱ የክልሉ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ነበር) ከትምህርት ገበታቸው እንዲባረሩ ተደረገ፡፡ ልጆቹ ግን በአመፁ ጊዜ አመፁን ህጋዊ መስመር ለማስያዝና ሰላማዊ እንዲሆን ለማስቻል ተሰብስበው እየመከሩ እንጂ አመፅ እያደራጁ አልነበረም፡፡ እነዚያ ምስኪን ልጆች ለመጓጓዣ ከጓደኞቻቸው ለምነው በቀጥታ ወደ እኛው ግቢ ስድስት ኪሎ መጡ፡፡ “ለትምህርት ሚንስትሯ ወይዘሮ ገነት ዘውዴ አቤት በሉልን” አሉ፡፡
በስድስት ኪሎ ግቢ መኝታና ምግብ እንዲያገኙ አስድርገን በሚቀጥለው ጧት እኔና አሰግድ ወደ ሚንስትሯ ቢሮ ቁልቁል በረርን፡፡ ትንሽ ከተወያየን በኋላ አሰግድ እንዲህ አላት፤ “አሁን ያለሽን ብቸኛ ተስፋ አንቺ ነሽ፤ ውሳኔው በድሃይቱ ሃገርና በድሃዎቹ ወላጆቻቸው ላይ ከባድ ኪሳራ የሚያስከትል፣ አሳፋሪና የአካዳሚክና የመደራጀት መብትን አፈር ድሜ ያስጋጠ ውሳኔ ነው፡፡ ስለዚህ አስቀልብሽልን፡፡”
“እንደ ትምህርት ሚንስትርነቴ በክልሉ መንግስት ውሳኔ ውስጥ ጣልቃ መግባት አልችልም። ቢሆንም ግን እንደ ብአዴን አባልነቴ አያሌው ጓዴ ስለሆነ ውሳኔውን እንዲቀይር እለምነዋለሁ” ብላ ስልክ ለመደወል ተነሳች፡፡ “እባክህ አያሌው ውሳኔህን እንደገና እይላቸው፤ መቼስ ምን ይደረግ፤ ወጣቶች አይደሉ? እኛም እኮ ተማሪ እያለን እንረብሽ ነበር… ይኸው ከስድስት ኪሎ የመጡ ሁለት ልጆች ውሳኔውን ካላስቀየርሽ ከቢሮሽ አንወጣም ብለውኝ እኮ ነው…” መቼም እያዋዛች ማግባባት ትችልበታለች፡፡ (ሚንስትሯን ትንሽ ቀረብ ብዬ ስለማውቃት የምታገለግለው መንግስት ወለፈንድ ሆኖባት እንጂ ከተማሪ ጋር በቀላሉ መግባባት አያቅታትም ነበር፤ ተማሪን/ወጣትን የመረዳት ችሎታና ፍላጎቱ ነበራት፡፡)
ያም ሆነ ይህ ግትሩ አያሌው በውሳኔው ፀና፡፡ እንደገና እንደምትለምነው ነግራን በሚቀጥለው ጧት እንድንመለስ ነገረችን፡፡ ሰውዬው የጠላት ሀገር ዜጋ ከሀገር ያባረረ ይመስል አቋሙን ሳይቀይር ቀረ፡፡ የገበሬ ልጅ የሆነው “ገበሬው” አያሌው በገበሬ ገንዘብ፣ የገበሬ ሀገር በሆነችው ሀገር ጥሪት በሚማሩ የገበሬ ልጆች ላይ ያልተማረ ገበሬ እንኳን የማይወስነውን አርቆ አሳቢነት የጎደለው ውሳኔ በማሳለፍ ተማሪዎቹ እንደገና ተመልሰው ገበሬ እንዲሆኑ ፈረደባቸው፡፡ ከ18 ዓመታት በኋላ በቱርክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆኖ እነዚያ ተማሪዎች ሊቀመጡበት በሚገባቸው ቦታ ላይ ተቀምጦ የጡረታ ዕድሜውን ይገፋል፡፡ አይ ኢትዮጵያ! ምፀት የበዛብሽ የጉድ ሀገር!
በሰሞኑ አመፅ ሳቢያ በርካታ ተማሪዎች ከየዩኒቨርስቲዎች ከትምህርት ገበታቸው እየተባረሩ መሆኑን እሰማለሁ፡፡ አንዳንዶች ማስታወቂያዎች እንዲያውም ተማሪዎች ለአንድ ዓመት ይታገዱ ወይስ ለዘላለሙ ይባረሩ ግልፅ አይደሉም፡፡ በርካታ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ማሰናበት ግለሰብን፣ ቤተሰብን፣ ማህበረሰብን፣ ሀገርን… ምን ያህል መራራ ዋጋ እንደሚያስከፍል እስኪ አስሉት… አይ የድሃ ልጆች አበሳ! አይ የድሃ ቤተሰቦች እንባ! አይ የዚህች የጉድ ሀገር መከራ! ፍፁማዊ አገዛዝ የነበራቸው አፄ ኃይለ ስላሴ እኮ ተማሪ ዙፋኔን ተዳፈረ፣ እንቁላልና ስጋ እየቀለብኩት አመፀብኝ… ብለው ተማሪ አባረው አያውቁም… የደርግ ባህሪም ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነበር! ጥፋት ቢያጠፉ እንኳን ተግሳፅ ተሰጥቷቸው ይስተካከላሉ እንጂ እንዴት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው በጅምላ ይባረራሉ…? የት እንዲሄዱ ነው የሚባረሩት…? ዩኒቨርስቲዎቸ እኮ የሰፊው ድሃ ገበሬ ንብረቶች ናቸው…

Ethiopia opposition: 80 killed in protests against land plan

$
0
0

ADDIS ABABA, Ethiopia (AP) — Ethiopian government forces have killed more than 80 people in the past four weeks in protests in the country’s Oromia region, an Ethiopian opposition party charged Wednesday.

The killings should be investigated, said the Ethiopian Federal Democratic Unity Forum, a coalition of four opposition parties, at a press conference.

“Trigger-happy government forces have killed more than 80 peaceful protesters in Ethiopia during the past four weeks,” Beyene Petros, president of the party told reporters, adding that hundreds of others were wounded and arrested. “We are still discovering disfigured bodies in various locations. The government has continued its brutal killings so we call on the international community and donors to step in and force the government to stop these inhumane actions.”

 Beyene Petros

Beyene Petros


Party officials provided names of the alleged victims to The Associated Press.

The government has rejected, for the second time, the opposition party’s request to hold a public demonstration on Dec. 27 to protest the controversial Addis Ababa Master Plan, the opposition leader said.

The opposition party’s charge comes after a report last week by Human Rights Watch that said government forces killed at least 75 people protesting the government plan to incorporate some rural areas into the capital city, Addis Ababa.

Violent clashes between protesters and security forces have spread across Ethiopia’s Oromia Region, the biggest and most populous of Ethiopia’s federal states. Oromo students have led protests against the government’s plan which they charge will take lands from their region and displace thousands of farmers.

The government charges that the protesters are working with “terrorists.” It claims that only five protesters have been killed and that the development plan for Addis Ababa will not deprive farmers of land. Prime Minister Hailemariam Desalegn warned that the government “will take merciless legitimate action against any force bent on destabilizing the area,” speaking on Ethiopian state television.

But the protests have continued.

“This is the biggest demonstration in the region’s history. The immediate cause is the so-called Addis Ababa Master Plan that will rob Oromo farmers of their land and rights, the main reason is that people are fed up with cadres and politicians of the ruling party,” said Merara Gudina, a prominent Oromo opposition figure, told the Associated Press.

Many of the areas of Oromia are now under military control, said Gudina, vice-chairman of the Ethiopian Federal Democratic Unity Forum.

Amnesty International urged officials not to use draconian anti-terrorism measures to quell protests.

“The suggestion that these Oromo — protesting against a real threat to their livelihoods — are aligned to terrorists will have a chilling effect on freedom of expression for rights activists,” Muthoni Wanyeki, Amnesty International’s Regional Director for East Africa said.

The U.S. State Department has expressed concern over the clashes. “The United States is deeply concerned by the recent clashes in the Oromia region of Ethiopia that reportedly have resulted in the deaths of numerous protesters,” said spokesman Mark Toner in a statement. “We urge the government of Ethiopia to permit peaceful protest and commit to a constructive dialogue to address legitimate grievances. We also urge those protesting to refrain from violence and to be open to dialogue.”

The situation in and around the Woliso University campus seems calm but all the entrances to the Woliso town are guarded by soldiers, Seyoum Teshome, a professor at school, which was one of the protest sites, told the Associated Press by phone: “The situation seems calm at the moment but you could feel the tense atmosphere.”

From left to right, Gebru Gebremariam.Secretary General of the Ethiopian Federal Democratic Unity Forum, Beyene Petros, President of the Ethiopian Federal Democratic Unity Forum and Merara Merara Gudina, Vice- President of the Ethiopian Federal Democratic Unity Forum, during  press conference in Addis Ababa, Ethiopia, Wednesday, Dec 23, 2015. An Ethiopian opposition party said more than 80 people have been killed by government forces during massive protests in the past four weeks in the country’s Oromia region, the biggest of the country’s federal states. The Ethiopian Federal Democratic Unity Forum, a coalition of four opposition parties, has blamed the government on Sunday for the killings and has called for a criminal investigation.(AP Photo/Mulugeta Ayene )

From left to right, Gebru Gebremariam.Secretary General of the Ethiopian Federal Democratic Unity Forum, Beyene Petros, President of the Ethiopian Federal Democratic Unity Forum and Merara Merara Gudina, Vice- President of the Ethiopian Federal Democratic Unity Forum, during press conference in Addis Ababa, Ethiopia, Wednesday, Dec 23, 2015. An Ethiopian opposition party said more than 80 people have been killed by government forces during massive protests in the past four weeks in the country’s Oromia region, the biggest of the country’s federal states. The Ethiopian Federal Democratic Unity Forum, a coalition of four opposition parties, has blamed the government on Sunday for the killings and has called for a criminal investigation.(AP Photo/Mulugeta Ayene )


dailymail.co.uk

አቶ በቀለ ገርባ ታሠሩ – VOA Amharic

$
0
0

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላንና ከኦሮሚያ ከተሞች ዐዋጅ ጋር ተያይዞ ኦሮሚያ ውስጥ በተነሣው ተቃውሞና ግጭት የበርካታ ሰው ሕይወት መጥፋቱና ከ3,500 ሰው በላይ መታሠሩን ኦ.ፌ.ኮ አስታወቀ፡፡ ከአምስት ወራት በፊት የተፈቱት የቀድሞ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ገርባም መታሠራቸው ታውቋል፡፡

ከአራት ዓመታት የእሥር ቆይታ በኋላ፤ የእሥር ጊዜያቸውን ጨርሰው ከአምስት ወራት በፊት የተፈቱት አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው ዕለት ታሠሩ፡፡


ፕ/ት ባራክ ኦባማ የሟቹ ወገናችን ቤተሰቦችን በግንባር ተገኝተው አጽናኑ (ታምሩ ገዳ)

$
0
0

wa
የአሜሪካው ፕሪዜዳንት ባራክ ኦባማ በቅርቡ( በታህሳስ 2, 2015 አ. ኤ. አ )በአሜሪካው የካሊፎርኒያ ግዛት በሰምበርላንዲኖ ክፍለ ከተማ ውስጥ ሁለት ባል እና ሚስት አሸባሪዎች የገና በአል ዋዜማን ለማክበር በተሰባሰቡ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ባደረሱት ጥቃት አንድ ኤርትራዊ ወገናችንን ጨምሮ 14 ነጹሃን ሰዎች መሞታቸውን እና 21 መቁሰላቸውን ተከትሎ ፕ/ቱ ሰሞኑን የሟቶች ቤተሰቦችን በግንባር ተገኝተው ማጽናናታቸው ታውቋል።
ባለፈው አርብ የሟቾች ቤተሰቦችን ለመጎብኘት ወደ ሰንበርላንዲኖ ጎራ ያሉት ኦባማ የሟቾች ቤተሰቦችን ከ አንድ መለሰተና ደረጃ የት/ቤት ቤተ መጽህፍት ውስጥ ለ ሶስት ሰአታት በፈጀ የተናጥል ውይይት “እግዚ አብሔር ያጸናችሁ “ በማለት ሃዘናቸውን ገልጸዋል ። የአክራሪዎቹ ሰለባዎች ከሆኑት መካከል የ60 አመቱ ኤርትራዊው የሆኑት የጤና ጥበቃ ሰራተኛው ኣቶ ይሳቅ እሚኖ የተባሉት ወገናችን ቤተሰቦችን በግንባር ያነጋገሩ ሲሆነ የሟች አቶ ይሳቅ ልጆችን ቀረብ ብለው ያነጋገሩት ኦባማ “እናንተ የይሳቅ ምትኮች (አሻራዎች ) ናችሁ”በማለት አጽናንተዋል።
የአቶ ይሳቅ ወንድም የሆኑት አቶ ሮቤል ተክለ አብ በበኩላቸው ለተለያዩ የዜና ስዎች በሰጡት አሰተያየት “የፕ/ቱ አቀራረብ ቤተሰባችንን ከዚህ ቀደም በአካል የሚያውቁ የመሰል ነበር። ወንድሜ ይሳቅ በሕይወት በነበረበት ወቅት ለፕ/ት ባራክ ኦባማ ልዩ ፍቅር እንደነበረው ይናገር ነበር ። ኦባማ በ2009 እኤአ ለፕ/ትንት ባእለ ሰሜታቸው ላይ እንዲገኝ ወንድሜ የእንግድነት ጥሪ ወረቀት ተልኮለት ነበር። ሰለ ነገ ብዙ መናገር ባልችልም ከፕ/ት ኦባማ ጋር ያደረግነው አጭር ቆይታ በጣም ገንቢ እና አጽናኝ ነበር “ብሏል። እ አኤ አ በ 2000 ለተሻለ ሕይወት ከ ኤርትራ ምድር ወደ አሜሪካ (ካሊፎርኒያ) የተሰደዱት ሟች አቶ ይሳቅ ለ 11 አመታት በጤና መኮንንት ያገለገሉ ሲሆን በ አሁኑ ወቅት የኮሌጅ ተማሪዎች የሆኑት ዮሴፍ፣ ብሩክ እና ሚልካ የተባሉት 3 ልጆቻቸውን በማሳደግ ለወግ ለማእርግ ለማብቃት ደከመኝ ሰለችኝ ሳይሉ ሲጥሩ ሕይወታቸው በድንገት የተቀጩ ታታሪ አባት እንደነበሩ የወንድማቸው /የእህታቸው ልጅ ዛኬ ገ/ኪዳን ያወሷቸዋል።
ሴት ልጃቸው ሚልካ ይሳቅ በበኩሏ ሰለወላጅ አባቷ ኣቶ ይሳቅ ስትናገር” አባቴ ርሁሩህ ሰው ነበር ። እናቴን ለምን እንዳገባት ሲነግረኝ አርሷን የመሰለች መለከመልካም እና ጥሩ ሴት ልጅ (ሚሊካን)ለማፈራት ሰለ ፈልግ በማሰብ እንደ ነበር ይመክረኝ ነበር። አባቴ ዛሬ በሁለት እግሮቼ ያለፈረሃት ቆሜ አንድሄድ ያስቻለኝ ታላቅ አባት ነበር። በማለት ሰለአባቷ ለጋሽነት፣ ግልጽነት እና የፍቅር ሰው መሆን ለ ሎሳንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ ተናግራለች።
ይህ በዚህ እንዳለ የአሜሪካው የፈደራል የምርመራ ቢሮ(FBI) ለአቶ ይሳቅ እና ሌሎች 13 ሰላማዊ ዜጎች ሞት መንሰኤ ናቸው ያላቸው ባል እና ሚስቱ ሳይድ ሪዝዋን ፋሩክ እና ታሽፊን ማሊክ ከመቼ ጀምሮ ወደ አክራሪነት እንደተለወጡ ቁርጥ ያለ መረጃ በማሰባሰብ ላይ መሆናቸው እና መረጃውንም ለማገኘት ከወራት በላይ እንደሚፈጅባቸው ሃሙስ ታህሳስ 24 2015 ለንባብ የበቃው ሎሳንጀለስ ታይምስ ጋዜጣ ዳስሶታል።
የፈርንጆቹን የገና በአልን ከውይት ሃውስ ቤተመንግስታቸው ውጪ ለማክበር ሻንጣቸውን ከመሽንከፋቸው በፊት ከቀዳማዊት እመቤት ሚሺል ኦባማ ጋር ሃዘንተኞችን ለማጽናናት በአካል ሰምበርላንዲኖ ከተማ የተገኙት የ ልእለ ሃያሏ አገር አሜሪካ፣ ፕ/ት ኦባማ ለሁሉም ሃዘንተኛ ቤተሰቦች በጋራ ፣ በአንድነት እና በፍቅር መኖር የአሜሪካ እና የሕዝቧ ታላቁ የባሕል እሴት እንደሆነ እና በዚህም ጊዜ ሁሉም ወገኖች ለዚህ መሰሉ ድርጊት ተግባራዊነት ተግተው እንዲሰሩ ምክራቸውን እና ጥሪያቸውን አሰተላልፈዋል። በተለይ ደግሞ “ላለፉት ሁለት ሺህ አመታት የክርስቶስን መወለድ (የገና በእልን ሲያከብሩ የነበሩ የመካከለኛው ምስራቅ ዜጎች (ኢራቅ እና ሶሪያ) በአሁኑ ወቅት እራሱን የ እስልምና መንግስት እያለ የሚጠራው በአክራሪው ኢይሲስ እየደረሰባቸው ባለው ግድያ እና መዋከብ ሳቢያ የጌታ የአየሱስ ክርስቶስ መወልድን ለማብሰር ደውል እንዳይደወሉ እና ጸሎት እንዳያደርጉ የተገደዱት ክርስቲያኖችን ልናሰባቸው እና ልንጸልይላቸው ይገባል።” ሲሉ በፈርንጆቹ ገና ዋዜማ ሃሙስ እለት ላይ ከጽ/ቤታቸው የላኩት መልክት ያስረዳል።

የአንዋር መስጊዱን የቦምብ ጥቃት አስመልክቶ በእስር ቤት ከሚገኙ የኮሚቴው አባላት የተሰጠ መግለጫ አርብ ታህሳስ 15/2008

$
0
0

kal
ህዝበ ሙስሊሙ ለተንኮለኞች ሴራ ሳይበገር አንድነቱን አጠንክሮ፣ አመለካከቱን አቻችሎ ሰላማዊ የመብት ትግሉን መቀጠል ይኖርበታል!
በአንዋር መስጊድ ቅጥር ግቢ ታህሳስ 01/2008 የደረሰው የቦንብ ጥቃት የዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ትኩረት እንዲሰጠው፣ ድርጊቱም በገለልተኛ አካላት በአስቸኳይ ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ ይደረግ ዘንድ እንጠይቃለን!
አርብ ታህሳስ 15/2008 /አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሕገመንግስታዊ የመብት ጥያቄያችንን ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ማቅረባችን ይታወቃል። ለጥያቄዎቻችን ተገቢውን እና ፍትሃዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ጥያቄውን በሀሰት በመፈረጅ ሰላማዊ ሂደቱን ለመቀልበስ ተደጋጋሚ ጥረት ተደርጓል። የህዝበ ሙስሊሙን የፍትህ ጥያቄን ለማጠልሸት እና በመካከሉ ልዩነትን ለመፍጠር የተለያዩ የፕሮፓጋንዳ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል። ለህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች መፍትሄ ለማፈላለግ ሕዝብ በወከለን መሰረት በመንቀሳቀሳችን ወንጀለኛነት እና የረጅም እስር ፍርድ እንዲወሰን ተደርጓል። ይህም ሁሉ ሆኖም የሙስሊሙን አንድነት መስበርም ሳይቻል ቀርቶ ለመብቱ መከበር የሚያደርገውን ትግል በተጠናከረ መልኩ እየቀጠለ ባለበት ወቅት እጅግ ጸያፍ የሆነ የቦምብ ጥቃት በእምነት ቤታችን ቅጥር ግቢ ውስጥ መሰንዘሩ እጅግ ያሳዘነን ክስተት ነው።

የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ ለመቀልበስ የሚደረጉ ሙከራዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ እና የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ የትግል ሂደት መንገድ ሊያስቱ እንደሚሞክሩ ደጋግመን ስናስጠነቅቅ ቆይተናል። የሸፍጥ ጥቃቶችን በስውር በመፈጸም ፓለቲካዊ ጥቅም የሚያስገኙ እርምጃዎችን ለመውሰድ የማመቻቸት ተግባር በተለያዩ ሀገሮች የምናየው ክስተት ነው። በሰላማዊ የትግል ሂደታችንም በተለያየ ጊዜ የተረዳነውና ያጋጠመንም ነው። ሆኖም ግን ሙስሊሙ ህብረተሰብ የመከላከል ስራዎች ላይ በልዩ ትኩረት በመስራቱ ሰላማዊ ሂደታችን ለፓለቲካ ግብዓት እንዳይውል እድሉን ነፍጓቸው ቆይቷል። እንግዲህ በአንዋር መስጊድ ቅጥር ግቢ ውስጥ ታህሳስ 01/2008 የደረሰው የቦንብ ጥቃት ቀደም ብለን እንደ ህዝብ ገምተን ስንከላከለው፣ መንግስትም የሀይማኖት ተቋማትን በተለይም የመስጂዶችን ደህንነት ለመጠበቅ በኩል ያለበትን ሀላፊነት በትክክል እንዲወጣ ስናስጠነቅቅበት የቆየነው እንጂ ሌላ አይደለም።

ሙስሊሙ ህብረተሰብ ፍትሃዊና ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ ለመቀጠል ዳግም ቃል እየተጋባ ባለበት በአሁኑ ወቅት እና አማኞች የፈጣሪያቸውን ግደታ ለመወጣት በተሰባሰቡበት ቦታና ሰዓት የቦንብ ጥቃት ማድረስ በእርግጥም የሙስሊሙን ሰላማዊ ሂደት ለማጠልሸት፣ የትግል ወኔውን ለመስበር፣ አንድነቱን ለመረበሽ ዛሬም የማይፈነቀል ድንጋይ እንደማይኖር የሚያረጋግጥ ነው። ከዚህ በመነሳት በቀጣይም በመስጊዶች ብቻ ሳይወሰን በክርስትና እና በሌሎች የአምልኮ ቦታዎችም ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶችን በማድረስ በተለያዩ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን መካከል ቅራኔን ለመፍጠር ሙከራዎች እንደሚደረጉ መገመት ከእውነታ የራቀ አይሆንም። በዚህ አይነት የተንኮለኞች ሴራ አገራችን እና ህዝባችን አደገኛ ወደ ሆነ አቅጣጫ እንዲመሩ አንፈቅድም። በመሆኑም ጉዳዩ የዓለም አቀፋዊ ማህበረሰብ ትኩረት እንዲቸረው እና ይህ እኩይ ተግባር በገለልተኛ አካል ይጣራ ዘንድ ሀገር እና ወገን ወዳድ የሆኑ ሁሉ ጥረት እንዲያደርጉ አጥብቀን እንጠይቃለን። በደረሰው ጥቃት ለተጎዱት ወገኖቻችን፣ እንዲሁም ለመላው ሙስሊም ህብረተሰብ እና ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በሁኔታው የተሰማንን ሀዘን እንገልጻለን። ህዝበ ሙስሊሙም በፍንዳታው ጉዳት ለደረሰባቸው ወንድሞቹ እና ለቤተሰቦቻቸው አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ እና ከጎናቸው በመቆም አጋርነቱን፣ አንድነቱን እና ከምንም በላይ የትኛውም አይነት ሴራ የማይበግረውን ከፈጣሪው በተዘረጋ የእምነት ገመድ ላይ ያለውን የአንድነት ትስስር በተግባር ሊያሳይ ይገባል።

የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄያች ፍትሀዊ ናቸው፡፡ ሂደቱም ሰላማዊ ነው። በህዝበ ሙስሊሙ መካከል ጥርጣሬን ለማስፈን፣ ክፍፍልን በማምጣት እርስ በርሱ ለማጋጨት የሚፈጸም የትኛውም ደባ የከሸፈ ከንቱ ጥረት ነው። ህዝባችን በዚህ እና መሰል ሴራዎች ሳይበገር አንድነቱን ጠብቆ፣ አመለካከቱን አቻችሎ ሰላማዊ የመብት ትግሉን ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ እንዲቀጥል እናሳስባለን።

አገራችን ያለችበትን ተጫባጭ የታሪክ ፈታኝ ምእራፍ በመረዳት ህብረተሰባችን ያለአንዳች የብሄር፣ የዘር፣ የሃይማኖትና የጾታ ልዩነት ለፍትህ እና ለሕግ የበላይነት በመቆም ዜጎቿ በሰላም ተሳስበን የምንኖርባት ሀገር ትሆንልን ዘንድ ጠንክረን መታገል ይኖርብናል። ለዚህ ስኬት ከጥረታችን ባሻገር ሁላችንም ፈጣሪያችንን በጽኑ እንለምን። በመተናነስ፣ በጸሎት፣ በሰደቃ እና በመልካም ተግባር ወደፈጣሪያችን አላህ (ሱ.ወ) መቃረብ እንደሚኖርብን ህዝባችንንም ራሳችንንም ሳናስታውስ አናልፍም!

ድል የሚከጀለው ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማል!
አላሁ አክበር!

ጋዜጠኛ ደረጀ ሀይሌ እና አርቲስት አዜብ ወርቁ “የደራ ጨዋታ”አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም ጀመሩ!!

$
0
0

dar
“የደራ ጨዋታ” አዲስ የራድዮ ፕሮግራም በፋና FM 98.1 በድምፀ መረዋው ጋዜጠኛ ደረጀ ሀይሌ(ሀይሌ ዘብቅሎ ቤት) እና በደራሲ አዜብ ወርቁ ተዘጋጅቶ ዘወትር አርብ ከቀኑ 9:00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት የሚቀርበው ኘሮግራም ዛሬ ታህሳስ 15/2008 ዓ·ም በልዩ አቀራረብ ጀመረ።
መደበኛ ኘሮግራሙን ከሁለት ሳምንት በኋላ ጥልቅ ይዘት ባላቸው ኘሮግራሞች በይፋ ይጀምራል የተባለ ሲሆን ተመሳሳይና አሰልቺ የሆነው የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ያነቃቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።የፕሮግራሙ መስራቾች ከሆኑት አንዱ የሆነው ጋዜጠኛ ደረጀ ሀይሌ በተለያዩ ሚዲያዎች በጋዜጠኝነት የሰራ ሲሆን በኢትዮጵያ ሬዲዮ፣አይረሴ በሆነው ጨዋታ ፕሮግራም ላይ ከሸገር መስራቾች መአዛ ና ተፈሪ ጋር ፣በኢትዮጵ ጋዜጣና መፅሔት፣በቃልኪዳን መፅሔት፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጥያቄና መልስ ፣ከአለምነህ ዋሴ ጋር በፋና ሬዲዮ፣የአውዳመት ልዩ ፕሮግራም በራዲዮ ከሰራቸው መካከል ይጠቀሳሉ።ጋዜጠኛ ደረጄ ሀይሌ(ሀይሌ ዘብቅሎ ቤት) የሚሰራቸው ፕሮግራሞች እንግዶቹን የሚያነጋግርበት የቃለመጠይቅ መንገዱ ድንቅነት የተነሳ ፕሮግራሞቹን መስማት ጀምሮ ማቋረጥ የማይታሰብ አድማጮችን የሚማርክ ልዩ ክህሎት ያለው ጋዜጠኛ ነው።
ጋዜጠኛ ደረጄ ሀይሌ በጋዜጠኝነቱ ብቻ ሳይሆን ድንቅ መድረክ መሪ በመሆኑም ይታወቃል።በገጠመው ሀዘን ምክንያት ከሞያው የራቀው ደረጄ
“የደራጨዋታ ” አዲሱ ፕሮግራሙ ላይ አዲስ ነገር ይዞ ይመጣል በሚል ብዙዎች በጉጉት እየጠበቁት ነው።
በዚህ የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ከደረጀ ጋር የተጣመረችው አርቲስት አዜብ ወርቁ በዳና ተከታታይ ድራማ፣ በገመና ሁለት ድራማ፣ኮንዶሚኒየሙ ፌልም፣ስምንቱ ሴቶች ትያትር ተርጓሚ፣የሚስት ያለህ ትያትር ተርጓሚ ስትሆን በበርካታ ሰራዎች ላይም በተዋናይነት የሰራች ባለብዙ ተስጦ አርቲስት ነች።
በፕሮግራሙ መጀመር የተደሰቱ የሁለቱ ባለሞያዎች አድናቂዎች “አዙና ደሩ ጨዋታውን እንደምታደሩት እናምናለን”ሲሉ በፕሮግራሙ መጀመር የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

በደህንነቶች የታሰሩት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው እና የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ፍርድ ቤት የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ሰጠባቸው።

$
0
0

‹‹ካሁን በፊት ይዝቱብኝ ነበር፤ ጋዜጠኛ በመሆኔ ነው የታሰርኩት›› ጌታቸው ሺፈራ
nb
ትናንት ታህሳስ 15/2008 ዓ.ም በያሉበት ታድነው የታሰሩት ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ዳንኤል ተስፋየ እና ሸዋታጠቅ ኃ/መስቀል ዛሬ ታህሳስ 16/2008 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ በሽብር ተጠርጥረው መታሰራቸውን በመግለጽ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ ፖሊስ ታሳሪዎቹ የተጠረጠሩበትን ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው፣ ተጠርጣሪዎች ‹‹የአርበኞች ግንቦት 7 አባል በመሆን፣ በመመልመል፣ በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ግንኙነት በመፍጠር የሽብር ወንጀል ሊፈጽሙ ሲሉ ተይዘዋል›› ብሏል፡፡
ተጠርጣሪዎች ስለተጠረጠሩበት ወንጀል እና ስለተጠየቀባቸው የጊዜ ቀጠሮ አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ‹‹ካሁን በፊት በተደጋጋሚ ይዝቱብኝ ነበር፤ እኔ ጋዜጠኛ በመሆኔ ነው የተያዝኩት፡፡ ቤቴ ሲፈተሽ የተገኘውም የህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች (ሰማያዊና መድረክ) መግለጫዎችና ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ ከተባለው ወንጀል ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፤ በነጻ ልሰናበት ይገባል›› ሲል ተናግሯል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ አባሉ አቶ ዳንኤል ተስፋየ በበኩሉ ‹‹በፍተሻ የተያዙብኝ ባንዲራ፣ ሲዲ እና ስልክ ናቸው፡፡ ስለዚህ ለምርመራ የተጠየቀውን ያህል ጊዜ መፈቀድ የለበትም፤ አጭር ቀጠሮ ይሰጠን›› ሲል ጠይቋል፡፡
ሦስተኛው ተጠርጣሪ አቶ ሸዋታጠቅ ኃ/መስቀል ደግሞ ‹‹እኔ በቂርቆስ ክ/ከተማ በኢህአዴግ ተደራጅቼ የምሰራ ሰው ነኝ፡፡ ፖሊስ ከገለጸው ድርጅት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም፤ ድርጅቱን ጭራሽ አላውቀውም፤ የልጅ አባት ስለሆንኩ አጭር ቀጠሮ ይሰጠኝ›› በማለት አመልክቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ ግን ፖሊስ የጠየቀውን 28 ቀናት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ለጥር 14/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በተመሳሳይ ከሁለት ወራት በፊት ከአርባምንጭ ተይዘው ወደማዕከላዊ የመጡት በአርባምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እነ ሉሉ መሰለ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው 28 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በሌላ በኩል ትናንት ለእስር ከተዳረጉት መካከል የሆኑት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አቶ ኤርሚያስ ጸጋየ፣ አቶ ፍሬው ተክሌ እና አቶ ቴዎድሮስ አስፋው ዛሬ ከሰዓት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

በጊንጪ አሁንም ውጥረት አለ-VOA Amharic

$
0
0

በኦሮሚያ ክልል የሚካሄደው ተቃውሞ ሁለተኛ ወሩን ይዟል።
ሕዝቡ ከማስተር ፕላኑ ብቻ ሳይሆን የስብአዊ መብት ረገጣ፣የኑሮ ውድነት፣እና ሌሎች በርካታ መአበራዊ ጥያቄዎችም አሉት።ተቃውሞ በትላንትናው እለት ታህሳስ 15,2008 በአንዳንድ አከባቢዎች በአዲስ መልክ ተጀምሯል።
በወለጋ ዩኒቨርሲቲና በሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ ቱሉ ምልኪ ከተማ ከፍተኛ ተቃውሞ የነበረ ሲሆን በአሰበ ተፈሪ(ጭሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት) ደግሞ የታሰሩ ተማሪዎች ካልተፈቱ አንማርም በማለት ተማሪው ረብሾ ወደ ቤቱ መበታተኑ ታውቋል።

የቪኦኤዋ ዘጋቢ ማርተ ፋን ደር ቮልፍ ተቃውሞው በህዳር መግቢያ ከተጀመረባት ጊንጪ ከተማ ሆና በአሁኑ ወቅት ያለውን ሁኔታ ዘግባለች።

በጊንጪ ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው ያለችው ማርታ “።የንግድ ቤቶች ለሣምንታት ከተዘጉ በኋላ እየተከፈቱ ነው፡፡ ሆኖም ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ትንሿ ከተማ ጊንጪ ውጥረት ሰፍኖ ሰንብቷል” ብላለች።

ወታደሮች በዋናው ጎዳና ላይ ይዘዋወራሉ፤ ጋዜጠኛን የሚያነጋግሩ ሰዎች ማንነታቸው እንዳይገለፅ ይጠይቃሉ፤

አንዲት ለሁከቱ የዐይን እማኝ የነበረች የሻይ ቤት ሠራተኛ ንግድ ቤቱ ቢከፈትም በጊንጪ ግን አሁንም ውጥረት እንዳለ ተናግራለች፡፡ ዝርዝሩን ከቪኦኤ ያዳምጡ።

‹‹ባለሥልጣናት መሬቴን ከነኩ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ ውጤቱን ያገኙታል››ሳይ ራማክሪሽና ካሩቱሪ

$
0
0

zxa
ሳይ ራማክሪሽና ካሩቱሪ፣ የካሩቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ መሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር
መንግሥት በኢትዮጵያ የሰፋፊ እርሻ ኢንቨስትመንት ላይ በትልቁ ይጠቅሳቸው ከነበሩ ትልልቅ ኩባንያዎች ዋናው የህንዱ ካሩቱሪ ግሎባል ነው፡፡ የኩባንያው መሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳይ ራማክሪሽና ካሩቱሪ እዚህ አገር ካሩቱሪ አግሮ ፕሮዳክስት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያን በመመሥረት፣ በጋምቤላ ክልል ሰፊ መሬት ወስደው ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ ከመነሻው ጀምሮ ግን በውዝግብ የተሞላ ሒደት ያሳለፉት ራም ካሩቱሪ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ተፋጠዋል፡፡ ባንኩ ለሁለተኛ ጊዜ ሐራጅ አውጥቶባቸዋል፡፡ በቅርቡ ታኅሳስ 12 ቀንም በ55.8 ሚሊዮን ብር ዕዳ ምክንያት ባንኩ ለጨረታ ያቀረበው የእርሻ መሬት በፍርድ ቤት ዕግድ ምክንያት ከመሸጥ አምልጧል፡፡ ሆኖም ከባንኩ ጋር ያላቸው ጠብ በብድር ዕዳ እንዳልጀመረ ይናገራሉ፡፡ በአገሪቱ የእርሻ ሥራቸው መዳከም ሳቢያ ከመንግሥት ባለሥልጣናት የሚቀርብባቸውን ወቀሳም ይኮንናሉ፡፡ ይብሱን ለውድቀቴ የሚተጉ የሚሏቸውን በስም እየጠቀሱ ያብጠለጥላሉ፡፡ በጋምቤላ ክልል የተሰጣቸው 300 ሺሕ ሔክታር መሬት እንደነበር፣ እሳቸው የጠየቁትን ግን 10 ሺሕ ሔክታር ብቻ እንደነበር፣ የተሰጣቸው መሬትም በጎርፍ የሚጥለቀለቅ፣ በዛፍ የተሞላና ለምንጠራ ብዙ ወጪ የሚጠይቅ እንደነበር በመጥቀስ በርካታ ቅሬታዎችን አሰምተዋል፡፡ ንግድ ባንክ ያወጣውን የሐራጅ ጨረታ መነሻ በማድረግ ብርሃኑ ፈቃደ ራም ካሩቱሪን አነጋግሯቸዋል፡፡
ሪፖርተር፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ የሐራጅ ማስታወቂያ በእርስዎ ኩባንያ ላይ አውጥቷል፡፡ ከዚህ ቀደም ዘመን ባንክም ከእርስዎ ጋር በብድር ምክንያት አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፡፡
ራም ካሩቱሪ፡- በዚህ አገር ብዙ ኢንቨስት አድርገናል፡፡ እዚህ ኢንቨስት ያደረግሁት የራሴን ገንዘብ ነው፡፡ እርግጥ ነው ባንኮች የተወሰነ ብድር ሰጥተውናል፡፡ አዎ ዘመን ባንክ 70 ወይም 80 ሚሊዮን ብር አበድሮን ነበር፡፡ ከንግድ ባንክም ተበድረናል፡፡
ሪፖርተር፡- ዳሸን ባንክም አበድሯችሁ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ራም ካሩቱሪ፡- ዳሸን ባንክ አበድሮን የነበረው 10 ሚሊዮን ብር ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ2006 ያበደረንን ብድር በዓመቱ መልሰናል፡፡ ስለዚህ ምንም ዓይነት የዳሸን ባንክ ብድር የለብንም፡፡ ዕዳ ያለብን የዘመን ባንክና የንግድ ባንክ ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ለዘመን ባንክ መክፈል ያለብን 26 ሚሊዮን ብር ሲሆን ይህንን ለመክፈል በምንችለበት አቋም ላይ እንገኛለን፡፡
ሪፖርተር፡- ዘመን ባንክ ብድር አልተከፈለኝም በማለት ፍርድ ቤት ጉዳይዎን ወስዶትም ነበር፡፡
ራም ካሩቱሪ፡- ኢትዮጵያ የራሷ ሕጎች፣ ባህልና ውርስ ያላት አገር ነች፡፡ ከዚህ አገር ባህል ጋር ተጣጥሞ ለመሥራት ካስፈለገ ሕጎችና ደንቦችን ማክበር ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ሥርዓቱን የሚመራባቸው መመርያዎች አሉት፡፡ ባንኮች የሚጠየቁት ብድር አጠራጣሪ ከመሰላቸው ከብድሩ መቶ እጥፍ በላይ ሀብት ቢኖርህ እንኳ አያበድሩህም፡፡ የተበላሸ ብድር እንዳይሆንም ይከታተላሉ፡፡ ይህ ሆኖ ሲገኝም ጨረታ ያወጣሉ፡፡ ምክንያቱም ገንዘባቸውን እንዳያጡ ስለሚፈሩ ነው፡፡ ይህ ለምን ይሆናል ብዬ አልጠይቅም፡፡ ሆኖም ግን ይህን እንዲደረግ የምትፈቅደው አገርና ሕጎቿ መልሰው ለተበዳሪዎች ማገገሚያ ሥርዓትን ስለሚፈቅዱ፣ ብድራቸውን መክፈል እስከቻሉና ለብድሩ ማስያዣ ንብረት እንስካላቸው ድረስ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያጵያዊም ሆነ የውጭ ኢንቨስተር ማሟላት የሚገባውን ቅድመ ሁኔታዎች እስካሟላ ድረስ፣ ሕጉ ወደ ፍርድ ቤት በመሄድ ጉዳዩን እንዲያቀርብና ከብሔራዊ ባንኩ ገዳቢ ሕጎች አኳያ ለሚመጣበት ጫና ማስታረቂያ መፍትሔ ይሰጠዋል፡፡ በመሆኑም ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ በኋላ የዘመን ባንክን ብድር በሦስት ቀናት ውስጥ መልሰናል፡፡ ምክንያቱም ገንዘባችን እየመጣ የነበረ ቢሆንም፣ እነሱ ግን ሊታገሱ አልቻሉም፡፡ ስለዚህ ማድረግ ያለባቸውን አደረጉ፡፡ እኛ ግን ገንዘቡ እየመጣልን ስለነበር እንደምንከፍላቸው እናውቅ ነበር፡፡ በሕጉ ገዳቢነት ሳቢያ ባንክ ሆነህ ስታየው እንዲህ ያለውን ነገር በማመን ለመሥራት ትቸገር ይሆናል፡፡ ይሁንና ዘመን ባንክ የፍርድ ቤት ሒደቱን አቋርጠዋል፡፡
እኔ የኢትዮጵያ ወዳጅ ነኝ፡፡ እዚህ የመጣሁት አገሪቱን ስለምወድ ነው፡፡ በመሆኑም ብዙ ገንዘብ ኢንቨስት አድርጌያለሁ፡፡ መንግሥት አምኖኝ እንዳለማ በጋምቤላ መሬት ሰጥቶኛል፡፡ ይህንን ማሳካት ነው ዓላማዬ፡፡ እኔ የዓለም የአበባ ንግድ ንጉሥ ነኝ፡፡ ይህንን ለማንም መንገር አይጠበቅብኝም፡፡ ሁሉም ያውቀዋል፡፡ የዓለምን አሥር በመቶ የገበያ ድርሻ ይዣለሁ፡፡ በአንድ ወቅት በዚህ መንግሥት ውስጥ ትልቅ ሥልጣን ከነበራቸው ከአንድ ትልቅ ሰው ጋር ተገናኘሁ፡፡ ከእሳቸው ጋር ቀጠሮ ስለነበረኝ ቢሯቸው እንግዳ መቀበያ ቁጭ ባልኩበት ጋዜጣ ላይ የተጻፈ ነገር አነበብሁ፡፡ ኢትዮጵያ 70 ሺሕ ቶን ስንዴ ከደቡብ አፍሪካ ታስመጣለች ይላል፡፡ ከሰውየው ጋር የነበረኝን ጉዳይ ከጨረስኩ በኋላ ግን 80 ሚሊዮን ሕዝብ ባለበት አገር፣ 100 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ባለው አገር፣ ከበቂ በላይ ዝናብና ፀሐይ በሚገኝበት አገር ውስጥ ምግብ ከደቡብ አፍሪካ ማስመጣት ያሳምመኛል አልኳቸው፡፡ ለዚህ አገር እኔ ምንም ነኝ፡፡ የዓለም ባንክም አይደለሁም፡፡ ግን ነገርየው ያሳምማል፡፡ ታላቁ መሪ ግብርና ላይ ኢንቨስት እንዳደርግ ጠየቁኝ፡፡ እኔ ግን ሐሳቡም አልነበረኝም፡፡ እኔ ስለአበባ ብቻ ነው የማውቀው፡፡ ሆኖም ባኮ ላይ መሬት ተሰጠኝ፡፡ እዚያ ማልማት ጀመርኩ፡፡ ከዚያ የጋምቤላ ፕሬዚዳንት ሊያገኙኝ እንደሚፈልጉ ሰማሁ፡፡ ኤምባሲያቸው የት ነው ብዬ ነበር የጠቅሁት፡፡ ጋምቤላ ሌላ አገር እንጂ ክልል አልመሰለኝም ነበር፡፡ ላለማወቄ አትታዘቡኝ፡፡ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በግዮን ሆቴል ስንነጋገር በጋምቤላ መሬት እንደሚሰጠኝ ገለጹልኝ፡፡ በፕሬዚዳንቱና በጋምቤላ ክልል መንግሥት ግብዣ ቦታውን ለማየት ሄድን፡፡ እኛ የጠየቅነው 10 ሺሕ ሔክታር መሬት ነበር፡፡
ሪፖርተር፡- እርስዎ 10 ሺሕ ሔክታር ጠየቅሁ ቢሉም እኛ የምናውቀው ግን 300 ሺሕ ሔክታር መሬት እንደተቀበሉ ነው፡፡ ይህ እውነት አይደለም እንዴ?
ራም ካሪቱሪ፡- የተመዘገበና በየትኛውም ፍርድ ቤት ላረጋግጠው የምችለው ሀቅ አለኝ፡፡ የጋምቤላ ክልል መንግሥት ካቢኔ በሙሉ ስብሰባ ከተቀመጠ በኋላ 10 ሺሕ ብቻማ አንሰጥህም አሉኝ፡፡ እኔ ግን አቅሜ ይኸው ብቻ እንደሆነ ገልጬላቸዋለሁ፡፡ ከስብሰባቸው በኋላ 300 ሺሕ ሔክታር መሬት እንደሚሰጡኝ ይልቁንም እኔ በማምንበት ዋጋ እንድከፍል፣ ከዚያ ያነሰ መሬት ግን እንደማይሰጡኝ አስታወቁ፡፡ ምርጫ አልነበረኝም፡፡
ሪፖርተር፡- ለእርስዎ 300 ሺሕ ሔክታር መሬት ለምን እንደተሰጠ ሚዲያው ሁልጊዜ መንግሥትን ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡
ራም ካሪቱሪ፡- እኔ አልወሰድኩም፡፡ አንተ በአንዴ መብላት የምትችለው አንድ እንጀራ ነው፡፡ አምስት እንጀራ በግድ ብላ ብዬ እሰጥሃለሁ፡፡ ከሆነ ጊዜ በኋላ ስመለስ ለምን አልጨረስከውም ብዬ የምወቅስህ ከሆነ እንዲህ ያለው ነገር አመክንዮው ምንድነው? በወቅቱ የውጭ ኢንቨስተር ለማግኘት በጣም ትፈልጉ ነበር …
ሪፖርተር፡- የመንግሥት ኃላፊዎች ለምንድነው አንድ ጊዜ ተሳስተው እንኳ እርስዎ ጠይቀው የነበረው 10 ሺሕ ሔክታር መሬት እንደነበር የማይናገሩት? መንግሥት በይፋ ሲናገር የቆየው 100 ሺሕ ሔክታር መሬት እንደተሰጠዎ ነው፡፡ ሆኖም በተግባር የተሰጠዎ ግን 300 ሺሕ ሔክታር ነው፡፡
ራም ካሪቱሪ፡- ስምምነቱ በተረቀቀበት ወቅት 300 ሺሕ ሔክታር ብለው እንዳያሰፍሩ ተማጽኛቸው ነበር፡፡ እነሱ ግን በግድ ይሁን ብለው 300 ሺሕ ሔክታር አደረጉት፡፡
ሪፖርተር፡- መንግሥት ቢክደውም ለእርስዎ የተሰጠዎ መሬት ስፋት 300 ሺሕ ሔክታር እንደሆነ የሚያሳይ የስምምነታችሁ ሰነድ ቅጅ እኛም አለን፡፡
ራም ካሪቱሪ፡- ሊኖራችሁ የሚችለው በወቅቱ ግብርና ሚኒስቴር (የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስተር) ያወጣው ሰነድ ቅጅ ነው፡፡ ዋናው ሰነድ እሱ አይደለም፡፡ ዋናው ሰነድ ከጋምቤላ ክልል ጋር የተስማማንበት ነው፡፡ ይህ ስምምነት የ300 ሺሕ ሔክታር መሬት ነው፡፡ በኋላ ግን አዲስ ስምምነት ተደርጎ 100 ሺሕ ሔክታር መሬት እንዲሰጠኝና እንዳለማ ቀሪው 200 ሺሕ ወደፊት ስፈልግና የተሰጠኝን ካለማሁ በኋላ የሚጨመር ተደርጐ በታሳቢነት የተያዘ ነበር፡፡ ይህንን ሁሉ ያስከተለው የእኔ ምርጫ ነው ወይስ የእናንተ ኢንቨስተር ለማግኘት የነበራችሁ ፍላጐት? በዚህ አገር ሰፋፊ እርሻን ያስተዋወቅሁና የፈጠርሁ እኔ ነኝ፡፡ ይህ ደግሞ እኔ በራሴ አንደበት የተናገርኩት ሳይሆን የዚህ አገር ሰዎች የሚሉት ነው፡፡ መንግሥት የአበባ እርሻ በመፍጠሩ፣ የሥጋ ኤክስፖርት በመጀመሩ ደስተኛ ሆኖ ነበር፡፡ በውጭ አልሚዎች የሚንቀሳቀስ የሰፋፊ እርሻ ሥራ ግን አልነበረም፡፡ ኢንቨስተሮችም አቅሙ እንዳለ አላሰቡም ነበር፡፡ በመሆኑም ካሩቱሪ ጀማሪ በመሆን አስፋፋው፡፡
ሪፖርተር፡- በመንግሥት ደካማ ከተባለው ውስጥ የሚመደብ ቢሆንም ሳዑዲ ስታር መሰለኝ ቀደምት የሰፋፊ እርሻ ሥራ ጀማሪ?
ራም ካሪቱሪ፡- ስለሼክ መሐመድ አል አሙዲ ማውራት ተገቢ አይሆንም፡፡ እሳቸው ራሳቸውን የቻሉ መንግሥት ማለት ናቸውና፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር ዓለም አቀፍ ዕውቅና የመጣው፡፡ የተወሰኑት የሰፋፊ እርሻን ሲደግፉ የተወሰኑት ተቃወሙት፡፡ በመሀሉ በመንደር የማሰባሰብ ፕሮግራም በመምጣቱ ነገሩን ይበልጥ አወሳሰበው፡፡ ፕሮግራሙ የነዋሪዎችን መሬት በመውሰድ ለሰፋፊ እርሻዎች ለመስጠት የመጣ ነው ብለው የተቃወሙም ነበሩ፡፡ እንዲህ ያሉት መግለጫዎች በፍጥነት በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተራግበዋል፡፡ ሚዲያው ስለአፍሪካ መጥፎውን እንጂ ጥሩውን አይዘግብም፡፡ በህንድም እንዲህ ያለው ነገር አጋጥሞን ያውቃል፡፡ በወቅቱ መንግሥት ከሦስት እስከ አራት ሚሊዮን ሔክታር የሚገመት መሬት ለሰፋፊ እርሻዎች ሰጥቶ ነበር፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት ካሩቱሪና ሳዑዲ ስታር ብቻ ናቸው የቀሩት፡፡ ሌላ ሦስተኛ ኩባንያ ስለመኖሩ ልትጠራልኝ አትችልም፡፡ ሁሉም ጥለው ሄደዋል፡፡ እኔም እንድሄድ ትፈለጋላችሁ እንዴ?
ሪፖርተር፡- ግን ምን ያህል ጊዜ መፍጀት አለበት? በስድስት ዓመታት ውስጥ ምንም ነገር ካልተገኘ ስንት ዓመት መጠበቅ ሊያስፈልግ ነው?
ራም ካሪቱሪ፡- አላውቅም፡፡ 60 ዓመትም ሊፈጅ ይችላል፡፡ በግልገል ጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ወቅት ያልታሰበ ፍልውኃ ሲገኝ፣ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ምን ያህል ጊዜ እንደሚጠይቅ ልትነግረኝ ትችላለህ? ለሁለት ዓመት ያህል በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል ላገኝ ባለመቻሌ እቤቴ በጄኔሬተር ለመጠቀም ተገድጃለሁ፡፡ ሙቅ ውኃ በግድቡ ቦይ በኩል በመምጣቱ የማን ስህተት ነው? ይህ የእግዜር ሥራ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- ወደ ሐራጁ ጉዳይ እንመለስ፡፡
ራም ካሪቱሪ፡- እንደ እኔ ከሆነ ሐራጅ የሚባል ነገር የለም፡፡ ካለም ሄደህ ስለ እሱ መጻፍ ትችላለህ፡፡ አንድ የዚህ አገር ኩባንያ (ስሙን ጠቅሰዋል ማረጋገጫ አላገኘንለትም) ሊከፍለኝ የሚገባው 100 ሚሊዮን ብር ዕዳ አለበት፡፡ ከገበያው የሚሰበሰብ 350 ሚሊዮን ብር አለኝ፡፡ ሆኖም በንግድ ባንክ የሚፈለግብኝ ዕዳ 55 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡ ባንኩ በሕግ መጽሐፍ ብቻ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው፡፡ ይህ በመሆኑ ቅሬታም ፀፀትም የለኝም፡፡ ሥራቸውንም አከብራለሁ፡፡
ሪፖርተር፡- ባለፈው ዓመት በስልክ እንደነገሩኝ ከነበረብዎት የ65 ሚሊዮን ብር ዕዳ 25 በመቶ ከፍለው ቀሪውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚያጠናቅቁ ነበር፡፡ ከአንድ ዓመት በኋላም በባንኩ የሚፈለግብዎን ዕዳ አልከፈሉም፡፡
ራም ካሪቱሪ፡- አዎ፡፡ ግን እነሱ እንቢ ስላሉ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- እንቢ ስላሉ ነው ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?
ራም ካሪቱሪ፡- በተለያዩ ቴክኒካዊ ምክንያቶች ነው፡፡ ይህ ሁሌም የሚሆን ነው፡፡ አንዳንዴ የቴክኒካዊ ጉዳዮች …
ሪፖርተር፡- የቴክኒክ ጉዳይ ከምን አኳያ?
ራም ካሪቱሪ፡- ይህንን ለመረዳት ውስብስብ ነገር ነው፡፡ የብድሩ መክፈያ ጊዜ መራዘም ነበረበት፡፡ በብሔራዊ ባንክ መመርያ የተነሳ ግን ሊሆን አልቻለም፡፡ ሕጉ 25 በመቶ የብድሩ መጠን መከፈል አለበት ይላል፡፡ እኛም ያንኑ ከፍለናል፡፡
ሪፖርተር፡- ብድሩን ሙሉ በሙሉ ለመክፈል ፈልጋችሁ ያገዳችሁ የቴክኒክ ምክንያት ሊታየኝ አልቻለም፡፡ በየትኛውም ጊዜ መክፈል ከቻላችሁ ምንድነው ችግሩ?
ራም ካሪቱሪ፡- 25 ከመቶውን ከፍለናል፡፡ ማስረጃም አለን፡፡ ሆኖም ብሔራዊ ባንክ ቀሪው ብድር የሚከፈልበት ጊዜ መራዘም አለበት ቢልም እነሱ ግን ይህንን አላደረጉም፡፡ በንግድ ባንክ ቦታ ገብቼ መመለስ አልችልም፡፡ ተጨማሪ እንድከፍል ጠየቁኝ፣ ከፈልኩ፡፡ ባለፈው ወር አራት ሚሊዮን ብር ከፍያለሁ፡፡ ገበያው አያፈናፍንም፡፡ የንግድ ባንክ ሰዎች እኔን በመወትወት ከህንድ ቼክ አምጥቼ እንድከፍላቸው ያስባሉ፡፡ ይህንን ማድረግ እችላለሁ፡፡ ነገር ግን አላደርገውም፡፡ ክብሬን የማውቅ ሰው ነኝ፡፡ በዚህ አገር የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዕዳ የለብኝም፡፡ የትኛውንም ሕግ አልጣስኩም፡፡ በየትኛውም ፍርድ ቤት አልተቀጣሁም፡፡ ለሁሉም አክብሮት አለኝ፡፡ ወደ ጋምቤላ የሄድኩ አንበሳ ነኝ፡፡ ቆስዬ ይሆናል ግን አሁንም አንበሳ ነኝ፡፡ ለጉራ ወይም ለመኮፈስ አይደለም፡፡ ስንቱ ነው ጋምቤላ ሄዶ የሚያውቅ? ኢትዮጵያዊ ጓደኞቼ ወደ ጋምቤላ መሄዴን እንደ ዕብደት ቆጥረውት ነበር፡፡ ስላሰቡልኝ አመስግኜ ምንም እንደማልሆን ነግሬያቸው ሄጃለሁ፡፡ ወደ ጋምቤላ የሄድኩት የአገሪቱን የምግብ ምርት ለመጨመር በማሰብ ነው፡፡ ይኼ ከመቼ ጀምሮ ወንጀል እንደሆነ አላውቅም፡፡ ገንዘቤን አውጥቼ ነው እርሻ እያለማሁ ያለሁት፡፡ እዚህ አንድ ኪሎ ሩዝ 60 ብር ወይም ሦስት ዶላር ይሸጣል፡፡ በዓለም ገበያ የሩዝ ዋጋ በቶን 350 ዶላር ነው፡፡ ለጂቡቲ መንግሥት በቶን 350 ዶላር ሒሳብ ሩዝ እያቀረብሁ ነው፡፡ እዚህ ግን ለአንድ ቶን ሩዝ 3,000 ዶላር እያወጣችሁ ነው፡፡ ለምን ይህንን ሁሉ ገንዘብ ታወጣላችሁ? ስለድሆቻችሁስ ምን ታስባላችሁ? የምግብ አቅርቦትን ለመጨመር እየሞከርኩ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለምን እንደ ወንጀለኛ ይቆጥረኛል? መንግሥትና ሚዲያውስ ለምን ወንጀለኛ እንደሆንኩ ለሚያስቡኝ አሳልፈው ይሰጡኛል? ለምን ከዚህ አገር እንድሄድ ይገፉኛል?
ሪፖርተር፡- ከፕሬስ አኳያ ስህተት ሲፈጸም መጠየቅ ተገቢነት ያለው ነገር አይደለም እንዴ?
ራም ካሪቱሪ፡- ይኼ ተገቢነቱ እንዴት ነው? ህንድ እያለሁ ባለፈው ጊዜ ደውለህልኝ ሐሳቤን ገልጬልህ ጽፈሃል፡፡ የእኔን ሐሳብ የሚቃረን ነገርም ጽፈሃል፡፡ የግብርና ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ስለእኔ የሰጠውን ትልቅ የተዛባ መግለጫም ጽፈሃል፡፡ ስለተጻፈው ነገር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጬ ጽፌላቸዋለሁ፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣን ስለሆኑ ብቻ ሰድበውኛል ብዬ ጽፌያለሁ፡፡ ማንም ይሁን የሰዎችን ታማኝነት የሚያጥላላና ጥላሸት የሚቀባ ነገር እንዲያደርግ ሊፈቀድለት አይገባም፡፡ ይሁንና ሐራጅ የተባለው ይካሄድ እንደሆነ የምናየው ነው፡፡
ሪፖርተር፡- እንደ ፕሬስ የሰዎችን አመለካከቶች ሚዛናዊ በሆነ መንገድ አቅርበናል፡፡ እርስዎን እንዳነጋገርነው ሁሉ የመንግሥት ኃላፊዎችንም ስለጉዳዩ ጠይቀናል፡፡ ከዚህ በላይ ምን ነበር ማድረግ የሚገባን?
ራም ካሪቱሪ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን አነጋግሩ፡፡
ሪፖርተር፡- ትላልቅ ባለሥልጣናት ካሩቱሪ ለኢትዮጵያ ሰፋፊ እርሻ ትልቅ ተስፋ ቢጣልበትም ውጤት ሊያመጣ አልቻለም፣ ደካማ ነው እያሉ ስለእርስዎ እየተናገሩ እኮ ነው?
ራም ካሪቱሪ፡- አፈጻጸማችን የሚያበሳጭ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ከዚህ በላይ ግን መሄድ አይገባም፡፡ እምነት የማይጣልበት ተብዬ በመንግሥት ባለሥልጣን ልገለጽ አይገባም ነበር፡፡ መሬታችንን እንደሚወስዱ መናገር አይችሉም፡፡ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ መሬቴ በንግድ ባንክ ሥር በዕዳ ምክንያት ያለ ነው፡፡ በንድፈ ሐሳብ ደረጃም ቢሆን ማለት ነው፡፡ ታዲያ እንዴት ነው መሬቱ የሚወሰደው? በንግድ ባንክ ያለብኝን ዕዳ ይከፍላሉ ማለት ነው? እንዲህ ባለው ነገር ላይ ስንከራከር ብስለት ሊኖረን ይገባል፡፡ መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ ባለሥልጣናት አያስፈራሩኝም፡፡ ጋምቤላ ሄጄ ሁሉን ያየሁ ሰው ነኝ፡፡ በድንኳን ውስጥ ለበርካታ ጊዜያት የኖርኩ፣ ከዘንዶውም፣ ከእባቡም፣ ከአንበሳውና ከሚሊዮን ጐሽ ጋር የተጋፈጥኩ ነኝ፡፡ እኔን የምታስፈራሩ ይመስልሃል? ይኼን ሌላ ቦታ ሄዶ መሞከር ነው፡፡ በሕጉ መሠረት ያለኝን መብት ያልተጠቀምኩ፣ ሆኖም በአንዳንድ ቀልደኞች ቸል የተባልኩ ይመስለኛል፡፡ በህንድና በኢትዮጵያ መካከል የኢንቨስትመንት ከለላ የሁለትዮሽ ስምምነት ስላለ ይኼም እኔን ይከላከልልኛል፡፡ መሬቴን ንኩና የህንድን ኃያልነት ታያላችሁ፡፡ ይኼ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ የእስካሁኑ የሚበቃ መሰለኝ፡፡ ራሴን መከላከል አያስፈልገኝም፡፡ ባለሥልጣናት መሬቴን ከነኩ በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ ውጤቱን ያገኙታል፡፡
ሪፖርተር፡- የመንግሥት ኃላፊዎች ተግባራቸውን እየተወጡ እንደሆነ አይገነዘቡም ማለት ነው?
ራም ካሪቱሪ፡- የሕይወቴን አሥር ዓመት እዚህ አሳልፌያለሁ፡፡ አገሪቱን አሁንም ድረስ ሙሉ ለሙሉ አላውቃትም፡፡ በዚህ አገር አስገራሚ የመንግሥት አወቃቀር አለ፡፡ ከላይ ያለው ከፍተኛው የመንግሥት መዋቅር በአብዛኛው በታማኝ፣ ለሚሠሩት ሥራ ቦታ በሚሰጡና በብልህ አመራሮች የተዋቀረ ነው፡፡ ተግባራዊም ባይሆን ከመልካም እሳቤ በመነሳት የሚመሩ ሰዎች ያሉበት ነው፡፡ ሆኖም መካከለኛው ላይ ሥርወ መንግሥት አለ፡፡ በፓርቲ አባልነት የተነሳ ከኃላፊነት ገሸሸ ሊደረጉ የማይችሉ ነገር ግን ለብዙዎች ችግር የሆኑ ኃላፊዎች አሉ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ በግልጽ የፖለቲካ ክርክር እንዲካሄድ በሙሉ ልብ እሞግታለሁ፡፡ ይሁንና ማለት ከሚገባኝ በላይ መናገር አልችልም፡፡ ኢትዮጵያዊ ስላልሆንኩኝ፡፡ ለአገሩ እንግዳ ነኝ፡፡
ሪፖርተር፡- አፈጻጸምዎ መንግሥት በሚጠብቀው ልክ ካልሆነ እኮ …?
ራም ካሪቱሪ፡- መንግሥት ማነው? የሚጠብቀውስ ምንድነው? መንግሥትን እየጠየቅሁ ነው፡፡ አባቴ የሰጠኝን ገንዘብ ነው ጋምቤላ ላይ ያዋልኩት፡፡ ምን አድርጋችሁልኛል? መንግሥት ምንድነው የሰጠኝ?
ሪፖርተር፡- ለመጥቀስ ካስፈለገ ቢያንስ ለም መሬት ሰጥቶዎታል፡፡
ራም ካሪቱሪ፡- ቡል … ይህንን ቃል አትመው፡፡ የተሰጠኝ መሬት ዘጠኝ ወራት ሙሉ ጐርፍ የሚተኛበት ነው፡፡ እዚህ ውስጥ ነው የግብርና መሬት ለመፍጠር እየሞከርኩ ያለሁት፡፡ ይህንን የምትሞግት ከሆነ በቂ አኃዝ አለልህ፡፡ የባሮ ወንዝ ጐርፍ የሚማተኛበት ቦታ ስለሆነ ውኃው ሱዳን ደርሶ ሲመለስ እርሻውን ያጥለቀልቀዋል፡፡ ይኼንን መሬት ነው የሰጣችሁኝ፡፡ ምንም ዋጋ የሌለው ነው፡፡ የተሰጠኝ መሬት ከውኃ ወጥቶ የግብርና መሬት እስኪሆን ድረስ ገንዘብ የሚጠይቅ ነው፡፡ የመንግሥት አስተዳደርን ለመንቀፍ ባይሆንም፣ ሁሉም ኢንቨስተር ከመንግሥት የተሰጠው መሬት ዋጋ ቢስ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- ዋጋ ቢስ ነው ማለት ግን ከባድ ውንጀላ አይሆንም?
ራም ካሪቱሪ፡- አዎ ዋጋ ቢስ ነው፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ሁላችንንም ወደዚህ እንድንመጣ ጋበዛችሁን፡፡ በወቅቱ ይኼ መንግሥት ብልህ ነው ብዬ ነበር፡፡ መሬት በሔክታር 135 ብር እያስከፈሉ ይሰጡ ነበር፡፡ አሁን ከተማ በሆነው ሆለታ አካባቢ ከጋምቤላ ይልቅ ውድ የሆነ መሬት አለ፡፡ የጋምቤላ መሬት ከ10 እስከ 12 በመቶው ተዳፋትና በባህር ዛፍ የተሞላ ነው፡፡ መሬቱን መንጥሮ ለማስተካከል በሔክታር አንድ ሺሕ ዶላር ይጠይቃል፡፡ በዚያ ላይ ለ50 ዓመታት ነው የተሰጠኝ፡፡
ሪፖርተር፡- ስለመሬቱ አስቸጋሪነትና ለማስተካከል ስለሚጠይቀው ወጪ ከመንግሥት ኃላፊዎች ጋር ተነጋግረዋል?
ራም ካሪቱሪ፡- አዎን፡፡ የውጭ ኢንቨስተር ገንዘቡን ይዞ ከመምጣቱ በፊት የሚሰጠው ዋጋና ገንዘቡን ካመጣ በኋላ ያለው ዋጋ አንድ አይደለም፡፡ ይኼ የትም ዓለም ላይ ያለ እውነታ ነው፡፡ በወቅቱ የአበባ እርሻን ያስተዳድሩ ለነበሩት ከፍተኛ ሚኒስትር ጉዳዩን ገልጬላቸው ነበር፡፡ የተሰጠኝ መሬት ጥሩ ባለመሆኑ ለጥ ያለ ሜዳማ መሬት እንደምፈልግ ነገርኳቸው፡፡ ከ20 ሔክታር በላይ አንሰጥም አሉ፡፡ እኔ የምፈልገው ግን ከ100 ሔክታር በላይ ነበር፡፡ ትቼ ስሄድ ግን ከገበሬዎች መግዛት ትችላለህ አሉኝ፡፡ ይኼን ማድረግ እንደሚቻል አላውቅም ነበር፡፡ ከገበሬዎች በቀጥታ መኮናተር እንደሚቻል ተገነዘብኩ፡፡ ከሆለታ ገበሬዎች ጋር ተደራድሬ በዚህ አገር የመጀመሪያውን ኢንቨስትመንት በሆለታ አካሄድኩ፡፡ በሔክታር 30 ሺሕ ብር ከፍዬ መሬት በሊዝ ገዛኋቸው፡፡ የሆለታ እርሻዬ ከብድርም ሆነ ከመንግሥት የተገኘ አይደለም፡፡ ገበሬዎች የሰጡኝ ነው፡፡ ታዲያ ምኑ ነው መሬት ወራሪ፣ ተቀራማች የሚያሰኘኝ? መንግሥት በሔክታር 135 ብር እስከከፈልኩ ድረስ ሊሰጠኝ ፈቃደኛ ነበር፡፡ እኔ ግን አመስግኜ በሔክታር 30 ሺሕ ብር ከፍዬ ወደምገዛበት ሄድኩኝ፡፡ ይህንን በማድረጌ ደደብ ነኝ ማለት ነው፡፡ መንግሥት ግን በዚህ ተገርሞ ወሊሶ ላይ የተንጣለለ መሬት ሊሰጠኝ ተገዷል፡፡
ሪፖርተር፡- ንግድ ባንክ ዕዳዬ ይከፈለኝ እያለ ነው፡፡ ሌሎችም ባንኮች እንዲሁ፡፡ የመንግሥት ኃላፊዎችም ደስተኛ አይደለንም ብለዋል፡፡ ታዲያ የእርስዎ መጨረሻ ምንድነው?
ራም ካሪቱሪ፡- ነገዬን መተንበይ አልችልም፡፡ ነገን ግን መፍጠር እችላለሁ፡፡ ለምንድን ነው ግን ሁሉም ውድቀቴን የሚፈልገው? ሞቴን ለማየት ለምን ይቸኩላሉ? ሁሉን ነገር ዘጋግቼ ባዶ የምቀር እመስላለሁ እንዴ? ይህ ከሆነ ሐሳባችሁ የተሳሳተ ነው፡፡
ሪፖርተር፡- ተስፋ መቁረጥዎን እያሳዩኝ ነው?
ራም ካሪቱሪ፡- በአሥር ዓመት የኢትዮጵያ ኑሮዬ አንድ ነገር ተምሬያለሁ፡፡ አትሞክር፣ ከሞከርክ ግን ማሳካት አለብህ፡፡ ከወደቅህ ትሰቀላለህ፡፡ ማናችሁ እኔን የምትሰቅሉ? እዚህ አገር ውድቀት ቦታ የለውም፡፡ በአሜሪካ ሲሊከን ቫሊ ውስጥ ግን ውድቀት ትልቅ ሀብት ነው፡፡ በአፍሪካ የወደቀ ያበቃለታል፡፡ ስትወድቅ ጥንብ አንሳው ሁሉ ተሰብስቦ ሊበላህ ሞትህን ይጠባበቃል፡፡ መንግሥትንም ሆነ የባንክ ሰዎችን ዕርዳታ እየጠየቅሁ ወይም እስኪሻለኝ ተንከባከቡኝ እያልኩ አይደለም፡፡ ዕርዳታ አልጠየቅሁም፡፡ ማንንም አላስቸገርኩም፡፡ ለማድረግ እየጣርኩ ያለሁት የተከበረ ተግባር ነው፡፡ ምግብ ማምረት ነው፡፡
ሪፖርተር፡- በግብርና ኢንቨስትመንት ጉዳይ ላይ በእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ሥር ያለው የኢትዮጵያ ግብርና ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ነው ኃላፊነት ተሰጥቶት እንደናንተ ያሉትን እርሻዎች የሚከታተለው፡፡ በመሆኑም የኤጀንሲውን ኃላፊዎች መሞገቱም ሆነ ሚናቸውን ማጣጣሉ ምንም ነጥብ ያለው አይመስልም፡፡
ራም ካሩቱሪ፡- የኢትዮጵያ ግብርና ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ሰፋፊ እርሻዎችን እንዲከታተል ነው የተቋቋመው፡፡ እስከዚህ ባለው ሒደት ምንም ቅራኔ የለኝም፡፡ ሆኖም ካሩቱሪ በዚህ ኤጀንሲ ሥር ነው ወይም ኤጀንሲውም ሆነ ኃላፊዎች እኛን ይቆጣጠራሉ ወይ ከተባለ መልሱ በጭራሽ አይደለም ነው፡፡ ካሩቱሪ ክትትል የሚደረግበት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ነው፡፡ ለምን ብለህ አትጠይቀኝ ይኼው ነው የሆነው፡፡ ስለዚህ ለግብርና ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ተጠሪ አይደለንም፡፡ በእኛ ላይ ሥልጣን ስለሌላቸው ገለል በሉ እላቸዋለሁ፡፡ ከእኛ ፕሮጀክት ጋር ለሚያያዝ ማንኛውም ነገር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን ማነጋገር ትችላለህ፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ፕሮጀክት ቢሳካ ጥቅሙ ለኢትዮጵያ ነው፡፡ ቢሰናከል ግን ማንንም ሳይሆን ካሩቱሪን ነው የሚጎዳው፡፡ እ.ኤ.አ. በ2007 የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ካፒታሌን ለማሳደግ እንዲረዳኝ የአክሲዮን ድርሻ እንድሸጥ ነግረውኝ ነበር፡፡ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የሚያስችል ገንዘብ እንዳለኝ ነግሬያቸዋለሁ፡፡ አክሲዮን ለመሸጥ ወደ ገበያ መምጣት አላስፈለገኝም፡፡ በጊዜው የአክሲዮን ገበያው እንዳሁኑ ቁጥጥር አልተደረገበትም ነበር፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ልማት ባንክም መሄድ አላስፈለገኝም፡፡
ሪፖርተር፡- ሆኖም ከንግድ ባንክ ለሥራ ማስኬጃ ገንዘብ ተበድረዋል፡፡
ራም ካሩቱሪ፡- ይህ እውነት አይደለም፡፡ ከንግድ ባንክ ጋር ያለን ጠብ በአንድ መነሻ ምክንያት ነው፡፡ ፕሮጀክቱን ለማልማት 180 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለማምጣት እየሠራሁ ነበር፡፡ ብሔራዊ ባንክ ገንዘቡን ማምጣት የምችልበት ፈቃድ እንዲሰጠኝ አመልክቼ ነበር፡፡ ገንዘቡ በብድር የሚመጣ በመሆኑም መልሼ ማስወጣት እንድችልም ነበር የጠየቅሁት፡፡ ብሔራዊ ባንክ በገንዘቡ መምጣት ላይ መወሰን አልቻለም፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አማክሬ ገንዘቡን ለውጭ የምታመጣው ከሆነ ምንም ችግር የለውም ስላሉ፣ በኋላም ገዥው ባንክ ስለፈቀደ የውጭ አበዳሪዎቼ ከህንድ በመምጣት 180 ሚሊዮን ዶላሩን ሊሰጡን ዝግጁ ነበሩ፡፡ ይሁንና ጠበቆች ምን ሲደረግ በአገር ውስጥ ፈቃድ የሌለው ባንክ እንዴት ንብረት አስይዞ ይበደራል? ሕጉ አይፈቅድም አሉ፡፡ ስለዚህ እዚህ ያለኝን ንብረት በዋስትና በማስያዝ መበደር አይቻልም ማለት ነው፡፡ ይህ ሲሆን ከአገር ውስጥ ባንኮች አነስተኛ ገንዘብ በመበደርና እነሱን አጋር በማድረግ በሚጽፉልን የዋስትና ሰነድ ብድሩን ልናገኝበት የምንችልበት ዕድል እንዳለ ምክር ስላገኘን ለንግድ ባንክ የብድር ጥያቄ አቀረብን፡፡ ከመነሻው 25 ሺሕ ሔክታር በማስያዝ ነበር ብድር የጠየቅነው፡፡ ሆኖም የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ስለንብረት ሲጠየቅ 100 ሺሕ ሔክታር ነው በማለት ሙሉውን መሬት ለማስያዣነት ሰጣቸው፡፡ ከዚሁ ሁሉ በኋላም ንግድ ባንክ የዋስትና ሰነዱን ይሰጠናል ብለን በተስፋ ብንጠብቅም ለአምስት ዓመታት ያህል ቆይቶም አልተሰጠንም፡፡ ይህንን ላደረጉበት በርካታ ምክንያቶችን ያቀርባሉ፡፡ በዚህ ሒደት አበዳሪዎቼ ፍላጎት በማጣት ሄደዋል፡፡ የ180 ሚሊዮን ዶላሩን ብድር ያጣሁትም በንግድ ባንክ እንቢተኛነት ነው፡፡ ስለዚህ አሁን ላይ የምንፋለምበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ልናገር ከምችልበት ርቀት በላይ መናገር አልችልም፡፡ ነገር ግን ያለኝ ማስረጃ በርካታ ሰዎችን ሊጎዳ ይችላል፡፡ ይህ ግን ለእኔ ምንም አይጠቅመኝም፡፡
ምንጭ ሪፖርተር

መድረክ የሰልፍ ጥያቄውን በድጋሚ ለማቅረብ መወሰኑን አስታወቀ-VOA Amharic

$
0
0

በኦሮሚያ ክልል በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰዱ የኃይል እርምጃዎችንና የተፈፀሙ ግድያዎችን ለማውገዝ በሚል ለዛሬ ጠርቶት የነበረ ሰልፍ ዕውቅና ባለማግኘቱ ጥያቄውን በድጋሚ ለማቅረብ መወሰኑን መድረክ አስታውቋል፡፡
መድረክ ትናንት ባካሄደው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ስብሰባ ነው ውሣኔውን ያሳለፈው፡፡
የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሰጡት መግለጫ የሰልፉ ዓላማ ሲያብራሩ ሕገወጥ ግድያዎችንና ሕገ መንግሥታዊ የሆነውን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግን ነፃነት በመፃረር የተወሰዱ የኃይል እርምጃዎችን ለመኮነን እና ለዚህም ለተሰዉት ወገኖቻችን ያለንን ክብር ለመግለፅ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር ለሰልፉ ዕውቅና እንዳይሰጥ ያደረጉትን ምክንያቶች ሲዘረዝር “ሰልፉ የሚያልፍባቸው አካባቢዎች በልማት ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ ያለባቸውና በርካታ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት የሚገኙባቸው መሆናቸውን ገልፆ “እንዲሁም አሁን ባለው የወቅቱ ሁኔታም ጥያቄውን ተቀብለን ዕውቅና ለመስጠት እንቸገራለን” ብሏል፡፡


አዲስ አባባ ስለምን ታወዛግባለች?(በዘላለም ክብረት)

$
0
0

ሕሩይ ሚናስ አስደናቂ ሰው ነው፡፡ የገበሬ ልጅ፣ በአስራዎቹ መጨረሻ አዲስ አበባ የገባ፡፡ ከዛም የአብነት ተማሪ ሆነና ቅዳሴና ቅኔ ሞካከረ፡፡ እሱ አልሆን ሲለው ጎዳና ወጥቶ ጎዳና አዳሪ ሆነ፡፡ ቀጠለና የለማኝ መሪ (sighted guide) ሆነ፡፡ እሱም ሲያልፍ ‹ለምን አልማርም?› ብሎ ትምህርት ተማረና ዩንቨርሲቲ በገባ በዓመቱ ‹ማርክሲስት› ሆነ፡፡ ትምህርቱንም ለአቢዮቱ ሲባል ተወውና መፅሃፍ ነጋዴ ሆነ፡፡ ማርክሲስት ነጋዴ! ‹ከወገብ በላይ ታቦት፣ ከወገብ በታች ጣኦት› እንዲሉ የትናንት ቀዳሹ ሕሩይ ዛሬ ማርክስዚምን ወደደ፡፡ የሕሩይ ማርክሲዝም ከትናንት ማንነቱ እጅግ በተለየ መንገድ ወሰደው፣ የመፅሃፍ አርታኢነት፡፡ መፅሃፍ ሲያነብ፣ ሲተረጉም፣ ሲፅፍና የአርትኦ ስራ ሲሰራ ውሎ ጫት ይቅማል፤ በዛ ላይ አረቄም ይሞካክራል፡፡ በመጨረሻ አበደ፡፡ ከዛ በኋላ ያለው የሕይወቱ ምዕራፍ ብዙ ያሳዝናል፡፡
በኋላ ከአዕምሮ ሕመሙ ሲያገግም ግን የሚገርም ነገር አደረገ፡፡ ‹እብድ› እያለ ሲያደርጋቸው ነበሩትንና የሚያስታውሳቸውን ነገሮች ሁሉ በተርታ ፅፎ ‹እብዱ› በሚል ርዕስ መፅሃፍ አሳተመ፡፡ ይህ መፅሃፉ ለሕሩይ ከብዙ ስራዎቹ አንዱ ነው፡፡ ስለ አዲስ አበባ ለመፃፍ ከሕሩይ የተሻለ ምሳሌ ማግኝት ይከብዳል፡፡ እሱም ‹ወይ ዐዲስ ዓበባ› በሚል ርዕስ (እውነትን መሰረት ያደረገ) መፅሃፍ ፅፎ አዲስ አበባ ከሩቅ ሲያይዋት ምን እንደምትመስል ይተርካል፡፡ በሕሩይ የገጠር ሕይወት አይን አዲስ አበባ ገነት ነበረች፡፡ ሕሩይ እንዲያውም በመደነቅ ‹‹ለካ የዐዲስ ዓበባን ሰው ፎቶ እያነሱ ነው ወደ ገጠር ‹ምስለ መላዕክትና ሰማዕት› እያሉ የሚልኩልን›› በማለት እሱ ከሚያውቀው ገጠርና ሕዝቡ አንፃር አዲስ አበባ ገነት፣ ነዋሪዎቿም መልዓክት እንደሆኑ ይገልፃል፡፡ ገነት ሆና ከሩቅ የታየችው አዲስ አበባ ሲገባባት ጎዳና ላይ አስተኝታዋላች፣ ‹አቢዮተኛ› አድርጋዋለች፣ አሳብዳ አስለፍልፋዋለች … በስተርጅናውም ‹ከጋራ ኮንዶሚኒየም ቤቶቿ› በአንዱ ይኖር ዘንድ ፈቅዳለታለች፡፡ ሕሩይ አዲስ አባባን ከሩቅ አይቶ ጎምጅቶባታል፡፡ አዲስ አበባን ጉያዋ ስር ሆኖም ተሰቃይቶባታል፡፡ ዛሬ ደግሞ አዲስ አበባ ሕሩይን እንከባከብኻለሁ እያለችው ነው፡፡ ሕሩይ ሚናስ – ራሱን ‹አውግቸው ተረፈ› ብሎ የሰየመ ሰው፡፡
ይህ የሕሩይ ብቻ ታሪክ አይደለም፡፡ የብዙ ኢትዮጵያዊያንም እንጂ፡፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ አዲስ አበባን ከከተማም በላይ የስልጣኔ ምልክት አድርጎ ነው የሚቆጥራት፡፡ እንዲያውም ሌሎች ከተሞች የሚለሙት ከአዲስ አበባ የሚመጡ ነዋሪዎች እንዲዝናኑባቸው ሁሉ እስኪመስል ድረስ የሌሎች ከተሞችን ዕድገት ሁሉ ወሳኟ አዲስ አበባ እየሆነች ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ አካባቢዎች ‹የአዲስ አበባ እንግዶች መጥተዋል› ከተባለ ነገሩ ትልቅ ነው፡፡ አንዳንዴማ ‹እሷ እኮ አዲስ አበባ ቤት አላት› ሲባል ሁሉ ነው ሃብት የሚቆጠረው፡፡
አዲስ አበባ አንድ ከተማ ብቻ ነች ማለት ከባድ ነው፡፡ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ 3.6 በመቶው ብቻ ቢሆንም አዲስ አበባ የሚኖረው ቀሪው የሀገሪቱ ሕዝብ ያለ አዲስ አበባ ምንድን ነው? እስኪባል ድረስ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ለተባለው ዓለም የስበት ማዕከል (center of gravity) ናት፡፡

1. “Addis Ababa: The 3rd most ‘Primate City’ on earth”
ጅኦግራፈሩ ማርክ ጀፈርሰን በጎርጎሮሳዊያን አቆጣጠር በ1939 አንድ የከተሞች እድገት ምጥጥን (balance) የሚገልፅ ሃሳብ ይዞ ብቅ አለ፡፡ የአውራ ከተማ (Primate City) ፅንሰ ሃሳብን፡፡ እንደ ጀፈርሰን አገላለፅ አንድ ከተማ በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ሌሎች ከተሞች መካከል በሕዝብ ቁጥር ትልቁ ሲሆንና የሕዝብ ቁጥሩም በሁለተኝነት ከሚከተለው ከተማ በእጥፍ ሲበልጥ ያ ከተማ ‹አውራ ከተማ› (Primate City) ይባላል፡፡ (በኋላ በጀርመናዊው ጅኦግራፈር ዋልተር ክራይስትለር የተፈጠረው የCentral Place Theory (CPT) በበኩሉ አውራነት የሚለካው አውራው ከተማ ከተከታዩ በሁለት ዕጥፍ ከበለጠ ነው በማለት ሌላ መከራከሪያ አቅርቧል)፡፡ ለማንኛውም ጀፈርሰን ይሄን የከተማ አውራነት መስፈርት (primacy rule) ካስቀመጠ ከአስር ዓመታት በኋላ በተለምዶ ‘Zipf’s law’ የሚባለውና በሳይንሳዊው አጠራር ‘Rank Size Rule’ እየተባለ የሚጠራው የምጥጥን (proportionality) ሂሳብ በአሜሪካዊው የስነ ቋንቋ ምሁር ጆርጅ ዚፒፍ ብቅ አለ፡፡ ዚፒፍ ምጥጥኑን ከቋንቋ ጋር አያይዞ ያቀረበው ቢሆንም በኋላ ወደሌሎች ጉዳዮችም አድጓል፡፡ በዚህም መሰረት እንደ ዚፒፍ ሎው የአንድ ሀገር የከተማ እድገት ጤነኛ ነው የሚባለው በአንድ ሀገር ውስጥ ካለው በሕዝብ ቁጥሩ ትልቁ ከተማ ቀጥሎ በሁለተኝነት የሚገኝው ሁለተኛው ከተማ በሕዝብ ትልቁ የሆነውን ከተማ ግማሽ ያክል ሕዝብ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ሶስተኛው ትልቅ ከተማ ደግሞ የትልቁን ከተማ ሲሶ ያህል ሕዝብ ሊኖርበት ይገባል፡፡ አራተኛው ትልቅ ከተማ ደግሞ የትልቁን ከተማ ሩብ ያህል ሕዝብ ሊኖርበት ይገባል… እያለ ምጥጥኑን ይቀጥላል፡፡
እንግዲህ ይሄን ህልዮታዊ መነሻ ይዘን፡፡ የአውራ ከተማ መኖር ምንን ያመላክታል የሚለውን ጉዳይ ስናይ ነው የሕልዮቶቹ መሰረት የሚገለፅልን፡፡ አንድ ሀገር አውራ ከተማ አላት ማለት አውራ የተባለው ከተማ የሀገሪቱ የትኩረት ነጥብ (national focal point) ነው ማለት ነው፡፡ ከዛም ባለፈ ያ ከተማ የሀገሪቱን ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በዋነኛነት በያኝ (strong pull factor) ነው ማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ሀገሪቱ የንጉሳዊ ግርማ (King Effect) ሰለባ ነች ማለት ነው፡፡ ስለ ሀገሪቱ ማውራት ማለት ስለ አውራው ከተማ ማውራት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በመዓከሉ (center) እና በዳር ሀገሩ (periphery) መካከል የእኩልነት ሚዛን እጅግ ተዛብቷል (imbalance) እንደማለት ነው፡፡

1.1. ሁለተኛ ከተማ (Secondary City)
በሌላ በኩል ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአውራ ከተማን ፈተና ለመከላከልና ፍትሃዊ የከተማ እድገት እንዲኖር ሲባል የዓለም ባንክን ጨምሮ ብዙ ፖሊሲ አውጭዎች የሁለተኛ ከተማ (Secondary City) አማራጭን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም ማለት ከትልቁ ከተማ ባለፈ በሀገራት ውስጥ ከትልቁ ከተማ ብዙም ያልራቁ (አንዳንዶች ከ500,000 – 3,000,000 ነዋሪ ያለባቸው ከተሞች ሲሉ ሁለተኛ ከተማነትን ያብራራሉ) አማራጭ ከተሞችን መፍጠር ነው፡፡ ደቡብ ምስራቅ እስያ በዚህ በኩል በጣም የተሳካለት የዓለማችን ክፍል ነው፡፡

1.2. ኢትዮጵያስ?
የኢትዮጵያን ጉዳይ ስንመለከት ከላይ ከቀረቡት ሕልዮቶችና የፖሊሲ አውጭዎች ምክረ ሃሳብ እጅግ በተቃራኒው እናገኛታለን፡፡ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን በሃምሌ 2007 ባወጣው ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ 973 ከተሞች እንዳሏት የገለፀ ሲሆን፤ ከሀገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብም 19 በመቶ የሚሆነው (ይህ አሃዝ አከራካሪ ነው) በከተማ ውስጥ ይኖራል ይላል ሪፖርቱ፡፡ ምንም እንኳን ኢትዮጵያ 973 ከተሞች ቢኖሯትም ከአምስቱ የከተማ ነዋሪዎች መካከል አንዱ በአዲስ አበባ ከተማ ነው የሚኖረው፡፡ በሌላ አነጋገር በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ (አዲስ አበባን ሳይጨምር) ከአንድ መቶ ሺህ ሕዝብ በላይ ያላቸው አስራ ስድስት ከተሞች ያሉ ሲሆን፤ የአስራ ስድስቱ ከተሞች ሕዝብ ተደምሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ጋር እኩል ነው፡፡
የማርክ ጀፈርሰንን የአውራነት ሕግ (primacy rule) እዚህ ላይ አምጥተን ስንመለከት አዲስ አበባን ከአውራም አውራ ሆና እናገኛታለን፡፡ ይሄም የሚሆነው በአንድ ሀገር ውስጥ ያለው ትልቅ ከተማ (አዲስ አበባ) በሀገሪቱ ውስጥ ካለው ሁለተኛ ትልቅ ከተማ (በሃምሌው የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን ሪፖርት መሰረት አዳማ ከተማ ናት ሁለተኛዋ ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማ) በእጥፍ ከበለጠ አውራ ከተማ እንደሚባል ከላይ ያየን ሲሆን፣ በዚህ ስሌት መሰረትም አዲስ አበባ ከተከታዩ አዳማ ወደ አስራ አንድ እጥፍ እንደምትበልጥና ይሄም አዲስ አበባ ከታይላንዷ፣ ባንኮክና ከፔሩዋ ሊማ ቀጥላ በዓለም ላይ ሶስተኛዋ አውራ ከተማ ሲያደርጋት በአፍሪካ ደግሞ አንደኛዋ ያደርጋታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ግዝፈቷ የዚኮፍን የምጥጥን ሎው እንኳን መተግበር ማሰብም ከባድ ያደርገዋል፡፡ ይህ የተዛባ ምጥጥን አዲስ አበባ ከመመስረቷ ጀምሮ የተፈጠረ ነው ማለት ደግሞ ከባድ ነው፡፡ የአለፈውን የመቶ ዓመት እድገት እንኳን ብንመለከት በ1910 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 65,000 የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥርም በጊዜው ከሀረር ከተማ ሕዝብ ጋር እኩል ነበር፡፡ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ 1935 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 100,000 ሆነ፡፡ ከሌላ ሃያ አምስት ዓመታት በኋላ በ1961 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 443,728 ደረሰ፡፡ አሁንም ከሌላ ሃያ አምስት ዓመታትም በኋላ በ1984 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ 1,423,111 ደረሰ፡፡ በመጨረሻም ከ35 ዓመታት በኋላ በ2015 የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ከእጥፍ በላይ ጨምሮ ዛሬ 3,194,000 ደርሷል፡፡ ከመቶ ዓመታት በፊት በጊዜው በሕዝብ ቁጥር ሁለተኛ ከነበረችው የሀረር ከተማ ጋር ተመጣጣኝ ቁጥር የነበረው የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ዛሬ በሁለተኝነት ከምትገኝው አዳማ ከተማ አስራ አንድ እጥፍ በልጣ በአውራ ከተማነት በሩቅ ተቀምጣለች፡፡
ስታንሊ ብሩን የተባሉ ፀሃፊ ‹‹የአውራ ከተማ መኖር በራሱ የሀገሪቱ እድገት ጤናማ እንዳልሆነና የተዛባ እንደሆነ ማሳያ ነው፡፡ ይሄም ማዕከሉ (center) ከዳሩ (periphery) አለመመጣጠናቸውን ያስገነዝበናል› ይላሉ፡፡ እንግዲህ የአሁኗ ኢትዮጵያን ፍትሃዊነት አዲስ አበባ በደንብ የምትገልፃት ይመስላል፡፡
አዲስ አበባ በታሪኳ ሶስት ጊዜ ከዋና ከተማነቷ የመቀየር እጣ ፋንታ ተጋርጦባት እንደምንም አልፋዋለች፡፡ የመጀመሪያው በአፄ ምኒልክ ዘመን በአካባቢዋ ያለው የማገዶ እንጨት በማለቁ ምክንያት ዋና ከተማው ወደ አዲስ ዓለም ለመቀየር በታሰበበት ወቅት ባህር ዛፍ ከአውስትራሊያ መጥቶ አዲስ አበባን ከመቀየር አድኗታል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ ጣሊያን አዲስ አበባን በተቆጣጠረበት ወቅት አዲስ አበባ ተራራማ ከተማ ላይ በመሆኗ ጣሊያኖቹ የራሳቸውን የቅኝ ግዛት ዋና ከተማ (colonial city) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ ለመመስረት ጥረት አድርገው በፋይናንስ እጥረት ምክንያት ሊተዉት ችለዋል፡፡ እንዲሁም አፄ ኃይለስላሴ የቀደመውን የተንቀሳቃሽ ዋና ከተማ (roving cities) ልምድ ለማስቀጠልና የራሳቸውን ዋና ከተማ ለማቋቋም በማሰብ ባህርዳርን ዋና ከተማቸው ለማድረግ አስበው እንደነበር ታሪክ ፀሃፊው በላይ ግደይ ‹አዲስ አበባ ያብባል ገና› ባሉት መፅሃፋቸው ላይ ይጠቁማሉ፡፡ ዛሬ አዲስ አበባ ዋና ከተማ ብቻ ሳትሆን ‹ሀገር› ናት፡፡ የበታቾቿን በሩቅ የምታይ ከተማ፡፡
በሌላ በኩል እነ ዓለም ባንክ እያስተዋወቁት የሚገኝው የሁለተኛ ከተማ (Secondary City) ፅንሰ ሃሳብም በአሁኗ ኢትዮጵያ ቦታ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ በፖለቲካና የንግድ ማዕከልነት የአውራዋን አዲስ አበባን ሚዛን የሚገዳደር አይደለም፤ ተስፋ እንኳን ያለው ከተማ አለ ማለት በጣም ከባድ ነው፡፡ ይህ የአዲስ አበባ አውራነትም ከተማዋን በሀገሪቱ ውስጥ በነዋሪ ደረጃ የመሰረታዊ አገልግሎቶች በቀላሉ የሚገኝባት (the highest concentration of basic service facilities per population) ቀዳሚ ከተማ አድርጓታል፡፡ ይሄም ከተማዋን ‘privileged position’ ያሰጣት ከመሆኑም ሌላ፤ አዲስ አበባን እጅግ ግዙፍና የማይደረስባት አይነት ከተማ አድርጓታል፡፡
ከአዲስ አበባ ምስረታ ጋር ተያይዘው ከሚነገሩ አፈ ታሪኮች አንዱ፣ የአፄ ምኒልክ ሃይለ መለኮት አያት የሆኑት ንጉሰ ሸዋ ሳህለስላሴ በአንድ ወቅት ጉለሌ የሚገኝ አንድ ዛፍ ስር ቁጭ ብለው ‹እዚህ አካባቢ የልጅ ልጆቼ ትልቅ ከተማ ሲመሰርቱ ይታየኛል› ብለው ነበር ይላል፡፡ ሳህለስላሴ የዛሬዋን አዲስ አበባ ቢያዩ ‹እንዴ እኔ በራዕይ ያየሁት እኮ ሀገር አይደለም ከተማ ነው› ብለው መደናገራቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡
የፌደራል ሀገሮች ተሞክሮ እንደሚያሳየን ፌደራሊዝም ‹አውራ ከተማን› (Primate City) ያጠፋል፡፡ የደቡብ ምስራቅ ተሞክሮ እንደሚያሳየን ደግሞ ልማታዊ መንግስት በዛ ያሉ ሁለተኛ ከተሞችን (Secondary Cities) ይፈጥራል፡፡ አውራዋ አዲስ አበባ የአውራዎች አውራ እየሆነች እየሄደች ሲሆን፡፡ አውራ ብቻ ሳትሆን ሁለተኛ ከተማም (Secondary City) ራሷ አዲስ አበባ ነች፡፡ አዲስ አበባ ብቻዋን እንዲህ ገዝፋ የአውራም አውራ እስክትሆን ድረስ ፖሊሲ አውጭዎቹ የት ሂደው ነው ብሎ መጠየቅ እዚህ ጋር ተገቢ ነው፡፡ የአሁኗ አዲስ አበባ ሕጋዊ (Legal status) ምንድን ነው ብለንም መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡

2. አዲስ አበባ ምንድን ናት?
ኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓትን በሕገ መንግስት ደረጃ ከተቀበለች ሁለት አስርት ዓመታትን አስቆጥራለች፡፡ የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓትም በሕገ መንግስት ደረጃ ዘጠኝ ክልሎችንና አዲስ አበባን እንደ አንድ የፌደራል ከተማ አስተዳደር (ድሬ ዳዋ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች መካከል ያለው የይገባኛል ጥያቄ ‹ዘላቂ የሆነ ሕጋዊ መፍትሔ እስኪያገኝ› ለፌደራል መንግስቱ ተጠሪ በመሆን በአዋጅ ቁጥር 416/1996 የተቋቋመች የከተማ አስተዳደር ናት) በማድረግ ተቋቁሟል፡፡ በሕገ መንግስቱም ሆነ በኋላ ከተማዋን በሕግ ለማቋቋም በወጡት ቻርተሮች የከተማዋ ሕጋዊ ‹ስታተስ› (ከዋና ከተማነት ባለፈ) በግልፅ ባለመቀመጡም የከተማዋ ‹ስታተስ› ለተመሳሳይ ጥያቄ የተለያዩ መልሶችን እየሰጠ ቀጥሏል፡፡ ዓለም ላይ ባሉ የተለያዩ የፌደራል ስርዓቶች ዋና ከተማ ከዚህ በሚከተሉት ሶስት ጎራዎች በአንዱ ላይ ይመደባል፡፡ ራሱን የቻለ ክልል (City State)፣ በሕግ በፌደራል ቀጠናነት የተመደበ ከተማ (Federal District)፣ እና በአንድ ክልል ውስጥ የሚገኝ አንድ ከተማ (A City in A State)፡፡ ኢትዮጵያም በሕግ የፌደራል ስርዓትን ያቋቋመች ሀገር በመሆኗ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በየትኛው ጎራ ትመደባለች ለሚለው ጥያቄ አንድ አይነት መልስ ማግኝት አስቸጋሪ ነው፡፡ ይህ አስቸጋሪ ሁኔታም ነው በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል መካከል ያለው ውዝግብ እንዳይፈታ አይነተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ያለው፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ሶስቱ መደቦች አንፃር የአዲስ አበባን ‹ስታተስ መመልከት› ጉዳዩን በበለጠ እንድንረዳው ይረዳናልና እሱን እንመልከት፡፡ ለመሆኑ አዲስ አበባ ምንድን ናት?

2.1. ራሷን የቻለች ክልል (City State) ናት
የፌደራል ስርዓትን ተግባራዊ ያደረጉ ሀገሮች ከሚያጋጥሟቸው ፈተናዎች አንዱ ዋና ከተማን መምረጥና መሰየም ነው (የስዊዘርላንድ ሕገ መንግስት በሕገ መንግስት ደረጃ ዋና ከተማ ከመሰየም የተቆጠበውም በዚህ ውዝግብ ምክንያት ነው)፡፡ የፌደራል ስርኣት የመንግስት ስራን በማዕከሉ መንግስትና በክልሎች መካከል የሚከፍል በመሆኑ ዋና ከተማዋን የትኛው ክልል ላይ ማድረግ አለብን የሚለው ጥያቄ አወዛጋቢ ነው፡፡ እንደ ጀርመን እና ቤልጅየም ያሉ የፌደራል ሀገሮች ለዚህ መፍትሔ ብለው ያቀረቡት ሀሳብ ዋና ከተማውን ራሱን የክልል ማዕረግ በመስጠት ከፌደራሉም ሆነ ከክልል መንግስታት ነፃ ማውጣትን ነው፡፡ በመሆኑም በርሊን በአሁኑ ወቅት ከአስራ ስድስቱ የጀርመን ክልሎች አንዷና ዋና ከተማ ስትሆን የቤልጀሟ ብራሰልስም ከቤልጅየም ሶስት ክልሎች አንዷ በመሆን የተፎካካሪዎቹ ፍሌሚሽና ዋሎን ክልሎች አስታራቂ ሁና በመሃል ትገኛለች፡፡
ታዲያ አዲስ አበባ ከዚህ ሞዴል ጋር ምን አገናኛት? በርግጥ አሁን በስራ ላይ ያለው ሕገመንግስት ያቋቋመው ዘጠኝ ክልሎችን ብቻ ነው፡፡ አዲስ አበባ ደግሞ ከነዚህ ክልሎች ውጭ ናት፡፡ ነገር ግን አዲስ አበባን በዋና ከተማነት ያቋቋመው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 49ን በጥልቀት ስንመለከት በንዑስ አንቀፅ ሁለት ላይ አዲስ አበባን ራሷን በራሷ የማስተዳደር ሙሉ መብት ይሰጣታል፡፡ ይህ አንቀፅም በሽግግር መንግስቱ ወቅት በአዋጅ ቁጥር 07/1984 እንደ ራስ ገዝ አስተዳደር በመሆን የተቋቋመችውን አዲስ አበባን መንፈስ ያጠናክራል፡፡ ይሄንም ስንመለከት አዲስ አበባ በተግባር (de facto) ራሷን የቻለች ክልል ትመስላለች፡፡ በነገራችን ላይ አዲስ አበባ ራሷን ችላ በሕግ ደረጃ (de jure) ክልል እንድትሆን ከሽግግሩ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የሚጎተጉቱ አካላት ብዙ ናቸው፡፡

2.2. የፌደራል ቀጠና (Federal District) ናት
በሌላ በኩል የፌደራል ዋና ከተማን የመምረጥ ፈተና ለማለፍ በዛ ያሉት ፌደራል ሀገሮች ዋና ከተማዋን በፌደራል ቀጠናነት (Federal District) በሕግ በመከለል ተጠሪነቷን ሙሉ ለሙሉ ለፌደራል መንግስት የማድረግን አሰራር ይጠቀማሉ፡፡ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆኑት አሜሪካና ሕንድ ናቸው፡፡ አሜሪካ ከሜሪላንድና ከቨርጅኒያ ግዛቶች መሬት በመውሰድ ዋሽንግተን ዲሲን በዋና ከተማነት ሰይማ (ስፋቱ ከአስር ማይል መብለጥ የለበትም የሚል ገደብ በማስቀመጥ) ተጠሪነቷን ለኮንግረስ አድርጋለች፡፡ ሕንድም ዴልሂን ዋና ከተማና የፌደራል ቀጠና አድርጋ ተጠሪነቱን ለምክር ቤት አድርጋለች፡፡ ይህ አይነት የዋና ከተማ አደረጃጀት የራሱ የሆነ (በተለይም ከምርጫ፣ ግብር እና የክልሎች መብት አንፃር) ችግሮች ያሉበት ነው፡፡ ከታች ለማየት እንሞክራለን፡፡
አዲስ አበባን ስንመለከት የህገ መንግስቱ አንቀፅ 49 (3) እና (4) አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌደራሉ መንግስት መሆኑን በመግለፅ የአዲስ አበባ ቀጠና የፌደራል ቀጠና እንደሆነ በተዘዋዋሪ ያስረዳል፡፡ ይህ ብዙ ሰዎች የሚስማሙበት ሃሳብ ቢሆንም ተያያዥ ችግሮች ግን በየጊዜው መነሳቸው አልቀረም፡፡

2.3. በአንድ ክልል የምትገኝ አንድ ከተማ (A City in a State) ናት
ሌላው ከፌደራል ዋና ከተማ አመሰራረት ጋር ተያይዞ የሚቀርበው መፍትሔ ደግሞ ዋና ከተማዋን ከክልሎች (States) በአንዱ ከተማ ላይ ማድረግና ክልሎች ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኙ ማድረግ የሚለው ነው፡፡ የዚህ መፍትሔ ምሳሌ ተደርጋ የምትቀርበው ካናዳ ነች፡፡ የካናዳዋ ዋና ከተማ ኦታዋ ከካናዳ ስድስት ክልሎች አንዷ በሆነችው ኦንታሪዎ ግዛት ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ ኦንታሪዎም እንደ ዋና ከተማ መቀመጫ ክልልነቷ ከኦታዋ ማግኝት የሚገባት ጥቅም በሕግ የተደነገገና የፀና ነው፡፡ ይህ አካሔድ በሌሎች ክልሎች ዘንድ ቅሬታ ይፈጥራል የሚል ትችት ይቀርብበታል፡፡
የአዲስ አበባን ጉዳይ ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ደግሞ ከላይ በጠቀስነው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 49 (5) ላይ ‹የኦሮሚያ ክልል […] አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሃል ላይ የሚገኝ በመሆኑ […] ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል› ይላል፡፡ ይሄም ማለት በሌላ አነጋገር አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ አንድ ከተማ ነች እንደማለት ነው፡፡

2.4. ቻርተርድ ከተማ (Chartered City) ናት
አዲስ አበባ ሶስቱንም የፌደራል ዋና ከተማ ባህሪ አዳለ በመያዝ በየትኛው ሕጋዊ ‹ሰታተስ› ላይ እንዳለች ግራ የምታጋባ ከተማ ነች፡፡ ከዚህ በባሰ ደግሞ ከተማዋ በራሴ ቻርተር የምትተዳደር ከተማ (Chartered City) ነኝ በማለት ራሷን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ቻርተር 87/1989 አቋቁማለች (ቻርተሩ በ1995 በአዋጅ ቁጥር 311/1995 እና በአዋጅ ቁጥር 361/1995 ሙሉ ለሙሉ ተሸሽሏል፡፡ እንዲሁም በ1996 በአዋጅ ቁጥር 408/1996 በከፊል ተሻሽሏል)፡፡ ይህ በዋናነት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የከተማ ድህነትን ለመቀነስ እንደስትራቴጅ እየተወሰደ ያለ የአወቃቀር አይነት አዲስ አበባ ለምን እንደመረጠችው ብዙም ግልፅ ባይሆንም፤ በሁሉም ቻርተሮች ላይ ዋነኛ ዓላማው ‹የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ስልጣን እንዳለው […] በሕገ መንግስቱ በመደንገጉ› ምክንያት እንደሆነ ተገልፆ እናገኛለን፡፡ አዲስ አበባ ቻርተርድ ከተማ ነች ማለትም ከላይ 2.1 ላይ ለማመላከት የተሞከረውን የክልል ማዕረግ (status of state) የሚያጠናክር ሃሳብ ሆኖ የከተማዋን ስታተስ ለመወሰን ከላይ ያየናቸውን የዋና ከተማ ብያኔ ክርክር የበለጠ ያጦዘዋል፡፡
እንግዲህ አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል ናት፣ ተጠሪነቷ ለፌደራል መንግስቱ የሆነች የፌደራል ቀጠና ናት፣ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኝ አንድ ከተማ ናት እንዲሁም በራሷ የቆመች ቻርተርድ ከተማ ነች የሚሉ የራሳቸው አሳማኝ ምክንያት ያላቸው መከራከሪዎች ይቀርባሉ፡፡ ይህ ግልፅነት የጎደለው የከተማዋ ‹ስታተስም› አሁን ከተማዋን አስመልክቶ ለሚነሱ ውዝግቦች መነሻና መድረሻ ነው፡፡

3. ‹የአንተም ተው፣ አንችም ተይ ፌደራሊዝም› እና መዘዙ
[የኢትዮጵያ የሕገ መንግስት ኮሚሽን] ሰብሳቢ [አቶ ክፍሌ ወዳጆ] [የኮሚሽኑ] አባላት ተሳትፎና ኮሚሽን የሥራ ሒደት በተመለከተ አልፎ አልፎ አባላት በስብሰባ ላይ ያለመገኝት ሁኔታ በማሳየታቸው የስራ መጓተት እየተከሰተ መሆኑን፣ ከፓናሎች የሚጠበቁ ሪፖርቶች በተፈለገው ጊዜ ሊቀርቡ እንዳልቻሉና ይኸውም የፓናል አባላቶች በስብሰባ አለመገኘት ዋነኛው ምክንያት መሆኑን ገልፀው፣ ለመጪው ጊዜ በእያንዳንዱ ስብሰባ በሚነሱ ጉዳዮች ላይ በበቂ በመዘጋጀት ለውሳኔ የሚያበቃ ሰፈ ግንዛቤ በመጨበጥ መገኘት ከእያንዳንዱ አባል እንደሚጠበቅ አሳስበው፣ […] የአዲስ አበባን የመናገሻ ከተማነት ደረጃ (status) እና ወደፊት አከላለስ ሊኖራት የሚችለውን ቦታ አስመልክቶ በሚዘጋጀው የመወያያ ሰነድ (working paper) ውስጥ እንዴት ማስቀመጥ እንደሚቻል ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡››
ይህ ሐሳብ የተገለፀው የአሁኑን የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት ለማርቀቅ የተቋቋመው የሕገ መንግስት ኮሚሽን ሰብሳቢ በነበሩት አቶ ክፍሌ ወዳጆ ጳጉሜ 1- 1985 በኮሚሽኑ 39ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ እንደ ሰብሳቢው ሐሳብ ከሆነ ሕገ መንግስትን ያህል ሰነድ ለማርቀቅ የተዋቀረው ኮሚሽን አባላት በኮሚሽኑ ስብሰባ ላይ አለመገኘታቸው አሳስቧቸውና የአዲስ አበባን ደረጃ (status) ገና ሳይወስኑ እስከ አሁን መቆየታቸው አሳስቧቸው ነው፡፡ ሰብሳቢው አቶ ክፍሌ ይሄን ቢሉም ይሄን ማስጠንቀቂያ በተናገሩበት እለት እንኳን ከ27 የኮሚሽኑ አባላት መካከል ስምንት የሚሆኑት አልተገኙም ነበር፡፡ አዲስ አበባን አስመልክቶ የቀረቡት ጉዳዮች በሕገ መንግስታዊው ጉባኤ የተወሰነ ውይይት ቢደረግበትም፣ በኮሚሽን ደረጃ ብዙም ውይይት እንዳልተደረገበት በጊዜው የኮሚሽኑ አባል የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይገልፃሉ፡፡ እንግዲህ ያ በቸልተኝነት የታለፈ ጉዳይ ነው አንዱ የዛሬው ችግር መነሻ፡፡ አዲስ አበባ የክልልም፣ የፌደራል ግዛትም እንዲሁም የአንድ ክልል ከተማ መልክ ይዛ ከሶስቱ አንዱን መሆን አለመቻሏ በጊዜው ሲሟገቱ የነበሩ ሁሉንም አካላት ለማስደሰት በሚል የታለፈ ጉዳይ ይመስላል፡፡
የተለያዩ ምሁራን አዲስ አበባን አስመልክቶ የተለያዩ ጥያቄዎችን እያነሱ ሕገ መንግስቱ መመለስ አለመቻሉን ሊያሳዩን ይሞክራሉ፡፡ መሰረታዊዎቹን ጥያቄዎች እዚህ ላይ ማንሳት ተገቢ ስለሚሆን አንስተን እንመልከታቸው፡፡
1. የአሜሪካ ዋና ከተማ የሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ በተቋቋመችበት ወቅት መሬት ከሜሪላንድና ከቨርጅኒያ ስቴቶች ተቆርጦ ተሰጥቷት ነው የተቋቋመችው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ቨርጅኒያ መሬቴን መልሽልኝ በማለት መሬቷን በሕዝበ ውሳኔ መሬት የማስመለስ ሒደት (retrocession) መሰረት አስመልሳለች፡፡ ሜሪላንድም እስከ አሁን አልጠየቀችም እንጂ ብትጠይቅ ልታገኝ እንደምትችል የሕገ መንግስት ምሁራን ይገልፃሉ፡፡ አዲስ አበባ የምትገኝው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እንደሆነ ሕገ መንግስቱ በግልፅ ይደነግጋል፡፡ ታዲያ ኦሮሚያ ‹መሬቴን ራሴ አስተዳድራለሁ› ብትል በምን አግባብ ነው መልስ የሚሰጠው?
2. አሁንም እዛው ዋሽንግተን ዲሲ እንቆይና ባራክ ኦባማን ጨምሮ ብዙ የአሜሪካ ፖለቲከኞች ዋሽንግተን ዲሲ ራሷን የቻለች ሃምሳ አንደኛ የአሜሪካ ‹ስቴት› ብትሆን ፍላጎት እንዳላቸው (ከመራጭነት መብት አንፃር) ይገልፃሉ፡፡ ሐሳቡ ወደ ፊት ሊተገበር የሚችል ጉዳይ እንደሆነም ምሁራን እያስረዱ ይገኛሉ፡፡ አዲስ አበባ ራሴን ችዬ ክልል ልሁን ብትል በምን አግባብ ነው የሚስተናገደው ለሚለው ጥያቄ የራስን ክልል የመመስረት መብት የሚሰጠው የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 47 (2) መብቱን የሚሰጠው ‹ለብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች› ሲሆን አዲስ አበባ በምን ጎራ ላይ እንደምታርፍ ምንም የተገለፀ ነገር የለም፡፡
3. አዲስ አበባ አሁን ባላት ቁመና ቻርተርድ ከተማ እንደሆነች ከላይ ለማየት ሞክረናል፡፡ ቻርተርድ ከተሞችን (Chartered Cities) ከሌሎች ከተሞች (General Law Cities) የሚለያቸው ዋነኛው ጉዳይ ደግሞ የፌደራልንም ሆነ የክልል መንግስታትን ጣልቃ ገብነትን የሚያስወግድ አሰራር መተግበራቸው ነው፡፡ ታዲያ አዲስ አበባ ቻርተርድ ከተማ እንደመሆኗ ‹የፌደራል መንግስቱን ጣልቃ ገብነት አልፈልግም› ብትል ሕገ መንግስቱ ምን መልስ ይሰጣል?
እነዚህን ሕልዮታዊ ጉዳዮች ያነሳነው የአሁኑ የኢትዮጵያ ፌደሬሽን በተግባር የሌለ ብቻ ሳይሆን በአወቃቀር ደረጃም የማይመልሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መኖራቸውን ለማመላከት ነው እንጂ፤ ‹ጠያቂም መላሽም› እንደሌለ መረዳት ከባድ ሆኖ አይደለም፡፡
አዲስ አበባም ፖለቲካዊ፣ ሕጋዊ እንዲሁም መዋቅራዊ ችግሮቿ ሰንገው በያዟት በዚህ ወቅት ነው ‹የአዲስ አበባና ዙሪያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን [የተቀናጀ] የጋራ ልማት ፕላን› ተብሎ የተሰየመው የሃያ አምስት አመታት ዕቅድ ብቅ ያለው፡፡

4. ‹[የተቀናጀ] የጋራ ልማት ፕላን› እና አዲስ አበባ
ስድስተኛው የዓለም የከተሞች ፎረም በጣሊያን ኔፕልስ ከሴፕቴምበር 02 እስከ 07 – 2012 ነበር የተካሔደው፡፡ ፎረሙ በተባበሩት መንግስታት ከተቋቋመበት ከ2002 ጀምሮ ባሉት አስር ዓመታት ውስት ለስድስተኛ ጊዜ ስብሰባ ማድረጉ ነበር፡፡ ከመላው ዓለም ከመጡ የተለያዩ ሀገር ተወካዮች አማካኝነት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተወያየ ሲሆን የፎረሙ ዋነኛ አጀንዳም ‹Urban Future› የሚል ሲሆን በዋናነትም አራት መሰረታዊ ጉዳዮችን እንደመወያያ ይዞ ተካሂዷል፡፡ ከነዚህ አራት የውይይት ርዕሶች መካከል ቀዳሚው ‹Urban Planning: Institutions and Regulations› የሚል ነበር፡፡ በውይይቶቹ መጨረሻ ‹የዓለም የከተሞች ማንፌስቶን› ጨምሮ የተለያዩ የውይይቱ ውጤቶች ይፋ የተደረጉ ሲሆን፤ ከነዚህ የውይይቱ ውጤቶች መካከልም የዓለም ከተሞች የተቀናጀ የልማት ዕቅድን (Integrated Development Plan – IDP) ተግባራዊ እንዲያደርጉ የሚመክረው (recommendation) ይገኝበታል፡፡ ይህ በተባበሩት መንግስታት ደረጃ የቀረበው በ2012 ቢሆንም ከዛ በፊት በ2007 ‘Leipzig Charter on Sustainable European Cities’ የአውሮፓ ሀገሮች ይሄን የተቀናጀ አካሄድ በከተሞቻቸው ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ተስማምተው ነበር፡፡
ከዚህ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች የተቀናጀውን አካሄድ ተግባራዊ ሲያደርጉ ተስተውሏል፡፡ የደቡብ አፍሪካዋ ኬፕ ታውን (ከ2012 -2017) እና የኬኒያዋ ናይሮቢ (ከ2014 -2019) በዚህ ረገድ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ደቡብ አፍሪካ እንዲያውም በሃገሪቱ ላሉ ከተሞች አጠቃላይ የተቀናጀ የልማት ዕቅድን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መመሪያ እስከማውጣት ደርሳለች፡፡

4.1. የተቀናጀ የልማት ዕቅድ (Integrated Development Plan – IDP) ምን ለማለት ነው?
አንድ አይነት እና ወጥ የሆነ መልስ ማግኝት ባይቻልም የተለያዩ ከተሞች ከሰጡት የተለያየ ትርጉም አንፃር ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን ማግኘት እንችላለን፡፡ 1. ሁሉም መሰረተ ልማት ላይ የሚሰሩ አካላት (የትራንስፖርት፣ የመብራት፣ የቤቶች ወዘተ) ተቀናጅተው ለተመሳሳይ ግብ እንዲተጉ ማድረግና 2. እቅዱን ያወጣው አካል ከእቅዱ ባለቤት (የከተማው ነዋሪ) ጋር አሳታፊ (participatory) በሆነ መንገድ በየጊዜው በመወያየት ተቀናጅቶ የሚሰራበት አካሄድ ነው፡፡ እንደ ናይሮቢ ያሉ ከተሞች በተቀናጀ የልማት ዕቅዳቸው የመሰረተ ልማት አገልግሎት (በተለይም ትራንስፖርት) በዙሪያው ካሉ አካባቢዎች (surroundings) ጋርም ለማቀናጀት ሙከራ አድርገዋል፡፡
በዚህ ጊዜ አዲስ አበባም በ1996 አዘጋጅታው የነበረው የከተማ ልማት እቅድ (ማስተር ፕላን) የትግበራ ጊዜው እያለቀ ነበርና የራሷን አዲስ ዕቅድ ለማዘጋጀት ቢሮ ከፍታ እንቅስቃሴ የጀመረችበት ጊዜ ነበር፡፡ መጀመር ብቻም ሳይሆን ስድስተኛው የዓለም የከተሞች ፎረም በተካሔደበት በመስከረም 2005 ለእቅዱ የሚያስፈልገውን መረጃ ለቀማ እንዳጠናቀቀች ይፋ አድርጋ እቅዱንም በጥቂት ወራት ውስጥ አጠናቅቄ ይፋ አደርጋለሁ ብላ ነበር፡፡ እንደተባለው እቅዱ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደተጠናቀቀ ውስጥ ለውስጥ የተነገረ ሲሆን የመጀመሪያውንም ተቃውሞ በግንቦት 2005 ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በወጣ መግለጫ አስተናግዳ ከዛ በኋላ የሆነውና እየሆነ ያለው ጉዳይ ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡ እዚህ ላይ ትክክለኛውን አከራካሪ ጉዳይ ለመለየት እንችል ዘንድ የእቅዱን መሰረት እና ይዘት ማየት ተገቢ ጉዳይ ነው፡፡

4.2. ‹ኢንደስትሪያላይዜሽን› ዘመነኛው ካርድ
‹‹የህዝባችን ኑሮ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚደርሰው አገራችን በኢንዱስትሪ የበለፀገች አገር ስትሆን ነው፡፡ አገራችን በአለም አቀፋዊው ኢኮኖሚያዊ ትብብር ውስጥ የሚኖራት ድርሻና ከዚሁ የምታገኝው ጥቅም በከፍተኛ ደረጃ ሊያድግ የሚችለው በኢንዱስትሪ የበለፀገች ስትሆን ነው፡፡ በመሆኑም የኢኮኖሚ ልማት እንቅስቃሴያችን ግብ በኢንዱስትሪ የበለፀገች አገርን መፍጠር መሆን አለበት፡፡ ሌላው ቀርቶ የግብርናና የገጠር ልማት እንቅስቃሴያችን የመጨረሻው ግብ አገራችን በኢንዱስትሪ የበለፀገች እንድትሆን ማድረግ ነው፡፡››
ይህ ሀሳብ የተገለፀው በ1994 በወጣው የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጅ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው የግሉን ባለሃብት የኢንደስትሪያላይዜሽኑ መሰረት ማድረግና ግብርናው ኢንደስትሪውን እንዲመራው ማስቻል (Agriculture Development Led Industrialization – ADLI ) መሰረታዊ ጉዳይ እንደሆነ አስቀምጦ ያልፋል፡፡ ከዚህ ስትራተጅ የተከተሉት የእድገትና እና ትራንስፎርሜሽን እቅዶችም ዓላማቸው ግብርና የሚመራውን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ወደ ኢንደስትሪ መር ማሸጋገርን (transformation) ዓላማ አድረገው የተቀረፁ ናቸው፡፡ ቁጥሮች እንደሚነግሩን ግን ኢሕአዴግ በኢንደስትሪው መስክ አልተሳካለትም፡፡ ኢንደስትሪው ያለፉት 50 አመታትን ተመሳሳይ መንገድ ይዞ የሚያዘግም ነው፡፡ ኢንደስትሪውን ይመሩታል የተባሉት ግብርና እና የግል ባለሃብቱም ከፕሮፓጋንዳ ባለፈ ብዙም በአካባቢው አይታዩም፡፡
ኢንደስትሪው የትም እንዳልደረሰ እና ‹ትራንስፎርም› የሆነ ብዙም ነገር እንደሌለ የተረዳው ኢሕአዴግ በድንጋጤ (frustration) የደቡብ ምስራቅ እስያ ተሞክሮ የሆነውን መንግስት መር (statist) ኢንደስትሪያላይዜሽን ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት ኢንደስትሪውን ይመራዋል የተባለው ገበያና የግል ባለሃብትም ከአመራርነት ወርደው ቦታቸውን ለመንግስት አስረክበው ይገኛሉ፡፡
እንግዲህ በዚህ የኢሕአዴግ የኢንደስትሪያላይዜሽን ድንጋጤ ወቅት ነው ‹የአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ [የተቀናጀ] የልማት ፕላንም› የመጣው፡፡ የፕላኑ ዋነኛ ግብ ‹ሀገሪቱ የሰነቀችውን የኢንደስትሪ ሽግግር ዕውን መሆን ወሳኝ አስተዋፅኦ የሚያደርግ የኢንዱስትሪ ልማት ማስተናገድ [የሚችል ክልል መፍጠር]› እንደሆነ በእቅዱ መግቢያ ላይ ተገልፆል፡፡ (ክልል የተባለው ምን እንደሆነ ወደታች የምናው ጉዳይ ነው)፡፡ በእቅዱ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ‹‹ክልሉ የሀገሪቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በአጠቃላይ የዕቅዱ ዋና አካል የሆነውን የኢንደስትሪ ሽግግር በተለይም እውን በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና መጫወት ይጠበቅበታል››፣ ‹‹ከግብርና ወደ ኢንደስትሪ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ››፣ ‹‹በ2030 በምስራቅ አፍሪካ ተወዳደሪ የሆነና በኢኮኖሚ ውስጥ መሪ ሚና የሚጫወት ማዕከል መፍጠር››፣ ‹‹የከተማዋን እና የዙሪያ ኦሮሚያ አካባቢን በጋራ በአፍሪካ ቀንድ ቀዳሚ የኢንዱስትሪ ክልል ማድረግ›› ወዘተ የሚሉ የዕቅዱ ዋነኛ ትኩረት ‹ኢንደስትሪያላይዜሽን› እንደሆነ የሚያመላክቱ ጉዳዮችን እናያለን፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ኢሕአዴግ ስልጣን ከያዘ ወዲህ የአሁኑን ጨምሮ ለአዲስ አበባ ከተማ የተዘጋጁትን እቅዶች ስንመለከት ‹የዘመኑ መንፈስ› እንደሚመራቸው እናያለን፡፡ የመጀመሪያውና በ1986 የተዘጋጀው እቅድ ዋነኛ ትኩረቱ ‹ሰላማዊ ከተማ› መገንባት እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፤ በ1996 የፀደቀው የከተማዋ የልማት እቅድ ደግሞ በጊዜው የኢሕአዴግ ዋነኛ ማጠንጠኛ የነበረውን ‹ኢንቨስትመንት› መሰረት ያደረገ ሲሆን በጊዜው የከተማዋን መሪ ፕላን ለማጽደቅ በከተማዋ አዲስ ነጋሪት ጋዜጣ ላይ በወጣው አዋጅ ቁጥር 17/1996 ላይም እንደተገለፀው ‹‹[…] ኢንቨስትመንትን በተሳለጠና ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማካሔድ [ማስቻል]…›› እንደሆነ ተገልፆ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ‹የዘመኑ መንፈስ› ኢንደስትሪያላይዜሽን ነውና እቅዱ ዋነኛ ትኩረቱን ኢንደስትሪ ላይ ማድረጉ የሚጠበቅና የሚገርም ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገር ግን ከተማዋ የምስራቅ አፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን ኢንደስትሪ የምትገነባበት በቂ ቦታ የላትምና አወዛጋቢውን መስፋፋት ለማድረግ ተነሳች ማለት እንችላለን፡፡ ይሄ እንዴት ሆነ?

4.3. መሪ እቅድ (Master Plan) ወይስ አዲስ ክልል (New State)?
ሰኞ ግንቦት 18፣ 2000 በጊዜው የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የነበሩት በአቶ መኩሪያ ሀይሌ እና ከአዲስ አበባ አስራ ሰባት እህት ከተሞች አንዷ በሆነችው የፈረንሳዩ፣ የሊዮን ከተማ ምክትል ከንቲባ Monsier Hubert Julien-Laferriere መካከል አንድ የትብብር ሰነድ ተፈረመ፡፡ የትብብር ሰነዱ በሁለቱ ከተሞች መካከል የተደረገው የአምስት ቀናት ውይይት ውጤት ነበር፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሃሳብ ያቀረበው የፌደራል የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት በአዋጅ ቁጥር 450/1997 ከተሰጡት ስልጣኖች አንዱን በመጠቀም ሊዮን ከተማ አዲስ አበባን ልትረዳ የምትችልባቸው ሶስት አጀንዳዎችን አቀረበ፡፡ እነዚህም ሶስት አጀንዳዎች፡
1. የአዲስ አበባ ከተማን መሪ እቅድ (Master Plan) የመከለስ ስራ፣
2. በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ መካከል በጋራ ለመፍጠር ስለታሰበው ክልላዊ እቅድ (Regional Planning) እና፣
3. ስለ አዲስ አበባ ከተማ የውስጥ የልማት ስራ (Local Development Plan – LDP) ናቸው፡፡
በውይይቱ ማጠናቀቂያም በሶስቱ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ በመደረሱ የሁለቱ ከተሞች አቻ ባለስልጣናት የትብብር ሰነዱን ተስማምተው ፈረሙ፡፡ የመሪ እቅዱ እና የውስጥ የልማት ስራው ከዚህ በፊት የተለመዱ ጉዳዮች በመሆናቸው ብዙም ግርታን የሚፈጥሩ አልነበሩም፡፡ ነገር ግን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ መካከል ሊፈጠር የታሰበው ክልላዊ የልማት እቅድ የተለመደ ስላልነበር አፈፃፀሙን ለማየት የሚያጓጓ ነበር፡፡ የዚህ ክልላዊ እቅድ መነሻ ግን አሁንም ወደኋላ ወደ 1996 ይወስደናል፡፡ በ1996 የወጣው የአዲስ ነጋሪቱ ‹የአዲስ አበባ ከተማ መሪ ፕላን አዘገጃጀትና አወጣጥ› አዋጅ ቁጥር 17/1996 በአንቀፅ 8 (2) ላይ ‹የአዲስ አበባ መዋቅራዊ ፕላን ከመዘጋጀቱ በፊት [ከኦሮሚያ ክልል ጋር] በፈቃደኝነት በጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ የአዲስ አበባና አካባቢዎች ፕላን እንዲዘጋጅ አስተዳደሩ ሁኔታዎችን ያመቻቻል› በማለት ክልላዊ እቅድ መታቀድ ከጀመረ ቆየት ያለ ጊዜ እንዳስቆጠረ ያመላክተናል፡፡
አሁን መንግስት ያዘጋጀው የተቀናጀ የጋራ የልማት እቅድ ሰነድም (የዚህ ፅሁፍ ፀሃፊ እዚህ ላይ ያገኘው ሰነድ) እነዚህን የኋላ ታሪክ በመያዝ ክልላዊ እቅድን (Regional Planning) ከመሪ እቅድ (Master Plan) በመቀየጥ የተዘጋጀ ነው፡፡ ያለውን የፌደራል ስርዓት አይተን ትግበራው ምን ሊመስል ነው ብለን ማሰብ የሚከብደን አይነት እቅድም ነው፡፡ የእቅዱ ስያሜ እንኳን መሪ እቅድ (Master Plan) ሳይሆን ክልላዊ እቅድ (Regional Plan) ነው፡፡ ግቡም አዲስ አበባን በ 100 ኪሎ ሜትር ሬዲየስ የሚከብ ሰፊ ክልልን ማልማት ነው፡፡ 36 ከተሞችን እንደሚያካትትም ተጠቅሷል፡፡ ከአዲስ አበባ ሌላ በስም በእቅዱ ላይ ተጠቅሰው የምናገኛቸው ከተሞችም ዱከም፣ ገላን፣ ሰበታ፣ አዋሽ፣ ለገዳዲ፣ ለገጣፎ (ሁሉም በኦሮሚያ ክልል፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ከተሞችን ማለት ነው) ናቸው፡፡ በልማት እቅዱ ውስጥ የተካተተው አካባቢም 85 በመቶው ገጠር እንዲሁም 15 በመቶው ደግሞ የከተማ አካባቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ እንዲሁም በአምስቱ ኦሮሚያ ክልል፣ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን አምስት ከተሞችን ውስጥ በ25 ዓመታት ውስጥ ከ30 ሺህ እስከ 40 ሺህ ነዋሪዎችን ማስፈርን በእቅድነት ይዟል፡፡ ይሄም ዓላማ ያደረገው ‹የክልሉን ነዋሪ ከአስከፊ ድህነት ማላቀቅ› ነው የሚል ሲሆን፤ እዚህ ላይ የየትኛውን ክልል ነዋሪ ማለታችን ተገቢ ነው፡፡
እነዚህን ጉዳዮች ስንመለከትም እቅዱ በዋናነት ክልላዊ እቅድ እንጂ የከተማ መሪ እቅድ እንዳልሆነ ለመረዳት ብዙም አያዳግተንም፡፡ ሰፊ የገጠር አካባቢን (85 በመቶው የእቅዱ አካባቢ) አካልሎ ግቡን ኢንደስትሪያላይዜሽን ማድረጉንም ስናይ ‹ግዙፏ አዲስ አበባ በተግባር ደረጃ (de facto) የራሷ የሆነ ክልል (አስረኛዋ የኢትዮጵያ ክልል) ለመመስረት ጥረት እያደረገች ነው እንዴ?› ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል፡፡ ከላይ የጠቀስነው አደናጋሪው በፌደራል ስርዓቱ ውስጥ የአዲስ አበባ ‹ስታተስ› ጉዳይም እዚህ ላይ መሰረታዊው የጥያቄ ነጥብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

4.4. ኦሮሚያ፣ አዲስ አበባ እና ‹እቅዱ›
ከላይ በተራ ቁጥር 3 ላይ ሕገ መንግስቱ በተረቀቀበት ወቅት የነበረው የአዲስ አበባን ‹ስታተስ› ግልፅ ያለማድረግ ችግርና አዲስ አበባ ከምትገኝበት ኦሮሚያ ክልል ጋር የሚኖራትን ግንኙነት ግልፅ ያለማድረግ ችግር ሕልዮታዊ ጥያቄዎችን ለማንሳት ሙከራ አድርገናል፡፡ እዚህ ላይ ደግሞ በተግባር እያጋጠሙ ያሉ ቸግሮችን በማንሳት የወደፊቱን ሁኔታ ለማየት እንሞክር፡፡
አብዛኛው የአዲስ አበባ ከተማና የኦሮሚያ ክልል ውዝግቦች የሚነሱት ከድንበርና ከሉዓላዊነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡ አዲስ አበባ ያለ ቅጥ እየተስፋፋች ነው፣ የኦሮሞን ባህልና ቋንቋ እያጠፋች ነው፣ በሕገ መንግስቱ ለኦሮሚያ ክልል የተሰጣት ልዩ ጥቅም እስከ አሁን በሕግ ባለመወሰኑ ጉዳዩን አወሳስቦታል ወዘተ የሚሉ ትችቶች እየቀረቡ እስከ አሁን ቀጥሏል፡፡

4.4.1. ድንበር
የአዲስ አበባ ስፋት ባለፉት ሃምሳ አመታት ከእጥፍ በላይ አድጓል፡፡ በ1953 በሔክታር 21,800 የነበረው የአዲስ አበባ የቆዳ ስፋት በ1986 ወደ 53,014 ሔክታር ሰፍቶ፤ አሁን ያለውን የ54,000 ሔክታር ስፋት ደግሞ በ1996ቱን በከተማዋ መሪ ዕቅድ የተሰፈረላት ነው፡፡ በሀምሳ ዓመታት ውስጥ ከተማዋ በእጥፍ ያደገች ቢሆንም በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ግን አሁን ካላት ስፋት ብዙም የተለየ ነገር አላሳየችም፡፡ የከተማዋ ከኦሮሚያ ጋር ያላት የድንበር ውዝግብ ዋነኛ መነሻ የሆነው የድንበሩ አለመካለል (demarcation ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ ውዝግቦች በጊዜው እንደሚነሱ ይሰማል፡፡ ተሾመ ያሚ የተባሉ የሕግ ባለሙያም በጉዳዩ ላይ ባደረጉት ጥናት የኮልፌ-ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከቡራዩ ከተማ አስተዳደር ጋር እንዲሁም የንፋስ ስልክ-ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሰበታ ከተማ አስተዳደር ጋር በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የድንበር ይገባኛል ውዝግብ ውስጥ እንደገቡ ይገልፃሉ፡፡ እንዲሁም የገቢ ምንጭን አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል የማዕድን ኤጀንሲ ቢሮ ከአዲስ አበባ አቻው ጋር የተወዛገበባቸው አካባቢዎች እንዳሉ አያይዘው ይገልፃሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች ግን መንግስት ሕጋዊ መፍትሔ ከመስጠት እና የሕግ አፈታቱን ከማሳደግ ይልቅ ተለመደውን ፖለቲካዊ መፍትሔ እየሰጠ ችግሩ አሁንም በዘላቂነት ያልተፈታ ጉዳይ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡
አዲስ አበባ አሁን ካላት ቦታ ውጭ (54,000 ሔክታር ወይም 527 ኪሜ ስኩየር) መስፋት አትችልም ወይ? ለሚለው ጥያቄ ሕጋዊ መፍትሔ የሚሰጠን በ1996 የወጣው የአዲስ ነጋሪቱ ‹የአዲስ አበባ ከተማ መሪ ፕላን አዘገጃጀትና አወጣጥ› አዋጅ ቁጥር 17/1996 ሲሆን አዋጁም ‹‹[የአዲስ አበባ የ] መስፋፊያ አካባቢ [የሚባለው] በማስተር ኘላኑ የቦታ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ተከልሎ ባለ የአርሶ አደር ወረዳዎች ስር የሚገኝ የለማ እና ወደፊት የሚለማ መሬት የሚገኝበት አካባቢ ነው፡፡›› በማለት ከተማዋ አሁን ካላት ቦታ ውጭ እንደማትስፋፋ ይገልፃል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያለው ግንኙነት አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የመመስረቻ ቻርተር 87/1989ም ሆነ ይሄን ቻርተር ሙሉ ለሙሉ ያሻሻሉት አዋጅ ቁጥር 311/1995 እና በአዋጅ ቁጥር 361/1995 የድንበሩ ጉዳይ ‹ወደፊት በውይይት ይካለላል› ከማለት በስተቀር ያስቀመጡት ነገር የለም፡፡ በሌላ በኩል የአዲስ አበባ መለጠጥ ያሳሰበው እና ይሄም መገታት አለበት ብሎ ያሰበው የኦሮሚያ ክልል በ2000 የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በሚል አዲስ ዞን የአዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ክልልን ግንኙነት ለማሳለጥ በሚል ሰበብ አቋቁሟል፡፡ አሁን የቀረበው ‹የልማት እቅድ› ደግሞ የልዩ ዞኑን ከተሞች ሙሉ ለሙሉ በማስገባት ሌላ አዲስ መካረር ፈጥሯል፡፡

4.4.2. ቋንቋ
የአሜሪካዋ ቨርጂኒያ ስቴት ለዋና ከታማዋ ዋሽንግተን ዲሲ የሰጠሁት መሬት ይመለስልኝ በማለት መሬቷን በ1846 አስመልሳለች፡፡ በሌላ በኩል አሁን ያለችውና መሬት ከሜሪላንድ ‹ስቴት› ወስዳ የቆመችው ዋሽንግተን ዲሲ ‹ራሷን የቻለች ክልል ትሁን የሚለውም› ሃሳብ ብዙም ተቃውሞ አይቀርብበትም፡፡ ለዚህም ለስላሳ ግንኙነት ዋነኛው መሰረትም የዋሽንግተን እና የዙሪያዋ ያለው የባህልና ቋንቋ መመሳሰል ነው፡፡
በተቃራኒው አዲስ አበባ የምትናገረው ቋንቋ በዙሪያዋ ካለው ቋንቋ የተለየ ነው፡፡ አዲስ አበባ አማርኛን ታወራለች ዙሪያዋ ደግሞ ኦሮምኛን ይናገራል፡፡ የቋንቋ ምሁሩ ፕሮፌሰር ባየ ይማም ‹አዲስ አበባ ለአማርኛ፣ አማርኛ ለአዲስ አበባ› ባሉት ፅሁፋቸው የአማርኛንና የአዲስ አበባን ግንኙነት ሲያስረዱ፡
ከአዲስ አበባ ከተማ ምሥረታ በኋላ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በየምክንያቱ ወደ ከተማዋ በመግባት በጉርብትና አብረው መኖርና መሥራት ጀመሩ፡፡ ይህም ሁኔታ ሕዝቦችን ከተለያየ ቋንቋ ተናጋሪነት ወደ አንድ የጋራ ቋንቋ ተጠቃሚነት አሸጋገረ:: ልሳነ ዋህድ የነበረው ብሄረሰብ ልሳነ ክልዔ እየሆነ መጣ። አማርኛ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ከተመኛውን ሁሉ የሚያገናኝ የጋራ ቋንቋ ሆነ፡፡
አዲስ አበባና አማርኛ፣ ለርስበርሳቸው ብሎም ለመላው ኢትዮጵያ የለውጥ ተምሳሌት ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ብሄረሰብ በቤቱም ሆነ በአደባባይ የሚናገረው የራሱን ቋንቋና አማርኛን ነው ለማለት ይቻላል፡፡ የአዲስ አበባ ሕዝብ ግን ከዚህ ይለያል፡፡ በአደባባይ ሁሉም የሚናረው አማርኛን ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ መርካቶ የሚሰማው ቋንቋ ሌላ ሳይሆን አማርኛ ነው፡፡ አዲስ አበባ የሕብረ-ብሔራዊነት ተምሳሌት እንደሆነች ሁሉ፣ አማርኛም የዚሁ መግለጫ ነው፡፡ ከሁሉም ይወስዳል፣ መልሶ ለሁሉም ያሰራጫል፡፡ ሁሉንም ያገናኛል፣ ከሁሉም ቃል ይወስዳል፣ ለሁሉም ቃል ይሰጣል፡፡
በማለት ይገልፃሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት አዲስ አበባን ያለ አማርኛ ማሰብ በፍፁም የማይቻል ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በዙሪያዋ ያሉት የአዲስ አበባ ከባቢዎች ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም ‹ይህች እንደ አንድ ከተማ ብቻ ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ ስልጣኔ ምልክት እየተደረገች የምትታይ ከተማ የምትናገረው ቋንቋ በዙሪያዋ ያለውን ኦሮምኛ ቋንቋ ያጨቁነዋል› የሚለው ሃሳብ የሚሰነዝሩ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ ክልላዊ የልማት እቅድ ቀርቧል፡፡ እቅዱም ከቋንቋ ጋር በተገናኝ ያለውን ተቃውሞና ውዝግብ የበለጠ አክርሮታል፡፡

4.4.3. የገበሬ መሬት ለከተሜ?
ከአዲስ አበባ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ሌላው እየቀረበ ያለው ጉዳይ አዲስ አበባ በሰፋች ቁጥር ገበሬዎችን እያፈናቀለች ቤት አልባ ታደርጋለች የሚለው ሲሆን፡፡ የተለያዩ ጥናቶችም ይሄን ያመላክታሉ፡፡ ፈየራ አብዲ የተባሉ አጥኝ አዲስ አበባ ከምስረታዋ ጀምሮ አሁን ያለችበትን ስፋት ለሜድረስ በዓመት በአማካኝ 400 ሔክታር ያህል ስትሰፋ ነበር ይላሉ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ከተማዋ በሕግ አግባብ ልትሰፋ የምትችለው ከተማዋ በቻርተር ከተማነት በተቋቋመችበት አዋጅ ቁጥር 87/1989 ላይ የተገለፀውን ‹የአዲስ አበባ ከተማ የከተማውን ክልል እና በመስተዳደሩ ክልል ውስጥ የሚገኙትን ሃያ ሶስት የገጠር ቀበሌዎች ያጠቃልላል›› ተብሎ በተገለፀው አግባብ ወዳሉት ሃያ ሶስት የገጠር ቀበሌዎች ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው፡፡ በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 40 (4) ላይ ‹‹የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኝትና ከመሬታቸው ያለመነቀል መብታቸው የተከበረ ነው፡፡›› ተብሎ የተከበረውን የገበሬዎችን መብት ይጥሳል የሚሉ ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ ነገር ግን በዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 8 ላይ ‹‹መንግስት ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሁኖ ሲያገኝው ተመጣጣኝ የካሣ ክፍያ በቅድሚያ በመክፈል […] [መሬቱን] ሊወስደው ይችላል›› ተብሎ በመደንገጉ ይህ የገበሬዎች መብት ገደብ ያለው ነው የሚለው ሃሳብም እዚህ ላይ መሰረታዊ ነገር ነው፡፡
ነገር ግን አሁን እየቀረበ ያለው ‹የተቀናጀ የጋራ እቅድ› ዓላማው ኢንደስትሪያላይዜሽን እንደሆነ ያስቀመጠ ሲሆን 1.1 ሚሊዮን ሔክታርን ያቀፈና 17 የሚሆኑ ወረዳዎችን የያዘ እንደሆነ ተገልፆል፡፡ ይሄም እጅግ ብዙ የገጠር ቀበሌዎችን እንደሚያካትት ግልፅ ነው፡፡ ኢንደስትሪያላይዜሽንን መሰረት ያደረገ እቅድ በዚህ ያህል ቦታ ሲታቀድ ገበሬዎችን በገፍ አያፈናቅልም ብሎ ማሰብ ራስን ከማሞኘት ባለፈ ፋይዳ ያለው ነገር አይደለም፡፡ መፈናቀሉንም ‹ለሕዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሁኖ ስለተገን› ነው ብሎ ማሰብ የባሰ ሞኝነት ነው የሚሆነው፡፡
ሲጠቃለልም አዲስ አበባ በተሳሳተ የከተማ ልማት ፖሊሲ ሌሎች ከተሞች በሀገሪቱ ውስጥ የሉም እስኪባል ድረስ ያለልክ ገዝፋለች፡፡ በዚህም ምክንያት አዲስ አበባ ላይ የሚደረግ ማንኛውም እቅድ አካባቢያዊ እቅድ ከመሆን ይልቅ ሀገራዊ እቅድ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በመሃሉና በዳር ሀገሩ መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ከመስራት ይልቅ አሁንም በፖሊሲ ደረጃ የአዲስ አበባን ግዙፍነት በበለጠ የማስቀጠል አካሔድ ነው አሁን እየተካሔደ ያለው፡፡ ይህ አካሔድ ደግሞ በፌደራል ስርዓት ሊኖር የሚገባው ግልፅ የሆነ ድንበር እና ‹ስታተስ› ካለመኖሩ ጀምሮ የተነሳ ሲሆን፤ በተግባርም ችግሮችን በፖለቲካዊ ውሳኔ አድበስብሶ የማለፍ ውጤት ሲጠራቀም ቆይቶ አሁን ላይ የደረሰ ጉዳይ ነው፡፡ እንዲህ የገዘፈ እቅድን (ያውም ‹መሪ እቅድ› ይሆን ‹ክልላዊ እቅድ› በግልፅ ያልተቀመጠ እቅድ) ከአንድ ከተማ ጋር አያይዞ ማቅረብም ለጉልበተኛው የከተማ ገዥ ልሒቅ ተጨማሪ ሃይል በመስጠት ገበሬውን ከራሱ መሬት ወደ ጭሰኝነት የሚገፋ ነው የሚሆነው፡፡ ላልተሳካ ኢንደስትሪያላይዜሽን መሰረታዊ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ የፌደራል ስርኣቱን በግዴለሽነት በመግፋትና በመሰለኝ ለማሳካት መሞከር ነገም ሌላ ችግር ነው የሚመዘው፡፡ ሕሩይ ሚናስን ከሩቅ ገነት ሁና በመግነጢሳዊ ሃይሏ ስባ ቤተኛ ያደረገችው አዲስ አበባስ እስከ መቼ ነው ሀገሪቱ በፖሊሲ ክሽፈት እየወደቀች ያለችውን የተለያየ ፈተና ለማለፍ መሳሪያ የምትሆነው? የፌደራል ስርዓቱስ እስከ መቼ ነው ሕጋዊነትን ሳይተዋወቅ የሚዘልቀው?

ማኅበራዊ ሚዲያ እና ኢትዮጵያውያን – VOA Amharic

$
0
0

ኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ሚዲያን እንዴት ይጠቀሙበታል? እንዲሁም ታዋቂ ኢትዮጵውያን እና የማያውቁት የፌስቡክ ገጾቻቸው በሚል ርእስ ጽዮን ግርማ ውይይት አዘጋጅታለች፡፡ እንዳልካቸው ኀይለ ሚካኤል፣ የትነበርክ ታደለ፣በእውቀቱ ስዩም ፣ ሳያት ደምሴ፣ አምለሰት ሙጬ እና ኤልሻዳይ ነጋሽ በዚህ ዘገባ ተካተዋል፡፡

ኢትዮጵያ “መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች” –ዶ/ር መረራ ጉዲና ቃለ ምልልስ-VOA Amharic

$
0
0

ኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎችና ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ውስጥ ዛሬም ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭቶች እንደነበሩ ጉዳቶች መድረሣቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

“በመላው ኦሮሚያ መንግስት እየወሰደ ያለው ግድያና እስራት ህዝቡን ይበልጥ እንዳስቆጣውና በቀጣይ ከፍተኛ ቀውስ እንደሚፈጠር፤ ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነች” ሲሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ለቪኦኤ በሰጡት ቃለምልልስ ተናግረዋል።
ኦሮሚያ ውስጥ እየታየ ያለውን ሁኔታ ያነሣሣውና እያቀጣጠለ ያለው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የ24 አመት ግፍ ውጤት ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ወጣት በስርአቱ ተማሯል፣ድግሪ ይዞ ዲንጋይ ፈለጣ ውስጥ ነው የገባው። በዚህ ሰርዓት ላይ ተስፋ ቆርጧል። ዛሬ ሲጨንቃቸው ሞተዋል ያሏቸውን ድርጅቶች አሉ እያሉን ነው።ከወራት በፊት ግንቦት 7 እና ኦነግ ሞቷል በማለት በፓርላማው ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲናገር ነበር ዛሬ የህዝብ ብሶት ገንፍሎ ሲወጣ ከምን ጀርባ ግንቦት 7 አለ ኦነግ አለ በማለት ጭንቀታቸውን ደጋግመው ይናገራሉ ድርግ ትላንት እነሱኑ ይላቸው የነበረውን አንድ ችግር ሲነሳ “የውጪ ኃይሎች እጅ አለበት”ይላሉ ከአፄ ኃይለስላሴና ከደርግ የተማሩትን ደጋግመው ሲሉ ይሰማል።ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂቶች በልጽገው ብዙ ሰው በችግር ነው የሚኖረው ።ወጣቱ በአገሩ ተስፋ ቆርጦ በስደት ሊቢያ ላይ ታርደዋል፣ስንቱ እንደወጣ ቀርቷል በማለት ተናግረዋል። በሚፈጸመው ግድያ የተቆጡ በርካታ ወጣቶች ከሚሊሻ መሳሪያ እየቀሙ ጫካ እየገቡ ነው። በርዷል ህዝባዊ ቁጣው ማለት አይቻልም እያገረሸ ነው ያሉት ዶ/ር መራራ የርስ በርስ ግጭት እንዳይነሣ እንደሚሠጉ ገልጸው መቶ ሚሊዮን ህዝብን እያስፈራሩ እና እያሰሩ መግዛት አይቻልም ብለዋል።ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ሙሉውን ያዳምጡ።

አቶ ዮናታን ተስፋዬ ታሠረ-VOA Amharic

$
0
0

የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ በዛሬው ዕለት መታሠራቸውን የፓርቲው ሊቀመንበር ኣቶ ይልቃል ጌትነት ኣስታወቁ። ኣቶ ይልቃል ጌትነት ይህንና ወቅታቂ ጉዳዮችን በተመለከተም በነገው ዕለት መግለጫ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።ይህ ጉዳይ በተመለከተ ከቶ ይልቃል ጌትነት ጋር አጠር ያለ ቆይታ ያደረገችው ጽዮን ግርማ ነች።

“ኦሮሚያ ውስጥ እሥራትና ድብደባው እየከፋ ሄዷል”ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ-VOA Amharic

$
0
0

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የፀጥታ ኃይሎች “እያደረሱ ነው የሚሉት ድብደባና እሥራት – እየከፋ ሄዷል” ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎችና ተማሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል፡፡
በምዕራብ ወለጋ ዞን በገንጂ ወረዳ እና ከተማ ውስጥ በሚገኝ የሁለተኛ ደረጃ መሰናዶ ትመሕርት ቤት ተማሪዎች፤ ትናንትና እና ዛሬ ለሰላማዊ ሰልፍ በወጡበት ወቅት ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸመባቸው።
የቪኦኤን ዘገባ ያድምጡት።

Viewing all 212 articles
Browse latest View live