Quantcast
Channel: Kalkidan Amharic – Kal Tube
Viewing all 212 articles
Browse latest View live

አፍሪካ ፊልም አካዳሚ አዋርድ ላይ”ሦስት ማዕዘን”ፊልም በሽልማት ተንበሸበሸ (ቴዎድሮስ ጌታሁን)

$
0
0

ትላንት ማምሻውን በውቢቷ ፖርት ኤልዛቤት ከተማ በተካሄደው አስራ አንደኛው የ አፍሪካ ፊልም አካዳሚ አዋርድ ላይ፣ በ
ስምንት ዘርፎች እጩ ሆኖ የቀረበው የ ቴዎድሮስ ተሾመ “ሦስት ማዕዘን” ፊልም በ ሦስት ዘርፎች አሸናፊ በመሆን ታሪክ ሰራ።
Triangle going to America ወይም ሦስት ማዕዘን የመጀመሪያ ሽልማቱን ያገኘው ምርጥ የማጀቢያ ሙዚቃ
በሚለው ዘርፍ ሲሆን በዚህም ድምፃዊ ጌትሽ ማሞ ወደ መድረክ በመውጣት የተዘጋጀለትን ሽልማት ተቀብሏል
11209425_10153604035928468_4045435456848260961_n
በዚህ ዘርፍ የናይጄሪያዎቹ ታዋቂ ፊልሞች A place in the star, Iyore እንዲሁም የ አንጎላው Queen of angole እና
የሞሪታኒያው Timbectu እጩ ሆነው ቢቀርቡም ሦስት ማዕዘን ፊልምን ያጀበው ጌትሽ ማሞን ሚቆመው አልተገኘም ቀጥሎ በምርጥ ተዋናይ ዘርፍ በተካሄደ ውድድር አሁንም ሦስት ማዕዘን ፊልም አሸናፊ መሆን ችሏል
በዚህ ዘርፍ የደቡብ አፍሪካው I number number, የናይጄሪያው October, የ ካሜሮኑ Leperdes እና የ ኮትዲቫሩ Run ፊልሞች ላይ በመሪ ተዋናይነት የተወኑ አርቲስቶች ቀርበው በመጨረሻም ኢትዮጵያዊው አክተር ሳምሶን ታደሠ ቤቢ አሸናፊ መሆን ችሏል
ሽልማቱን ለመቀበል ወደ መድረክ የወጣው ሳምሶን ንግግሩን በአማርኛ ያደረገ ሲሆን በዚህም “…ስለሁሉም የረዳኝን
እግዚአብሔር አመሰግናለሁ እዚህ ደረጃ ደርሳለሁ ብዬ በህይወቴ አስቤ አላውቅም ነበር አሁን ደስታዬ ወደር የለውም
በመጨረሻ ዓለም ወደደም ጠላም አፍሪካ አንድ ትሆናለች” ብሏል
12019983_10153604125178468_8386492795609769509_n

የ አማርኛውን ንግግር ወደ መድረክ በመውጣት ወደ እንግሊዝኛ የተረጎመለት የፊልሙ ደራሲ’ና ፕሮዲውሰር ቴዎድሮስ ተሾመ
ነበር ቀጥሎ በ ሽማግሌዎች ወይም በ እንግዶች ምርጮ የ አፍሪካ ምርጥ ፊልም በሚል ዘርፍ Le president ካሜሩን Timbectu ሞሪታኒያ October ናይጄሪያ Run ኮትዲቮር እና I number number ደቡብ አፍሪካ በ እጩ ዘርፍ ቀርበው አሁንምኢትዮጵያዊው ሦስት ማዕዘን ፊልም አሸናፊ መሆን ችሏል ይህን ሽልማት ለመቀበል ደራሲ እና ፕሮዲውሰር ቴዎድሮስ ተሸሞ መሪ ተዋንያኖቹ ሳምሶን ታደሠ ቤቢ እና ሰለሞን ቦጋለ እንዲሁም የ ማጀቢያ ሙዚቃውን የሠራው ድምፃዊ ጌትሽ ማሞ ወደ መድረክ በመውጣት ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ የ ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠን ኢትዮጵያ ሀገሬ የሚለውን ዜማ በጋራ ከተመልካቹ ጋር በማቅረብ ታዳሚውን ማዝናናት ችለዋል።


ደመራው ሲደመር

$
0
0

ኃይለ ገብርኤል ብሩክ መስከረም ከባተ በኋላ ከሚመጣው የመስቀል ደመራ ጋር ልዩ ትዝታ አለው፡፡ ‹‹ኢዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ፤ መስከረም ሲጠባ ወደ አዲስ አበባ›› እየተባለ የሚዘመርበት ጊዜን፣ በተለይ መስከረም 16 ቀን

በቀዳማዊው ኃይለ ሥላሴ ዘመን በመስቀል አደባባይ ሲከበር የነበረውን ልዩ ልዩ ሥነ ሥርዓቶች ያስታውሳል፡፡ አከባበሩ እንደዘመነ ደርግ በ‹‹አብዮት አደባባይ›› ወይም በዚህኛው ዘመን በመስቀል አደባባይ ብቻ የተወሰነና የታጠረ አልነበረም፡፡
a86f81678f657ec34261292f611d3c0b_L

በወቅቱ ደመራው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ከተባረከና ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከለኮሱት በኋላ ከመንፈሳዊው ሥነ ሥርዓት ጎን ለጎን በሥነ በዓሉ ላይ የተገኙት ከከተማዋ የተለያየ ኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ የሰልፍ ትርዒት የሚያሳዩበት ነበር፡፡ የክብር ዘበኛ፣ የጦርና የፖሊስ ሠራዊት በችቦ የታጀበ የሰልፍ ትርዒት ሲያሳዩ፣ መኩሪያ የተሰኘው የንጉሠ ነገሥቱ አንበሳ የተቀመጠበት ሰረገላ ደግሞ በፊት መሪነት በንጉሠ ነገሥቱ ፊት እያለፈ ይጓዝ ነበር፡፡ በዳግማዊ ምኒልክ ጎዳና እስከ ስድስት ኪሎ ድረስ ግራና ቀኝና በየጥጋ ጥጉ ቆሞ የሚመለከተውን የበዓሉ ተሳታፊንም ሰላምታ እየሰጡ ያልፋሉ፡፡

በተለይ ከ50 ዓመት በፊት ከየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ የተውጣጡ ከተሜዎች የሚንቦለቦል ችቦ ይዘው ይሰለፉ የነበሩት ሁሉም እጀ ጠባብ የባህል ልብስ ለብሰው ነበር፡፡ ታዳጊ ወጣቶችም ነጭ ሸሚዝና ነጭ ቁምጣ ሱሪ አድርገው በምድር ጦር ማርሽ ታጅበው ስለመስቀሉ ክብር እየዘመሩ ከጦር ኃይሎች ወደ መስቀል አደባባይ ያመሩ እንደነበር ኃይለ ገብርኤል ያስታውሳል፡፡

በአራተኛው ምእት ዓመት፣ በንግሥት እሌኒ አማካይነት ክርስቶስ ኢየሱስ የተሰቀለበት መስቀል መገኘቱ የሚታሰብበት የመስቀል ደመራ በዓል፣ በኢትዮጵያ ለሁለት ሺሕ ግድም ዓመታት ሲከበር ኖሯል፡፡ የበዓሉን ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ትውፊታዊ ገጽታ የተመለከተው ዓለም አቀፉ የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ አድርጎ ከመዘገበው ሁለት ዓመት ሆኖታል፡፡

ክብረ በዓሉ በአማራና በትግራይ ‹‹መስቀል›› ሲባል፣ በተለያዩ ብሔረሰቦች እንደየአካባቢው ቋንቋ የተለያየ መጠርያ አለው፡፡ ለምሳሌ በኦሮሞ ‹‹ጉባ›› ወይም ‹‹መስቀላ››፣ በሀድያ፣ በወላይታ፣ በዳውሮ፣ በጋሞ፣ በጎፋ ‹‹መስቀላ››፣ በከምባታ ‹‹መሳላ››፣ በየም ‹‹ሔቦ››፣ በጉራጌ ‹‹መስቀር››፣ በካፊቾና ሻኪቾ ‹‹መሽቀሮ›› ይባላል፡፡

ምንነቱ

የመስቀል ክብረ በዓል በአብዛኞቹ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበር ብሔራዊ በዓል ነው፡፡ የመስቀል በዓል አጀማመር የክርስትና እምነት መሠረት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል፣ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከተቀበረበት ተቆፍሮ መገኘትና በተለይም የመስቀሉ አንድ ክንፍ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በግሸን ዐምባ መቀመጥ ጋር ቀጥተኛ የሆነ ቁርኝት ቢኖረውም፣ እያንዳንዱ ብሔረሰብ በዓሉን የሚያከብርበት እንደባህሉ፣ አኗኗሩ፣ ወጉ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ገጽታው የራሱ መንገድ አለው፡፡

የመስቀል በዓል መለያው ደመራው ነው፡፡ ደመራ ንግሥት እሌኒ፣ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት በኢየሩሳሌም ቀራንዮ በሚባል አካባቢ በጎልጎታ ቁፋሮ ያስጀመረችበትን ቀን ለማሰብ የሚከበር ሥነ ሥርዓት ነው፡፡ የደመራ ሥነ ሥርዓቱ በመጠኑም ቢሆን ከቦታ ቦታ ይለያያል፡፡ በአክሱም፣ በዓዲግራት፣ በላስታ፣ ላሊበላ፣ በዋግ ሕምራ፣ በከፊል ጎጃምና በአዊ ዞን ደመራው መስከረም 16 ቀን ቢደመርም ሥርዓተ ጸሎቱ የሚካሄደውና ደመራው የሚለኮሰው መስከረም 17 ቀን ንጋት ላይ ነው፡፡ በአንፃሩ አዲስ አበባን ጨምሮ በሸዋና በከፊል ጎጃም፣ በሐዲያ፣ በጉራጌ፣ በሸከቾ፣ ካፊቾ፣ ኮንታ ደመራው የሚበራው በዋዜማው መስከረም 16 ቀን ምሽት ነው፡፡ የደመራው አደማመርና አበራር ሥነ ሥርዓት ግን በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ነው፡፡

የመስቀል ደመራ በዓል በብሔራዊ ደረጃ የሚከበረው በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ሲሆን፣ እዚህ ደመራ የሚደመረውና ሥርዓተ ጸሎት ተደርጎ የሚቀጣጠለው መስከረም 16 ቀን ወደ ማታ ነው፡፡ በዚሁ በዓል ላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአገር ውስጥና የውጭ ታዳሚዎች ይገኙበታል፡፡ ዘንድሮ በተለይ የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ፖፕ ቴዎድሮስ ዳግማዊ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ባደረጉላቸው ግብዣ መሠረት በክብረ በዓሉ ይገኛሉ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ባንድ የሰልፍ ትርዒትና በዘመናዊ መሣሪያ በመታገዝ ልዩ ልዩ ጣዕመ ዝማሬን ያሰማል፡፡ ሠረገላ ይነዳል (ይጐተታል)፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ወርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በዓሉን በተመለከተ ትምህርትና ቡራኬ ከሰጡ በኋላ ደመራውን ባርከው ችቦ በእሳት በማያያዝ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ከሚገኙ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ጋር በመሆን ደመራውን ይለኩሳሉ፡፡

ደመራው ወደ አመድነት እስኪለወጥ ይነዳል፡፡ በዚሁ ወቅት ሕዝቡ ‹‹ኢዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ›› በማለት ይዘፍናል፡፡ ሴቶች እልል ይላሉ፡፡ ደመራው የተጸለየበትና የተባረከ ስለሆነ ሕዝቡ አመዱንና ትርኳሹን እየተሻማ ወደቤቱ ይዞ ይሄዳል፡፡ አንዳንዶቹ በአመዱ ግንባራቸው ላይ የመስቀል ምልክት ያበጃሉ፡፡ አመዱ ለሰውም ሆነ ለከብቶች ፍቱን መድኃኒት ነው የሚል እምነት አለ፡፡ በደመራው ማግስት መስከረም 17 ቀን በሚከበረው ዋናው የመስቀል በዓል ምዕመኑ ቤተ ክርስቲያን አስቀድሶ ከተመለሰ በኋላ ሲበላና ሲጠጣ፣ ከጎረቤትና ዘመድ አዝማድ ሲገባበዝና ሲጠያየቅ በፍቅርና በደስታ በዓሉን ሲያከብር ይውላል፡፡

የምርቃት ሒደት

ክብረ በዓሉን ከሚገልጹት ባህላዊ መገለጫዎች አንዱ ምርቃት ነው፡፡ ለዓይነት የስድስቱን ብሔረሰቦች አመራረቅ ከተለያዩ ምንጮች ያገኘነውን እነሆ፡፡

በሀዲያ

ደመራ የሚቀጣጠለው መስከረም 16 ሲሆን፣ መጀመሪያ በዕድሜ ትልቅ የሆኑ በየመንደሩ ያሉ አዛውንቶች ‹‹እንኳን በሰላም አደረሰን እንኳን በሰላም ብርሃን አየን ከጨለማም ወጣን›› እያሉ በመመረቅ ችቦ ይለኩሳሉ፡፡ ከዚያም ወጣቶች እየተጫወቱ ደመራውን ይዞራሉ፡፡ ሲነጋጋ ከብቶች ደመራውን ይዞራሉ፡፡

በወላይታ

ጨዋታው ሲያበቃ ለመስቀል የታረደውን በሬ እየተመገቡ ይመራረቃሉ፡፡ ‹‹እስከ መጨረሻው እንኖራለን የዳሞታ ተራራ እንደኖረ፣ የኮይሻ ተራራ እንደኖረ እኛም እንኖራለን፡፡ አህያ ቀንድ እስኪያወጣ እንኖራለን፡፡ ኮንድቾ በጣም አጭር እንጨት ምሰሶ እስከሚሆን እንኖራለን፤›› እያሉ መጪውን ዘመን በተስፋ በመቀበል ይለያያሉ፡፡

በሸከቾ

በበዓሉ ቀን ጧፍ በማብራት በየጓዳው በየእህል ማስቀመጫው ይዞ በመግባት ‹‹መጥፎ ነገር ከቤት ውጣ፣ ሀብት ግባ›› እያሉ ከመረቁ በኋላ ጎረቤት ተጠራርቶና ተሰባስቦ ችቦ ይበራል፡፡ በነጋታው የእርድ ሥርዓት የሚከናወን ሲሆን ቤተሰብና ጎረቤት በመስቀል ይጠራራል ይገባበዛል፡፡

በየም

በዋዜማው ሌሊት ሊነጋ አቅራቢያ ‹‹የረሀብ ምንቸት ውጣ ጥጋብ ግባ›› በማለት ችቦ ከተለኮሰ በኋላ ወደ ደመራው ቦታ ሁሉም ያመራል፡፡ ደመራው በአዛውንቶች ተመርቆ ይለኮሳል፡፡

በካፍቾ

የደመራ በዓሉም የሚከበረው በባህላዊ እምነት መሪው ግቢ ውስጥ ሲሆን እያንዳንዱ ሰው ችቦ በየቤቱ ለኩሶ በራሱ ቤት ዙሪያ በመዞር ድህነት ውጣ፣ ሀብት ግባ ብሎ መልካም ምኞቱን ከገለጸ በኋላ የተቀጣጠለውን ችቦ የባህላዊ እምነት መሪው ግቢ በተዘጋጀው ደመራ ላይ ወስዶ ይለኩሳል፡፡ በማግስቱ ሠንጋ ይታረድና የደመራው እሳት በነደደበት ቦታ ላይ እሳቱን ለማቀዝቀዝ ሲባል ደም ይፈስበታል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ደሙን በእጁ በመንካትና ከአመድ ጋር በመለወስ ግንባሩ ላይ ይቀባል፡፡

በጎፋ

ማስቃላ ዮ! ዮ! እያሉ የተለያዩ የበረከት ሀሳቦችን ይለዋወጣሉ (መስቀል እንኳን መጣህልን) ማለት ነው፡፡ አስከትለውም እየደጋገሙ ማስቃላ ዮ! ዮ! ዳናው ዳና አልባ ዙማዳን ዳና (አልባ ዙማ በአካባቢው የሚገኘው ትልቅ ተራራ ሲሆን እንደሱ እንኖራለን እንደ ማለት ነው፡፡) ክንቲ ሻላዳን ዳና (ክንቲ ሻላ ማለት በአካባቢው የሚገኘው ትልቁ አለት ሲሆን እንደሱ እንኖራለን እንደ ማለት ነው፡፡) መሪናው ዳና (ለዘለዓለም እንኖራለን) ማለት ነው፡፡ ሀረይ ካጨ ከሳናዳን (አህያ ቀንድ እስከሚያበቅል ድረስ እንኖራለን፡፡) ገላኦ ገል ውራናስ ዳና (ሁሉም ልጃገረዶች እስኪያገቡ ድረስ እንኖራለን)፡፡ እንዲህ እያሉ እርስ በርስ ይሸካከማሉ ይተቃቀፋሉም፡፡

የመስቀል በዓል በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች፣ በገጠርም በከተማም፣ በደብርም በገዳምም እንደ ኅብረተሰቡ ባህልና ልማድ በታላቅ አክብሮት በየዓመቱ ይከበራል፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ብሔረሰቦች እንደ ካፊቾ፣ ወላይታ፣ ሸክቾ፣ ኮንታ ያሉት እንደዘመን መለወጫ ይቆጥሩታል፡፡ በተለይ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በሸከቾ በመሽቀሬ ባሮ በዓል ላይ ደመራ ነዶ ሲያበቃ አስራ ሁለት ጉማጅ እንጨቶችን ከውስጡ በመልቀም ስልቻ ውስጥ ያስቀምጡና አንድ ወር ባለፈ ቁጥር አንድ ጉማጅ እየተጣለ ከአሥራ ሁለት ላይ ሁለት ጉማጆች ብቻ ሲቀሩ የዘመን መለወጫ በዓል እየደረሰ መሆኑንና ድግሱ ከወዲሁ መጀመር እንዳለበት ኅብረተሰቡን ያሳስቡታል፡፡

የኢትዮጵያውያን የመስቀል በዓል አከባበር ከተቀረው የዓለም ክፍል የተለየ፣ ወቅቱም ክረምቱ አልፎ የበጋ በመሆኑ በዓሉ ካለው ሃይማኖታዊ ፋይዳ ባሻገር በርካታ ማኅበራዊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ይጠቀሳል፡፡

መስቀል በዓልን ባለም ቅርስነት ባስመዘገበው የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን መረጃ መሠረት፣ ዓመቱን በሙሉ ተለያይተው የኖሩ የቤተሰብ አባላትና ዘመዳሞች የሚገናኙበትና የሚጠያየቁበት፣ ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን የሚፈቱበትና የሚረዳዱበት፣ ወጣቶች የሚተጫጩበትና ራሳቸውን ለጋብቻ የሚያዘጋጁበት፣ በጋብቻ የተሳሰሩ ቤተሰቦች የሚጠያየቁበት፣ የተጣሉ ግለሰቦች፣ ቡድኖች እና በጥል የተለያዩ ባልና ሚስቶች ባጠቃላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በመፍታት እርቅ የሚወርድበትና ሰላም የሚሰፍንበት ነው፡፡

መስቀል፣ በማኅበረሰቡ አባላት መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር የጎላ ድርሻ የሚያበረክት፣ እንደ ቤተሰብና አካባቢው በአዲሱ ዓመት የሚሠሩ ሥራዎች ተለይተው እንዴት መሠራት እንዳለባቸው የሚመከርበትና የሚታቀድበት፣ በአንዳንድ አካባቢዎች እዳ የሚሰረዝበትም ነው፡፡

ወጣቶች በአባቶች የሚመረቁበት፣ ጎልማሶች ዕውቀትን ከአባቶች የሚቀስሙበት፣ ኃላፊነት የሚረከቡበት፣ ለኢትዮጵያ ሠላምና ብልጽግናን በመመኘት ጸሎት የሚደረግበት፣ ሕዝቡ የሚዘፍንበት፣ የሚጨፍርበት፣ የሚደሰትበት፣ ግጥም የሚገጥምበት ድምፁን የሚያሟሽበት፣ ወጣቱ የሚኮራበት፣ ባህሉን የሚያጠናበት፣ የሚለወጥበት ወቅትና በአጠቃላይም ቤተ ክርስቲያን ለበዓሉ ከምትሰጠው ሃይማኖታዊ ትርጉምና ሥርዓት በመነሣት በበርካታ ብሔረሰቦች ዘንድ ጥልቅ የሆነ የመተሳሰብ፣ የፍቅር፣ የወዳጅነት መንፈስ የሚጎለብትበት ወቅት መሆኑ ከፋይዳው ይጠቀሳሉ፡፡

በዓሉን በተመለከተ በኢንቬንተሪም ሆነ በጥናትና ምርምር የተገኙ ዕውቀቶችንና ልምዶችን በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ማካተት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና አዋቂዎች ስለመስቀል በዓል ቅርስ ምንነትና ጠቀሜታ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለወጣቶች ማስተዋወቅ እንዲችሉ ማመቻቸት ለቅርሱ ቀጣይነት እየተደረጉ ያሉ እንክብካቤዎች መሆናቸውን ባለሥልጣኑ አመልክቷል፡፡
ምንጭ ሪፖርተር ተጻፈ በ ሔኖክ ያሬድ

.ስለ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ያገባናል !‪#‎YemenFreeGirumTekelaimanot‬

$
0
0

* ትናንት እኔም በወህኒ ነበርኩ ፣ ከእውነት ጋር ነበርኩና ዛሬ ነጻ ነኝ
* የከበደው ወህኒ ስቃይ ጽዋ የዛሬው ተረኛ አንተ ትሆን ዘንድ ግድ ሆኗል
ብርቱ ወዳጀ ጋዜጠኛ ግሩም ዛሬ ነጻ አይደለም ። የሁቱ አማጽያን በሚያስተዳድሯት የመን ዋና ከተማ በሰንዓ ለእስር ተዳርጓል። በማይመች ፣ በማይደላው ፣ ህይዎት በሰቀቀን በሚገፋበት የየመን ስደት ለወገኖቹ ብቸኛ ተጠሪ አምባሳደር የነበረው ጋዜጠኛ ግሩም ከሳምንት አሰሳ በኋላ ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል። የመታሰሩ ተጨባጭና ብርቱ መረጃ እንደደረሰኝ የመያዝ መታሰሩን ዜና ከቤተሰቡና ከባለቤቱ ከገጣሚ ጸሀይ በየነ ለማረጋገጥ ችያለሁ!

10153762_10203553130969803_8777235016974074501_n
በሽዎች የሚቆጠሩ የእኔ ቢጤ ተስፈኛ ወገኖቻችን ሰርተው ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ለመደገፍ ” ወደ ተስፋዋ ምድር” ወደ ሳውዲ ይሰደዳሉ። ስደቱ እስካሁን ድረስ አላቆመም ። ታዲያ መከራ ሰቆቃን ችለው በሚያደርጉት ግሩሜ ” የሞት ጉዞ !” በሚለው ስደት ከቀይ ባህርን ማዕበል ፣ ከየመን በርሃ ሀሩርና ከደላሎች የሚደርሰውን አበሳ ችለው የመን ይደርሳሉ! በማይመቸው የየመን ሲኦል ምድር የተረፉት አባት ደግሞ ጋዜጠኛ ግሩም ነበር ። ግሩም የተቸሩትን ፣ የተከፉትን እማኝ አድርጎ ዘር ሀይማኖት ሳይለይ ድምጻቸውን የሚያሰማ የሚያስተጋብ ብቸኛ የግፉአን ድምጽ ሆኖ አመታትን ገፍቷል ። ጋዜጠኛ ግሩም እንደ ስደተኛ ጋዜጠኛ ድምጻቸውን ከማሰማት ባሻገር የተቸገሩትን በመርዳት ፣ የተራቡትን በማብላት ፣ የታተዙትን በማልበስ ፣ የታመሙትን በማሳከም ፣ ወህኒ የወረዱትን በመጠየቅ ታላቅ ሰብአዊ ተግባር በመከዎኑ የማከብረው ጉምቱ ሰብአዊ ወንድምም ነው !
ብርቱው ሰው ግሩሜን ማን አሳሰረው ? ብየ ጠየቅኩ … መልስም አገኘሁ ፣ ያገኘሁት መልስ ያማል ! ተቸግሮ የደገፈው ፣ ታርዞ ያለበሰው ፣ በቤቱ አሳርፎ የጭንቅ ቀንበሩን ከላዩ ላይ ያወረደለት አንድ የሃገሩ ልጅ ስደተኛ ነው አሉ ፣ የእሱ አልደነቀኝም ፣ የከሳሽ ምስክሮች በየመን ጦርነት አካላቸው የጎደለ ወንድሞች አሉበት ሲባል መስማት ግን ልብን ይሰብራል! ያማል … ያማል… ያማል !
ትናንት ከቀትር በኋላ መታሰሩን እንደሰማሁ ፣ ከዚያም አመሻሹ ላይ ማምሻውን ውድ ባለቤቷን ጋዜጠኛ ግሩምን ካለበት እስር ቤት የጠየቀችው ገጣሚ ጸሃይ በስልክ አግኝቻት ስለታሰረበት ጉዳይ ከፖሊስ የተሰጣትን መልስና ስለ ከሳሽ ምስክሮች ዘርዘር አድርጋ አጫውታኛለች ! ግሩሜን ማሰር ይቻላል ፣ እውነቱን ከውስጡ እምነቱን ከውስጡ መቅፈፍ ግን የሚቻለው የለም !
ትናንት እኔም በወህኒ ነበርኩ ፣ ከእውነት ጋር ነበርኩና ዛሬ ነጻ ነኝ … ግን ምን እየተዶለተልኝ እንደሆነ የሚጠብቅ ፈጣሪ ስለ እውነት ይተብቀኛል እንጅ በሰው ልጅ አስተማማኝ ጥበቃ ላይ አይደለሁም ፣ ጠባቂው የእውነት አምላክ ነው ! … ከስደት መከራው አልፎ የከበደው ወህኒ ስቃይ ጽዋ የዛሬው ተረኛ አንተ ትሆን ዘንድ ግድ ሆኗል ፣ ይብላኝ ለከሳሽ መስካሪዎች እንጅ አንተም እኔም መታሰርክን እናቀው ነበር ፣ አይዞህ ግሩሜ የጨለመው ወህኒ የከበደው ቀንና መአልት ያልፋል ፣ ነገም ሌላ ቀን ነውና ይነጋል !
ወዳጆቸ ፣ አቅም በፈቀደ መጠን ከባለቤቱ ጋር ያፈረግኩትን ቃለ ምልልስ በቅርቡ አጋራችኋለሁ !
ስለ ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ያገባኛል ፣ ያገባናል!
‪#‎YemenFreeGirumTekelaimanot‬
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 19 ቀን 2008 ዓም

የተቦርነ በየነ በቴዲ አፍሮ ላይ ያለው ጥላቻ መነሻ እና ከአፈርኩ አይመልሰኝ (ቤተልሄም ክፍሌ ከቨርጂኒያ)

$
0
0

ተቦርነ በየነ በወያኔ ራድዮ ላይ ሲያገለግል የቆየና በአሁኑ ወቅት ደግሞ በኢሳት ራድዮ ላይ የሚሰራ ጋዜጠኛ ነው:: ይህ ሰው ስለሙዚቃ ያለው እውቀት የሚያስወድሰውን ያህል በቴዲ አፍሮ ላይ ያለው ጥላቻ ግን እጅጉን የሚስተዛዝብ ነው::

images

ቴዲ አፍሮ እምነቱን በሙዚቃዎቹ የሚያስተላልፍ ጀግና በመሆኑና ተቦርነ እንደሚያደንቃቸው ዘፋኞች ስለጥርስና ስለአይን የማይዘፍን አርቲስት ባለመሆኑ በኢትዮጵያ ውስጥ የተከበረ ሆኖ እንዲቆይ አድርጎታል:: ቴዲ አሁን ባለው ስርዓት በየጊዜው የሚደርስበት ጫና እና ስም ማጥፋት ሳይበግረው ዛሬ ድረስ በጥንካሬ አለ::

ከ9 ዓመት በፊት በስልጣን ላይ ያለው መግስት በቴዲ አፍሮ ላይ በየራዲዮው የስም ማጥፋት ሲጀምርሰው ተቦርነ አንዱ አራጋቢ ነበር:: ቴዲ አፍሮ “እንደ ቢራቢሮ’ የሚለውን ዘፈን ከሰው ወስዶ እንደሰራ በማስመሰልና የፈጠራ እንዳልሆነ በማድረግ እያቀረበ በሕዝብ ዘንድ ያለውን ከበሬታ እንዲቀንስ ከወያኔ ጋር ተባብሮ ቢሰራም አልተሳካለትም::

ዛሬ ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ “እንደ ቢራቢሮ” የሚለውን ዘፈን በሸክላ ሰርቼው ነበር ሲል ሃብቴ አወሎም የተባለ ዘፋኝ በባላገሩ አይዶል የመዝጊያ ዝግጅት ላይ መናገሩን ተከትሎና ተቦርነ በየነም በፌስቡክ ገጹ ላይ የአወሎምን ንግግር ይዞ ፈንጠዝያውን ሲለቅ ታዝቤ ነው::

እንደቢራቢሮ የሚለውን የሃብቴ አወሎምን ዘፈን ደጋግሜ ሰማሁት:: የቴዲ አፍሮን በደንብ ሰማሁት:: “እንደቢራቢሮ ሁሉን አትቅሰሚ እኔ እበቃሻለሁ ተይ ፍቅሬ ስሚ” ከምትለው አዝማች በቀር የሁለቱም ዘፈኖች አይገናኙም:: በሃገራችን አማርኛ ላይ እንደቢራቢሮ እንዲህ አትሁኚ የሚለው አባባል የተለመደና በዘወትር አነጋገራችን ላይ የምንጠቀምበት አረፍተ ነገር በመሆኑ ይህ አዝማች የሃብቴ አወሎም ነው ብሎ መደምደም አይቻልም::

ቴዲ አፍሮም በቢሆን በመጀመሪያ አልበሙ ላይ የሰው ዘፈኖችን በሲዲው ላይ ማካከቱን አስመልክቱ በወቅቱ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ባሰጠው ቃለ ምልልስ ቃል በቃል ባይሆንም እንዲህ ብሎ ነበር:: “የመጀመሪያ አልበሜ እንደመሆኑ አሳታሚዎች ሲዲው ይሸጣል ብለው እምነት አይኖራቸውም… ስለዚህ አንድ ሁለት የሰው ዘፈኖችን እንድታካትት ያስገድዱሃል:: የራሴ ብዙ ሥራዎች ቢኖሩኝም የሰዎችን ዘፈኖች ያካተትኩት በአሳታሚዎች ግፊት ነው”

በወያኔ ራድዮ ላይ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር በመሆን የቴዲ አፍሮን ስም ሲያጠፋ የከረመው ተቦርነ ለሰይፉ ፋንታሁን ሰርግ ቭዲዮ ቀርጾ መልዕክት ለማስተላለፍ ጊዜውን ሲያጠፋ በቴዲ አፍሮ ላይ መንግስት ባደረገው ጫና የአዲስ ዓመትም ሆነ የመስቀል ኮንሰርት ሲሰረዝ ድምጹን ሲያሰማ አላየነውም:: የዘፋኞች ጉዳይ ሲነሳ እኔ አውቃለሁ ብሎ በቅድሚያ ፊት የሚቆመው ተቦርነ አንዳችም ቀን በቴዲ አፍሮ ላይ ይህ መንግስት የሚሰራበትን ግፍ “ግፉ ይብቃ” ብሎ ሲናገር አላየንም – አልሰማንም:: ያስተዛዝባል:: አሁን የሃብቴን ንግግር ተከትሎ ከ9 ዓመት በፊት እኔም ይህን ስል ነበር እያለ ራሱን እንደ እውነተኛ አድርጎ ለመቁጠርና ዛሬም ድረስ በቴዲ አፍሮ ላይ ያለውን ጥላቻ “ትክክል ነበርኩ” በሚል ለማሳረግ መሞከሩ እርግጥም ጥላቻው አብሮ ያደረ እንደሆነ ያሳብቅበታል:: ካፈርኩ አይመልሰኝም ነው::

ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የተወደደና የተከበረ ነው:: በተቦርነ እና በቤተሰቡ ተወደደ አልተወደደ የሚመጣበት ነገር የለም:: (ከ2 ዓመት በፊት “ቴዲም በዚህ ቁመቱ ‘ሰው በልኬ’ እያለ ዘፈነ” ሲል መድረክ ላይ ማን እንደተዋረደ ሁላችሁም ታስታውሳላችሁ)
ይልቁንም ከአዲስ አበባው የወያኔ ራድዮ ተንደርድሮ የምንወደው ኢሳት ጓዳ የተቀላቀለው ተቦርነ በቴዲ ላይ እጅህን አንሳ:: በሃገሩ ላይ በነፃነት እንዳይሰራ እየተዋከበ ያለው ቴዲ አፍሮን በቤተሰባዊ ጥላቻ ከማጥቃት ይልቅ ከጎኑ ቆመን ወከባውን የምንጋራበት ወቅት ላይ ነን:: ወያኔ የሚያሰቃየው ይበቃዋል እላለሁ::

በቀጣይ እስከምንገናኝ ቸር እንሰንብት – አለ ጋዜጠኛ::

በሽብርተኝነት የተከሰሱት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለጥቅምት 3 ተቀጠረባቸው

$
0
0

11053372_826118777474147_1371325407605832008_n

• አቶ ዳንኤል ሽበሽ ጨለማ ቤት ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል
ሀምሌ 14/2007 ዓ.ም የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲለቀቁ ወስኖላቸው የነበሩት አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሽበሽና አቶ አብርሃም ሰለሞን ላይ ተጠይቆባቸው የነበረው ይግባኝ ተቀባይነት በማግኘቱ ለጥቅምት 3/2008 ዓ.ም ለቃል ክርክር ተቀጥረዋል፡፡
አምስቱ ተከሳሾች የተጠየቀባቸው ይግባኝ ተቀባይነት ይኖረዋል አይኖረውም የሚለውን ጉዳይ ለመወሰን ዛሬ መስከረም 21/2008 ዓ.ም በጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቀጥረው የነበር ሲሆን አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ አብርሃም ሰለሞን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሲቀርቡ አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታና አቶ ዳንኤል ሽበሽ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡
አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታና አቶ ዳንኤል ሽበሽ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሳይቀርቡ በውስጥ ይግባኙ ተቀባይነት አግኝቶ ቀጠሮ እንደተሰጠባቸው ከመዝገብ ቤት የታወቀ ሲሆን ሶስቱ መቀጠራቸው ከታወቀ በኋላ ዘግይተው ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደረሱት አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ አብርሃም ሰለሞን በቢሮ ተመሳሳይ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ እነ ሀብታሙ በቀረቡበት ወቅት አቃቤ ህግ ያልተገኘ ሲሆን ስለ ቀጠሮው ምንም አይነት ምክንያት እንዳልተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል ከተከሳሾቹ መካከል በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኘው አቶ ዳንኤል ሽበሽ በጨለማ ቤት ታስሮ እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ኢትዮጵያዊቷ ብርቅዪ አትሌት እና አሳዛኙ የአሜሪካ ገጠመኟ-(ታምሩ ገዳ)

$
0
0

“ወደ ኢትዮጵያ ከምመለስ እራሴን እዚሁ ባጠፋ እመርጣለሁ”ሌላኛው አትሌት

Ethiopian runner Genet Lire cries while looking through her photo album, having fled her home and family for a new life in the US. Photograph: Toni L Sandys/The Washington Post

Ethiopian runner Genet Lire cries while looking through her photo album, having fled her home and family for a new life in the US. Photograph: Toni L Sandys/The Washington Post


የ18 አመቷ ገነት ሊሪ በ400 ሜትር ወድድር ብሄራዊ ሪኮርድ በመሰበር አገሪቱ ካፈራቻቸው እና ሰሟን ከሚያሰጠሯት ጥቂት ብርቅዮ አትሌቶች መካከል አንዷ ስትሆን በመጭው 2016 እኤአ ኢትዮጵያን በመወከል ወደ ብራዚል ትጓዛለች ተብላ ከፍተኛ ተሰፋ የተጣለባት አትሌት ነበረች።ይሁን እና ከወራት በፊት ወደ አሜሪካ ለውድድር ተጉዛ “በ አገሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖሊቲካ አባል ካልሆንሺ በሚል ምክንያት የተለያዩ በድሎች ደረሰወብኛል” በማለት አዚያው አሜሪካ የቀረችው ብርቅየዋ አትሌት ገነት ኑሮ በአሜሪካ አልጋ በአልጋ አልሆንልሽ ብሏታል።

እንደ ሰሞነኛው ታዋቂው የዋሽንገተን ፖስት እና የአንግሊዙ ጋርዲያን ጋዜጣ ተመሳሳይ ዘገባዎች ከሆነ ከሰድሰት ወራት በፊት አሜሪካ ወስጥ የጥግኝነት ማመልከቻ አቅርባ አስካሁን ድረስ ምላሽ ያላገኘችው አትሌት ገነት የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ኑሮ በአሜሪካ እጅግ ፈተናዎች የተሞሎባት ነበር ። በወር 400 ዶላር የተከራየችውን ቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻሏ ለተወሰኑ ቀናት ከ ደጃፍ አሰከ ማደር ደረሳለች።በአሁኑም ወቅት ቢሆን የምትጠጋው (የሚረዳት ባለመኖሩ) ጉዳይዋን ከያዘላት ግለሰብ አንሰተኛ ክፍል ወስጥ ከሶፋ ላይ በመተኛት ለመዳበል ተገደዳለች ። ምንም እንኳን አርሱዋን የመሰሉ ወደ 30 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊይን አትሌቶች ዋሽንግተን ዲሰ አቅራቢያ ቢኖሩም የቤተሰብ ነገር ሲነሳ ገነት የቤተሰቦቿ ፎቶዎችን (ታሪኮቿን )በማየት ማንባት ይቀናታል። በዚህ ወጣ ውረድ ውስጥ ግን ገነት አንድ ትልቅ ህልም አላት አርሱም ለየተኛው አገር እንደ ሆነ በውል ባታውቀውም በኦሎምፒክ ውድድር ላይ በመወዳደረ የወርቅ ሜዳሊያ ለማጥለቅ እና ሰንደቃላማ ማውለብለብ ነው ።

አንደ አትሌት ገነት ሁሉ አርሱም የገዢው መንግሰት” የፓርቲ አባል ካልሆንክ” ተበሎ የተለያዩ በደሎች እንደደረሱበት የሚናገረው የ25 አመቱ የረጅም ረቀት ጀግናው አትሌት ሃይሌ መንገሻ በአሁኑ ወቅት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአንድ የመጠጥ መሽጫ መደብር ውስጥ ተቅጥሮ ኑሮውን የሚገፋ ሲሆን “ምንም እንኳን ብዙ ቀናት ቢጨልምም ፣የወደፊቱ እድሌን በቁርጠኝነት ባላውቀውም ወደ ኢትዮጵያ ከምመለስ እራሴን እዚሁ ባጠፋ እመርጣለሁ።” በማለት ደረሰብኝ ካለው በደሉ የተነሳ ከፈጥረቱ አንስቶ ደጉን እና ክፉን ካየባት አናት አገሩ( ኢትዮጵያ) ለጊዜውም ቢሆን ጥላ ከለላ የሆነችው አሜሪካንን መርጧል።

በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያን በአለማቀፍ የአትሊቲክስ ወድድሮች ላይ የሚወክሉት ፡ የአውሮፓ፣ የአሜሪካ ፣ የቻይና የመሳሰሉት ጎዳናዎች ላይ አረንጓዴውን ፣ቢጫውን እና ቀዩ ሰንደቃላማችንን በማውለብለብ የሁሌም አምባሳደሮቻችን የሆኑት ብርቅየዎቹ አትሌቶቻችን በሰበበ ባሰባቡ በወጡበት በመቅረት ለተለያዩ ባእዳን አገሮች የመሮጣቸው ነገር ሁኔታውን በቅርብ ለሚከታተሉ በርካታ ወገኖች በእጅጉ ያሳዘናል፣እንደ አገርም እንደ ሕዝብም ያሳፍራል ። ችግሩን ችግራቸን አድርገን መፍትሔውን ን በጋራ ካለፈላለግን “ዛሬ ቁጭ ብለው የሰቀሉት ነገ ቆመው ለማውረድ ይከበዳል “እንዳይሆን ደጋግሞ ማሰቡ ትልቅ አዋቂነት ነው። እስቲ እኛም ለምን ብርቅዪ አትሌቶቻችን ይኮበለላሉ? ብለን እነጠይቅ።

“ልጄ በተሰጣቸው ዜማም ሆነ በግሉ በዘፈነው ምንም እንከን አይወጣለትም፤ አንደኛ መሆን ሲገባው ሁለተኛ መሆኑ እኔንም ሆነ የአካባቢዬን ሰዎች ሀዘን ላይ ጥሎናል” -የኢሳያስ እናት

$
0
0

የኢሳያስ እናት የ“ባላገሩ ምርጥ”ን ዳኝነት ተችተዋል
“60 በመቶ ለተመልካች የተሰጠው ዳኝነት ልጄን ጐድቶታል” የኢሳያስ እናት
• “በባላገሩ ውድድር እዚህ ደረጃ መድረሴ ትልቅ እድል ነው” – ቢኒያም እሸቱ
• “በዳኞች ውጤት ኢሳያስና ዳዊት እኩል ነጥብ ላይ ነበሩ” – አረጋኸኝ ወራሽ
• “የአብርሃም ወልዴ መታመም በግሌ ጐድቶኛል – ባልከው ዓለሙ
e258f927d93aa12e0cf9aa267dd8876e_XL

የባላገሩ አይዶል አዘጋጅ አብርሃም ወልዴ ለመጨረሻ ውድድር የሚቀርቡትን የባላገሩ ምርጥ የድምፅ ተወዳዳሪዎች ሲመክር፤ “ጉንፋን እንኳን እንዳይዛችሁ መጠንቀቅ አለባችሁ” ብሎ ነበር፡፡ ለተወዳዳሪዎቹ ተጨንቆ እንዲጠነቀቁ ሲመክራቸው የከረመው አብርሐም ወልዴ ግን በማጠናቀቂያው ዝግጅት ላይ ራሱ ታሞ መምጣቱ የብዙዎቹን አንጀት በልቷል፡፡
ባለፈው የመስቀል በዓል በሚሊኒየም አዳራሽ የተካሄደው የመጨረሻ የባላገሩ ምርጦች ውድድር ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ሁኔታ በድምቀት ተጠናቋል፡፡ በዳኝነቱና በውጤት አሰጣጡ ላይ ከዚህ ቀደም እንደነበሩ ውድድሮች ከፍተኛ ውዝግብ ባይነሳም የተወሰኑ ተቃውሞና ትችቶች መፍጠሩ አልቀረም፡፡
በድምፅ ውድድር ሁለተኛ የወጣው ኢሳያስ ታምራትን ለማነጋገር ሰሞኑን ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ ወደሚገኘው ቤቱ ብንሄድም በአካል ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡ በስልክ ስናነጋግረውም በውጤቱ ዙሪያ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆነ ገልፆልናል፡፡
የኢሳያስ እናት ወ/ሮ አልማዝ ተሰማ ግን በልጃቸው ውጤት ዙሪያ ያልጠበቅነውን የሰላ አስተያየት ሰነዘሩ፡-
“ልጄ በተሰጣቸው ዜማም ሆነ በግሉ በዘፈነው ምንም እንከን አይወጣለትም፤ አንደኛ መሆን ሲገባው ሁለተኛ መሆኑ እኔንም ሆነ የአካባቢዬን ሰዎች ሀዘን ላይ ጥሎናል” ያሉት ወ/ሮ አልማዝ፤ “ውድድሩ ብቃት ባላቸው ዳኞች እየተመራ 60 በመቶ ለተመልካች መሰጠቱ ልጄን በእጅጉ ጐድቶታል” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡ እስካሁን በተካሄዱት ውድድሮች ዳኞቹ “የሴት፣ የወንድ፣ የሽማግሌና የወጣት ዘፈን ለመዝፈን የተመቸ ድምጽ ሰጥቶሃል” እያሉ ኢሳያስን ሲያሞካሹት እንደነበር ያስታወሱት እናቱ፤ ልጃቸው በቲፎዞ ብዛት እንጂ በችሎታው እንዳልተበለጠ እርግጠኛ መሆናቸውን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
“ከዱባይ ድረስ እየተመላለሰ ሲወዳደር የነበረው ለብር ወይም ለሽልማት ብሎ ሳይሆን ብቃቱንና ችሎታውን ለማሳየት ነው” ያሉት ወ/ሮ አልማዝ፤ “ልጄ የግድ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን ለመለየት ሲባል መስዋዕት ሆኗል፤ ውጤቱም አይገባውም” ብለዋል፡፡ “በዚህም” ልጅ አዋቂው የኢሳያስ አድናቂ በእንባ ተራጭቷል፤ እኔም ቅስሜ ተሰብሯል” በማለት ስሜታቸውን ገልፀዋል፡፡
ሌላው የባላገሩ ምርጦች ተወዳዳሪ ባልከው ዓለሙ፤ እስከ ምርጥ ስድስት የተካሄደው ዳኝነት፣ ግልጽነት የተሞላበትና ትክክለኛ እንደነበር ያስታውሳል፡፡ የመጨረሻው ውጤት አሰጣጥ ግን የተድበሰበሰና ግልጽነት የጐደለው በመሆኑ በውጤቱ ቅር መሰኘቱን ተናግሯል፡፡
“ባላገሩ ትልቅ እውቅናና እድል ስለሰጠኝ በሂደቱም፣ በአዘጋጁ አብርሃም ወልዴም በጣም ደስተኛ ነኝ” ያለው ባልከው፤ የውድድሩ ዕለት አብርሃም የገጠመው የጤና ዕክል በዳኝነቱ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል ባይ ነው፡፡
“እስከ ምርጥ ስድስት ድረስ ዳኞቹ እየሰበሰቡ ስለ ውጤት አሰጣጡና ስለ ዳኝነት ሂደቱ ይነግሩን ነበር፤ የመጨረሻው ላይ ግን ውድድሩን እንዴት እንደዳኙት፣ ውጤት አሰጣጡ ምን እንደሚመስል ምንም የሚታወቅ ነገር የለም” ብሏል – ባልከው፡፡ “ይሄ ደግሞ በአብርሃም ህመም ሳቢያ የተፈጠረ ችግር ነው” ያለው ተወዳዳሪው፤ “ሌላው ቀርቶ ከውጤት በኋላ ዳኞች ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት ሲገባቸው አልሰጡም” ሲልም አስተያየቱን ሰንዝሯል፡፡ በውድድሩ ምን ውጤት ጠብቆ እንደነበር ተጠይቆም፤ “በተመልካች ምርጫ ውጤት እስኪነገር ድረስ ወደ ሰባት ሺህ የሚጠጋ ድጋፍ ነበረኝ፤ ይህም የሶስተኝነት ደረጃ እንደማገኝ አመልካች ነበር፤ ነገር ግን የዳኝነቱን ሂደት ግልጽ ሳያደርጉ፣ ዳኞቹ ያለ ተፅዕኖ የፈለጉትን አድርገዋል” ሲል ቅሬታውን ገልጿል፡፡ እንዲያም ሆኖ ባላገሩ አይዶል የፈጠረለትን ትልቅ ዕድል አመስግኗል፡፡ “እዚህ እንድደርስ በስልጠና ብዙ ነገር ያሳወቀኝ ባላገሩ አይዶልንና አዘጋጁን አብርሃም ወልዴን ከልብ አመሰግናለሁ፤ ለባላገሩም ሆነ ለአዘጋጁ ትልቅ አክብሮት አለኝ” ብሏል፤ በቅርቡ ከአንድ ድርጅት ጋር ለመስራት ውል እየፈፀምኩ ነው፤ ይህ ሁሉ እድል የተገኘው በባላገሩ ስለሆነ በድጋሚ አመሰግናለሁ በማለት አስተያየቱን ቋጭቷል፡፡
ምርጥ ስድስት ውስጥ ከገቡት ድምፃዊያን አንዱ የሆነው ወጣት ቢኒያም እሸቱ ደግሞ በሁሉም ነገር ደስተኛ ነኝ ይላል፡፡ መጀመሪያም በቤተሰብና በጓደኛ ግፊት ሳይፈልግ ወደ ውድድሩ መግባቱን የጠቆመው ተወዳዳሪው፤ ተጀምሮ እስኪያልቅ በነበረው የውድድር ሂደት ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ለቢኒያም ደረጃና ሽልማት ዋናው ጉዳይ አይደለም፡፡ “በእስከዛሬው የውድድር ሂደት ላይ ዳኞቹ በሰጡኝ አስተያየት እየተመራሁ፣ ድክመቶቼን እያስተካከልኩ፣ እዚህ መድረሴና በራሴ ላይ ለውጥ ማምጣቴ ለእኔ ትልቅ እድል ነው” ብሏል፡፡
“ባላገሩ አይዶል ወደ ህይወቴ ከመጡ መልካም አጋጣሚዎች አንዱና ትልቁ ነው” የሚለው ተወዳዳሪው፤ “ደረጃና ሽልማት አስቤ ባለመግባቴ በዳኝነቱም ሆነ በውጤቱ ቅሬታ የለኝም፤ ባላገሩ አይዶል በፈጠረልኝ እውቅና የራሴን ስራ ሰርቼ ወደ ህዝቡ ለመቅረብ እጥራለሁ” ሲል ዕቅዱን ተናግሯል፡፡ “ባላገሩ አይዶል ወደ ህዝቡ ለመግባት ለስድስታችንም ሁኔታዎችን አቅልሎልናል፤ ይህን እድል መጠቀምና አለመጠቀም የእኛ ፋንታ ነው” ብሏል – ቢኒያም፡፡
የባላገሩ አይዶል የድምፅ ዳኛ አንጋፋው ድምፃዊ አረጋኸኝ ወራሽ ስለባላገሩ አይዶል ሲናገር፤ “ባላገሩ አይዶል በዚህች አገር የሙዚቃ ታሪክ ላይ የተለየና ጉልህ አሻራ ማሳረፍ የቻለ ትልቅ ፕሮግራም ነበር” በማለት አድናቆቱን ገልጿል፡፡ ባላገሩ በሁሉ ነገሩ የተለየ መሆኑን ሲገልፅም፡- ለምርጥ 25 ተወዳዳሪዎች በኩሪፍቱ የክህሎትና የዲስፒሊን ስልጠና መስጠቱ፣ በቁንጮ የሰራው አኒሜሽን፣ በከለር ካርዶች ውጤት እንዲሰጥ ማድረጉ፣ ከአልባሳት ጀምሮ ተወዳዳሪዎች ለሙያው ክብር እንዲኖራቸውና በራስ መተማመናቸው እንዲጐለብት መደረጉን ጠቃቅሷል፡፡
“በዚህ ሂደት ውስጥ ችሎታ ያላቸው 25 ምርጥ ባለሙያዎች ወደ ሙዚቃው ኢንዱስትሪ መቀላቀል ችለዋል” ያለው አረጋኸኝ፤ “ትውልዱ እድለኛ ነው፤ በእኛ ዘመን ድምፃዊያን ያላገኙት ሰፊ ዕድል ተፈጥሮለታል” ብሏል፡፡ “በውድድር ተሳታፊ ሆነው፣ ስልጠና ተመቻችቶላቸው፣ እውቅና አግኝተው፣ በመጨረሻም ተሸልመው ከመሄድ በላይ እድለኝነት የለም”፡፡ በባላገሩ አይዶል ያሳለፈውን የዳኝነት ጊዜ በተመለከተ ተጠይቆም፤ “እነዚህን የመሰሉ በስነ – ምግባር የታነፁ፣ ልዩ ችሎታና ብቃት ያላቸው፣ የሚያኮሩ ባለሙያዎች ባፈራው ባላገሩ አይዶል ላይ በዳኝነት እስከዚህ በመድረሴ ደስታም ኩራትም ይሰማኛል” ሲል መልሷል፡፡
በመጨረሻው የውድድር እለት በዳኞች ምዘና 1ኛ የወጣው ማን ነበር? በሚል ለቀረለበለት ጥያቄ፤ “በእኛ የዳኝነት ሂደት የሁለቱም (ዳዊት ፅጌና ኢሳያስ ታምራት) ነጥብ እኩል ነበር፤ ነገር ግን በተመልካች ድምጽና በታዛቢዎች ዳኝነት በጣም ጥቃቅን በሆነ ልዩነት አንደኛና ሁለተኛ ሆነዋል እንጂ… ሁለቱን እንዴት ማበላለጥ ይቻላል”፡፡
ሙዚቃ ሙያ ነው፤ መዳኘት ያለበት በባለሙያዎች እንጂ እንዴት በተመልካች ይሆናል፤ የተመልካች ድምፅ የግድ ነው ከተባለም እንዴት አብላጫውን ነጥብ (60%) ይይዛል? የሚል አስተያየት ከተለያዩ ወገኖች ይሰነዘራል፡፡ አረጋኸኝ በሰጠው የአንተ አስተያየት፤ “እኛ ስድስቱንም አንደኛ ማድረግ እንፈልግ ነበር፤ ነገር ግን ውድድር ስለሆነ እኛ በዳኝነት ብዙዎቹን እስከዚህ ድረስ አምጥተናል፤ ተመልካቹ በአሁን ሰዓት በሙዚቃ እውቀቱ የመጠቀ ስለሆነ በድምፁ መዳኘቱ ችግር ያለው አይመስለኝም” ብሏል፡፡
የባላገሩ አይዶል አዘጋጅና ዳይሬክተር አብርሃም ወልዴን ለማነጋገር ሞክረን ከህመሙ ጋር በተያያዘ ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡ ከእኛ ቀደም ብሎ ለ”ታዲያስ አዲስ” በሰጠው አስተያየት፤ “ማሸነፍ ያለበት አሸንፏል፤ የኦዲየንሱም ድምፅ ወሳኝ ነበር፤ አንድ ሰው ሮል ሞዴል የሚሆነው በብዙ አስተያየቶችና ውጤቶች ጥርቅም ነው” ብሏል፡፡ የዳዊትንና የኢሳያስን የመጨረሻ ትንቅንቅ በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄም፤ “ኢሳያስ በጣም ብቃቱን አሳይቷል፤ ነገር ግን ሪስክም ወስዷል፤ ብቻ በእለቱ ማሸነፍ የነበረበት አሸንፏል፡፡ የዳዊት አንደኛ መውጣት ግን የሌሎቹን ብቃት ጥያቄ ውስጥ የሚከት አይደለም” ያለው አብርሃም፣ “እኔ የሚያሳስበኝ አሁን አንደኛ ሁለተኛ መሆናቸው ሳይሆን ወደፊታቸው ምን ይሆናል፤ ነገ ምን ላይ ደርሰው አያቸዋለሁ” የሚለው ነው ብሏል፡፡
በገጠመው የጤና እክል የፕሮግራሙ ፍፃሜ እሱ ባሰበውና ባቀደው መልኩ አለመካሄዱ ቁጭት እንደፈጠረበት የጠቆመው አብርሃም፤ ህዝቡ ያደረገውን አስተዋፅኦና ያሳየውን ፍቅር በቃላት ለመግለፅ እንደሚቸግረው ለ”ታዲያስ አዲስ” ተናግሯል፡፡ለ3 ዓመት የዘለቀው ባላገሩ አይዶል ተጠናቋል፡፡ ነገር ግን ባላገሩ አይዶል አይቀጥልም እየተባለ ነው፡፡ ፕሮግራሙ ከተቀዳጀው ስኬትና ካበረከተው አስተዋጽኦ አንፃር ቀጣይነቱ ጥያቄ ውስጥ መግባት ነበረበት ወይ? በሚል ለድምፃዊ አረጋኸኝ ወራሽ ላቀረብንለት ጥያቄ፤ “በእውነቱ ይሄን አዘጋጁን መጠየቅ ይቀላል፤ ነገር ግን እንደ ተመልካች ሆኜ ስናገር፣ ሁሉ ነገሩ ጥሩና ለየት ያለ በመሆኑ ቢቀጥል ደስ ይለኛል” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ ባላገሩ አይዶል ይቀጥላል አይቀጥልም? ሌሎች ተጨማሪ 25 ወጣት ድምፃውያንን ያፈራል አያፈራም? ጊዜ መልሱን ይነግረናል፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ-ናፍቆት ዮሴፍ

“መንግሥት ተቃዋሚዎችን አወያያለሁ የሚለው ለፖለቲካ ፍጆታ ብቻ ነው”

$
0
0

አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ ወይም የግል ተወካይ የማይኖርበት 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፊታችን ሰኞ የሚመሰረት ሲሆን ም/ቤቱ አማራጭ የፖሊሲ ሃሳቦችና የሰሉ ትችቶች የማይደመጡበት እንደሚሆን ተቃዋሚዎች ገለፁ፡፡
47c629a4f6076e499d018d8ee19bbf41_XL
በፓርላማው የተቃዋሚ ፓርቲ ድምፅ አለመኖር ህዝቡን ይጐዳል ያሉት የመድረክ ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፤ “ከዚህ ቀደም በፓርላማ በነበረን ጊዜ ያለመታከት የህዝብን ሰቆቃና እሮሮ ስናሰማ ነበር፤ አሁን ፓርላማው ከዚህ አይነቱ ጥያቄና አስተያየት ውጭ ነው” ብለዋል፡፡ በውጭም በሃገር ውስጥም ከማንኛውም መድረክ ይልቅ ተደማጭ የሚሆነው በፓርላማ የሚሰነዘር ሃሳብ ነው የሚሉት ፕ/ር በየነ፤ ይህ መድረክ አለመኖሩ ተቃዋሚው በሃገሩ ጉዳይ ያለውን ሃሳብ ህብረተሰቡ እንዳይረዳ እንቅፋት ይሆናል ብለዋል፡፡
ገዢው ፓርቲ እንደ ተምሳሌት ከሚከተለው የቻይና መንግሥት ጋር በዚህ ረገድ በሚገባ ተቀራርበዋል ያሉት ፕ/ሩ፤ ይህ ሁኔታ ግን ለኢትዮጵያ ህዝብ አደገኛ እንደሆነና የህዝብ እውነተኛ ድምፅ ሊታፈን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያውያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው፤ “እስከዛሬ ከመንግሥት ጋር ተቀራርበን ለመስራት ያደረግነው ጥረት ውጤት አላስገኘም፣ ከዚህ በኋላ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራው የስርዓት ለውጥ እንዴት መምጣት አለበት በሚለው ላይ ነው” ብለዋል፡፡
የመድብለ ፓርቲ ስርአት ፍፁም የደበዘዘበትና ህዝቡ ተስፋ የቆረጠበት ሁኔታ ነው የሚታየው የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ፓርላማውም ቢሆን የአንድን ፓርቲ አስተሳሰብ በቻ የሚያንፀባርቅ በመሆኑ ለመጪዎቹ 5 አመታት ከፓርላማው ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅም ነገር ይገኛል ብለን አናምንም ብለዋል፡፡
በፓርላማው የህግና የፖሊሲ ክርክር አድርጐ ለውጥ ለማምጣት ገዢው ፓርቲ ፍላጐት የለውም የሚሉት ዶ/ር ጫኔ፤ ምናልባት ይህ አካሄድ የተቃዋሚ ሃሳቦችን ከመድረኩ የማጥፋት ስትራቴጂ ውጤት ሊሆን ይችላል ይላሉ፡፡
የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ ደግሞ አዲስ የሚመሰረተው ፓርላማ ለሃገሪቱም ሆነ ለመንግስት አይበጅም ባይ ናቸው፡፡ ምክንያታቸውን ሲጠቅሱም፤ ፓርላማው ሁሉን አቀፍ አሳታፊ ባለመሆኑ ነው ይላሉ፡፡ “አሳታፊ ያልሆነ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደግሞ በምንም መልኩ ውጤታማ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም” ብለዋል አቶ አበባው፡፡
የተቃዋሚዎች ድምፅ በፓርላማ አለመኖሩ እምብዛም እንደማያሳስበው የሚገልፀው መንግሥት በበኩሉ፣ በሌላ መንገድ ከተቃዋሚዎች ጋር የተለያዩ የውይይት መድረኮችን በመክፈት በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደርጋለሁ ብሏል፡፡ በኢህአዴግ 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ መንግስታቸው ከተቃዋሚዎች ጋር በወሳኝ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ዝግጁ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
ተቃዋሚዎች ግን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር እምነት እንደሌላቸው ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
መድረክ በተደጋጋሚ ከገዢው ፓርቲ ጋር ለመወያየት ያቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘታቸውን የሚያስታውሱት ፕ/ር በየነ፤ “የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም እንደ ወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሁሉ ተቃዋሚዎችን እናወያያለን ሲሉ የነበረ ቢሆንም አንድም ቀን አላወያዩንም፤ አሁንም እናወያያለን የሚለው ሃሳብ የለጋሾችን ቀልብ ለመግዛት ካልሆነ በስተቀር ተግባራዊ የሚሆን አይደለም ብለዋል፡፡ እንዲያም ሆኖ መድረክ አሁንም ከመንግሥት ጋር ለመወያየት ጥረት እንደሚያደርግ ፕሮፌሰር በየነ ገልፀዋል፡፡ ፡
የኢዴፓ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው፤ በየጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቃዋሚዎችን እናወያያለን የሚሉት ፈፅሞ አምባገነናዊ ስርአት ነው ላለመባልና ዲሞክራሲያዊ ስርአት ያለ ለማስመሰል ነው ብለዋል፡፡ “አንድም ቀን መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲን አቅርቦ አወያይቶ አያውቅም፣ በየጊዜው እናወያያለን ቢልም ወደ ተግባር ሲቀየር አላየንም” ብለዋል ዶ/ር ጫኔ፡፡ ነገሩ ከፖለቲካና ዲፕሎማሲያዊ ንግግር የዘለለ አይደለም ባይ ናቸው፡፡
የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሃሪም የሁለቱን ፖለቲከኞች ሃሳብ ይጋራሉ፡፡ መንግሥት በተደጋጋሚ ተቃዋሚዎችን አወያያለሁ ቢልም እስከዛሬ ሲፈጽመው አልታየም፤ ለወደፊትም ያነጋግረናል የሚል ተስፋ የለኝም ይላሉ፡፡ “በትክክል ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚደረግ ጥረት ያለ አይመስለኝም፤ ተቃዋሚዎች ‘አባሎቻችን ላይ ወከባና ድብደባ ደረሰብን’ ሲሉ ጆሮ ዳቦ ልበስ እየተባሉ፣ መንግሥት በምን ጉዳይ አወያያለሁ እንደሚል አይገባኝም” ብለዋል፡፡
የህዝብ ውይይት እየተካሄደበት እንደሆነ በሚነገርለት 2ኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዙሪያ መንግሥት ተቃዋሚዎችን እንደሚያወያይ መግለፁ የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡም ለሁሉም ፓርቲዎች በስልክ የውይይት ግብዣ ጥሪ መደረጉንና ተቃዋሚዎችም ጉዳዩ በደብዳቤ ተጠቅሶ ጥሪ ይቅረብልን የሚል ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል፡፡ ይህን ተከትሎም በደብዳቤ ጥሪ ይደረግላችኋል እንደተባሉና የውይይት ጊዜው እንደተቀየረም ተቃዋሚዎቹ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ አለማየሁ አንበሴ


ጋዜጠኛ፣ታዋቂ ዲፕሎማትና የታሪክ ተመራማሪ አምባሳደር ዘውዴ ረታ አረፉ!(አቻምየለህ ታምሩ)

$
0
0

የሀያኛውን መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ በአራት ተከታታይ የታሪክ
ትውልዶች በመክፈል፤ የየትውልዱን ታሪክ ሰሪዎች የህይወት ታሪክና
ትሩፋቶቻቸውን በሚገባ በማሳየትና በመተንተንድ በይዘታቸውም ሆነ በቅርጻቸው
ትላልቅ ሊባሉ በሚችሉ ሶስት [አራተኛው በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል ተብሎ
እየተጠበቀ ነበር] ሰፊ ተቀባይነትን ያገኙ መጽሀፍት በመጻፍ በግራ ፖለቲካ
ልክፍት ተተብትቦ ሲዛባ የኖረውን ታሪካችንን ከምንጩና ትክክለኛ የታሪክ
ሠነዶችን በመያዝ እውነተኛውን የኢትዮጵያ ታሪክ ለትውልድ ካስተላለፉት
የኢትዮጵያ ታሪክ ጸሀፊዎችና ተመራማሪዎች መካከል ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው
አምባሳደር ዘውዴ ረታ በተወለዱ በ81 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

12092261_1508794322767975_1868976334_n
አምባሳደር ዘውዴ ረታ ከታሪክ ጸሀፊነታቸውና ተመራማሪነታቸው ሌላ የትልቅ
ታሪክ ባለቤት አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ባጠቃላይ አምባሳደር ዘውዴ ረታ
ለሀገራቸው በሙያቸው ብዙ ተግባራትን ያበረከቱ ታላቅ ሰው ነበሩ።
በመጽሐፍቶቻቸው ውስጥ የአምባሳደር ዘውዴ ረታ አጭር የሕይወት ታሪክ
እንደሚያሳየው፣ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ነሐሴ 7 ቀን 1927 ዓ.ም አዲስ አበባ
ውስጥ ተወልደው ከ1933 ዓ.ም እስከ 1945 ዓ.ም ድረስም ቀድሞ
ደጅአዝማች ገብረማርያም ይባል በነበረውና ኋላ “ሊሴ ገብረማርያም” ተብሎ
በተሰየመው የፈረንሳይ ት/ቤት የመጀመሪያውንና የሁለተኛ ደረጃ
ትምህርታቸውን አከናውነዋል።
ከዚያም ከ1945 ዓ.ም እስከ 1948 ዓ.ም በጋዜጣና ማስታወቂያ መሥሪያ
ቤት፣ የቤተ-መንግሥት ዜና ጋዜጠኛና በራዲዮ ዜና አቅራቢነት ሠርተዋል።
ቀጥሎም ከ1948 ዓ.ም እስከ 1952 ዓ.ም ድረስ በፓሪስ የጋዜጠኝነት
ትምህርት በማጥናት በዲፕሎማ ተመርቀዋል። ከትምህርታቸው መጠናቀቂያ
በኋላ ከ1952 ዓ.ም እስከ 1954 ዓ.ም የኢትዮጵያ ድምጽ ጋዜጣና የመነን
መጽሔት ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል። በኋላም ከ1954 እስከ 1955 ዓ.ም
ለአንድ ዓመት የኢትዮጵያ ራዲዮ ብሔራዊ አገልግሎት ዳይሬክተር ሆነው
ሰርተዋል። ከ1955 ዓ.ም እስከ 1958 ዓ.ም ደግሞ የኢትዮጵያ ወሬ ምንጭ
ዋና ዳይሬክተር ነበሩ። ከ1958 ዓ.ም እስከ 1960 ዓ.ም የማስታወቂያ
ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል። ከዚህ በመቀጠል ከ1960 ዓ.ም
እስከ 1962 ዓ.ም ድረስ ደግሞ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ዋና ሥራ
አስኪያጅ በመሆን አገልግለዋል። ከ1956 ዓ.ም እስከ 1962 ዓ.ም የፓን
አፍሪካ ኒውስ ኤጀንሲ ማኅበር ፕሬዝደንት ሆነውም ሰርተዋል። ከ1962 ዓ.ም
እስከ 1967 ዓ.ም ድረስ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተዘዋውረው በሦስት
ዘርፎች አገራቸውን አገልግለዋል። እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፡-
1ኛ. በፓሪስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሚኒስትር ካውንስለር
2ኛ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ም/ሚኒስትር
3ኛ. በሮም እና በቱኒዚያ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አምባሳደር ሆነው
ሰርተዋል።
በጠቅላላው በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የሀያ ሁለት ዓመታት
አገልግሎት። ካበረከተ በኋላ በደርግ ዘመን ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ ስደተኛ ሆኖ
በአውሮፓ በቆየበት ዘመን በሮም የኢንተርናሽናል ድርጅት ውስጥ [IFAD]
ለአሥራ ሦስት ዓመታት በፕሮቶኮልና በመንግሥታት ግንኙነት ጉዳይ ኃላፊ ሆኖ
ሠርቷል።
አምባሳደር ዘውዴ በ1959 ዓ.ም ጋብቻውን መሥርቶ ከሕግ ባለቤታቸው
ከወይዘሮ ገሊላ ተፈራ ጋር ሦስት ልጆች አፍርተዋል። ከንጉሠ ነገሥቱ
መንግሥት የምኒልክ የመኮንን ደረጃና የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ አዛዥ መኮንን
ኒሻን ተሸልመዋል። እንዲሁም ከአፍሪካ ፣ ከእስያና ከአውሮፓ በድምሩ ከሀያ
ሁለት አገሮች የታላቅ መኮንን ደረጃ ኒሻኖች ተሸልመዋል። ከዚህ ቀደም
በ1945 እና በ1946 ዓ.ም ካዘጋጇቸው አራት ቲያትሮች ሌላ ፤ በ1992 ዓ.ም
የኤርትራ ጉዳይ፤ በ1997 ዓ.ም ተፈሪ መኮንን ረጅሙ የስልጣን ጉዞና በ2004
ዓ.ም ደግሞ የቀድሞ ኃይለሥላሴ መንግሥት የተሰኙትን መጻሕፍቶች ጽፈዋል።
የአምባሳደር ዘውዴ ረታ «የኤርትራ ጉዳይ» ብለው በጻፉት መጽሀፋቸው ውስጥ
ተጽፎ የቀረበው ታሪክ በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የተመረኮዘ ነው፡-
1ኛ. አብዛኛው የኤርትራ ሕዝብ ፣ ከባዕድ አገዛዝ ለመላቀቅና ወደ መሠረት
አገሩ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ኢትዮጵያ ወይ ሞት ብሎ በመታገል ምን ያህል
መከራና ፈተና እንደተቀበለ፤
2ኛ. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ኤርትራን ከኢትዮጵያ ጋር ለማዋኃድ
በአራቱ ኃያላን መንግሥታት ዳኝነትና ቀጥሎም በተባበሩት መንግሥታት ሸንጎ
ላይ ለብዙ ዓመታት ያደረገው ፋታ የሌለው ሙግት ምን ውጤት እንደሰጠ፤
3ኛ. በተባበሩ መንግሥታት ሸንጎ ላይ ኤርትራ በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር
እንድትቀላቀል፣ ፍርዱ እንዴት እንደተወሰነና፣ ከዚያም ለአሥር ዓመታት
የተካሄደው የፌዴሬሽን አስተዳደር በምን መልክ ይሠራበት እንደነበረና በኃላም
በምን አኳኋን እንደፈረሰ እውነተኛውን ታሪክ የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦች
እንዲያውቁት በዝርዝር በማዘጋጀት ረገድ ከፍ ያለ ጥረት አድርገዋል።
«ተፈሪ መኰንን ረዥሙ የሥልጣን ጉዞ» የሚለው ሁለተኛ የታሪክ መጽሀፋቸው
ደግሞ በሐምሌ 1997 ዓ.ም ለአንባቢዎች የቀረበ ሲሆን መጽሐፉ ቀዳማዊ
ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ-ነገሥት ሆነው ኢትዮጵያን መምራት ከመጀመራቸው በፊት
ደጃዝማች ተፈራ መኰነን ከሐረር ጠቅላይ ገዥነት ተነስተው በምን አኳኋን
ባለሙሉ ሥልጣን አልጋወራሽ ለመሆን እንደበቁና ዘውድ እስከጫኑበት ጊዜ
ድረስ የኢትዮጵያን መንግሥት እንዴት ሲመሩ እንደቆዩ የሚያስረዳ ነው።
ከአፄ ምኒልክ ሕይወት ፍጻሜ በኋላ በአገራችን በያለበት እየተቀመመ ይሰራጭ
በነበረው ወሬ መሰረት ተፈሪ መኮንን የኢትዮጵያ መሪ ለመሆን የበቁት ልጅ
ኢያሱን በኩዴታ ጥለው ንግሥት ዘውዲቱን በሐኪም መርፌ አስገድለው ነው
የሚል ነበር።
ደራሲው ግን በዚያን ዘመን የተካሄደውን የኢትዮጵያን ታሪክ ለረዥም ጊዜ
ምርምርና ጥናት በማካሄድ፡-
1ኛ. ልጅ ኢያሱ ከሥልጣን እንዴት እንደወረዱ ፣ ወይዘሮ ዘውዲቱ ምኒልክ
ንግሥተ ነገሥታት ተብለው ዘውድ ለመጫን እንደበቁ፤
2ኛ. ለመንግሥቱ ሥራ አመራር የራስ መኰንን ልጅ ተፈሪ መኰነን ባለሙሉ
ሥልጣን እንደራሴና አልጋ ወራሽ እንዴት ሆነው እንደተመረጡ፤
3ኛ. ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ ከዚህ ዓለም በሞት እንዴት እንደተለዩ
ትክክለኛውን ታሪክ ለአንባቢዎች በማቅረብ ብርቱ ጥረት አድርገዋል።
በመጨረሻም አምባሳደር ዘውዴ ረታ «የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት»
በሚል ርዕስ በጻፉት ባለ811 ገጽ መጽሀፍ ኢትዮጵያን ለአርባ አምስት ዓመታት
ያህል በንጉሠ ነገሥትነት ሲያስተዳድሯት የኖሩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ
የመጀመሪያዎቹ ሃያ አምስት ዓመታት የመንግሥታቸው አመራር ታሪክ ምን
ይመስል እንደነበር ተንትነው አቅርበዋል።
መጽሀፉ ውስጥ ከተካተቱት የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሃያ አምስት ዓመታት ዘመነ
መንግሥት ውስጥ ታሪኮች ውስጥ፡-
1ኛ . የፋሽስት ጣሊያን ወረራ አመጣጥ፤
2ኛ. የኢትዮጵያን ነጻነት ለማዳን ንጉሠ ነገሥቱ በዤኔቭ የመንግሥታት ማህበር
ሸንጎ ላይ ያደረጉት ሙግትና በመጨረሻም ሊግ ኦፍ ኔሽን ያደረገው አሳዛኝ
ውሳኔ፤
3ኛ. ሙሶሊኒ ከሂትለር ጋር ተሰልፎ የአውሮፓን መንግሥት በጦር ሲወጋ ፣
እንግሊዞች የኢትዮጵያን ነፃነት ለማስመለስ አገራችንን ከያዙ በኋላ የጫኑብን
የሞግዚት አስተዳደር እንዴት እንደነበር፤
4ኛ. ነፃነታችን ከፋሽስት እጅ ከተመለሰ በኋላ ከእንግሊዞች የሞግዚት አስተዳደር
ለመላቀቅ ምን ያህል ድካም እደጠየቀ፤
5ኛ. ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በምሥጢር ወደ ስዌዝ ካናል ተጉዘው ከአሜሪካው
መሪ ከፕሬዚዳንት ሩዝቬልት ጋር ያደረጉት ንግግር ይዘት፤
6ኛ. ኢትዮጵያ ከእንግሊዞች የሞግዚት አስተዳደር ከተላቀቀች በኋላ በአገር
ውስጥ የሁለት ሰዎች [መኮንን ሀብተወልድና ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ]
የሥልጣን አነሳስና ትብብር ንጉሠ ነገሥቱን ምን ያህል እንደአሳሰባቸው፤
7ኛ. ከእነዚህ ከሁለቱ ሰዎች መካከል የሥልጣን ኃይላቸው አስጊ ሆኖ
የተገመተውን ጸሐፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዮርጊስን በሽረት ከካቢኒያቸው ለማራቅ
ንጉሠ ነገሥቱ የወሰዱትን እርምጃ አምባሳደር ዘውዴ በዝርዝር በመግለጽ
ለኢትዮጵያ ሕዝብ እውነተኛ ታሪክ አቅርበዋል።
አምባሳደር ዘውዴ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚመለከት ሊጽፉ ቃል ከገቧቸው አራት
መጽሀፍት መካከል አራተኛውንና የመጨረሻውን መፍሀፋቸውን በመጻፍ ላይ
እንዳሉ ሞት ቀደማቸው። በሰው ላይ ሞትን የሚያህል እዳ አለና አምባሳደር
ዘውዴም ያሰቡትን ሁሉ ለመፈጸም ባለመቻላቸው እጅግ ያሳዝናል።
እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያኑረው። ለወዳጆቻቸውና ለቤተሰባቸው በሙሉ
ጽናትንና ብርታትን እግዚያብሄር እንዲሰጣቸው ከልብ እመኛለሁ።

ባልተፈጸመ ወንጀል፣ ባልቀረበ ማስረጃ ዜጎችን ማንገላታት ይቁም፡፡

$
0
0

Zone9 with አመለወርቅ ታምሩ:_
በዛሬው ዕለት በነሶልያና የክስ መዝገብ በዞን ዘጠኝ ጦማርያን ላይ ማለትም በሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ናትናኤል ፈለቀ እና በፍቃዱ ኃይሉ ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ችሎት ዳኞች “አዳማ ስልጠና ላይ ናቸው” በሚል ባለመገኘታቸው ምክንያት ለጥቅምት 5/2008 ዓ/ም ለ 38ተኛ ጊዜ ቀጠሮ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሁለቱ ዳኞች የመሃል ዳኛው አቶ ሸለመ እና አቶ ዘርሁን ተቀይረዋል የሚባል መረጃ የተገኘ ሲሆን አቶ ታረቀኝ ብቻ ችሎቱ ላይ ይቀጥላሉ ተብሏል። ለችሎቱ አዲስ የተሾሙት ዳኞች ማንነት እስካሁን አልታወቀም።
12122843_884572701631223_3359022899394364924_n
በእስር 531ኛ ቀናቸውን እያሳለፉ የሚገኙት ጦማርያኑ ይህ የ”ፍርድ ቤት” ቀጠሮአቸው ለ38ኛ ጊዜ የተሰጣቸው ነው ፣ የቀረበባቸው ማስረጃን ገምግሞ ይከላከሉ ወይስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ ይሰናበቱ የሚለውን ውሳኔ ለማሰማት “ፍርድ ቤቱ” የዛሬውን ጨምሮ ለ5ኛ ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ስሜት የማይሰጡ ክሶች እና የተራዘሙ የፍርድ ሂደቶች ዜጎችን በአገራቸው የበለጠ ተስፋ እንዲቆርጡ የሚያደርጋቸው ከመሆኑም በላይ ያለዋስትና በፍርሃት እንዲኖሩ የሚያደርግ ነው፣ ይህ እንዲሆን ካልተፈለገ በቀር በቀጠሮዎች መራዘም ንጹሃንን ጥፋተኛ ማድረግ እንደማይቻል የዞን9 ጦማርያን እናምናለን፡፡

ባልተፈጸመ ወንጀል፣ ባልቀረበ ማስረጃ ዜጎችን ማንገላታት ይቁም፡፡
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎FreeZone9Bloggers‬

ሙሉጌታ ሉሌ ሐምሌ 1933 – መስከረም 23 ቀን 2008 ( July 12, 1941 – Oct 4, 2015)-አጭር የሕይወት ታሪክ በጋዜጠኛ ደረጄ ደስታ

$
0
0

ያለፉት 50 ዓመታት ስመ ገናናው ጋዜጠኛ፣ ፀሐፊ፣ የታሪክና ፖለቲካ ተንታኝ ሙሉጌታ ሉሌ በ1933 ቀን ዓ.ም በጎጃም ክፍለ አገር ቢቸና ይልማና ዴንሳ በምትባል ሥፍራ ተወለደ። በአምቦ ከተማ ማዕረገ ሕይወት ቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ትምህርት ቤት አንደኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቀቀ። በደብረ ብረሀን ኃይለማርያም ማሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱንም ተከታትሏል።

12047037_1080053575338858_3699956726967469170_n
በ1950 ዎቹ መጀመሪያ ላይ፣ ወደ ናዝሬት የባይብል አካዳሚ በመግባት፣ ብዙ ነገር የገበየበትን ትምህርትና፣ ዘላቂ መሠረት የሆነውን እውቀት በመውሰድ፣ የሥራ ዓለምን አንድ ብሎ የጀመረው፣ እዚያው በሰለጠነበት የባይብል አካዳሚ መምህር በመሆን ነበር። በቆይታውም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እውቅ የሆኑትን እንደነ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ዶ/ር ላጲሶ ጋዴቦ፣ አቶ ሌንጮ ለታና የመሳሰሉትን ማስተማሩ ተዘግቦለታል። ጋሽ ሙሉጌታ የስነ መለኮትና የቤተክርስቲያን ታሪክን በጥልቀት ማወቁም ይነገርለታል።
በ1955 አካባቢ አንስቶ የምስራች ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያ ውስጥ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ ሥራውንና ብዕሩን በአድናቆት የተመለከቱ የሥራ ባልደረቦቹና አለቆቹ የሆኑት፣ እነ ጳውሎስ ኞኞና ብርሃኑ ዘሪሁን፣ ወደ ማስታወቂያ ሚኒስቴር መጥቶ እንዲሠራ አግባብተውታል። በዚህ መሠረት አቶ ሙሉጌታ በ1957 ግድም በአዲስ ዘመን ተቀጠረ። ለበርካታ ዓመታት አቶ ሙሉጌታን በወዳጅነት የሚያውቁት አቶ አሰፋ ጫቦ እንደተናገሩት፣ አቶ ሙሉጌታ አዲስ ዘመን ላይ ይቀጠር እንጂ በተለያዩ ጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ ጽሑፎቹን የሚያሳትም ዘርፈ ብዙ ጋዜጠኛ ነበር። እንደ ሔራልድ፣ የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ፣ የኢትዮጵያ ድምጽ፣ መነንና አዲስ ሪፖተር የመሳሰሉት ጋዜጦች ላይ በአማርኛና በእንግሊዝኛ በርካታ ጽሑፎችን አቅርቧል፣ የመነን መጽሔት ዋና አዘጋጅ የነበረም ሲሆን ፣አንዳንዶቹም ላይ በረዳት አዘጋጅነት ሰርቷል።
ከ1954 ጀምሮ ጽሑፎችን በማቅረብ ኋላም የቀድሞው መንግሥት የባህልና ማስታወቂያ ሚኒስትር የነበሩት ሻለቃ ግርማ ይልማ አቶ ሙሉጌታ ሉሌን በአካል የሚያውቁት ከ1963 ጀምሮ መሆኑን ገልጸዋል። መቸም ኢትዮጵያ ውስጥ
ከህትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ጋር ግንኙነት አለኝ የሚል ሰው ሙሉጌታ ሉሌን ያውቃል። ያነበበም እንዲሁ ነው። ህዝብን በሚያኮራ መንገድ ሲያገልግል የኖረ በመሆኑም ግዴታውን ተወጥቶ ያለፈ ትልቅ ሰው ነው።
አቶ ሙሉጌታ በ1968 ወደ ኤርትራ፣ በልዩ የግዳጅ ሥራ ተጉዞ “ኢትዮጵያ” የተሰኘችዋን ሳምንታዊ ጋዜጣ በዋና አዘጋጅነት እንዲያጠናክር ተመድቦ መሄዱን፣ በሪፖርተርነት አብሮ ተመድቦ የሄደው፣ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ፕሬዚዳንት ክፍሌ ሙላት ገልጿል። እዚያም ጥቂት እንዳገለገለ የምስራቁን የሶማልያን ወረራ ለመመከት የሚያስችል ልዩ የፕሮፖጋንዳና ሥነ ጽሑፍ ክፍል በማስፈለጉ በማስታወቂያ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሬዲዮ ጋር ልዩ መመሪያ ሲቋቋም መምሪያውን እንዲመራ የታጨው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ መሆኑን ክፍሌ ገልጧል። በዚህ መሠረት መንግሥት በ1970 መጀመሪያ ላይ አቶ ሙሉጌታ ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያንቀሳቅስ የፕሮፖጋንዳና ሥነጽሑፍ ሥራ እንዲመራ አድርጓል። አሉ የተባሉ ከየመምሪያው የተውጣጡ ባለሙያዎችና የሥነጽሁፍ ሰዎችን በመምራት ይህንንም ግዳጁን በብቃት የተወጣና ለአገሪቱ ድልም ከበስተጀርባ ሆኖ ትልቁን ድርሻ የተጫወተ ጀግና መሆኑን አንጋፋው ጋዜጠኛ ክፍሌ ሙላት መስክሯል።
ይህ መሆኑን በትክክል የሚያስታውሱት አቶ አሰፋ ጫቦም ሙሉጌታ ሉሌ፣ የሶማልያና የኤርትራን የፖለቲካና ታሪክ ነክ ጉዳዮች በሚገባ አንብቦና ተንትኖ የሚያውቅ ባለሙያ ነው። ባልደረቦቹንም እየሠራ ጭምር ሲያስረዳና ሲያማክር እንደነበር ማወቃቸውን ተናግረዋል። አቶ አሰፋ እንኳን የአገሩን ታሪክና የፖለቲካ ትንታኔና ትችቶች ቀርቶ፣ የአውሮፓንና የአሜሪካን የፖለቲካ ትንታትኔዎችን የሚያነብና አሳምሮ የሚያውቅ ሰው ነው። ይህንንም በጽሑፎቹ ውስጥ የሚጠቃቅሳቸው ከመሆኑም ሌላ “ይህን መጽሐፍ አንብበሃል ይህን ተመልክተኸዋል?” እያለ አዲስ አበባ ተቀምጦ አሜሪካ ያለን ሰው የሚፈትን አንባቢ መሆኑን ገልጧል።
በኤርትራም የቀይ ኮከብ ዘመቻ ሲጀመር፣ አቶ ሙሉጌታ ሉሌ፣ በበዓሉ ግርማ የተመራውን የጋዜጠኞች ቡድን በምክትልነት እየመራ ሥራውን ያከናውን እንደነበረ ክፍሌ ገልጧል። የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዘዳንትና አንጋፋው ጋዜጠኛ ክፍሌ ሙላት ራሱ በደረሰበት አደጋ ከሚያገግምበት ሆስፒታል አልጋ እያቃሰተና እያለቀሰ – የሙያ አባቴ ስለሚለው አቶ ሙሉጌታ ሉሌ ተናግሮ የሚጠግብ አልሆነም። ሙሉጌታ ለሱ ተገልጾ አያልቅም። ምክንያቱም “ብዙ ሰዎችን አፍርቷል። ለኢትዮጵያም ሞቶላታል። እንደ ወታደር ተዋግቶላታል፣ እንደ ከያኒ ዘምቶላታል… “እያለ ይቀጥላል ክፍሌ።
እስከ 1975 ድረስ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ኃላፊነት በመሾም ሲሰራ የነበረው አቶ ሙሉጌታ ሉሌ፣ በፖለቲካና የቅስቀሳ ሥራዎች ብቻ ሳይወሰን፣ ተወዳጅ የሆኑ ማህበራዊና የመዝናኛ ዝግጅቶችንም በመምራትና ጽሑፎችንም በማበርከት ይታወቃል። እውቁ የቪኦኤው ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ ስለዚሁ ሲገልጽ “ በተለይ በወቅቱ የእሁድ ፕሮግራም ሲዘጋጅ አቶ ገዳሙ አብርሃ የእሁዱ ጧት ፕሮግራም ኃላፊነት ተረክቦ እኔና ንጉሤ አክሊሉን በሟቹ ታደሠ ሙሉነህ አስተብባሪነት እንዲቀጥል አድርጓል፡፡ አንዳንዴ ስክሪፕት ጽፎ ይሰጠናል። ይሄ ጽሑፉ እንጨት እንጨት ይላል ማነው የጻፈው ይላል? ወይ እኔ ንጉሤ ነው እላለሁ፣ ወይ ንጉሤ አዲሱ ነው ይላል። “ሁለታችሁም ያው ቄሶች ናቸው ዞር በሉልኝ!” ብሎ ይቀልድብናል። ከዚያ ደላልዞ እንደገና የመጻፍ ያህል አስተካክሎ ይሰጠናል።
አዲሱ እንደሚለው ልክ እንደ ጽሑፉ ለሬዲዮም የሚጠቀምባቸው የተለያዩ የብዕር ስሞች ነበሩት። በእሁድ ጧት ፕሮግራም በተለመደ ስም በየሳምንቱ የማይቀር ጽሑፍ ነበረው። አቶ ሙሉጌታ ሉሌ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ በመሆን ከ 1975እስከ 1983 አገልግሏል። በዚህ ቆይታው በሥሩ- አዲስ ዘመን፣ ኢትዮጵያን ሄራልድ፣ የዛሬዪቱ፣ በሪሣ (በኦሮምኛ የሚታተም) እና አል አኻረም የተባለ የአረብኛ ጋዜጦችን መርቶ አስተዳድሯል። ማስተዳደር ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያን ሄራልድ አዲስ ዘመንና የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ጽሑፎችን ሲያበረክት ርዕሰ አንቀጽ ሳይቀር ጽፎ እየሰጠ ሠርቶ ሲያሠራ ኖሯል።
የመንግሥት ለውጥ እስከ ተካሄደበት እስከ 1983 ድረስ ሲያገለግል ከቆየ በኋላም እንደ ብዙዎቹ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ለዓመታት ካገለገለበት ከሥራ ገበታው ተፈናቅሏል። ከሥራው ይፈናቀል እንጂ፣ ከሙያው ያልተፈናቀለ ባለመሆኑ፣ ገና በለውጡ የመጀመሪያው ዓመት (በ1984) ከሙያ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን የጦቢያ መጽሔትን አቋቋሟል። ይበልጥ ገናና የሆነበት ብዕሩን በጉጉት ከሚጠበቅ መጽሔት ጋር ለህዝብ ማብቃቱን አሳይቷል። እነ ፀጋዬ ገብረ መድህን አርአያ የተባሉት ስመ ጥር የብዕር ጀኔራሎች የተወለዱትም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው። ጋሽ ሙሉጌታ ተርቡ፣ ስንሻው ተገኝ፣ ስልቁና የመሳሰሉ ሌሎች የብዕር ስሞችም ነበሩት።
. የነጻውን ፕሬስ ጫናና የነፀጋዬ ገብረመድህንን ጡጫ መቋቋም ያልቻለው መንግሥት፣ የሙያ አባት የሆኑትን፣ እነ አቶ ሙሉጌታ ሉሌን ሳይቀር፣ በክስና እስራት ያጣዳፍ ጀመር። አቶ ሙሉጌታ ብዙ ወጥቶ ወርዷል። ከ16 ጊዜ በላይ ክሶች የተመሰረቱበት ሲሆን ለተደጋጋሚ ጊዜ ታስሯል። በደህንነት ሰዎች መኪና ተድጦ ሊገደል ከአፋፍ ተርፎ የወጣ መሆኑ ሁሉ በሰፊው የተነገረበት፣ ቢሮው በእሳት የጋየበት ጋዜጠኛ ነው። አገር ቢቀማም ብዕሩን ያልተቀማ ጀግና ነበር። ወዳጆቹ እንደሚናገሩት በተለይ በግድያ ሙከራነቱ ሰለሚጠረጠረው የመኪና አደጋ ፣ በተአምር ተርፎ ሆስፒታል በተኛበት ወቅት ሆስፒታልም ድረስ እየተከታተሉ ያስቸገሩትን የደህንነት አባላት ለመሸሽ ህክምናውን በመኖሪያ ቤቱ ተኝቶ በወዳጅ ሐኪሞች ለመከታተል የተገደደበት ሁኔታ ሁሉ ነበር። “እንኳን እጄን አልቆረጡኝ ፣ብዕር የምይዝበት እጄ እስካለ ድረስ ተርፌያለሁ” እያለ ወዳጆቹን ያጽናና እንደነበር በቅርብ የሚያውቁት ወዳጁ አቶ ዮሐንስ አበበ ተናግረዋል።
ሁኔታው እየበዛ በመምጣቱም በብርቱ የወዳጅ ጉትጎታ አገር ትቶ እንዲወጣ ተወስኖ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በወዳጆቹ ድጋፍ እንዲወጣ ተደርጓል። ምክንያቱም እስከ 16 የሚደርሱ ክሶች የተመሠረቱበት ሰው ነበር። “ለምን አትወጣም እስኪገድሉህ ነው እንዴ የምትጠብቀው?” ሲባል “በአንድ ስሙ ወይ 20 ወይም 30 ይሙሉና ጊነስ ቡክ ውስጥ ይመዘገባል” እያለ ይቀልድ ነበር፡፡ ነገሩ ግን የሕይወት እንጂ የቀልድ አልነበረም። ስለ እስር እንግልቱ ለምን በአደባባይ በብዛት እንደማያወራ ሲጠየቅ “ የእነዚህን ድንክ ሰዎች ሥራ ማውራት ሌሎች ታዳጊ ጋዜጠኞችን ማስበርገግ ይሆናል” የሚል መልስ ይሰጥ ነበር። እሱ ግን ለሌሎቹ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች መብት ሁሌም እንደቆመ እንደተቆረቆረ ነበር።
አቶ ሙሉጌታ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜኞች ማህበር መስራች አባል ሲሆን እነ አቶ ከፍያለው ማሞ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ጊዜ ም/ፕሬዚዳንት ሆኖ አገልግሏል። እንደ ሲፒጄ ካሉ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለሙያ ልጆቹና አጋሮቹ መብት ጥብቅና ሲቆም ኖሯል።
ጋዜጠኛ ክፍሌ ሙላት “ሙሉጌታ አፍርቶናል ፤ እኛ ፍሬዎቹ ነን። የኢትዮጵያን ፕሬስ ያነጸና ለኢትዮጵያ ያነባላት ሰው ነው። በአጽሙ እኮራለሁ። የኔ የሙያ አጋሮች የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ተጽናኑ! ተበራቱ! ጋሽ ሙሉጌታ በአምባገነኖች ፣በዘረኞችና በትምክህተኞች ጫማ ስር አልወደቀም! አልተንበረከከም። ቃሉን አላጣፈም። እኛን አፍርቷል። የሙሉጌታ ልጆች ስለሆንን እጽናናለሁ።” በማለትም የሙያ አጋሮቹ ጋዜጠኞቹ እንዲጽናኑ መክሯል።
በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞችም “መልካም ስም ከመቃብር በላይ ዘላለማዊ ሆኖ ይኖራል” በሚል ርዕስ ባወጡት የሐዘን መግለጫ፣ አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ለአዲሱ የፕሬስ ትውልድ ፈር ቀዳጅ ነው” ብለዋል። አንጋፋው ጋዜጠኛ “በአንደበቱ እውነትን የመሰከረ፤ በሰላ ብዕሩ ሃቅን የፈነጠቀ ለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ምሳሌ ሆኖ ያለፈ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ነው” ሲሉም አክብሮታቸውን ገልጠውለታል።
Mulugeta_05
ጋዜጠኞቹ “እንደታላቅ ወንድም፤ እንደሙያ አጋር እና እንደ ጥሩ ምሳሌ እያነሱ መልካም ተጋድሎውን ያስታውሳሉ። የነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች ገድል ሲታወስ ደግሞ፤ የጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ መልካም ስም እንደ ፈርጥ ያንጸባርቃል። በውጭ አገር የምንገኝ የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ የጋሽ ሙሉጌታ ሉሌን መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላልና የጋሽ ሙሉጌታ ስራ እና ስም ለዘለአለም በክብር ይታወሳሉ።” የሚል መግለጫ አውጥተውለታል።
አቶ ሙሉጌታ ባለሞገስ ነበር። ሆይ ሆይታ አይጥመውም። ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌም ይህንኑ ነው ያሉት “ ረጋ ያለ ነው። ነገርን ግራና ቀኝ ማስተዋል ይችላል፡፡ እውነትን ለመፈለግ ብዙ ይጥራል፡፡ እውነትን ለመናገር ወደኋላ አይልም- አርቆ ያያል። ሙሉጌታ ሰበር ዜና፣ ትኩስ ዜና የሚጥመው ሰው አይደለም። እሱ የሚያተኩረው ትምህርት ሰጪና ጠለቅ ያሉ ነገሮች ላይ ነው። በሰውነቱ ታጋሽ ነገሮችን በትዕግስት ማለፍ የሚችል ነው። ብዙ ጽሑፎችን ትቷል። አርአያ ሊሆን የሚችል ሰው ነው። ራሱ አውቃለሁ ብሎ ከሚያውቀው በላይ የሚያውቅ ሰው ነው። ትሑት ነው። ቢያውቅ እንኳ እንደማያውቅ ሆኖ ይጠይቃል። ከኔ ሰው ይማራል የሚል እምነት የለውም። ይሄን የዘመናችንን ፖለቲካና ታሪክ ያውቀዋልና እኔም ሁሌ ደውዬ እጠይቀዋለሁ።
ያን ያህል እየታመመ እሱ ስለ ሰው ጤንነት ይጠይቃል እንጂ ስለራሱ አይናገርም። እስከመጨረሻ ለአገሩ ለኢትዮጵያ ያስብ ነበር፤፡ አጫጭር ድርሰት አያውቅም። ምክናያቱም ብዙ ያነባል። ስለሆነም ብዙ ያውቃል። ብዙ የሚያውቀው ነገር ስላለ ደግሞ ያንን ተናግሮ ማቆም ያቅተዋል። ያ የእውቀቱን ምልክት ነው የሚያሳየው። እኔ እንደታናሽ ወንድሜ ነበር የማየው እሱም እንደ ታላቅ ወንድሙ ነበር የሚመለከተኝ። ቤተሰቦቹን እግዚአብሔር ያጽናቸው ከማለትና እኔም አቅም እያነሰኝ ከቤት ሆኜ ስለሱ ብቻዬን ከማልቀስ በቀር ምን አደርጋለሁ?
ንባብ አፍቃሪነቱ ገና ከልጅነት ከተማሪነቱ ነው። የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሳለ የሼክስፒር መጻሕፍትን እነ ሐምሌት ማክብዜ እና ኦቴሎ የመሳሰሉትን በቃሉ ይወጣቸው ነበር። ጽፈትም ይሆንለታል። እንዲያውም ካንዳዊው መምህር ይህን ሌላ ሰው
ጽፎልህ ይሆናል እንጂ፣ የዚህ ጽሑፍ ባለቤት እንደምን አንተ ልትሆን ትችላለህ ብሎ ያመጣውን ጽሑፍ ለመቀበል ያንገራግር እንደነበር በጨዋታ ማንሳቱ ተሰምቷል፡፡ ወደፊት ትልቅ ጸሐፊ ትሆናለህ ብሎኝም ያውቃል እያለም ይቀልድ ነበር። ከትህትናውና ይሉኝታው ብዛት ራሱን የሚያሽሟጥጥ ሰው በመሆኑ አንተ ግን ስለራስህ የማትጽፈው ስለምንድነው ተብሎ ሲጠየቅ እሽም እምቢም ሳይል በፈገግታ ይሸኛል። ስለ ግለ ታሪኩ እንኳ ቃለ መጠይቅ ሲጠየቅ ማውራት የማይፈቅድ ሌላውን ግን ሲተነትን ለሰዓታት ቢቀመጥ የማይታክተው ሰው ነው። ልጻፍ ብሎ የተነሳማ እንደሁ ፍጥነቱ አይደረሰበትም።
“እኔም በጣም የሚደንቀኝ ችሎታው እሱ ነው” ብሏል ሰሎሞን ክፍሌ። ቀድሞ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አሁንም የቪኦኤ እውቅ ጋዜጠኛ የሆነው ሰሎሞን ክፍሌ ጋሽ ሙሉጌታ እንደፎቶግራፍ ያየውን ያነበበውን የሰማውን ቀርጾ ማስቀረት የሚችል የተለየ ጭንቅላት አለው። ሀሳቡንም እንዲሁ አንዴ ፎቶ ያነሳዋል መሰለኝ ወረቀት ላይ ቁጭ ሲያደርገው ወዲያው ነው። ለምሳሌ አንድ ጊዜ በመኪና ረጅም መንገድ እየተጓዝን ነበርን። ያኔ ከወጣም በኋላ ጦቢያ መጽሔት ላይ ይሠራ በነበረበት ጊዜ ነው። እና ለካ እሱ ሁለት አርቲክል አሁኑኑ አድርስ ተብሎ ኖሯል። መኪና ውስጥ ሆኖ ከጎኔ ተቀምጦ ይሞነጫጭራል። እረ ጎሹ ለጦቢያ መጽሔት አድርስ ያለኝ ሁለት አርቲክል አለ እያለ አንድ ጊዜ መሞነጫጨር ጀመረ። በኋላ ገረመኝ ከዲሲ ተነስተን ቦልቲሞር እስክንድረስ አንደኛው አልቋል አለኝ። ፔንሲልቪኒያ ስንደርስ ሁለተኛውን ጨርሶታል። በል አሁን እዚህ እንውረድና ጽሁፎቹን እንላክላቸው ሲለኝ በጣም በጣም ደነቀኝ። ያንን ሲያደርግ ከከኪሱ የሚያወጣቸው የሚያመሳክራቸው ምንም ነገር የለም። ብዙ ሰዎችን ብዙ ቀኖችን ዓመተ ምህረቶችን ነው የሚጠቅሰው። እና እነዚያን አርቲክሎች ሌላ ጊዜ በትክክል አንብቤያቸዋለሁ። ጥልቅ ናቸው። ይህ ሁል ጊዜም ይገርመኛል።” ብሏል ሰለሞን።
ባህርይው ከሥራው ውጭ ሌላው የሚያስደንቀኝ ደግሞ ይሄ ትልቅ ሰው ነው፣ ይሄ ትንሽ ሰው ነው የሚለው ነገር የለውም። ከሁሉም ጋር ቁጭ ብሎ በማንኛውም ርዕስ ላይ ይወያያል። እኔ ብቻ አውቃለሁ የሚል አይደለም። ለማስረዳት የሚያደርገው ጥረት ይገርመኛል።
በመጨረሻዎቹ ጊዚያት ከበውት ከሚዉሉ አድናቂዎቹ ወጣቶች አንዱ የሆነው ተስፋዬ ተሰማ ይህንኑ የሰሎሞን አባባል አረጋግጧል። “ እኛ ወደሱ ከፍ እያልን ሳይሆን እሱ ወደኛ ዝቅ ብሎ እየመጣ ነው ፣ ምንክንያቱም ጋሽ ሙሉጌታ ውሎው ትንሽ ትልቅ ብሎ የሚለይ አይደለም ብሏል። ደግ ሰው ፣ጋባዥ ትሁትና ተጫዋች ነው።
ሰሎሞን ክፍሌ እንደሚለው ጋሽ ሙሉጌታ የተለያየ ሰው የሚያገኝ ብቻ ሳይሆን ለተለያ ሰው የሚሆን ብዕርም አለው። በተለያየ የብዕር ስም ነበር የሚጽፈው። ይህን ሁሉ ነገር የአንድ ሰው የተሸከመው አይመስለኝም የብዙ ሰው ጭንቅላት የተሸከመ ነው የሚመስለኝ፡፤ የዛሬ 30 ዓመት የተለያየኸውን ሰው ስትጠይቀው እስከ እነ አባቱ እስከነ ቅድመ አያቱ ይነግርሃል። እዚህ አገር ቆይቶ ቢሆን ኖሮ እንደኛ የሶሻል ሴኩሪቲውን ቁጥር የጫማ ቁጥሩን ሁሉ ሳይነግረን አይቀርም ብሎ ቀልዷል።
በሀዘኑ እጅግ ከተነኩት አንዱ የሆነው ሰሎሞን “ጋሽ ሙሉጌታ ለአገሩ አፈር አለመብቃቱ ያሳዝነኛል፡፡ ወደመጨረሻው ላይ ዓይኑን አሞት እረ ታውሬ አይኔ ከሚታወር ለአገሬ አብቁኝ ቢፈልጉ ይግደሉኝ ይል ነበር። እሱ ሁሌም አብሮኝ ኖሮ ይረብሸኛል።”
በመረበሹስ ላይ ታማኝ በየነም አለበት። አባቴና ልጄ በሚባባሉት ታማኛና ሙሉጌታ ሉሌ መካከል ከ1988 ጀምሮ የሰነበተ ፍቅር መኖሩን ታማኝ ተናገሯል። እንዲያውም ያኔ ጋሽ ሙሉጌታን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁበት ነው እንጂ በጽሑፍ ከረታኝ ቆይቷል። ጋሽ ሙሉጌታን በጦቢያው ፀጋዬ ገ/መድህን ነው ይበልጥ የማውቀው። ከዚያም ውጭ አንባቢነቱን ስለማውቅና አክብሮትና ፍቅሬም ገደብ ስላልነበረው እሱን የምተዋወቅበትን ቀን እናፍቅ ነበር። መጽሐፍ እጅግ እንደሚወድ እስማ ስለነበር አንድ ቀን በዚያውም ትንሽ ፈገግ አደርገው እንደሁ ብዬ ከለንደን ጠረጴዛ የሚያክል ግዙፍ መጽሐፍ ይዤለት ወደ ኢትዮጵያ ቤቱ ድረስ ልጠይቀው ሄድኩ። ጊዜው የአድዋ በዓልም አካባቢና ጋሽ ሙሉጌታ በግጭቱ ጉዳት ደርሶበት የነበረበት እለት ነበር። እና ገና ከመነሻው ሳውቀው ተጎድቶ ነው። ከዚያ በኋላ ይበልጥ ያየሁትና የተዋወቅሁት ደግሞ እዚህ ነው። እዚህም በደህና ነገር ሳይሆን የአባቴን ሞት ሊያረዳኝ ቤቴ ድረስ መጥቶ ነው ያወቅኹት። እና ከዚያ በብዙ እየተቀራረብን መጣን። “የሚቆጣኝ ይህን በል ያን አትበል” የሚለኝ ሰው ነበር። “ይሄን ደግሞ በየወቅቱ እየወጣህ እኔ ትንሽ ሰው ነኝ የምትለውን ነገር ተው!” ይለኛል።
ደግሞ ሌላ ጊዜ በማደርገው ነገር ሰዳቢዎቼ በዝተው በጣም ሳዝን ይመጣብኛል። በተለይ በአንድ ወቅት የተናገረኝ ነገር መቼም አልዘነጋውም “ ስማ ታማኝ አንድ የፈረንሳይ ፈላስፋ ምን ይል ነበረ መሰለህ፣ “ሐውልቴ የሚሠራው ጠላቶቼ ከሚወረውሩብኝ ድንጋይ ብዛት ነው” ካለ በኋላ… እና ግን ምን ያደርጋል ጋሽ ሙሉጌታ ቀርቶብናል…. ብሏል።
ታማኝ የሚያዝነው በሁለት ነገር ነው። አንድም ጋሽ ሙሉጌታ ስለራሱ መጽሐፍ ሳይጽፍ በመሄዱ እና ትልቁና ዋነኛው ደግሞ ለአገሩ አፈር ሊበቃ አለመቻሉ ነው። ምክንያቱም ጋሽ ሙሉጌታ ስለአገሩ የነበረውን ፍቅርና ተመልሶ የማየት ጉጉት ያውቃል። ጋሽ ሙሉጌታን ለመጨረሻ ጊዜ የተሰናበተው ኢሳት ቢሮ ውስጥ አቀርቅሮ ሲጽፍ ነበር። ሁሌም “ማንበብ ምን ያደርጋል? ቁምነገሩ መጻፍ ነው እያለ..” የቀልዱን ያበሽቀው እንደ ነበር ይታወቃል።
ጋሽ ሙሉጌታ ከአገር ከወጣ በኋላ ለተወሰነ ጊዜ ጦቢያን ከዚያም የልሳነ ሕዝብን መጽሔት ላይ ተሳትፎውን የቀጠለ ቢሆንም ሁሉቱም እንዲቆሙ በመደረጋቸው ለተወሰነ ጊዜ የጽሑፍ አምሮቱን አምቆ ቆይቷል። አልፎ አልፎ በየዌብሳይቶቹ ላይ ቢጽፍም አያረካውም።
ወደ ኋላው ላይ ከአገር ወዳድ ወዳጆቹና ታማኝንም ጨምሮ ከተወሰኑ ጋዜጠኞች ጋር የጀመረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኔትዎርክ (ኢቲኤን) ከህልሙ የቻለውን ያህልም ቢሆን ፈጽሞ አልፎአል። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኔትዎርክ (ኢቴ ኤን) ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በመስራችነት ጭምር የሠራባት ያቺ ጊዜ ለብዙዎች ጋሽ ሙሉጌታ ጽሑፍ ሳይሆን፣ ከጽሑፍም በላይ የሚወደድ ሰብዕናው የተነበበት አጋጣሚ ነበረች።
አቶ ሙሉጌታ ከኢ.ቲ.ኤን ቀጥሎ ንቁ ተሳትፎ ያደርግበት በነበረው ኢሳት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ላይ ጭምር የሥራ ግንኙነት ያለው አቶ ነዓምን ዘለቀም ስለ አቶ ሙሉጌታ ተናግሯል።
አቶ ሙሉጌታ ከልጅነት እስከ አዋቂነት ድረስ በንባብ የማውቀው ቢሆንም በተለይም ላለፉት 18 ዓመታት አሜሪካ ከመጣ ጀምሮ እንደ አባት ወንድም መካሪና ጥሩ ወዳጄም ነበር። ኢትዮጵያን በልዩ ሁኔታ ከሚያፈቅሯትም ልዩ ሰዎች እንደ አንዱ አድርጌ የማየው ሰው ነው። ታላላቅ ሰዎች ቢያልፉም ሥራዎቻቸው አያልፍም እንደሚባለው የጋሽ ሙሉጌታ ሥራዎች የሚያልፉ አለመሆናቸው የሚያጽናና ነው። ወጣቶቹን የኢሳት ጋዜጠኞችን በአርአያነትና በሙያ በመግራት ያደረገው አስተዋጽኦም ቀላል የሚባል አይደለም። እንደ ኢሳት ባልደረባ በትንታኔዎቹ ኢንሳይክሎፒዲክ በሆነ እውቀቱ ሚሊዮኖቹን አስተምሯል። ብሏል።
ከቅርብ ወዳጆቹና የሥራ ባልደረቦቹም መካከል አንዷ የሆነችው አርቲስት ዓለም ፀሐይ ወዳጆም ጧት ጧት ሁሌም ወደ ሥራው ስትገባ አቀርቅሮ እንደምታገኘው ተናግራለች። ጋሽ ሙሉጌታ ሁሌም አጎንብሶ ወይ ሲያነብ ወይ ሲጽፍ ነው የማየው ብላለች። እንደሱ ያለመታከት ሲያነብ የኖረ ሰው አይቼ አላውቅም። ያም በመሆኑ ይመስለኛል የኢንፎርሜሽን ባህር የሆነልን። አንድ ጊዜ በአንድ ፕሮጀክት ስለ አፄ ዮሐንስ ሲያነብ ተመልክቼው ነበር። ሌላ ጊዜም እንደገና ሳየው አሁንም ሌላ ጊዜ ስለ አጼ ዮሐንስ ሲያነብ አየሁና፣ “እንዴ ይህን መጽሐፍ እስካሁን አልጨረስከውም እንዴ? ስለው አይይ ይህኛው ደግሞ ሌላ ነው- ሲለኝ ገረመኝ እንደ ብዙዎቻችን አንድ መጽሐፍ አንብቦ ሰለሷ ብቻ የሚያወራ አይደለም አይበቃውም።
ጋሽ ሙሉጌታ ምንም ነገር ቢጠቀስ ወይ እዚያ ነገር ውስጥ አለበት ወይም ስለሆነው ነገር ያነበበው ነገር አለ። ወይ ይኖርበታል ወይ አንብቦታል። ይህን ሰው እንዴት እናጣዋለን?
ጋሽ ሙሉጌታ ስሙ እንደተራራ የገዘፈ ቢሆንም በኑሮው የተመቸው አልነበረም። በስደት ሕይወቱ ከተለያዩ አገራት የሚመጡትን እንግዶችን ሲያስተናግድ ሲያበላ ሲያጠጣ መመልከቱ የሚያሳዝነኝ ህይወቱ ነበር። በዚያ ላይ በስደት ዓለም ለማይገባው ሰው ይገባዋል ብሎ ሲደክም የሚውለው ውሎ ሁሌም ያሳዝነኛል ብላለች።
ጋሽ ሙሉጌታ ከ1ሺ500 በላይ የሚደርሱትን አብዛኞቹን የመ/ቤቱ ሠራተኞች ስልክ ቁጥር በቃሉ ሲያውቅ ስመለከት አንድ ነገር የመያዝ ችሎታው ከኛ ጋር የማይመጣጠን ልዩ ፍጡር ያስመስለዋል ብላለች።
አቶ ከበደ አኒሳ ለአዲስ ኦብዘርቨር እንደተናገሩት “ሙሉጌታ የትውልድ ጋዜጠኛ ነው።” ከ-የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት መመሪያ ኃላፊ የነበሩት መርዕድ በቀለም የአቶ ሙሉጌታሞት “አገሪቱ ትልቅ ሰው ያጣችበት” ብለዋል።
ከፀጋዬ ገ/መድኅን አርአያ
“የፖለቲካውን ፋሽን” ሳልፈራ ሁለት የተከበሩ ዜጐች መኖሪያ ቤት ሄድሁ። አንደኛው ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ ነበሩ። ሁለተኛው ደግሞ ቢተወደድ ዘውዴ ገብረ ሕይወት ሲሆኑ ከጠላት በፊት ጀምሮ በአስተማሪነት፣ በዲፕሎማሲና በአገር አመራር ሰፊ ልምድና እውቅት ያካበቱ አባት ነበሩ። ሁለቱንም በተለያዩ ጊዜያት ቀጠሮ ይዤ አነጋገርኳቸው። ያን ጊዜ በአርሲ፣ በሐረርጌ፣ ዲማ የሚባል ሰብአዊ ፍጡር አማራ እያባረረ ይገድላል፤ በሐረርጌ በአሰቦት ነፍጠኛ ሁሉ እየተረሸነ ነው የሚባልበት ጊዜ ነበር። ያንን ደግሞ የሚያራግቡ፣ ትልልቁንና በጀግንነቱ የሚታወቀውን ኦሮሞ ጄኔራልና ራስ ሳይቀር በዘላን ቋንቋ የሚዘልፉ ጋዜጦች ወጣ ወጣ ማለት የጀመሩበት ነበር። ይኸ አካሄድ ለቢትወደድም ለኮሎኔል ዓለሙም አልጣማቸውም ነበርና ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በማሰብ በሰፊው ተወያየንበት። ሁለቱንም ጐምቱ ዜጐች ገጽ ለገጽ ማገናኘት አልቻልሁም። ዓላማችን ግን ኮሎኔሉ በኦሮሞ አባትነት፣ ቢተወደድ ደግሞ በአማራ አባትነት አደባባይ ወጥተው “ሕዝቡን ለማጫረስ የተጠነሰሰውን ሴራ በሚያጋልጥ መልክ እንዲያወግዙ ነበር። ሁለቱም የሚወክሉትን ኅብረተሰብ ባሕልና ሥርዓት ስለሚያውቁ ተቃቅፈው ፍቅራቸውን በመግለጥ፣ የሁለቱንም ታሪክና የደም ትስስር በማብራራት እያሳሰበ የመጣውን የፖለቲካ ደመና እንዲያከሽፉት ለመሞከር ነበር። በሦስተኛው ቀን ኰሎኔል ዓለሙ “ሁሉም ነገር ጥሩ ነበር። ትናንትና ከበቀለ ነዲ ጋር ስንነጋገርበት ከእኛ መካከል ወደ እብደት የወሰዳቸው አክራሪዎችን ይጠንቀቁ። እዚሁ አጠገባችን ያለውን..ሰው ይህን ቢያዋዩት ሊገድልዎ ይችላል። አላወቁትም መሰለኝ እንጂ አለኝ” አሉ። በዚህ የተነሣ ፕሮጀክቴ ወደቀ። እኔም አሜሪካ ከሚሉት አገር ገባሁ። ከአንድ የብስጭትና የጭንቅ መንፈስ፣ ከአንድ ማንም ያለመልሰልኝ ጥያቄ ጋር ቀረሁ። እንዲህ ያለውን ጭካኔና ጥላቻ ከቶ ከየት አመጡት? የተወሰኑ ባለስልጣኖች ልትጠላ ትችላለህ። አገር ሙሉ ሕዝብ- ግዑዝዋ አገር..እንዴት የጥላቻ ዒላማና የእልቂት ሰላባ ይሆናሉ? ለመሆኑ እነዚህ ዛሬ በወያኔ ገፋፊነት ከፍልፈል ዋሻ ወጥተው የሚጫጩት ትንንሽ ነፍሳት መጫረስና መፋጨት ለሕዝብ አንዳች መፍትሔ ይሰጣል ብለው እንዴት ሊያስቡ ቻሉ? ወይስ አጀንዳቸውንና የወደፊት ጉዞአቸውን ለምን በግልጽ አይነግሩንም?
የኢትዮጵያ ድምጽ፣ ኢትዮጵያ (አስመራ) ፣ አዲስ ዘመን፣ ኢትዮጵያን ሄራልድ፣
የዛሬዪቱ፣ መነን፣ የካቲት፣ ጦቢያ፣ ልሳነ ሕዝብና የመሳሰሉት የህትመት ውጤቶች አቶ ሙሉጌታ አሻራውን የተወባቸው ያነጻቸው የታነጸባቸው ናቸው። የምስራች ድምጽ፣ ዓለም አቀፍና ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኔትዎርክ (ኢቲኤን) በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ (ኢሳት) ጋሽ ሙሉጌታ የታየባቸው መስታውቶቹ ናቸው። በ1984 አጥፍቶ መጥፋት የሚል መጽሐፍም አሳትሟል።
እንግዲህ እሱ አቶ ጋሽ ሙሉጌታ ሉሌ ነው። ታላላቅ ስሞች እንኳ ቀድመውና ተሽቀዳድመው የሚያነሱት ትልቅ ስም ነው። ድንኮች ተንጠራርተው ያልደረሱበት፣ ጊዜ በሰጣቸው የቅል ዘመንተኞች ያልተደረመሰ የአለት ቋጥኝ ነበር። እንደ አባቶቹ ጦር ጎራዴ ጠላቶቹን በሰላ ብዕሩ ቃላት እየመዘዘ የሚያደባይ፣ ስዶችን በስድ ንባብ እየተቀኘ ልክ ማስገባት የሚችል ጀግና ነበር። ቃልና አንደበት ለቸገረው እየደረሰ የተበደለና የተገፋን አንጀት እንዳራሰ የኖረ የቀለም አንበሳ ነበር።
ብዙዎች እንደተስማሙበት አቶም ጋሼም የሆነው ሙሉጌታ ሉሌ ታሪክና ሁነትን በሰዓታትና ደቂቃዎች ቆጥሮ ማስረከብ የሚችል አዋቂ ነው። ያውቃል። በተፈለገው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለመናገር ተቀባብሎ የተቀመጠ መዝገብ ነው። ማንበብና መጻፍ ብቻ እንደሚችሉት ምሁራን ማንበብና መጻፍ ብቻ ይችላል የሚባል ሰው አይደለም። አገር አንብቦ አገር የሚጽፍ ታሪክ አብልቶ የሚያጠጣ የእውቀት ገበታና ማዕድ ነበር።
እንደ ጽሑፉ አለባበስና ነገረ ሥራውም ሽክ ያለና ወግ ያለው ነው። የተቆጠበ ጨዋ ዝግ ብሎ የሚናገር እዚህም እዚያም ጥልቅ የማይል የጋዜጠኝነትን መስመር አልፎ ያልሄደ አውቃለሁ አውቅላችኋለሁ የማይል፣ በተሰመረ የሙያ መስመር መጓዝ የሚችል ታላቅ ሰው ነበር። ከሚገባው በላይ ያነበበ ውጥንቅጡን ዓለም መልክ አስይዞ የተገነዘበ በሳል የፖለቲካ ሰው ነበር። ከሁሉም በላይ ደግሞ ቀርበው ላወቅቱ ገርና መልካም ሰው!
በቅርብ ቤተስቦቹ ላሉዬ በሚል የቁልምጫ ስም የሚታወቀው አቶ ሙሉጌታ፣ የአቶ ዮሐንስ ሙሉጌታ፣ አቶ ሉሌ ሙሉጌታ፣ የወ/ሮ ኤዶም ሙሉጌታ፣ እና የወ/ ት ሄርሜላ ሙሉጌታ አባት እና የ6 የልጅ ልጆች አያት ነው። እምንወዳት ህይወቱ እስካለፈችበት መስከረም 23 ቀን 2008 ድረስ በአሜሪካው የቨርጅኒያ ግዛት ከ 19 ዓመታት በላይ ኖሯል። በ75 ዓመቱ አንቀላፍቷል። ነፍስ ይማርልን!

ትንታግ ብዕር ነጠፈ!! (አስፋ ጫቦ)

$
0
0

Corpus Christi, Texas, USA
ወንድሜ፤ጓደኛዬ ፤ሙሉጌታ ሉሌ ተለየን! የቀበሩ ስነስርአት መስከረም 27,2008 (October 8,2015) እስክንድሪያ ፤ቨርጂኒያ፤አሜሪካ(Alexandria,Verginia,USA) ተፈጽሟል። የግዴን በሰዉ አገር ሟቾች ሙሾ አዉራጅ ሆንኩኝ።
12079462_10207730786858323_218579523484827242_n
ሌላው ወንድሜ፤ሻለቃ ፍስሀ ገዳ ከጥቂት ወራቶች በፊት አርፎ ሙሾ አውርጀ ነበር። ይኸኛው የሙሉ ሙሾ መሆኑ ነው።የሙሉጌታ ነገር እንዲያ የኢትዮጵያን ፍቅር በግጥም ጭመር ሲዘምርላት ኖሮ “እንደወጣ ቀረ!” የሆነውን ሰአሊውን ገብረ ክርስቶስ ደስታንና ሌሎችንም አስታወሰኝ
ሙሉ ማረፉን ወንድሜ ሻለቃ ግርማ ይልማ ከሲያትል፤ዋሽንግቶን(Seattle,Washington) ደውሎ አረዳኝ።አለም ፀሐይ ወዳጆ ከዋሺንግቶን ዲ፤ሲ (Washington,D.C)ደውላ እንዳረዳችው ነገረኝ።ግርማ ፤ሙሉጌታን፤እንደጋዜጠኝነቱ ብቻ ሳይሆን የማስታወቂያ ሚኒስቴር የነበረ ጊዜ አለቃዉ፣ እዚህም በስልክ ጭምር የገኘው ነበር። አለም ፀሐይንም በሌላው ዝናዋ ብቻ ሳይሆን ባህል ሚኒስቴር የነበር ጊዜ አለቃዋ የነበረ ይመስለኛናል። የአለምን ስልክ ሰጥቶጦኝ ደውልኩላት።
አለም ፀሐይ ገና ስላምታ ሳንለዋወጥ እሪታዋን ለቀቀችው። ያለፈ ስንትስ አመታት ዲ፤ሲአካባቢ ኗሪ ብቻ ሳይሆን ጓደኞች እንደሆኑ ለማወቅ እድል ገጥሞኝ ነበር።ለካስ እዚያ ሙሉጌታ ቤት ነበረች።አንድ አምስት ደቂቃ ያክል እንደተላቀስን የለችበትን ቤት እሪታ፤ኡኡታ እንደወረሰው፤እንደተረከበው ስልኩ ነገርኝ። አለምም ስልኩን ጣጥላ ተቀላቀለችበት።በስንት አመት የኢትዮጵያን ለቅሱ በድምጽም በመንፈስም ተካፈልኩ።ለአንድ አስራ አም ስት ደቂቃ ያክል ተካፋይ ከሆንኩ በኋላ፤አለምም ወደስልኩ ስለአለተመለሰች ዘግቼ ው ወደየግል ሐዘኔ ወረድኩ።
ሙሉን የማውቀው ድሮ-ድሮ ሳይሆን የጥንት-ጥንት መስሎ ይታየኛል።ያ የጥንት-ጥንት ደግሞ በመንፈሴ ትላንትናና ዛሬን መስሎ ይታየኛል። መሀል 1950ዎቹ ነበር የተዋወቅነዉ።ሙሉጌታ ያኔ የሚሰራው የምሥራች ድምጽ ራዲዮ ጣቢያ ነበር።ለግኑኝነታችን ዋናው ሰበቡ ሁለታችንም ለአማርኛ ጋዘዜጦች በተለይም ለአዲስ ዘመን እንጽፍ ስለነበረ ነው።አራት ኪሎ፤ወይ ጳውሎስ ኞኞ ወይም ብርሐኑ ዘሪይሁን፤የአዲስ ዘመን ምክትልና ዋና አዝጋጆች ቢሮ ይመስለኛል።”ለምን የምስራች ራዲዮ ጣቢያ መጥተህ ስራ አትጠይቅም?” አለኝና ሔጄ አንድ ፈረንጅ ቃለ መጠይቅ አድሮጎ አልጣምኩትም መስለኝ ሳይሆን ቀረ። የሙሉጌታ ወንድምነት፤ጓደኝነት ጸንቶ እስከ እለት ሞቱ ኖረ። ለመጨረሻ ጊዜ በስልክ ያነጋገርኩት ከመጨረሻው ቀን አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ነበር። የስልክ ወሬያችን የሚቋረጠው ወይ ባትሪው ሲሞት ወይ ሌላ አጣዳፊ ጉዳይ ሲመጣ ነበር።
አቶ ብርሐኑ ዘሪሁንና ጳውሎስ ኞኞ ሁለታችንም ወደማስታወቂያ ሚኒስቴር ተዛውረን እንድንስራ ሀሳብ አቀርቡ። ተስማማንበትና ለየመስሪያ ቤቶቻችን ደብዳቤ ተጻፈ።እኔ የምሰራው ሲቪል አቪየሸን ነበር። በጥያቄውና ደባዳቤው መሠረት ሙሉጌታ ወደማስታወቂያ ሚኒስቴር፤አዲስ ዘመን፣ ተዛዉሮ ስራውን ቀጠለ። እኔ፤በዚያው አመት ዩኒቨርስቲው ስለተቀበለኝና መማርም የምፈልገው ማታ ማታ እየሰረሁ ስለነበር ጋዜጠኝነቱ አመለጠኝ።ከሙሉጌታ ጋር ግን ወዳጅነታችን ቀጠለ።
አድሮ ዉሉ ጓደኝነታችን አዲስ ዘርፍም ከፈተ።ሲመሻሽ ባንኮኒ ላይ ቢያንስ በሳምንት አንድ ሁለቴ መገናኘት የተለመደ ሆነ።በወቅቱ ከሙሉጌታ ሌላ የባንኮኒ ላይ ጓደኛችን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጠኛ መርስኤ ሐዘን አበበ ነበር።ከመርስኤን ሙሉጌታና ጋር ባንኮኒ ላይ ማምሸት ለኔ ትምህርት ቤት ነበር።ሁለቱ እየተቀባበሉ የሚፈጥሩት ራሱን የቻለ ሌላ አለም ነበር።
መርስኤ ከሁለታችንም የላቀ፣ ጠለቅና ዘለቅ ያለ የቤተ ክህነት ትምህርት የነበረው ሰው ነበር። ጫወታም አዋቂ ነበር።ይህ የቤተ ክህነት እወቀት፤ዘመናይ ትምህርትና ጫወታ አዋቂነት ባንድ ሰው ላይ ሠምረው አምረው ሲገኙ የሚፈጥረውን ለዛ ሊያዉቁ የሚችሉ አጋጣሚውን ያገኙኑና የሚያውቁ ብቻ ይመስለኛል። አንድምታ፣ ሰምንና ወርቅ፤ቅኔም ጣል ጣል ይደርግበታል።
ሙሉጌታ ከሁለታችንም፤ምናልባትም እኔ ከማውቃቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች ለየት ያለ የአጨዋወት ዘይቤ ነበረው።ባንኮኒ ላይ ሆነ ከዚያ ባሻገር! ሌላው ባሕርዩ፤ሙሉጌታ የተዋጣለት አንባቢ ነበር። ራሴን አንባቢ ነኝ እያልኩ አኩራራለሁ። ከሙሉጌታ ሉሌ ጋር ግን በምኑም የሚመጥን አይመስለኝም።ሙሉጌታ ከንባቡ ያካበተው ግና የራሱ ንብረት(Internalize) ያደርገውን ጣል ጣል ሲደርገው ለጫወታው ጌጥና ፍርጥ ይሆናሉ።ይህም የሚጎንጩትን ወደ አናት ሳይሆን መዝናናኛና ጫወታ አድማቂ ያደርገዋል።ሌላው የባንኮኒ ተደርዳሪም የራሱን ጫወታ ይተውና ቀስ በቀስ ወደኛው ይጠጋል።ባለቡና ቤቶቹም ይወዱናል ይመስለኛል። ገበያቸውን ያደራለና!!ክፋቱ ጊዜይሮጣል!ስይታወቅ ወደእኩለ ሌሊትነት ይቀየራል!!
ሁለተኛው የሙሉጌታ ባህርይ አንዴ ማእከላዊ ወዳጄ ዘገየ አስፋው የነገረኝን አስታወሰኝ። ዘገየን፤የመሬት ይዞታ ሚኒስቴር የነበሩ አለቃው ስለዘመናይ ምሁራን ያሉትን ነበር የነገረኝ። “እናነተ የዘመኑ ወጣቶች የኢትዮጵያ እውቀታችህ ከመጽሐፍ ብቻ የተጠና ነው። ስለዚህም ኢትዮጵያን በሙሉ አታውቋትም። ስለኢትዮጵያ ለማወቅ በየለቅሶው፤በየእድሩ፤በየተዝካሩና ክርስትናው፤ በየሰርጉ መገኘት አስፈላጊ ነው። የውስጥ ታሪኳ የሚወራው፤ማን ማንን አገባ፤ፈታ? ለምን አገባ፣ ፈታ? የሚለው ያለው እዚያ ነው” ብለዋል ነው ያለኝ። ሙሉጌታ ያለተጻፈውን ፤ወይም ተጽፎ፤ተንቆ ያልተነበበውን የኢትዮጵያ ታሪክ ያውቃል።
ራሱ ከነገረኝ በመነሳት ለማስርዳት ልሞክር። ለምሳሌ የንጉሱን ዘመን ራስ መስፍን ስለሺን ፊድዋል፣ የመሬት ከበርቴ ብቻ ብለን ነው የምናወቀው።ነበሩ!! ሙሉጌታ ግን ራስ መስፍን ኦሮሞ መሆናቸውን፤ የልጃቸው ስም ጃራ መሆኑ የአያታቸው ይሁን የቅድመ አያታቸው ስም መሆኑን፤ ባለቤታቸው ወይዘሮ የሽእመቤት ጉማ ኦሮሞ በመሆናቸው ልጆቻቸው ኦሮሞ መሆናቸውን ይነገረኛል። የነገርን አጥንቱን ብቻ ሳይሆን ጉልጥምቱንም ፤የሚያይዘውን ቅባቱንም ጭምር ያውቃል።
ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ይመስለኛል ስለኦሮሞ ነጻ አውጭ ድርጀት (ኦነግ))በስልክ ስንወያይ የራስ ጎበና ዳጨን ነገር አነሳብኝ።። ራስ ጎበና ምንሊክ ከተዎድሮስ እስር ቤት አምልጠው ሸዋ ሲገቦ ጦር አስለፎ የተቀበሉ መሆናቸውን፤ምንሊክ ንጉስ ሲሆኑ የመጀመሪያው ራስ ሁነው የተሾሙት ጎበና መሆናቸውን፤ ያም ከምንሊክ አጎት፤ከራስ ዳርጌ የሚቀድም መሆኑን ነገረኝ። ያታሪክን፤ወይም የወጉን ሙሉ ስእል(Big Picture) የመቅረጽ ባሕይርይ ነበረው።
ሙሉጌታ ሉሌ ከሶስት ይሁን አራት ምሁራን ጋር ሆኖ ደርግ ጽሕፈት ቤት በኢትዮጵያና በሱማሌ መካከል ያለውንና የነበረውን ግኑኝነት ያጠና ነበር። እኔም ቢሮዬ እዚያ ስለነበር አልፎ አልፎ አዲስዋ ካፌ አብረን ቡና እንጠጣ ነበር። የዛሬ ሶስት ወርረ ገደማ ፤እኔ የረሳሁትን፤እዚያው ካፌ ከደርጉ ምክትል ሊቀ መንበር ከነበሩት ከኮሎኔል አጥናፉ አባተት ጋር የተለዋወጥነውን ነገረኝ።” ጓድ ኮሎኔል፤ እገሌ (የደርግ አባል ስም ጠርቼ) ለመሆኑ ንጉሱ የዛሬ ስንት አመት ከስልጣናቸው መውርዳቸውን ስምቷል? አልኩኝ።ምነው ቢሉ “ይኸው ዛሬም ኃይለ ሥላሴ ይሙት!!” ይላል አልኩ። ሙሉጌታ እንደሚነገርኝ ነው።ይህንን ማለቴን አስታውሳለሁ። ለአጥናፉ መሆኑን እሱ እስከሚነገርኝ ድረስ ረስቸው ነበር። “አንተ የት ነበርክ “ስለዉ “አላየኸኝምእንጅእዚያዉነበርኩ”አለኝ።ሙሉጌታ የሰማውን ቋጥሮ አስቀምጦ ወቅቱን እንዲጠብቅ የሚያደርግ ታላቅ መዝገብ ቤት ነበር ።ይህንኑ፤ “ የደርግ ጓደኝኞች ነበሩት “ ብሎ እንደክስና ውቅስ Ethio American News አቀረበበት።” የአዋጁን በጆር!” እንደማለት ይመስለኛል። አብሮ ይስራ ነበርኮ!!በዚህም ላይ የንጉሱም ይሁን የደርግ የሙሉጌታ ሉሌ ወዳጅ የነበሩ ብዙ ባለስልጣናት አውቃለሁ። ሙሉጌታ ሉሌ አድማሱም ግኑኝነቱም ሰፋ ያለ ነበር።
ይህን “ሙሉጌታ ሉሌ በበዓሉ ግዳይ ውስጥ እጁ አለበት” የሚለውን የፈጠራ (Conspiracy Theory)ወሬ መስማት ብቻ ሳይሆን በድህረ ገጾች ላይ ተጽፎ አንብቤ “ምነው መልስ ብትሰጥ?” ብየው መልስም ሰጥቶጦ ነበር። መልሱ፤ አንድ ጎንደሬ ደጃዝማች ብለዋል የሚባል ጠቅሶ “ለመሆኑ ማነው የላከህ? ከአለቃው ጋር እንጅ ከተላላኪው ጋር አፍ አልካፍትም “የሚል ነበር። እንደጠበኩትም የሙሉጌታ አመላለስ ነበር!! ያም ሁኖ አይጋና Ethio American News የሚባሉ ድሕረገጾች የሙሉጌታን እረፍት ምክንያት በማድረግ ያንኑ (Recycle ) የደጋግሙታል።”ለመሆኑ ማነው የላከህ?” የሚለውን የሙሉጌታ ሉሌን መልስና የወዳጄን የፍስሐ ደስታን መጽሐፍ ቢያነቡ መዝገባቸውን ይዘጉት ነበር።
ፍስሀ ደስታ (ሌ/ ኮሎኔል)የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክርሳዊ ሪፑብሊክ ም/ፕሬዚዳንት “አብዮቱና ትዝታዬ” በሚለው መጽሐፉ ገጽ 442 ስለበዓሉ ግርማ አማሟት እስር ቤት የድህንነት ሚንስቴር ከነበረው ከኮሎኔል ተስፋዬ ጋር ያደረገውን ውይይት እንደሚከተለው አስፍሮታል፤
ከደርግ ውድቀት በኋላ በእስር ላይ እያለን ፤”በዓሉ ለምን እርምጃ ተወሰደበት?” በማለት ተስፋዬን ጠጥየቅኩት።እሱም” መጽሐፉ ከወጣ ከጥቂት ወራት በኋላ ሻአቢያ በራዲዮ
ጣቢያው በማስተላለፍ በሠራዊቱ ላይ ለከፍተኛ ቅስቀሳና ፕሮፖጋንዳ ይጠቀምበት ጀመር።በዚህ ምክንያትም የፖለቲካ፤የደህንነት ሠራተኞችና አዛዦች ከፍተኛ እሮሮና ተቃውሞ ስለ አስሙ በተለይ በ አመራሩ ላይ ቅሬታቸውን ስለገለጹ ነው”የሚልና መገደሉን የሚያረጋግጥ መልስ ሰጠኝ።
ሙሉጌታ ሉሌን በአይነ ስጋ አግንቸው የተጨዋወትነው ከአስር አማታት በፊት ዋሺንግቶን ዲሲን ለመጎብኘት የሔድኩ ጊዜ ነበር። አለም ፀሐይ ወዳጆ፤ሙሉጌታና ካሳ ከበደ ራት ጋበዙኝ።ግሩም ራት ነበር። ከራቱ ይልቅ እኒህን ሶስቱን ባንድነት ማግኘት ለኔ ባለዞሆኑን ሎቶሪ እጣ እንደማገኘት ነበር። አለም ፀሐይን፤መላኩ አሻግሬ ማእከላዊ ይነገረኝ ከነበረው በስተቀር ይህንን ያክል አላውቃትም ነበር።መላኩ አንስቷት አይጠግብም ነበር። ካሳ ከበደ ከሙሉጌታ ጋር የሚጋራው የነገሮች አጥምት ጉልጥምት የማወቅ ስጦትም አለው። የተዘናና ፣የሚያረካ ምሽት ነበር። “በሩን ልንዘጋ ነውና ውጡለን!” ብለውን የወጣን ይመስለኛል።አድማጭ እንጅ እምብዛም ተናጋሪ እንዳልነበርኩ ይታወሰኛል።
ሙሉጌታ ሉሌ የተዋጣለት ጽሐፊ፤ተቺ፤ገምጋሚ ነበር። በስራው ባህርይ የተነሳ ኢትዮጵያን በአብዛኛው ዞሮ ያየ ሰው ነበር። የሚጽፈው የሚያውቀውን የሚያምነውን ነበር። እምነቱ ደግሞ መሠረት ፤ጥልቀት ካለው ባህር የሚቀዳ እንጅ ከድስት የሚጨለፍ አልነበርም። የእምነቱን፤ የጽሁፎችን ምንጮች ደግሞ “ዘከመ ይቤ እገሌና እግሌ!” ብሎ ማስረጃ ምንጭ ይጠቅሳል። ከሁሉም በላይ፤ሙሉ ሰው፤ዘመናይ ሰው፣ ዘመናይ ስልጡን (Cosmopolitan)ኢትዮጵያዊ ነበር። አጣናው!!
“የማይሞት ሰው ሞተ!!” ይባላል። አባባል ነው! ሰው ብቻ ሳይሆን ፍጥረት ሁሉ ይሞታል። የተካልክም!ተተኪው ዋንኛውን ላያክልም ሊበልጥም ይችላል። ሁላችንም ተፈጥሮ ያዘጋጅልን ባቡር ተስፋሪዎች ነን። መዉረጃ ጣቢያችንን ነው የማናውቀው። በስደት ባይሆን ጥሩ ነበር!!ያ ደግሞ የአገራችን አካልና አምሳል ፣ገላጭ ባህር ሆኗል! ዋናው ነገር እንዴት ሞተ መሆን ያለበት አይመስለኝም። “እንዴት ኖሮ ነበር!” ነው። ሙሉጌታ አንገቱ ቀና አድርጎ፤ያመነበትን በግልም በአደባባይም ተናግሮም ጽፎ ያለፈ ጀገና ነው። ። እኔ ብርቱ ወንድሜን፣ ወዳጀን አጣሁ! ኢትዮጵያ አንድ ተሟጋች ልጅዋን አጣች!ጥናቱን ይስጠን!
ለልጆቹ፤ለቤተሰቡ፤ዘመድ አዝማዱ ብርቱ መጽናናትን እመኛለሁ!!

ብልሹ አስተዳደርን የዴሞክራሲ ምህዳር በማስፋትና በተቋማት ግንባታ(ሜ/ጄ አበበ ተ/ሃይማኖት)

$
0
0

የአየር ኃይል አዛዥ የነበሩት እና የ1993ን የሕወሐት/ኢህአዴግ ክፍፍል ተከትሎ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለሀይማኖት በ”ሆርን አፌይርስ” ድረ ገጽ ባሰራጩት ጽሁፍ መንበረ ስልጣኑን በተቆናጠጠው ገዢ ፓርቲ ላይ ትችት አቀረቡ። በሕወሐት ልሳን “ወይን” መጽሔት ለቀረበባቸው ትችትና ክስ ምላሽ ሰጥተዋል።
ጄኔራሉ እንዲህ ብለዋል፦
” ባጠቃላይ ሲታይ ብዙ ማንነቶች፤ በርካታ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች፤መልስ እንሻለን የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ባሉበት አገር አንድ ግንባር (ኢህአዴግ) እና አጋሮቹ 100% መቀመጫውን መቆጣጠር እሚያሳየን ነገር፤አንድም ባጠቃላይ ፖለቲካዊ ስርዓቱ ላይ ችግር መኖሩን አልያም የምርጫ ስርዓቱ ችግር እንዳለበት ወይም ተግባራዊነት ላይ ችግር እንደነበረበት ነው፤ 100% እሚባል ውጤት አስቂኝ ግን ደግሞ አደገኛ ነው ፡፡ ይሄ ዉጤት አርቆ ለሚያስብ ሰው የአደጋ እንጂ የድል ምልክት ተደርጎ መቆጠር አይችልም። መሬት ላይ ያለዉን የተለያየ ፖለቲካዊ ፍላጎት እማያንፀባርቅ የምክር ቤት ሁኔታ የስጋት እንጂ የኩራት ምንጭ መሆን አይችልም።”
ሙሉውን ጽሁፍ ከ “ሆርን አፌይርስ” ወስደን አቅርበነዋል ይመልከቱ።
Photo-General-Abebe-Teklehaimanot-384x264
………………………………………………………………..
* በዴሞክራታይዜሽን እና ኢ-ዴሞክራታይዜሽን ሂደቶች ሁሌም መሳሳብ እና ዉጥረት ይኖራል። መንግስት እንደ መንግስት ግን የዴሞክራታይዜሽን አጋዥ አልያም የኢ-ዴሞክራታይዜሽን አሳላጭ ነው መሆን እሚችለው፤ መሀል ላይ የሚንገዋለል መንግስታዊና ተቛማዊ አቛም ሊኖር አይችልም።

* ባጠቃላይ ሲታይ ብዙ ማንነቶች፤ በርካታ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች፤መልስ እንሻለን የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ባሉበት አገር አንድ ግንባር (ኢህአዴግ) እና አጋሮቹ 100% መቀመጫውን መቆጣጠር እሚያሳየን ነገር፤አንድም ባጠቃላይ ፖለቲካዊ ስርዓቱ ላይ ችግር መኖሩን አልያም የምርጫ ስርዓቱ ችግር እንዳለበት ወይም ተግባራዊነት ላይ ችግር እንደነበረበት ነው፤ 100% እሚባል ውጤት አስቂኝ ግን ደግሞ አደገኛ ነው ፡፡ ይሄ ዉጤት አርቆ ለሚያስብ ሰው የአደጋ እንጂ የድል ምልክት ተደርጎ መቆጠር አይችልም። መሬት ላይ ያለዉን የተለያየ ፖለቲካዊ ፍላጎት እማያንፀባርቅ የምክር ቤት ሁኔታ የስጋት እንጂ የኩራት ምንጭ መሆን አይችልም።

* ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩ በጠበበ ቁጥር የዜጎች ተስፋ እተሟጠጠ ስጋታቸው እና ፍርሃታቸው እየጨመረ ከቁጥጥር ውጪ የመሆኑ እድል ይሰፋል፡፡ ይህን መሰል ሁኔታም ከውስጥም ከውጪም ለነሱ ለሚችሉ ፅንፈኛ ሃይሎች ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥር አገሪትዋን ወደላስፈላጊ መንገድ ሊመራ ይችላል፡፡ ፍትህ ተራ ፍርድ የማግኘት ጉዳይ አይደለም፡፡ ፍትህ የማህበራዊ ተቛም የመጀመርያ ፀጋው ነው ይላል ጆን ራዉልስ፡፡ ሙስናና መልካም ያልሆነ አስተዳደርም ሃገርን ሊበትን የሚችል፤እየታየ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እድገት ገደል የመክተት አቅም ያላቸው ስርዓታዊ በሽታዎች ናቸው፡፡የሶስቱም እናት ደግሞ የጠበበ ወይም የኮሰመነ የዲሞክራሲ ምህዳር ነው፡፡

* ከባዱ ስራ ግን ቀጥሎ መከሰት ያለበት እርምጃ ላይ ነው፤ከባድ እና ውስብስብ እሚሆነብት ምክኒያትም ትግሉ ከሞላ ጎደል ግልፅ ከሆነ ዉጫዊ ሃይል ወይም ተቛም ጋር ሳይሆን ከገዢው ፓርቲና መንግስታዊ መዋቅር ይዘው ከሚገኙ አመራር እና የነሱ ተባባሪዎች ጋር መሆኑ ነው።

* በተለይ ከ 10ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ማግስት በአንድ በኩል የመቀዛቀዝ በሌላ በኩል ደግሞ ችግሮች ቢኖሩም ብዙ እሚያስጨንቁ አይደሉም የማለት እና የማጣጣል አዝማምያዎች እየታዩ ነው። ጠቅላይ ሚንስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ምክርቤቶችን አስመልክተው፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ደመቀም ሚድያን አስመልክተው የተናገሩት ነገር ገምቢ እና አበረታች ቢሆንም ሌሎች የመንግስት አካላት ግን ችግሩ ቀለል አድርገው ሲመለከቱ እያየን ነው።

* ያገሪትዋን ከፍተኛ ስልጣን በህገ መንግስት የተረጋገጠለት ተቋም አሁን ያሉት አማራጮች ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው አማራጭ ህገ መንግስታዊ ስልጣኑን ተጠቅሞ የዜጎችን ጥቅም ማስከበር ሁለተኛው አማራጭ ህገ መንግስታዊ ስልጣኑን መጠቀም እማይቻል እና የህዝባችን አደራ መሸከም ካልቻለ ያገሪትዋን ሃብት ያላግባብ ከሚባክን ህዝበ ውሳኔ አዘጋጅቶ አይረቤነቱን ህጋዊ ድጋፍ ሰጥቶ ተቋሙን ማፍረስ፡፡

* [ወይን መፅሄት በ ሃምሳኛ እትሙ] የትግራይ ህዝብ እየለበለበው ያለዉን የብልሹ አስተዳደር ችግር እያለ እንደ ድሮ መሳፍንት ‘ራስ እገሌ ከ እገሌ ይበልጣል’ ዓይነት ፅሁፍ ይዞ መዉጣቱ በጣም የሚያሳፍር ነው። መወየን ተራማጅነትን የሚገልፅ ቢሆንም እየተደረገ ያለው ግን የ አድሃርያን ተግባር ነው፤ ወያነነቱም የት ሄደ? ያስብላል። ለመሆኑ ወይን በስራ ላይ ካሉት ኢታማዦር ሹም ምን ቢፈልግ ነው የህዝቡን ድምፅ ማሰማት ሲገባው ወደ ወረደ መሳርያነት ራሱን ያሸጋገረው? ፖለቲካዊ ዘመቻም ከሆነ ጡረታ ሲወጡ ያደርግላቸዋል። ሁለቱም ኢታማዦር ሹሞች የየራሳቸው እና የጋራ የሚያኮራ ታሪክ እያላቸው የ ‘አንዱ ይበልጣል’ ንፅፅር ምን አመጣው?

* ወይን መፅሄት “አብ መከላኸሊ ሓይሊ እዉን ክግበር ዝኽእል ዘይሕጋዊ መማረፂታት እንተልዩ ምሕሳብን ምፍታንን ጀሚሮም” ይላል። ትርጉም “በመከላከያ ሃይል ዉስጥም ማድረግ እሚቻል ህጋዊ ያልሆነ አማራጭ ካለ ብለው ማሳብና መሞከር ጀመሩ” ይላል። ለሌተናል ጄኔራል ፃድቃን እና እኔ ባለፉት ወራት አንዳንድ ከትጥቅ ትግሉ ጋር የተያያዘ የምናውቀዉን ፅፈን ነበር፤ ሰው ሊስማማ ላይስማማ ይችላል። የሚገርመው ግን ወይን ወይም ስፖንሰሮቹ “ህገ ወጥ ድርጊት በማስብ እና በመሞከር” ብለው ለማስፈራራት የሞከሩት ነገር ነው። ከአስራ አምስት ዓመት በኃላ ይህ ማስፈራርያ ለምን መጣ? አርፋቹህ ተቀመጡ ለማለት ነው? ወይንና ‘እማይታወቀው’ መሐመድ በወቅቱ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ (ነብሳቸው ይማርልን) እያወቁ “ምህረት” አድርገዋል፤ አሁን ግን የሚምራቹህ ሰው የለም እያሉን ይሆን እንዴ ?

* ጠንካራ የሃገር መከላከያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን ዘበኛ ቢሆንም፤ ከልክ በላይ ካበጠ ግን የ ኢ-ዴሞክራስያዊ ሃይሎች መሳርያ ስለሚሆን በዚህ ረገድ የተሰማሩ ሙሁራን ወታሃደራዊ ክፍሉ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ወይ ቅልበሳ (democratization and de-democratization) ላይ የሚኖረዉን ሚና እንዲያጠኑት መንግስት ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት፤

* የህወሓት 40ኛ አመት በትግራይ ቴሌቪዥን የወራት ሙሉ ሽፋን እንዲሁም በኢቢሲ (EBC) ላቅ ያለ ሽፋን የተሰጠው የምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ትንፋሽ ለመተንፈስ እንኳ የማትበቃ ጥቂት ደቂቃ በተመደበላቸው የምርጫ ወቅት መሆኑ ስንገነዘብ ነው የመንግስትና የህዝብ የመገናኛ ብዙሃን ባህሪ እና ማንነት መረዳት እምንችለው፡፡ እስኪ ህወሓት በትግራይ ቴሌቪዥን እና EBC ላሰራጨው የወራት ፕሮግራም ክፍያ ፈፅመዋል? ቢፈፅምስ ይህ ተገቢ ተግባር ነውን?

* ይህ የተጠቀሰው ዶክመንት በገፅ 123 ላይም እንዲህ ይላል “መላውን ህዝብ /አብዛኛው ክፍል/ ለአመታት ለአንድ ፓርቲ አመለካከት በማጋለጥ፣ ሌሎችን በመከላከል የሚደረግ አሰራር መከተል በሃሳቦች መካከል ነፃ ውድድር እንዳይኖር የሚያደርግ ነው የሃይለስላሴና የደርግ መንግስታት ይህም ማድረጋቸው የሚያመላክተው ፀረ ዴሞክራስያዊ ባህርያቸው ነው” (ኢህአዴግ፣ 1992 ዓ.ም ገጽ 123) ።
ንዑሳን-ርዕሶች
1. መግቢያ
2.ችግሮቻችን ምንድን ናቸው? መልካም አስተዳደር የወቅቱ ቁልፍ ችግር
2.1 በአሁኑ ግዜ የችግሮቻችን አውራ መልካም አስተዳደር ያለማስፈን ችግር ነው ተብሏል፡፡ ለመሆኑ መልካም/ዴሞክራስያዊ አስተዳደር ምን ማለት ነው?
2.2.የመልካም/ ዴሞክራስያዊ አስተዳደር ችግሮች ስፋትና ጥልቀት
3. የችግሮቻችን መሰረታዊ ምንጭ ምንድን ነው?
4. በኢህአዴግ እሚመራው መንግስት የዴሞክራሲ ምህዳሩ በማስፋት መልካም አስተዳደርን ለምን አላረጋገጠም?
5. የመፍተሄ ሀሳቦች
5.1 ጠንካራ ተቛማዊ ስብእና (Strong Institutional Integrity)
5.2 ምክር ቤቶች የዴሞክራስያዊ እንቕስቃስያችን ወሳኝ አምዶች ናቸው
5.2.1 ህገ መንግስታችን እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
5.2.2 የተወካዮች ምክርቤት ዓይነቶች
5.2.3 የተወካዮች ምክር ቤት እውነተኛ ገፅታ
5.3 የመገናኛ ብዙሃን
5.4 የአንድ ለአምስት ተቋም
6. ንቅናቄው እንዴት ይቀጣጠል?
– ማህበራዊ ንቅናቄ (Social Movement) ምንድን ነው?
–የግል መልእክት
– ዋቢ ምንጮች

1.መግቢያ

በኢህአዲግ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት “ሩቅ አስባ ሩቅ ለመደር እየተጋች ያለች አገር” በሚል መሪ ቃል ስር ላሳካዉ አንፃራዊ መረጋጋት እና ተጠቃሽ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ምስጋናየ ላቅ ያለ ነው፡፡ይሄም ስኬት ኩሩው የኢትዮጵያ ህዝብ ደስተኛ እንዲሆን እና ወጣቱም ተስፈኛ እንዲሆን እያስቻለው ነው፡፡ ባለፈው አስር ዓመት ኢትዮጵያ ከአለማችን ፈጣን ኢኮኖሚዎች በመጀመርያ ረድፍ እምትጠራ አገር ሁናለች። ይህ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትም ተጨባጭ እና ሊካዱ እማይችሉና እሰየው እሚያስብሉ ልማታዊ እና ማህበራዊ ለውጦችን አስከትልዋል። ከሞላ ጎደል የተሳካው የምእት አመቱ የልማት ግቦች፣ እንደ ህዳሴው ግድብ አይነት ታላላቅ ፕሮጀክቶች፣ እየተሳለጡ ያሉ ሰፋፊ የሱካርና የማዳበርያ ፋብሪካዎች ተከላ ሲታይ ይህን እዉን ያደረገዉን መንግስት እና አመራሩን ማመስገን ተገቢ ነው ብየ አምናለሁ።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ያገኙት የ South-South ሽልማትም የዚህ ጥረት ማሳያ ነው፤ ክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር እኔም እንዃን ደስ አልዎት ማለት እፈልጋለሁ። የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን አንድ (GTP 1) አጠቃላይ አገራዊ ያፈፃፀም ደረጃዉም አበረታች ነበር ማለት ይቻላል፤ በክልሎች መሃል ሊታረም እሚገባው አለመመጣጠን እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። በኢኮኖሚው መስክ አገራችን ኢትዮጵያም ገፅታዋንም በፍጥነት እየቀየረች ትገኛለች። GTP 1 አስፍቶ ማስብን እና አግዝፎ መስራትን ያስተማረ እቅድ ስለነበር እያንዳንዱ ዜጋ ላይ የፈጠረው መነሳሳት እንደ ቀላል የሚታይ አይደለም። የተለጠጠ እቅድ ይዘህ እጅግ በጣም ብዙ አልመህ ብዙ ብትሰራ በ ፐርሰንት ሲታይ ትንሽ ቢመስልም ትንሽ አቅዶ እስዋን ብቻ ከማሳካት ግን ሺ እጥፍ ይሻላልም ይበጃልም። ስለዚ ambitious ፕላን መሆኑ ሊደነቅ ይገባዋል። ክጀርባው ያለው እሳቤም ማደግ ካለብን ማህበረ ኢኮኖምያዊ ሽግግር ያስፈልገናል ይህ ለማድረግ ደግሞ ተለቅ ያለ ስራ መስራት አለብን ነው። ይሄም በጎ እሳቤ ነው። ትልቅ ነገር ሳያስቡ ትልቅ አገር መገንባት አይቻልም። ባጠቃላይ በትምህርት መስፋፋት (በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተቛማት መስፋፋት)፣ በጤና ኬላዎች መዳረስ፣ ለ አርሶ እና አርብቶ አደሩ የሚደረጉ ድጋፎች፣ ስፋፊ የትራስፖርት አውታሮች ያሳካ የኢኮኖሚ እድገት፣ ሃብታም ገበሬዎችን መፍጠር የቻለ ግብርና፣ ብዙ ወጣቶችን የፈጠራ እና የሃብት ባለቤት ማድረግ የቻለ ጉዞ ተገቢ እዉቅና ማግኘት አለበት። የኢንዱስትሪ ክፍሉም በብዙ ችግሮች የተሞላ ቢሆንም መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትክረት የላቀ መሆኑ ሊደነቅ ይገባል።Photo – General Abebe Teklehaimanot

አንፃራዊ ሰላም እና መረጋጋት በማስፈን እና ሰላም ላጡ ህዝቦች የሰላም ሃይል በመሆን እሚደረገው የዲፕሎማሲ እና የመከላከያ ሃይላችን ጥረትም እጅጉን እሚመሰገን ነው።ኢትዮጵያ ላይ የሰፈነው አንፃራዊ ሰላም እና መረጋጋት ዝቅ ተደርጎ ሊታይ እሚችል አይደለም፤ እነ ሶርያ እና ሊብያ ከነ ሙሉ ሃብታቸው ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉም መርሳት የለብንም። እነ ኬንያ እና ሶማልያ በአሸባሪዎች ሲታመሱ በሰላም ተኝተን እምናድረው የሰፈነዉን አንፃራዊ ሰላም ተማምነን ነው። ዋናው የሰላማችን ምንጭ ህገ-መንግስታዊ ስርዓታችን ቢሆንም የፀጥታ ሀይሎቻችን ልዩ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

በተለይም ትህዴንን (TPDM ) ለአዲስ ዓመት ስጦታ በማበርከታቸው አድናቆቴን መግለፅ እወዳለሁ፡፡ በተጨማሪም ከአባይ ወንዝ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚታየው የሶስትዮሽ ስምምነትም የኢትዮጵያ መንግስት አስተዋይነት እና ለብሄራዊ ጥቅሙ ያለው ተቆርቛሪነት ያረጋገጠበት ድርጊት ተደርጎ ሊቆጠር እሚገባው ነው።ተስፋ ሰጪ በሆነው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ምክንያት የተፈጠረው አገራዊ የህዳሴ መንፈስም ከምንም ሳይሆን መሬት ላይ ካለው እዉነታ የሚመንጭ አወንታዊ ቁጭት ስለሆነ ለለዉጥ ጉዞው እጅግ ጠቃሚ ግብአት ነው። ይሁን እንጂ የኑሮ ውድነት እጅግ እየሻቀበ በመሄዱና በሃብታምና ድሃ ያለው ልዩነት በዚህ ፍጥነት ከቀጠለ አድገኛ ስለሆነ ተገቢ እርምት መወሰድ አለበት እላለሁ፡፡

ልማታዊ ስኬቶቹ የመንግስትን ልማታዊነት ያሳያሉ ማለት ግን ዴሞክራስያዊነቱን ይገልፃል ማለት አይቻልም። ባጭሩ ሰላማዊ እና ልማታዊ ማለት ዴሞክራስያዊ ማለት አይደለም።ዴሞክራስያዊ ድባቡ እየሰፋ ነው ወይስ እየጠበበ ነው? የሚለው ማየት ተገቢ ነው። ይህን ለመመለስ መለከያ ያስፈለገናል፡፡ መመዘኛችን ህገ-መንገስታችን፤ የመንግሰትና የገዢው ፓረቲ አቑዋሞች መሰርት አድርገን ብናየው ስርኣቱን በበለጠ ለማየት ያስችለናል ብየ እገምታለሁ፡፡ “በትግላችንና በከፈልነው መስዋዕትነት የተገኘውን ዴሞክራሲና ሰላም ዘላቂነቱ ለማረጋገጥ” እና ለሌሎች ተዛማጀ “ዓላማዎችና እምነቶች ማሰርያ” እንዲሆን ህገ መንግስቱ መፅደቁ መግብያው ላይ ሰፍሮ እናገኛለን። ለዚህም ነው ሰላማችንንና ዴሞክራስያችንን ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ የሚደረግ ጥረት ህገ-መንግስቱን ለማረጋገጥ የሚደረግ ጥረት ነው የምለው።

በ 1994 ዓ.ም የማስታወቅያ ሚንስቴር “በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ጉዳዮች” በሚል ርእስ ባሳተመው ፅሁፍ ‘ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር የህልዉና ጥያቄ ነው’ ይላል።ይህ ሰነድ የተሟላ የዴሞክራሲ አስተሳሰብ የተቀመጠበት በመሆኑ የመመዘኛችን መነሻ እነዲሆን ወድጅያለሁ፡፡ ሰነዱ ዘርዘር አድርጎ የተመለከታቸው የዴሞክራሲ ተቛማት ብዙ መሆናቸው መገንዘብ ይቻላል። ይሄው የ 1994ቱ ሰነድ ምክርቤቶችን በተመለከተ እንዲህ ይላል “ምክር ቤቶች የህዝቡ ሉአላዊነት መገለጫ የዴሞክራስያዊ አስተዳደር እምብርትና የዴሞክራስያዊ አገዛዝ አውራ ተቛሞች ናቸው” ይላቸዋል። ሆኖም መሬት ላይ ያለው እውነታው ግን ከዚህ የራቀ ይመስላል። ለምን?

በተመሳሳይም በ 1992 ዓ.ም ለውይይት በተዘረጋው የኢህአዴግ ፅሁፍ ላይ ትምርህርት ቤቶችን በተመለከተ እሚከተለው ሰፍሮ እናገኛለን “ትምህርት ቤቶችን ወደ ኢህአዴግ ትምርህርት ቤትነትን ለመቀየር የማይቻል ከመሆኑም በላይ ሃቀኛ ዴሞክራስያዊም አይሆንም። መላዉን ህዝብ /አብዛኛው ክፍል/ ለአመታት አንድ ፓርቲ አመለካከት በማጋለጥ፣ ሌሎችን በመከላከል የሚደረግ አሰራር መከተል በሃሳቦች መካከል ነፃ ዉድድር እንዳይኖር የሚያደርግ ነው። የሃይለስላሴና የደርግ መንግስታት ይህን ማድረጋቸው የሚያመላክተው ፀረ ዴሞክራስያዊ ባህሪያቸዉን ነው።” አሁንም እውነታው ከዚህ የራቀ ይመስላል።ለምን?

ከአምስት ዓመት በኃላ በ 1999 ዓ.ም የመልካም አስተዳደር ችግር ፈጦ የወጣ ችግር ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሶ ከስረ መሰረቱ እንፈታዋል ተብሎ ተዝምሮለትም ነበር። ነበር ሆኖ ቀረ!! አሁንም በ 2007 ዓ.ም መጨረሻ ኢህአዴግ መልካም አስተዳደር ዋናው ችግሬ ነው እያለ ነው። ይህ ለምን ሆነ? የዚህ ፁሁፍ አላማም ለምን ይህ ችግር ሳይቀረፍ አለ ከተባለበት ግዜ ምንም መሻሻል ሳያሳይ እንደዉም ለምን እየተባባሰ እንደመጣ ለማሳየት እና የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመጠቆም ነው።

ኢህአዴግ በኢኮኖሚው መስክ ከሞላ ጎደል ያለመዉን እያሳካ ይታያል፤ ከዴሞክራሲ አዃያ ግን እግሩ ሲጎተት መመልከት የተለመደ ሁነት ከሆነ ሰነባብቷል። በዚህ ዙርያም በዴሞክራሲው መስክ ችግሮች እየታዩ ነው ብሎ ኢህአዴግ በ 1992-93 ዓ.ም ከገመገመበት ወቅት እስከ አሁንዋ ሰዓት ይህ ነው ሊባል እሚችል የሰፋ የዴሞክራሲ ድባብ ሳይፈጠር ካለንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።ችግሩ የክልስ ሃሳብ አለመሆኑ ሰነዶችን በመመልከት መገንዘብ ይቻላል።

GTP 1 በሚፈለገው መጠን እና ፍጥነት እንዳይሳካ ካደረጉት ምክንያቶች የመልካም አስተዳደር ችግር በዋናነት መጠቀስ ይቻላል። ካጠቃላይ የዴሞክራሲ ድባብ መጥበብ ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ የመልካም አስተዳደር አለመኖር፣ የሙስና እና የፍትህ መጏደል ናቸው የGTP 1ን አፈፃፀም በሚፈለገው ፍጥነት ያላስኬዱት። መልካም/ዴሞክራስያዊ አስተዳደር ማስፈን ከተበላሸ/ ካልተቻለ GTP 2 አይሳካም ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት አገራችን የሰራቻቸው የሚያፈርስ፣ሰላማችን እና መረጋጋታችን እንድናጣ የሚያደርግ በመሆኑ እዛ ላይ አተኩሬ ትዝብቴን እገልፃለሁ። ይህ ፅሁፍ በጥልቀት በተሰራ ጥናት እና ምርምር ሳይሆን ባጠቃላይ ቅኝት (General Observation) የተሞረኮዘ ሲሆን፤ የማነሳው ጉዳይ ሰፋ እና ዘርዘር ያለ ምርምር እንደሚያስፈልገውም መጠቆም እወዳለሁ። በጥልቅ ጥናት ላይ ያልተመሰረተ በመሆኑ አንዳድ ሁኔታዎችን በሚገባ ያልገለፅኩት ካለ ወይም በጣም ካጋነንኩት አንባብያንን ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

የዚህ ፅሁፍ ፀሀፊ በዲሞክራሲ ዙሪያ የሚታዩ እጥረቶች (Democratic deficiency) የችግሮቹ መንስኤዎች ሲሆኑ ቀጣይነት ያለው የተሟላ ዲሞክራሲያዊ እና ህገመንግስታዊ ተቋማት መገንባት ደግሞ መፍትሄዎቹ ናቸው ብሎ ያምናል:: ለዚህ ፅሁፍ ሲባል የህዝብ መወከያ ተቋማት (ፓርላማ እና በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ምክርቤቶች)፤የመገናኛ ብዙሃን እና የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ልቃኝ መርጭያለሁ፡፡ የፁሁፉ አወቃቀር እንደሚከተለው ይሆናል፤ በመጀመርያ አሉ ያልኳቸዉን መሰረታዊ ችግሮቻችንን ከዘረዘረ እና በሁለተኛው ክፍል ዋና መንስኢዎቻቸው ላይ ገለፃ ካድረገ በኃላ በሶስተኛው ክፍል ቀጣይነት ያለው የዴሞክራሲ ግምባታ የችግሮቻችን መፍትሄ የሚል ርእስ ላይ ያተኩራል። በመጨረሻም ንቅናቄው እንዴት መቀጣጠል እንዳለበት የሚያመላክት የመሰለኝኝ ሃሳብ አቀርባለሁ፤ መልካም ንባብ።

2.ችግሮቻችን ምንድን ናቸው? መልካም አስተዳደር የወቅቱ ቁልፍ ችግር

2.1 በአሁኑ ግዜ የችግሮቻችን አውራ መልካም አስተዳደር ያለማስፈን ችግር ነው ተብሏል፡፡ ለመሆኑ መልካም/ዴሞክራስያዊ አስተዳደር ምን ማለት ነው?

የመልካም ወይም ዴሞክራስያዊ አስተዳደር ምንነት በጣም አከራካሪና ሰፋ ያለ ሙግት እሚካሄድበት መስክ እንደሆነ ግንዛቤ ዉስጥ በመክተት ነው በዚህ ንዑስ ርእስ ስር ለዚህ ፅሁፍ ሲባል የተወሰኑ መሰረታዊ ነገሮች ላይ ማተኮር የመረጥኩት። መስተዳድር ወይም አስተዳደር የሚለው ንድፈ ሃሳብ አዲስ ያልሆነና ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጉም የሚሰጥ ነገር ነው። እንደ ናንዳ (Nanda, 2006: 271) ገለፃ አስተዳደር የሚለው ሃሳብ የትርጉም እልባት ያላገኝ እና ትርጉሙም ልናሳካ በምንፈልገው አላማ እና በምንከተለው ዘይቤ እንደሚመሰረት ታብራራለች። አስተዳደር የነባራዊው ፖለቲካዊ ስርዓት ነፀብራቅ ሲሆን በመጠነ ስፋቱ እና ተዛማጅ ትርጉሙም ከግዜ ወደ ግዜ እንዲሁም ከቦታ ወደ ቦታ የሚለያይ ነገር ነው። በፍፁማዊ የዘዉድ አገዛዝ እና ሌሎች የአምባገነን መንግስታት አስተዳደር ሊያሳካ እሚችለው የመጨረሻው አላማ የአስተዳደር ቢሮክራስያዊ ገፅታው፤ ማለትም ዉጤታማነት እና ብቁነት (ቅልጥፍና) ነው።

ማህበረ -ኢኮኖምያዊ እና ፖለቲካዊ እድገቶችን እና የዴሞክራሲ ጅማሬን ተከትሎ ግን አስተዳደር የሚለው ሃሳብ መልካም አስተዳደር ወይም ዴሞክራስያዊ አስተዳደር የሚሉትን በማካተት መልካም አተደዳደርን የዴሞክራሲ ፀጋ አድርጎ መቁጠር የተዘወተረ ነገር መሆን መጀመሩ መገንዘብ ይቻላል። መልካም አስተዳደር ወይም ዴሞክራስያዊ አስተዳደር ከዉጤታማነት እና ብቁነት የሰፋ እና የገዘፈ ሃሳብ ሲሆን፤ ላጠቃላይ የፖለቲካ ስርዓቱ የሚቆምና የዜጎችን ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ መብቶች እና ነፃነቶች የሚያስከብርና ማንኛዉምም ዓይነት አድልዎ የማይቀበል ሂደት ነው። ግልፅነት እና ተጠያቂነትም በሲቪል ሰርቪሱ ብቻ የማይታጠር በፖለቲካ አመራሩ እና ተቛማት ሊተገበር እሚገባው ቁልፍ የመልካም አስተዳደር አካሎች ናቸው።

ገብረቭቢ ‘Democracy, Democratic Institutions and Good Governance in Nigeria’ በተሰኘው ፁሁፉ አልካሊ የተባለ ተመራማሪን ጠቅሶ እንደሚለው አስተዳደር ማለት የፖለቲካ ስልጣንን ህዝባዊ ጉዳዮችን ለማስኬድ ማዋል እንደሆነ ይጠቅስና፤ አስተዳደር የሚዳስሳቸው ጉዳዮች ብሎ የህግ የበላይነትን፣ ተጠያቂነትና ግልፅነትን፣ ልማት ተኮር አመራርን፣ ራስን የመግለፅና የመደራጀት መብትን፣ መልስ ሰጪነትን፣ ሃላፊነት መዉሰድን፣ ወካይነትን፣ ዉጤታማነት እና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠትን እንደሚያካትት ይገልፃል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳው መልካም አስተዳደር እሚለው ጽንሰ ሃሳብ ነው፡፡ ሻቢር ቼማ እንደሚለው “መልካም አስተዳደር ያለዉን ሃብት ለጋራ ችግሮች እንዴት መዋል እንዳለባቸውና በምን አኳሃን መመራት እንዳለባቸው የሚመለከት እንደሆነ ይጠቅሳል። መገለጫ መርሆቹም አሳታፊነት፣ ግልፅነት፣ ተጠየቂነት፣ የህግ የበላይነት፣ ዉጤታማነት፣ ፍትሃዊነት እና ስትራቴጅያዊ ራዕይ መጨበጥን ያካትታል ይላል።” (2005:33).

አዳምስም በተመሳሳይ ስለ ዴሞክራስያዊ አስተዳደር የሚከተለውን ይላል ዴሞክራስያዊ አስተዳደር የህዝባዊ ተቛማት ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት ይፈልጋል። ዜጎችም ስለ መንግስት ፖሊሲ፣ ዉሳኔዎች እና ተግባራት መረጃ የማግኝት መብት ሊኖራቸው ይገባል። በኛ አገር ሁኔታ ይህ እንዳይሆን እንቅፋት ከሆነው አንዱ የመንግስት የመረጃ አያያዝ ደካማነት፣ የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት እንዳላቸው አለመገንዘብ እና በዋናነት ደግሞ ሚስጢራዊ እና ሚስጢራዊ የሆኑ መረጃዋች መለየት አለመቻል ነው፤ ይህ ሁኔታ ካልታረመ መሰረታዊ የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት ስለሚጋፋ ለዴሞክራሲ ምህዳር መጥበብ የራሱ አስተዋፅኦ ማድረጉ አይቀርም። አዳምስ አያይዞም በሃላፊነት ያሉ ሰዎች ለድርጊታቸው እና ላፈፃፀም ግብራቸው ተጠያቂ መሆን አለባቸው ይላል። የተጠያቂነት እና ግልፀኝነት መርህ መንግስት አካባቢ ለሚኖረው ሙስና ለመግታት እና የዜጎች ተሳትፎ ለማበርታት ጠቃሚ ነገሮች ናቸው ይላል። ዜጎች ሃሳብን እና ራስን በነፃ የመግለፅ፣ የመደራጀት እንዲሁም ማንንም ሳይፈሩ ድርጅት የመመስረት እና የተመቻቸውን ድርጅት የመቀላቀል መብት ሊኖራቸው እንደሚገባ ያትታል።ከዚህ መረዳት እምንችለው መልካም/ዴሞክራስያዊ አስተዳደር ሲባል ቁንፅል ፖለቲካዊ ሃሳብ ሳይሆን የዜጎችን ስብአዊ እና ዴሞክራስያዊ መብቶችን በአስተዳደር መዋቅር እና ትግበራ ከግምት ማስገባት ማለት እንደሆነ ነው::

እንደ ተመዱ የኤስያና ፓስፊክ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ኮሚሽን አረዳድ መልካም አስተዳደር ስምንት ዋና ባህርያት አሉት ይላል። እነዚህም አሳታፊነት፣ መግባባት ላይ ያተኮረ (Concensus oriented) ፣ ተጠያቂነት፣ ግልፅነት፣ መልስ ሰጪ (Responsive)፣ ዉጤታማ እና ብቁ (ቅልጥፍና)፣ፍትሃዊ እና ሁሉን አቃፊ (equitable and inclusive) እንዲሁም የህግ የበላይነት ናቸው ይላል። መልካም አስተዳደር የህዳጣን (Minorities) እና የሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ሃሳብ እና ድምፅ በዉሳኔ መስጠት ሂደት ላይ ግምት ዉስጥ መክተትንም ይጨምራል ይላል። አሁን ላለው እና ወደፊት ለሚመጣው ማህበረሰባዊ ፍላጎትም ጭምር ዝግጁ የሆነና መልስ መስጠት የሚችል አቅም እና መዋቅር መፍጠር ነው መልካም አስተዳደር። ሰለዚ አንድን ሰርአት መልካም ነው ወይስ መጥፎ አስተዳደር ነው ያለው የሚለዉን ለመገንዘብ ከነዚህ መለክያዎች አንፃር ነው ማየት ያለብን።

ዴሞክራስያዊ ፖለቲካዊ ስርዓት መንግስታዊ ስልጣን የያዙ ሰዎች ላይ ህጋዊ ገድብ ያስቀምጣል። ስልጣን ለተለያዩ የመንግስት አካላት የሚሰጥበት ምክንያትም በተወሰኑ ተቛማት ወይም ግለሰቦች ብቻ ሃይል እንዳይከማች ከሚል እሳቤ ነው። የተለያዩ የመንግስት አካላት በቂ የሆነ አቅም እና ነፃነት ኑሮዋቸው አንዱ መዋቅር ሌላኛዉን እሚቆጣጠርበት እና ህገ መንግስታዊ ሚዛን እሚጠብቅበት አሰራር ያስፈልገዋል። ወታደራዊ ተቛሙም በ ሲቪልያን ቁጥጥር ስር ማድረግ መቻል ለዴሞክራስያዊ አስተዳደር በጣም ወሳኝ ነው ይላል ፍራንሲስ አዳምስ። እንደ አዳምስ አነጋገር ወታደራዊ ሃይሉን በበላይነት የማዘዝ ስልጣኑ በምርጫ በሚቛቛመው አገራዊ ፖሊሲዎችን በሚያወጣው እና ያለ ወታሃደራዊ ጣልቃ ገብነት ስራዉን በሚተገብረው ሲቪል አስፋፃሚ መሆን አለበት ይላል።

[የኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 74/1 እንደሚለው “… ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ነው” እንዲሁም በአንቀፅ 87/2 መሰረት “የመከላከያ ሚኒስቴር ሆኖ የሚሾመው ሲቪል ይሆናል” ይላል።]

2.2.የመልካም/ ዴሞክራስያዊ አስተዳደር ችግሮች ስፋትና ጥልቀት

ባጠቃላይ የሃገራችን ሁኔታ ሲታይ መልካም አስተዳደር ማረጋገጥ አለመቻል፣ ሙስና፣ እና የፍትህ እጦት ሶስት አደገኛ የስርዓቱ በሽታዎች ናቸው፡፡ እነዚህ በሽታዎች አጠቃላይ የዲሞክራሲ ሁናቴው ሲቀጭጭ ከቁጥጥር ውጪ የመሆን እድላቸው ይሰፋና ማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ አዳጋች ይሆናል፡፡ እነዚህን ሶስት አደገኛ በሽታዎች ለዘመናት ከኛ ጋር የኖሩ እና አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈታተኑን የሚገኙ ስለሆኑ ኢኮኖሚያዊ ከሆኑ መንገዶች በተጨማሪ ሌላ መፍትሄ ማበጀት ካልተቻለ በቀጣይነት ግዝፈታቸው እየጨመሩ መሄዳቸው እማይቀር መሆኑ መገንዘብ አለብን:: ባጭር አማርኛ ችግሮቹ አብረውን የነበሩና አሁንም እያኗኗሩን ያሉ በሽታዎች ናቸው፡፡ ኢህአዲግ መሰረታዊ የስርዓቱ በሽታ ብሎ የዘረዘራቸው ሙስና፤ መልካም ያልሆነ አስተዳደር እና የፍትህ መጓደል እስካሁኑ የተገኙት ድሎችን መና ሊያስቀር እንደሚችል እውቅና መስጠቱም ይብል የሚያስብል ነው፡፡

አሁን ኢትዮጵያ ላይ ያለው የዴሞክራሲ ድባብ ሲታይ ዜጎች የሚስማቸውን ቅሬታ ለመግለጽ አብዛኞቹ መንገዶች የሳሱበት ፣ አማራጭ የመረጃ ምንጮች በከፍተኛ ፍጥነት እየቀጨጩ፣ የማበህራት ነፃነት እተገፋፋ፣ የመናገር እና ባጠቃላይ ሃሳብን የመግለጽ መብቶች በሚታዩ እና በማይታዩ ዘዴዎች እየተዳከሙ ያለበት ሁኔታ እታዘባለሁ፡፡ መልካም አስተዳደር ህልም የሆነበት ሙስና የያንዳንዱ መንግስታዊ መዋቅር እና ሰዎች “ልሙድ ተግባር” የሆነበት፣ ፍትህ ከርትዕ ርቆ የጉልበተኞች መጫወቻ እየሆነ ባጠቃላይ ዜጎች በፍርሃት የተሸበቡበት ፖለቲካዊ ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የፍርሃት ዋና መንስኤ ደግሞ ጤንነቱ የተዛባ የፖለቲካ ሁኔታ ነው።

አካፋን አካፋ ካላልን ግብዝነት ይነግሳል፣ ውሸት ሃይል አግኝቶ እውነትን ይተካል፡፡ በመንግስት በኩል ደግሞ የ “ማን አለብኝነት” ትእቢት እና ተቛሚዊ አሰራር መጥፋት እና ሌሎች ተደማምረው የአምባገነንነት ዝንባሌዎች (Dictatorial Tendency) እየታዩ ነው፡፡ 10ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ችግሮች ብሎ የለያቸው ሰናይ ከላይ የገለፅኩት ምስል ነው የሚያሳየን:: ለምሳሌ መቐለ በተካሄደው በኢህአዴግ 10ኛው ጉባኤ ዋና ዋና ድክመቶች ተብለው በጉባኤው ተቀባይነት ካገኙት ካነሳነው ጉዳይ ተያያዥ የሆኑትን ልጥቀስ፡፡ ምንጮቼ በጉባኤው በታዛቢነት ተሳትፎ አድርጎ የነበረዉ ሪፖርተር ጋዜጣና ያነጋገርዃቸው ተሳተፊዎች ናቸው።

* “ህዝባዊነት በግለኝነት እየተሸራረፈ ነው፡፡ ህዝብ የበላይ ወሳኝና ተቆጣጣሪ መሆኑ እየተዘነጋ የግል ጥቅም እና ምቾት ለማሳካት መንቀሳቀስ በኢህአዴግ ውስጥ እየተስፋፋ መጥቷል፡፡

* ኪራይ ሰብሳቢነት እና ሙስና እየተስፋፋ ነው፡፡

* መልካም አስተዳደር እየጠፋ ነው፡፡

* የፍትህ ስርአቱ እየተዳከመ ነው፡፡

* ተጠያቂነት እየጠፋ ነው፡፡

* የማህበራዊ አገልግሎት አቅርቦት ችግር አለ፡፡

ኢህአዴግ ባጭሩ እያለን ያለው “የሙስና፣ መልካም አስተዳደር የማሰፋን እና የፍትህ ችግሮች እየተባባሱ ነው” ነው፡፡ይህም በመሰረቱ ትክክል ነው። ህዝብን እሚሰማ እየጠፋ ‘እኔ አውቅልሃሎህ’ ባይ እየበዛ፣ ህዝቡ ችግሩ ሲናገር ከተቃዋሚዎች ጋር እያስተሳሰሩ ማሳደድ፣ ዝም ሲል ደግሞ እንደተመቸው አድርጎ ማሰብ፣ እንደ ፓርላማ የመሳሰሉ የዴሞክራሲ ተቋማት ግዴታዎችን በበቂ ሁኔታ አለመወጣታቸው የስራ አስፈፃሚውን ጡንቻ እያሳበጠ ሄዶ ሄዶ አሁን ላለንበት ሁኔታ አድርሶናል፡፡ የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ነው ዴሞክራሲያዊ ሁኔታውን ያጠበበው፣ የዚህ መጥበብ ልጆች ናቸው እነ ፍትህ ማጣት፣ ሙስና እና መልካም ያልሆነ አስተዳደር እሚባሉ በሽቶች፡፡

3. የችግሮቻችን መሰረታዊ ምንጭ ምንድን ነው?

ለበሽታዎቻችን እንደ የአቅም ማነስ፣ ድርጅታዊ ድክመት፣ ያልዳበረ ህዝባዊ የተሳትፎ ባህል የመሳሰሉት ነገሮች መነሻ ምክንያት ሊሆኑ ቢችሉም ዋናው እና ተጠቃሽ ምክንያት ግን አጠቃላይ የዴሞክራሲያዊ ሁናቴ እጥረት ነው፡፡ እንከን የለሽ ዴሞክራሲ እሚባል ነገር እንደሌለና ኢትዮጵያችንም ጀማሪ ዴሞክራሲ መሆንዋንም እረዳለሁ፡፡ በዚህ ምክንያትም ነው በኢትዮጵያ ዴሞክራያዊ ስርዓት ለመገንባትም ለመቀልበስም ሊያግዙ እሚችሉ ነገሮች በብዛት እሚገኙት፤ ለዚህም ነው ጀማሪ ዴሞክራሲያችንን ሊቀለብሱ እሚችሉ ሃይሎች እና ሁኔታዎችን በቅጡ ተገንዝበን እና ለይተን በቁርጠኝነት አረንቋውን ማድረቅ ያለብን፡፡ ለዚህም ነው ቲሊ ዴሞክራታይዜሽን መቼም ሙሉ መሆን እማይችል እና የ ኢ ዴሞክራታይዜሽን አደጋ ሊያጋጥመው የሚችል ተለዋዋጭ ሂደት ነው የሚለው። ኢ ዴሞክራታይዜሽን ማለት ቅልበሳ ማለት ነው። በተለያየ አቅጣጫ ተቀራርበው እሚንቀሳቀሱ ሂደቶች ዴሞክራታይዜሽንን እና ቅልበሳዉን ሊያመጡ ይችላሉ ይላል። “Closely related processes, moving in opposite directions, produce both democratization and de democratization”፡፡ ሙለር እና በርግማን እንደሚሉት ዴሞክራሲ ቀላልም ቀጥ ያለም ያልሆነ ግን ደግሞ ሊሳካ የሚችል ነገር ነው:: በነዚህ እና በሌሎች ምክንያት ነው አገሬ ላይ እዉን ሆኖ ማየት እምፈልገው ዴሞክራሲ ሃሳባዊ የሆነና ምንም እንከን የሌለው ዴሞክራሲ አይደለም የምለው፡፡

የአገራችን የዴሞክራሲ ሁኔታ ለጋ ነው ስል የሚከተለውን የቲሊ አባባል ያስታዉሰኛል፤ በቲሊ አረዳድ “We are not trying to explain yes-no swiches between undemocratic and democratic conditions. We are not trying to explain degrees and changes of democracy” ስለዚህ ስለ አገራችን የዴሞክራሲ ሁኔታ ሳወራ ስለ ሂደት እንጂ ህልመኛ ሆኜ መሆን የማይችለውን እና እስከአሁን አለም ላይ የሌለውን ገነት መሳይ ዴሞክራሲ ፈልጌ አይደለም፡፡ ለምሳሌ እ.ፋ.አ ከ 1789 ጀምሮ ፈረንሳይ በትንሹ አራት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ክፍሎች ስታይ በትንሹ ደግሞ ሶስት የዴሞክራሲ ስርዓት ቅልበሳ ግዝያቶች አሳልፋለች፡፡ ዘመናችን የዴሞክራሲ በመሆኑ እንደዚህ ኣይነት የቅልበሳ የቅንጦት (luxury of de-democratization) አማራጭ ግን የለንም። በኛ ሁኔታ ተደጋግሞ እንደተገለጸው ዴሞከራሲ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ እየተንገራገጨ ቢሆንም ሁሉ ግዜ ወደፊት መጏዙን ማረጋገጥ ይኖርብናል እንጂ አጠቀላይ ቅልበሳ አገሪቱ ወደ አደገኛ ቀዉስ ይመራታል፡፡

የዲሞክራሲ እጦት የተመረጠ እና ልዩ የመጥፎ አስተዳደር ማዳበሪያ ነው፡፡ የፈለገው ልማት ቢመጣ ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩ መጥበብ ካሳየ ሶስቱም በሽታዎች አለን!! አለን!! አለን!! ምን አባታቹህ ታመጣላቹህ! እያሉ መፈንጨታቸው አይቀርም::በሽታዎቹ እንዳይፈነጩብን በመሰረቱ የሚከላከልልንን ዲሞክራሲያዊ ህገ መንግስት አለን፡፡ ችግሩ ተግባር ላይ ሲዉል ህገ-መንግስቱ ባስቀመጠው መንፈስ (Sprit of the Constitution) አለመተግበሩ ነው፡፡ ከፍ ያለ ኢ-ህገ-መንግስታዊነት ሲበረታ ሶስቱ በሽታዎች የራሳቸው ሰንደቅ አላማ እያውለበለቡ ‘አሸናፍናቹህ፤ ረታናችሁ’ ይሉናል:: አጠቃላይ የዲሞክራሲ ከባቢው እየጠበበ ሲሄድ ሶስትም በሽታዎች ተጠናክረው፤ ተበረታተው፤ ተባዝተው እና ተኳኩለው ይፈነጩብናል፡፡ በዴሞክራታይዜሽን እና ኢ-ዴሞክራታይዜሽን ሂደቶች ሁሌም መሳሳብ እና ዉጥረት ይኖራል። መንግስት እንደ መንግስት ግን የዴሞክራታይዜሽን አጋዥ አልያም የኢ-ዴሞክራታይዜሽን አሳላጭ ነው መሆን እሚችለው፤ መሀል ላይ የሚንገዋለል መንግስታዊና ተቛማዊ አቛም ሊኖር አይችልም። ስለዚ ምርጫው አንድ እና አንድ ነው፤ ለዴሞክራሲ መስራት ወይም የፀረ ዴሞክራሲ ሃይል መሆን።

ዲሞክራሲያዊ ሁኔታ እና ሶስቱ በሽታዎች በተቃራኒ መንገድ ነው ጉዞአቸው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ሁኔታው ሲሰፋ በሽታዎቹ መጠጊያ እና መሸሸጊያ ፍለጋ ይኳትናሉ፡፡ ምሽግ ፈልገው ወይም ቆፍረው ይደበቃሉ፤ልክ የወባ በሽታ ከህክምና በኃላም ቢሆን በሆነ የሰውነታችን ክፍል እንደምትደበቀው፤ ይሄ ለመደበቅ እምታሳየው ባህሪ ነው፡፡ ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩ ሲጠብ ደግሞ በሽታዎቹ ወደ አደባባይ እየወጡ ህጋዊ ልባስ እየተጎናፀፉ መገናኛ ብዙሀንን ጭምር እየተጠቀሙ ይፈነጫሉ፤ ህዝብንና አገሪትዋንም በኃሊት ማርሽ ወደ አዘቀት ይከቷታል፡፡ ከስር እምታዩት ስእላዊ መግለጫ ይህንን ሃሳብ የበለጠ ለማስረዳት በፀሃፊው የተዘጋጀ ነው::

[ምስል አንድ: የዴሞክራሲ ምህዳር ሲሰፋ በሽታዎቹ ይቀጭጫሉ፤ በተቃራኒው የዴሞክራሲ ምህዳሩ ሲጠብ በሽታዎቹ ጎልተው እና ጠንክረው ይወጣሉ።]
Diagram-one_thumb
ልማት የዴሞክራሲ አካል መሆኑ ሳንዘነጋ፤ ህገ-መንግስቱን የመተርጎም ችግር አለ ሲባል ከዲሞክራሲ አኳያ የተደነገጉት የሲቭል እና ፖለቲካዊ መብቶች ተፈፃሚ አለማድረግ ማለት ነው:: በተጨማሪም በየጊዜው መንግስትን ለማቋቋም በሚደረገው ምርጫ የፍትሃዊነት እና የህዝባዊ ተቀባይነት (Legitimacy) ችግር ሲኖር ነው ህገ-መንግስቱ በአግባቡ እየተተረጎመ አይደለም የሚባለው፡፡
Diagram-one_thumb (1)
የ2007 ምርጫ ማሸነፍ ያለበት ፓርቲ አሸነፎል፡፡ በእጅጉ ከፍተኛ ድምጽመመረጡም ይገባዋል እላለሁ፤ ይችን አገር ከውድቀት አስነስቶ በመግቢያ እነደገለጽኩት ወደ ተስፋ ያላት አገር ወደ መሆን እቅጣጫ እየመራት ነው፡፡ አሸናፊነት አይበዛበትም፡፡ የተቃዋሚዎች ድክመት ተጨምሮበት በእጅጉ ከፍተኛ ድምፅ ቢመረጥ አያስገርምም:: ነገር ግን ለምሳሌ ያህል እኔ በመረጥኩበት የምርጫ ክልል እቤት ድረስ የዘለቀ የነበረው መዋከብ እና በኣንዳንድ ምርጫ ክልል አንድ ላምሰት የነበረው አሉታዊ ተጽእኖ ስሰማ፣ የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም የነበረው ከፍተኛ ኣድልዎ ስገነዘብ ምርጫው እንከን የለሽ ነው ሲባል እስቃለሁ። ህዝቦቻችን መብታቸውን ለማስጠበቅ ባልቻሉበት፡ ህገ-መንግስታዊ እና ዴሞከራሲያዊ ተቓሞቻችን ባልጠነከሩበት ሁኔታ፡ የመልካም አስተዳድር ችግር ባለበት ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ዴሞክራስያዊ ነው ማለት አይቻልም።

ባጠቃላይ ሲታይ ብዙ ማንነቶች፤ በርካታ ፖለቲካዊ ፍላጎቶች፤መልስ እንሻለን የሚሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ባሉበት አገር አንድ ግንባር (ኢህአዴግ) እና አጋሮቹ 100% መቀመጫውን መቆጣጠር እሚያሳየን ነገር፤አንድም ባጠቃላይ ፖለቲካዊ ስርዓቱ ላይ ችግር መኖሩን አልያም የምርጫ ስርዓቱ ችግር እንዳለበት ወይም ተግባራዊነት ላይ ችግር እንደነበረበት ነው፤ 100% እሚባል ውጤት አስቂኝ ግን ደግሞ አደገኛ ነው ፡፡ ይሄ ዉጤት አርቆ ለሚያስብ ሰው የአደጋ እንጂ የድል ምልክት ተደርጎ መቆጠር አይችልም። መሬት ላይ ያለዉን የተለያየ ፖለቲካዊ ፍላጎት እማያንፀባርቅ የምክር ቤት ሁኔታ የስጋት እንጂ የኩራት ምንጭ መሆን አይችልም።

የሰፋ ዴሞክራስያዊ ምህዳር ሲኖር የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በእኩልትን አለን የሚሉትን አማራጭነት ለህዝቡ እንዲያቀርቡ ያስችለዋል፡፡ ዴሞክራሲ ማለት እኮ የተለያዩ ሃሳቦች በእኩልነት ለዉድድር እሚቀርቡበት ፖለቲካዊ ገበያ ማለት:: ይህ ተጨባጭ ምሳሌ የሚነግረን ነገር አንድ እና አንድ ነው፤ እሱም አጠቃላይ የዲሞክራሲ ምህዳሩ ሲጠብ ሶስቱም በሽታዎች በግላጭ ባንዲራቸውን ለማውለብለብ እንደማይቸገሩ ነው፡፡

ህዝቡ በሶስቱም በሽታዎች ሲጠቃ ለምንድን ነው በሚሰማ ሰላማዊ ሰልፍ ፤ህዝባዊ ስብሰባዎች ፤ተወካዮችን በመሳብ (recall) እና ሌሎች መንገዶች ተጠቅሞ ምሬቱን ማሰማት ያልቻለው? እሚለው በደንብ መጤን አለበት ፡፡ ልክ በ10ኛው የኢእሀዴግ ጉባኤ እንደተገለፀው ‘ደህና ፤ ይስተካከሉ ይሆናል’ ከሚል መነሻ ሊሆን ይችላል፤ ሌሎች ምክኒያቶች ግን ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት አለብን፡፡ለምሳሌ ህዝብ ዝም ያለው መብቶቹን እሚያረጋግጥበት ሁኔታ ስላላገኘ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዴ መሰረታዊ በሆኑ የመኖር ጉዳይ ላይ እያማረረ እለታዊ እንቅስቃሴውም ጭምር ማከናወን እየተሳነው እያለም በግልጭ ተቋውምውን ማሰማት ያልቻለው ለምን ይሆን? ወይስ ተቓዉሞ መግለፅ እሚያስከፍለው ዋጋ ካቅሙ በላይ ስለሆነበት ነው? ወይስ ተባብሮ የመስራት ችግር (Collective Action Problem) ነው? ወይስ አፋኝ መዋቅሮች አላንቀሳቅስ ብለዉት ነው?

በውሃ ፤መብራት እና ሌሎች አገልግሎቶች በብዛት የሚማረር ህዝብ እንኳን መብቴ ተጣሰ ብሎ ውስጥ ለውስጥ ከማንሾካሾክ አልፎ መብቱን ሲያስከበር አይታይም:: ለምን? እሚለው ጥያቄ በጥልቀት ስንመረምር ነው ብዙ ነገር ሊገባን የሚችለው:: ይህ በንዲህ እንዳለህ አጠቃላይ ዲሞክራሲያዊ ሁኔታው እየሰፋ እና አመቺ እየሆነ ካልሄደ ሶስቱም በሽታዎች ህዝብ ላይ መፈንጨታቸው አይቀርም፡፡ ሁኔታዎች እንዲህ ባለ ጠባብ የዲሞክራሲ ምህዳር ሲቀጥል እሚያስከትሉት መዘዝ ዘርፈ ብዙና ብዙ ዋጋ ያስከፈለና ወደ ፊትም እሚያስከፍል ስለመሆኑ ለመተንበይ ነብይ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ GTP 1 በሚፈለገው መጠን ተግባራዊ እንዳይሆን ብቻ ሳይሆን GTP 2ንም ጭምር አደጋ ላይ ሊጥለው እሚችለው ይሄው ጠበብ የዲሞክራሲ ምህዳር ነው፡፡

ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩ በጠበበ ቁጥር የዜጎች ተስፋ እተሟጠጠ ስጋታቸው እና ፍርሃታቸው እየጨመረ ከቁጥጥር ውጪ የመሆኑ እድል ይሰፋል፡፡ ይህን መሰል ሁኔታም ከውስጥም ከውጪም ለነሱ ለሚችሉ ፅንፈኛ ሃይሎች ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥር አገሪትዋን ወደላስፈላጊ መንገድ ሊመራ ይችላል፡፡ ፍትህ ተራ ፍርድ የማግኘት ጉዳይ አይደለም፡፡ ፍትህ የማህበራዊ ተቛም የመጀመርያ ፀጋው ነው ይላል ጆን ራዉልስ፡፡ ሙስናና መልካም ያልሆነ አስተዳደርም ሃገርን ሊበትን የሚችል፤እየታየ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እድገት ገደል የመክተት አቅም ያላቸው ስርዓታዊ በሽታዎች ናቸው፡፡የሶስቱም እናት ደግሞ የጠበበ ወይም የኮሰመነ የዲሞክራሲ ምህዳር ነው፡፡

4. በኢህአዴግ እሚመራው መንግስት የዴሞክራሲ ምህዳሩ በማስፋት መልካም አስተዳደርን ለምን አላረጋገጠም?

አሁን ካሉት በርካታ ፓርቲዎች የ ሃያኛው እና ሃያአንደኛው ክፍለ ዘመን ቅይጥ አተሳሰብ ያላቸው ናቸው። የ1960ዎቹ ትውልድ “እኔ ያልኩት ካልሆነ ሌላው ዉድቅ ነው” የሚለው አስተሳስብ በትጥቅ ግዜ በነበረው ሁኔታ የድርጅቶች የመጥፋት አጋጣሚ በነበረበት ግዜ የተለያዩ ሃሳቦች እንዳይንሸራሸሩ እማያበረታታ ሁኔታ ሲፍጠር እየጎለበተ ሁኔታዎች ሲረጋጉ አየቀነስ እንደገና ድርጅቶቹ ከዓላማዎቻቸው በላይ ሲሆኑ “ድርጅታችን ልትጠፋ ነው፤ እንዳትጠፋ እናድናት” የሚለው አስተሳሰብ አሁንም በሰላሙ ግዜ ሲንጸባረቅ ይታያል:: ዴሞክራሲ የሚጠይቀው ተጣጣፊነት፣ መቻቻል እና የጋራ መግባባት በተወስኑ ኣመራር እና ወጣት ክፍል ቢንጸባርቀም አሁን ያለው ገዢ አስተሳሰብ ግን ያለመታረቅ ባህል፣ የመጋፈጥ ፖለቲካ እና መራራቅ (uncompromising militancy, confrontational politics and polarization) ነው።

ፈጣሪ ለኢህኣደግ ብቻ ልዮ ስጦታ እንደሰጠ በሚያስመስሉ ሁሉ “ከኢህአዴግ መንገድ ውጪ ሁሉም የጥፋት መንገድ ነው” እሚል አስተሳሰብ ህዝቦቻችን አማራጭ ሓሳቦችን ተዘርዝረው እና ተደራጅተው በዚህ መሰረት በፈለጉት ጉዳይ ላይ ይህን አማራጭ መሰረት አድርገው እንዲወስኑ ዕድል አይሰጣቸዉም። 1992-1993 በኢህአዴግ ዉስጥ የነበረው የዉስጥ ቀዉስ (Intra-party crisis) አፈታት እሚያሳየንም ይህንኑ ነው። “አንጃዎች” የተባሉት ከሌላኛው የፓርቲው ወገን የነበራቸው ልዩነት ለህዝቡ ለማቅረብ የመንግስት ሚድያ እድል ነፈጋቸው። ያሸነፈው “አንጃ” ግን የመንግስት ሚድያ ልክ የኢህአዴግ ሚድያ እንደሆነ በማድረግ እንደፈለገ ሲጠቀምበት ያለ ምንም ሃፍረት ነበር። ይህ አስተሳሰብ እስካልተወገደ ድረስ የዴሞክራሲ ምህዳሩ መስፋት አጠራጣሪ ነው።ዲሞክራሲያዊ ምህዳሩን በሁሉም መልኩ እየኮሰመነ እንዲሄድና ህገ-መንግስቱም በታለመለት መንፈስ እንዳይተገበር እያደረገ ያለ ይመስለኛል፡፡ በመቐለ ከተማ በግላጭ ባደባባይ ተቋዋሚዎች ኳኺቶ (አደገኛ እሾህ) የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸው መወገድ እንዳለባቸው አረም ተቆጠረው መቅረባቸው አሳፋሪ እና ፀረ ህገ-መንግስት የሆነ ድርጊት ነው፡፡

ዴሞክራሲ በአለም ዋና አጀንዳ በሆነበት ሁኔታ በኛ ሃገርም ተደጋግሞ ይዘመራል። በ 1992 ዓ.ም እና 1994 ዓ.ም በኢህአዴግ እና በመንግስት የቀረቡት ፁሁፎች በ ቀዉስ ማግስት የተፃፉ ናቸው። ቀደም ብሎ እንደተገለፀው በተነፃፃሪ ስለ ዴሞክራሲና ተቛሞቹ ጥርት ያለ ሃሳብ አለው። እነዚህ ዶክመንቶች ቀዉሱ ካለቀ በኃላ፤ ማለት መረጋጋት ከተረጋገጠ በኃላ፤ ሳይተገበሩ ሲቀሩ ሸልፍ ማሳመርያ ይሆን እንዴ የተፃፉት? እንድል ያደርገኛል። ዋናው ችግሩ ዴሞክራሲ እሚባል ነገር ከአፋ በላይ ሄዶ ሊዋሃደን አለመቻሉ ነው። Internalize አልተደረገም።

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በትጥቅ ትግል የነበረዉን አደረጃጀት እና አስተሳሰብ በመሰረቱ ሳይቀይር ነው መንግስትነትን የቀጠለው። እዚህ ጋ መሰመር ያለበት ጉዳይ የትጥቅ ትግል task እና መንግስት ከተሆነ ወዲህ የሚኖሩት tasks በአጠቀለይ በተለይ ከዴሞከራሲ ስርኣት በመሰረቱ የተለያዩ መሆናቸው ነው። በትጥቅ ትግል ወቀት እንድን ህዝብ ወይ አከባቢ በብቸንነት እንድትቆጣጠር የሚያስገድድ ህዝቡን በዋናነት ደርግን ለመድምስስ ሞቢሊዝ ማድርግ ሲሆን በኢፊዴሪ ሕገ-መንግሰት ግን ሕብረ-ፓርቲ ስርኣት መሆኑን መገንዘብ አለብን፡፡ ኢህአዴግ ለሕብረ-ፓርቲ ስርኣት በተማላ አልተዘጋጀም፡፡

ከድህነትና ከስላም ማጣት የባሰ የህዝብ ጠላት የለምና፤ በፀረ-ድህነት ትግሉ በስላም ማረጋግጥ አመረቂ ወጤት እየተመዝገበ በመሆኑ ህዝባዊነትና የዓላማ ፅናት የሚያሳይ ቢሆንም በዴሞክራሲና በመልካም አስተዳደር ዙሩያ እየታዩ ያሉት መሰረታዊ ችግሮች ህዝባዊነቱ እየተሸረሽሩ ድርጅቱ በመንታ መንገድ እየተጓዘ የገኛል:: በቀጣይነት እሚማር ተማሪ የሆነ ድርጅት (learning organization) መሆኑ እያቛረጠ በመምጣቱ አቅሙ እያሟጠጠ ምናልባትም ከ GTP2 በሃላ ወገቤ የሚል ደርጅት እንዳይሆን ያስጋል፡፡ ሁኔታው መሰረታዊ ለውጥን ይጠይቀል፡፡ የትውልድ እና ያስተሳሰብ መተካካት የሚጠይቅ ሁኔታ ተፍጥሯል፤ እያየን ያለነው መድረኩ የሚፈልገው መተካካት ሳይሆን መሸጋሸግ ነው። ዴሞከራቲክ አስተሳሰብ እና ብቃት ያለው መጪዉን ለመምራት የሚችል በአንፃራዊነት ሲታይ በዴሞክራቲክ ሁኔታ ያደገ ወጣት ሆኖ ህዝባዊ ተቆርቛሪነቱ የላቀ ሙሁር ወደ ስልጣን ከማምጠት እርስ በረሱ ይህ ይሻለል ያኛው እኬል ቡዙ ኣመት ስርተዋል ይተካ አይነት አባካኝ የሰዎች ዝውወር ነው እየተመለከትን ያለነው፡፡ ግዜው ቀጣይነት የለው የአስተሳሰብ ለወጥ ሲጠይቅ ይህን የሚያቀለጠፍ ሂደት ኣልተደራጀም፤ በኔኣረዳድ ወጣት ሆኖ ህዝባዊ ተቆርቛሪነቱ የላቀ ሙሁርና ኢህአዴግ ገና አልተቀራረቡም።ኢህአዴግ ያለማውን ሙሁር ወጣት መጠቀም የማይችል ድርጅት ይመስለኛል፡፡

በመንግስት መስርያ ቤቶች ያለው አመዳደብ በብቃት ሳይሆን ከገዢው ፓርቲ ባለው ቅርርብ በመሆኑ ጥቅመኛ (Opportunist) እንዲነግስ ያደርጋል። በማይገባው ቦታ የተመደበ ብቃት የሌለው ሰው ዋናው መሳርያው ኢ-ዴሞክራስያዊ አካሄድ ነው። ይህ እሚሆነው በራሱ ስለማይተማመን ነው። ተቛማት ማእከል ተደርጎ የተሰራ ስራ በጣም ደካማ በመሆኑ የተሻለ አስተሳሰብ እና ብቃት ያላቸው እየደገፉ ወሳኝ ቦታዎችን እንድይዙ ማድረግ አልተቻለም። እላይ የተጠቀሰው አስተሳሰብ እስካልተቀየረ ድረስ ዴሞክራሲ ሊስፋፋ አይችልም። አዲስ አስተሳሰብና ብቃት ባለው አዲስ ትውልድ ሲተካ ነው ዴሞክራሲ የሚያብበው። ይህ ለማድረግ 24 ዓመታት እጅግ ቡዙ ነው ባይባልም ትርጉም ያለው ለውጥ ሊመጣ ይችል ነበር፡፡
5. የመፍተሄ ሀሳቦች

ብዙ ጊዜ ሃላፊነትን ወደታችኛው እርከን ማሻገር በተለመደበት አህጉር ኢህአዴግ በድፍረት ዋናው ተጠያቂ የበላይ አመራር ነው ብሎ ማለቱ ምስጋና እንድቸረው ያደርገኛል፡፡በሽታውን እና ምልክቶቹን እውቅና ሰጥቶ ሃላፊነት መውሰድ ለለውጥ ሂደቱ እንደ መጀመሪያ እርምጃ መቆጠር አለበት፡፡ ከባዱ ስራ ግን ቀጥሎ መከሰት ያለበት እርምጃ ላይ ነው፤ ከባድ እና ውስብስብ እሚሆነብት ምክኒያትም ትግሉ ከሞላ ጎደል ግልፅ ከሆነ ዉጫዊ ሃይል ወይም ተቛም ጋር ሳይሆን ከገዢው ፓርቲና መንግስታዊ መዋቅር ይዘው ከሚገኙ አመራር እና የነሱ ተባባሪዎች ጋር መሆኑ ነው። ባጭሩ ሃላፊነት የወሰደው የበላይ አመራር ከሆነ ትግሉም እዛ ጋር ስለሚሆን ፈታኝ እና ውስብስብ እንደሚሆን ግልፅ ነው፡፡ የኢህአዲግ 10ኛው ጉባኤም ያስተጋባውም ወደፊት ብዙ መሰራት ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ ነው፡፡

ከፍተኛ አመራሩ (በደፈናውም ቢሆን) አደገኛ ሆነው ለተገኘት በሽታዎች ዋና ሃላፊነት ወሳጆች እኛው ነን ብለዋል። በርግጥ ስልጣን ሃላፊነትን ጭምር ተሸክሞ ስለሚመጣ በዴሞክራሲ በበለጸጉ አገራት ይህ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ እንደ ምልአት ህዝቡና የአህአዴግ አመራር ግንዛቤ በግዜ ተፈትኖ ስራውን በአግባቡ ማከናወን ሲገባው ድክመት ያሳያው አመራሩ ነው ማለቱ ባጭር ግዜ ሲታይ ህዝባዊ ተቀባይነት እና እምነት ሊጣልበት ቢችልም (ሃቅን በመቀበላቸው ምክንያት) ተከትሎ ሊመጣ እሚገባው ቀጣይ እርምጃ ካልተከላበት ግን ሃላፊነት ወስደናል እሚለው ውሳኔ ትርጉም አልባ ከመሆን አልፎ ተመልሶ ከፍተኛ አመራሩን ጥርስ ውስጥ እሚያስገባ ነገር መሆኑ አይቀርም፡፡

ካለው ነባራዊ ሁኔታ ተነስቼ ስቃኝው መንግስት ከሁለት እና ሶስት አመት በሃላ ‘እንዲህ ብለን ነበረ’ እያለ ችግሮቹ ሳይፈታ ሸፋፍኖ የመሄድ እድል አይኖረውም ማለት ይቻላል፡፡ከፍተኛ አመራሩ ሃላፊነት ወስጂያለው ሲል ከሙስና፣ መልካም ካልሆነ አስተዳደር እና የፍትህ መጏደል አኳያ እንዴት ነው በዝርዝር መታየት ያለበት? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው:: ሃላፊነት እምንወስደው እኛ የበላይ አመራር ነን የሚለው ውሳኔ በሆነ አይነት ህጋዊ፣ አስተዳደራዎ ወይም ፖለቲካዊ እርምጃ ካልታጀበ ትርጉሙ ምንድ ነው?

መፍትሄው ህዝብን ማእከል ያደረገ እንቅስቃሴ መሆን እንዳለበት የኢህአዴግ 10ኛው ጉባኤ ጭምር አመላክተዋል፡፡ ሆኖም የመፍትሄው እንቅስቃሴ (ንቅናቄ) ህገ መንግስታዊና ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መሰረት ያደረገ ካልሆነ ዘላቂነት ባለው መንገድ የሚፈለገው ውጤት አይገኝም፡፡ እነዚህ ተቋማት ለዴሞክራሲ ንቅናቄው ዋስትና መሆን እንደሚቻሉት ሁሉ፣ እየጎለበተ ላለው ፀረ ዴሞክራሲ ዝንባሌም መሳርያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ህገ መንግስታዊ ዴሞክራያዊ ተቋማት ስል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ስራ አስፈፃሚው ህግ ተርጓሚ በየእርከኑ ያሉትን ኮሚሽኖች እና ባለስልጣን መስርያ ቤቶች የፖለቲካ ድርጅቶች እና የሲቪል ማህበረሰቡን የሚያካትት ሰፊ ሃሳብ ነው፡፡

ለዚህ ፅሁፍ ሲባል ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የአንድ ለአምስት አደረጃጀትን ብቻ ለማየት መርጭያለሁ፣ ምክንያቱም ሁሉንም ተቋማት ማየት እማይቻልና የተመረጡበት መሰረታዊ ምክንያት ደግሞ ለነዚህ ሶስት ተቋማት እሚደረግ መሰረታዊ ለውጥ ላጠቃላይ የዴሞክራሲ ንቅናቄው እንደ መነሻ ከመጥቀም አልፎ የንቅናቄውን ቀጣይነትም ስለማያረጋግጥ ጭምር ነው፡፡ ይህ ሰላማዊ ንቅናቄ ካለ ስራ አስፈፃሚው ቅን እይታ ተሳትፎና አመራር ሊሳካ እንደማይቻል እምነነቴ ነው፡፡ ሆኖም መደረግ ላለበት የዴሞክራሲ ንቅናቄ የጎላ ተቃውሞ እሚመጣዉም ከስራ አስፃሚው እንደሚሆን ይገባኛል፡፡ ይህ ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ስራ አስፈፃሚ አካል ብዙ ስልጣኖች፣ አለም አቀፍ ትስስሮች፣ ጠንካራ የፋይናንስ አቅም፣ አደረጃጀት፣ ታንክ ያሉትና የደህንነት ተቋማት የሚያንቀሳቅስ አካል በመሆኑ የዚህ ክፍል ተቃውሞ ክብደቱ እጅግ የጎላ ያደርገዋል፡፡

ላሉት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ዕውቅና መስጠት እና ተያይዞ የመጣው የአመራሩ ሃላፊነቱ የኛ ነው የሚል ድምዳሜ ትልቅ እርምጃ ቢሆንም የችግሮቹ መሰረታዊ መንስኤዎች እና ሊወሰዱ ስለሚገባቸው መፍትሄዎች ግን በጥልቀት የታየ አይመስለኝም። በተለይ ከ 10ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ማግስት በአንድ በኩል የመቀዛቀዝ በሌላ በኩል ደግሞ ችግሮች ቢኖሩም ብዙ እሚያስጨንቁ አይደሉም የማለት እና የማጣጣል አዝማምያዎች እየታዩ ነው። ጠቅላይ ሚንስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ምክርቤቶችን አስመልክተው፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ደመቀም ሚድያን አስመልክተው የተናገሩት ነገር ገምቢ እና አበረታች ቢሆንም ሌሎች የመንግስት አካላት ግን ችግሩ ቀለል አድርገው ሲመለከቱ እያየን ነው። ይሄ ተቃርኖም የራሱ ተፅእኖ ሊያሳድር ስለሚችል ሊታሰብለት ይገባል። አሉን ለተባሉት ችግሮቻችን ተቛማዊ መልክ ያለው የዴሞክራሲ ተቛሞች ግንባታ ነው መሰረታዊው መፍትሄ። እነዚህ ተቛማት ገንቢ ሚና ሊጫወቱ እሚችሉት ተገቢ ስራቸዉን በአግባቡ ማከናወን ሲችሉ ነው። ይህ ለማድረግ ደግሞ ጠንካራ ተቛማዊ ስብእና መላበስ ይኖራቸዋል። ይህ ምን ማለት ነው?

5.1 ጠንካራ ተቛማዊ ስብእና (Strong Institutional Integrity)

ቀደም ብሎ እንደተገለጸው የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ሙስና፣ ብልሹ አስተዳደር እና የፍትህ እጦት ለሚባል በሽታዎች ዋና መፍትሄ ነው፡፡ ተቋም ሲባል ግን እምነት እሚጣልበት እና ቅንነት ያለው ሲሆን ብቻ ነው፡፡ በእንግሊዝኛው Institutional intergirty እንደሚባለው፡፡ ለአንድ ተቛም ስብእና ማለት የልቀት፣ የታማኝነት እና ህጋዊነት መመዘኛዎችን አካቶ ለመልካም የስራ ባህሪ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚይሳየው ቁርጠኝነት ነው።ሮቢን ክረይኪ ውጤታማ የ ተቛማዊ ስብእና መለክያ አለ ይለናል፡፡ እንደሱ አገላለፅ መጀመርያ የስርዓቱ ጤንነት እንደ መፈተሻ ሊጠቅሙን እሚችሉ ስራዎች መለየት፣ በሁለተኛ ደረጃ የስራዎቹ ስኬታማ አፈፃፀም ሊያመላክቱ እሚችሉ መመዘኛ ወይም መለክያዎችን ማበጀት፣ በሶስተኛ ደረጃ ያስቀመጥነዉን መለክያ መሰረት አድርገን ሪፖርት እምናቀርብበት ስርአት መገንባት፣ በመጨረሻም ተሰሩ የተባሉትን ስራዎች በተጨባጭ መስራታቸዉን (መሬት ላይ መኖራቸዉን) ቀድመን ካዘጋጀነው መለክያ ወይም መመዘኛ አንፃር ምን እንደሚመስሉ መገምገም ነው ይለናል። (2013).

የግለሰብ ስብእና የፓርቲ ስብእና እና ለመረጠው ተቛም ያለው ስብእና ተፃራሪ ሊሆን ይችላሉ። በቀጣይ ዉጥረትም ይኖራሉ። ለምሳሌ በተወካዮች ምክር ቤት ብንወስድ ከህገ መንግስታዊ ግዴታ ስንነሳ በአንድ በኩል ለህሊናው መቆም አለበት ይላል፤ በሌላ በኩል ለህገ መንግስቱ ይላል፤ በተጨማሪም የፓርቲ አደረጃጀት አባሉ ለፓርቲው ማሳየት ያለበት ስብእና አለ። በነዚህ ሶስት መሃል ያለው ቅራኔ አፈታት ዴሞክራሲዉን ወደፊት ወይም ወደሃላ ሊያስቀጥለው ይችላል። በአንድ በኩል ያለምንም ጥያቄ ለፓርቲ አቛም ድምፅ መስጠት አማራጭ ሃሳቦችን ያቐጭጫል፤ በሌላ መንገድ እያንዳንዱ የመሰለዉን ብቻ ከወሰነ ተደራጅቶ መታገልን ዉድቅ ያደርጋል። ጤናማ ዴሞክራሲ በነዚህ መሃል ያለዉን ዉጥረት አቻችሎ ይሄዳል። አብዛኛው ግዜ ለፓርቲ ዉሳኔ ድምፁን ቢሰጥም ከፓርቲው ወይም ከህገ መንግስታዊ መርሖች ወይም ስብእናው ተነስቶ ሊቃወም ይችላል። እንዲህ ዓይነት አቻቻይ ስርዓት ሲዘረጋ ጤናማ ዴሞክራሲ በተቛማት አለ ሊባል ይችላል።

የማዂዋየር መዝገበ ቃላት ስብእና ማለት የሞራል መርሆች እና ባህሪዎች ጥንካሬ፣ ቀናነት እና ቅንነት ነው ይላል። ሙሉ እና ሳያንሱ መገኘት ወይም አለመታወር ነው ይላል።. እያንዳንዱ ተቛም ስብእናዉን ጠብቆ የተጣለበትን ሃላፊነት መወጣት እና መብቶቹን ባግባቡ መጠቀም እሚችልበት ድባብ መፍጠር ቁልፍ መፍትሄ ነው። መንግስት የተቛማቱን ተገቢ ስብእና እሚጠብቁ እርምጃዎች እያከበረ የዴሞክራታይዜሽን ሃይል መሆን ገንቢው አማራጩ ሲሆን ይህን ችላ ካለ ግን መሃል ላይ መስፈር ብሎ ነገር ስለማይኖር የኢ-ዴሞክራታይዜሽን ሃይል ነው ሊሆን እሚችለው።

ያለን ህገ መንግስት በጥብቅ ተግባራዊ ማድረግ ዋናው መፍትሄ ነው፤ ይህን ለማድረግ ህገ መንግስቱ በጥብቅ ተግባራዊ ሲሆን ለበሽታዎቻችን መፍትሄ ማግኘት እንደሚቻል እሚያምን ቁርጠኛ አመራር ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማለት የህግ አስፈፃሚው አካል ቁርጠኝነት በጣም ያስፈልጋል ማለት ነው። ቀደም ብሎ በተጠቀሰው የኢህአዴግ ፅሁፍ የሚከተለውን ሰፍሮ እናገኛለን፡፡ “የህግ አስፈፃመሚ አካል የህግ የበላይት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ እንደ ፖሊሲና የመከላከያ ሃይል ያሉ ተቋሞችን የሚቆጣጠር በመሆኑ ለዴሞክራያዊ ስርዓት ግንባታው ታማኝ ካልሆነ የዴሞክራሲ ተቋሞችን አፈራርሶ ስርአቱን ለአደጋ ሊያጋልጠው ይችላል፡፡ በተግባርም የዴሞክራሲ ስርአትን የመፈታተን አደጋ የሚመነጨው በአብዛኛው ከህግ አስፈፃሚው አካል ነው” ይላል በገጽ 70 ላይ፡፡

ስለዚህ ህገ መንግስት በጥብቅ ተግባራዊ ማድረግ ማለት ህገ መንግስታዊነት በተግባር ማረጋገጥ እና ለሁሉም ዘላቂ ዋስትና መሆን የሚችል ህገ መንግስታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መገንባት ማለት ነው፡፡ ይህ ሲሆን ብቻ ነው አንድ ህገ መንግስት ትርጉም እና አርባና የሚኖረው፡፡

አገራዊ እና መንግስታዊ መዋቅሮች ከፓርቲ ተፅዕኖ አንፃራዊ ነፃነት እንዲኖራቸው ማስቻል፡፡ አንዱ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ምሰሶ የሆነው የተቋማት እርስ በርስ የመቆጣጠር እና ሚዛን የመጠበቅ ነው፡፡ ይህን እውን ለማድረግ የሚቻለው ደግሞ የመንግስት፣ የፓርቲ እና አገራዊ የሆኑትን ተቋማት ተገቢ ድንበራቸው ጠብቀው በተለይ ከፓርቲ መዋቅር ተነፃፃሪ ነፃነት ሲያገኝ ነው፡፡ ፓርቲ መንግስታዊ እና አገራዊ ተቋማትን በብቸኝነት ሲቆጣጠር በእኩልነት የተመሰረተ የምርጫ ውድድር አይኖርም በዚህም ምክንያት የህዝብ መሰረታዊ ዴሞክራያዊ እና ህገ መንግስታዊ መብቱ ይጣሳል፡፡ ይህ አንድ ምሳሌ ነው፡፡ በተጨማሪም ፓርቲ፣ መንግስት እና ቋሚ አገራዊ ተቋማት አንድ እና አንድ ሆነው የፓርቲው መሳርያ ከሆኑ፣ በፓርቲው ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮች ባጭር ግዜና በቀጥታ ወደ መንግስታዊ እና አገራዊ ተቋማት ተዛምተው መላ አገሪትዋን ሊበታትን የሚችል ክፍተት እና ተጋላጭነት ሊያስከትል ስለሚችል ጉዳቱ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ይሄም ለዴሞክራያዊ ስርዓት ግንባታ እንቅፋት ይሆናል፡፡

ሎርድ አክተን የሚባል ሰውዬ “Power corrupts, and absolute power corrupts absolutely” ይላል፡፡ የፓርቲ መዋቅር የመንግስት እና አገራዊ ተቋማትን ነፃነት ነፍጎ የግሉ ካደረገ ፍፁማዊ ሃይል ሆኖ ለቁጥጥር እሚያስቸግር ፈላጭ ቆራጭ የሆነ ፀረ ዴሞክራሲያዊ አስፈፃሚ ነው እሚሆነው፡፡ በዚህ እና በብዙ ሌሎች ምክንያቶች ምክንያት ነው የመንግስት እና አገራዊ ተቋማት ከፓርቲ መዋቅር አንፃራዊ ነፃነት ያስፈልጋቸዋል የምንለው፡፡ከስር እምታዮት ምስል በዴሞክራስያዊ አስተዳደር ተቛማት እና ሂደቶች፣ የነዚህ ጥራት እና ጥራቱ ላይ ተፅእኖ እሚያሳድሩ አላባውያን መሃል ያለው ግንኙነት እሚያሳይ ሞዴል ነው። በተለይ የቡዙሓነት ፀጋ በተጎናፀፉት እንደኛ ያሉ ታዳጊ አገሮች የሚገኙ የዴሞክራሲ ተቛማት በህዝቦች መሃል ሊገኝ የሚችለዉን የተለያዩ ፍላጎቶች እና እሴቶችን መሰረት አድርገው መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል።
Diagram-two_thumb
የአስተዳደር ይዘት እና ጥራት ላይ ተፅእኖ እሚያሳድሩ ዓዉዳዊ አላባውያን የሚለው፤ የተለያየ ማንነት ያላቸው የብሄር፣ በሄረሰብ፣ሃይማኖት፣የፆታ እና ሌሎች የማንነት ጥያቄዎች ሊያነሱ የሚችሉ ጉዳዮች ስርዓቱ እንዴት ያቻችላል (Accommodate ያደርጋል) የሚለዉን ማየት ጠቃሚ ነው። በተለይ የተለያዩ ቁሳዊ ፍላጎቶች እና የእሴት ጥያቄዎች ባለበት እነዚህ ሃይሎች ፍላጎታቸውን እና እሴቶቻቸዉን ማራመድ የሚችሉበት ድባብ መፈጠር አለበት። ሃሳባቸዉን ሳይሸማቀቁ መግለፅ መቻል አለባቸው፤ ይህ እንዲሆን የዴሞክራሲ መስተዳድር መኖር እና ዉጤታማ ተቓሞችና ሂደቶች በስምነቱ ባህርያት መለካት ያስፈልጋቸዋል:: ሃሳባቸዉን ሳይሸማቀቁ መግለፅ መቻል አለባቸው፤ ጠባብ፣ ትምክህተኛ፣ አክራሪ ተብለው ሳይፈረጁ። ጠባብነት፣ ትምክህት እና አክራሪነት ቢኖርም እኚህ ታርጋዎች እሚለጠፉት የማስረዳት አቅም ሲታጣ እንደሆነ እየተገነዘብን ነው።

ጠባብነት፣ ትምክህተኝነት እና አክራሪነት እንዲያብቡ እና ጉልበት አግኝተው የስጋት ምንጭ ሊሆኑ እሚችሉት መልካም አስተዳደር ሲጠፋ እና ፍት ሃዊ ልማት ማረጋገጥ ሳይቻል ሲቀር ነው። አሳታፊ፣ ግልፅ፣ ተጠያቂነት ያለው ለሚነሱ ጥያቄዎች ባፋጣኝ መልስ መስጠት የሚችል ብቁ እና ቀልጣፋ አስተዳደር ካለ ጠባብነት፣ ትምክህተኝነት እና አክራሪነት ሊፋፉበት እሚችሉበት እድል ስለሚዘጋ የስጋት ምንጭ አይሆኑም። ስለዚ ለጠባብነት፣ ትምክህተኝነት እና አክራሪነት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥረው የቀጨጨ የዴሞክራሲ ሁኔታ ስለሆነ እነዚህ ችግሮች ማስወገድ ካለብን ምንጫቸው የቀጨጨ ዴሞክራስያዊ ሁኔታ መሆኑ መገንዘብ አለብን። መሰረታዊ ምንጩ ሳይገባን ችግራችን ጠባብነት፣ ትምክህተኝነት እና አክራሪነት ነው ማለት ግን አጠቃላይ ሁኔታው እንዳለመረዳት ይቆጠራል።

5.2 ምክር ቤቶች የዴሞክራስያዊ እንቕስቃስያችን ወሳኝ አምዶች ናቸው

በኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 8 መሰረት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤቶች ናቸው ይላል፡፡ በዚህው አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 መሰረትም “ሉዓላዊነታቸውም የሚገልፀው በዚህ ሕገ መንግስት መሰረት በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸውና በቀጥታ በሚያዳርጉት ተሳትፎ አማካይነት ይሆናል” ይላል፡፡ ህዝቦች የሚወከሉባቸው ምክር ቤቶች (በየደረጃው ያሉት) መንግስት ወይም አስፈፃሚው አካል በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙርያ ይወያያሉ፣ ይራከራሉ፣ ቁጥጥር ያደርጋሉ፣ የተሰራውን ለህዝብ ያስተውቃሉ፣ የህዝብን አስተያየት እና ፍላጎት ላስፈፃሚ ያደርሳሉ፣ እንዲሁም አስፈፃሚው አካል ገቢ እሚሰበሰብበትን እና ስራ ላይ እሚያውልበትን አግባብ አሳይተው ተግባሩ እንዲያከናውን ስልጣን ይሰጣሉ፡፡ ይህንን ትልቅ ሃላፊነት ከሚወጡበት የአሰራር አይነቶች ደግሞ መንግስት በሚያቀርባቸው ረቂቆች ላይ ተወያይቶ መወሰን፣ የጥያቄ /ተጠየቅ መድረኮችን ማሰናዳት እና ቋሚ ኮሚቴዎችን አቋቁሞ ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በነሐሴ 1992 ዓ.ም “የዴሞክራሲ መሰረታዊ ጥያቄዎች በኢትዮጵያ” በሚል ርዕሰ ለውይይት በቀረበው የኢህአዴግ ፅሁፍ ላይ የሚከተለው ሰፍሮ እናገኛለን “አብዮታዊ ዴሞክራሲ ይህ (የህግ የበላይነት መርህ) በተሞላ መልክ ሊተገበር የሚችለው ከግልፅነትና ከተጠያቂነት ጋር ተዛምዶ መፈፀም ሲችል ነው የሚል እምነት አለው:: ግልፅነት ሲባል በየደረጃው ያሉ የመንግስት ሃላፊዎች የሚወሰንዎቸው ውሳኔዎች ምን እንደሆኑ፣ በየትኛው አግባብ እንደሚወሰኑ፣ ለምን እንደሚወሰኑ፣ ውጤቱ ምን እንደሆነ ግልፅ መሆን አለባቸው መደበቅ የለባቸውም ማለት ነው” (1992፡42) ይላል፡፡ ባጭሩ ተጠያቂነት በሌለበት የህግ የበላይነት በተሟላ መልክ ለመተግበር አይቻልም ይላል፡፡ ይህ ሰነድ አስከትሎም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ህዝቡ ተወካዮችን እንዲመርጥ ብቻ ሳይሆን በሚገባ የሚቆጣጠርበት አሰራርም ይከተላል …. በዚህ መስክ አብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚከተለው አሰራር ሊበራል ዴሞክራሲን መድረስ ወደሚችለው ከፍተኛ ጫፉ የሚያደርሰስና ህዝባዊ ባህሪ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው” (1992፡62) ይላል።

መሪው ድርጅት ኢህአዴግ የምክር ቤቶችን የበላይነት አስመልክቶ ቅድም በተጠቀሰው ፅሁፍ እንዲህ ይላል “አብዮታዊ ዴሞክራሲ በህዝብ የተመረጡ ምክር ቤቶች ብቸኛ ህጋዊ የሆኑ ወሳኝ አካላት መሆናቸውንና በዚህ መንፈስ መስራት ያለባቸው መሆናቸውን ይቀበላል” (1992፡63) ይላል። አያይዞም ህዝቡ ምን እንደተወሰነ ብቻ ሳይሆን በማንና ለምን እንደተወሰነም ሊያውቅና ሊከታተል ይገባል፡፡

5.2.1 ህገ መንግስታችን እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 50/3 ላይ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስልጣን አካል የፌዴራሉ መንግስት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው፡፡ ተጠሪነቱም ለሀገሪቱ ህዝብ ነው፤ የክልል ከፍተኛ የስልጣን አካል የክልሉ ምክር ቤት ነው፤ ተጠሪነቱም ለወከለው ክልል ህዝብ ነው ይላል፤ ቀደም ብለን እንደጠቀስነው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም ህገ መንግስታዊ ድንጋጌውን እንደሚቀበል አይተናል፡፡ ህገ መንግስቱ አስከትሎም የምክር ቤቱ አባላት የመላው ህዝብ ተወካዮች ናቸው፡፡ ተገዥታቸውም፤

ሀ. ለሕገ መንግስቱ

ለ. ለሕዝቡ እና

ሐ. ለሕሊናቸው ብቻ ይሆናል” ይላል ።

በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 55 መሠረትየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰፋ ያለ ሥልጣንና ተግባር የተሰጠው ሲሆን፤ በአንቀፅ 72/2 መሰረት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ካቢንያቸው ተጠሪነነታቸው ለተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ ይደነግጋል። በማስታወቅያ ሚኒስቴር ፕሬስና ኦድዮቪዥዋል መምርያ በ 1994 ዓ.ም በታተመው “በኢትዮጵያ የዴሞክራስያዊ ስርአት ግንባታ” እሚለው ፁሁፍ ላይ የሚከተለዉን ሰፍሮ እናገኛለን። “ምክር ቤቶች የህዝቡ ሉአላዊነት መገለጫ የዴሞክራስያዊ አስተዳደር እምብርትና የዴሞክራስያዊ አገዛዝ አዉራ ተቛሞች ናቸው። ሌሎች የዴሞክራስያዊ አገዛዝ ተቛሞች እና ድርጅቶች የሚመሰረቱት በምክር ቤቶቹና ምክር ቤቶቹ በሚስርዋቸው ስራዎች ላይ ነው። በመሆኑም የነዚህ ምክርቤቶች መቛቛምና መጠናከር ለዴሞክራስያዊ ስርአታችን መጠናከር ወሳኝ ነው።” (ገፅ, 58-59)

5.2.2 የተወካዮች ምክርቤት ዓይነቶች

ዊልያም ሮቢንሰን እና ኔልሰን ፖልስፐይ በዓለም ላይ ያሉ የተወካዮች ምክር ቤቶችን በአራት ይከፍላዋቸዋል። እነዚህም፡- A. Transformative Legislature; B. Arena Legislatures; C. Emerging Legislatures; D. Rubber Stamp Legislature በማለት ይዘርዝርዋቸዋል።

1.Rubber Stamp Legislature

ማህተም መቺ ምክርቤቶች (Rubber Stamp Legislature) በጣም ቀላል የምክርቤት አይነቶች ናቸው። እነዚህ ምክርቤቶች ሌላ ቦታ የተወሰነን ዉሳኔን ማፅደቅ ነው ስራቸው። የዚህ ዓይነት ምክር ቤቶች ዓይነተኛ ምሳሌዎች በአምባገነን መንግስታት ስር የሚገኙ ምክርቤቶች ሲሆኑ የስራ አስፈፃሚው ዉሳኔዎችን ሳያንገራግሩ ለይምሰል ከማፀደቅ ያለፈ ሚና የላቸዉም። እንዲህ አይነት ምክር ቤቶች ኢ-ዴሞክራስያዊ በሆኑ አገሮች ብቻ እሚገኝ አይደለም ይላሉ አጥኚዎቹ። ለምሳሌ ባደጉ አገራት እሚገኙ የሰራተኞች ህብረት ምክርቤቶች የመሪዎቻቸዉን ዉሳኔ ለማፅደቅ ነው እሚሰበሰቡት ብለው እንደ አብነት ይጠቅሱታል። ዓይነተኛ አብነት ተድርጎ እሚወሰደው ደግሞ የ ቀደሞው ሶቭየት ህብረት ምክር ቤት ነው።

2.Arena Legislatures

እንዲህ አይነት ምክርቤቶች ደግሞ በማህበረሰቡ ዉስጥ ያሉ የተለያዩ ሃሳቦች እሚወከሉበት እና ተናጋሪ እሚያገኙበት ዓይነት ምክር ቤት ነው። ሞቅ ያለ የፖሊሲ ክርክር እና መንግስትን በተለያየ መለክያ መገምገም እሚችል ዓይነት ፓርላማ ነው። ዓይነተኛ አብነት ተድርጎ እሚወሰደው ደግሞ የኢንግሊዝ የታችኛው ምክር ቤት (House of commons) ነው። እንዲህ ዓይነት ምክርቤቶች በማህበረሰቡ ያሉ የተለያዩ ፍላጎቶች መወከል ስለሚያስችሉ ነው እንዲህ ተደርገው እሚተገበሩት። ስለዚ ዋና ስራቸው በጉዳዮች ዘርያ መከራከር እና ከተለያየ አቅጣጫ ግምገማ ማካሄድ ነው። ስለዚ እንዲህ ዓይነት ምክር ቤቶች ስራቸዉን በአግባቡ ማከናወን እሚያስችላቸው ዉስጣዊ አደረጃጀት እና አሰራር ያስፈልጋቸዋል።

3. Emerging legislatures

እንዲህ ዓይነት ምክርቤቶች በሽግግር ወቅት እሚፈጠሩ ዓይነት ምክርቤቶች ናቸው። በዚህ አዃሃን የተለመደው መንገድ ብዙ ዉስጣዊ መዋቅር እና አቅም ሳይኖረው ማህበረሰቡን በመምራት ረገድ የራሱን አስተዋፅኦ ለማድረግ እሚሞክር የምክር ቤት ዓይነት ነው። የቦሊቭያው እና በርከት ያሉ የላቲን አሜሪካ እንዲሁም የቀደሞ ሶቭየት ህብረት አባል ሃገራት የነበሩ ምክርቤቶች የዚህ ዓይነት ምክር ቤት ተጠቃሽ አብነቶች ናቸው። በቅርቡ ሜክሲኮ ላይ እየታየ ያለ ከ አንድ ፓርቲ የበላይነት በዉድ ድር ወደሚመሰረት ስርዓት የሚደረገው ሽግግርም የምክርቤቱን አቅም እሚገነባ እና ከአስፈፃሚው ጥገኝነት እሚያላቅቀው ነው ይላሉ አጥኒዎቹ።

4. Transformative legislatures

ይህ ዓይነት ምክርቤት ደግሞ ብርቅየና እምብዛም እማይገኝ የምክርቤት ዓይነት ነው ይሉታል። እንዲህ ዓይነት ምክር ቤቶች የዉክልና ዓቅማቸዉም የማህበረሰቡን ፍላጎት ቅርፅ ማስያዙንም የሚችል ዓይነት ምክር ቤቶች ናቸው። ባጭሩ እንዲህ አይነት ምክርቤቶች የዉክልና ባህሪያቸው እንደተጠበቀ ሆኖ መምራት ላይም ይሳተፋሉ። ይህ ለምድረግ እንዲህ ዓይነት ምክር ቤቶች ስራቸዉን ባግባቡ ለማከናወን እሚያስችል ዉስጣዊ መዋቅር እና ግጭቶችንና ልዮነቶችን እሚያስተናግዱበት አሰራር ይፈልጋል። የአሬናው ዓይነት ምክርቤት ባካባቢው ያለዉን ሙቀት እንደሚለካ ቴርሞሜትር ሲሆን የ ትራንስፎርማቲቩ ምክርቤት ደግሞ አካባቢው ላይ ምን ያህል ሙቀት መኖር አለበት ብሎ እንደሚወስን ተርሞስታት ነው ይላል። እንደኔ እምነት የአሜሪካው ምክርቤት ለሰርዓቱ የቆመ ምክርቤት እና ዉግንናው ከጭቁኖች ያልሆነ መዋቅር ስለሆነ ትራንስፎርማቲቭ እሚሆነው ስርዓቱን ለመጠበቅ እና የዋና ፖለቲካዊ ተዋንያንን ጥቅም ለማስከበር የቆመ መዋቅር ነው እላለሁ።

5.2.3 የተወካዮች ምክር ቤት እውነተኛ ገፅታ

የኢትዮጵያ ምክርቤት በ Emerging እና በ Rubber Stamp መሃል እሚገኝ፤ አስፈላጊ መሰረታዊ ለውጥ ከተደረገለት ተገቢ ሚናዉን መጫወት እሚችል ምክርቤት ነው ያለን። ተወካዮች ምክር ቤት ከላይ በህገ መንግስቱ እንደተዘረዘረው ግዴታዉ እየተውጣ ነዉ የሚለዉ ለመመለስ መዋቅራዊ መነሻዉ ማጥናት ተገቢ ነዉ፡፡ መንግስትና ገዢ ፓርቲ አንድ እና አንድ ሆነዉ የማይለዩበት በሆኑበት ምክር ቤት አባላት አንድ የሚታይ ዉጥረት ነዉ፡፡

ይሄ ውጥረት በተወካዮች ህሊና፣ ለወከሉት ማህበረሰብ እና ለህገ መንግስቱ ባላቸው ታማኝነት፣ ለፓርቲ ማስመስከር በሚገባቸው ታማኝት እና የኑሮ ጉዳይ በሚፈጥረው ግፊት ምክንያት የሚፈጠር ውጥረት ነው፡፡ ባጭሩ ሲገቡ በሚፈፅሙት መሃላ እና የፓርትያቸው ዲሲፒሊናዊ አሰራር እና ኑሮ መሃከል የሚከሰት ውጥረት ነው፡፡ ይህ ነው ስብእናዎችን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ አቻችሎ አለመሄድ እሚያስከትለው መዘዝ። እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለበን ጉዳይ መንግስት ዋና ኢንቨስተር መሆኑን ብቻ ሳይሆን የElected dictatorship”ም አለማዊ እውነታ መሆኑ ነው፡፡

ከዚህ ተነስተን ፓርላማው ባለፈው የGTP1 ዘመን በኢኮኖሚ አድገቱ እና በዴሞክራሲ ዙሪያ ምን ሚና ነበረው? ስንል የሚሰጠን ምስል ደብዛዛ ነው፡፡ በተመዘገበው የኢኮኖሚ እድገት አወንታዊ ሚና ነበረው አልነበረዉም ብሎ አስተያየት ከመስጠት በፊት፤ በመጀመርያ ምክር ቤቱ አሳታፊ፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት የነበረው አሰራር ነበረው ውይ? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ ከአስፈፃሚው የመጣዉን አዋጅ/ሹመት ወይም ሌላ ነገር ምክርቤቱ ተገቢ ከመሰለው ሳይቀበል ቀርቶ reject ሲያደርግ፤ መስተካከል ካለበት ማስተካከያ እንዲደረግ መልሶ ወደ ስራ አስፈፃሚወ ልከዋል የሚል በመገናኛ ብዙሃን የሰማሁበት ግዜ አላስታዉስም። ህዝቦች የማወቅ መብት እና ምክር ቤቱ የማሳውቅ ግድታ እነዳላቸው ልብ ይሏል::

ሁልግዜ የምንሰማዉ በሙሉ ወይም በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ ሲባል ነው። ከቅርብ ግዜ ወዲህ አስፈፃሚዉን የመቆጣጠር አዝማምያ ቢኖርም ወጥነት የሌለው እና የተቆራረጠ ነገር ነው።ባጠቃላይ ሲታይ ምክር ቤቱ የመጣለትን የየዉሳኔ ሀሳብ ሲቅረብ ለዝረዝር እይታ ወደ እሚመለከተው ኮሚቴ መስተላለፍ እና የህዝብ ድምፅ የሚስማበተ መድርክ ማዝጋጀት እንደ ጥሩ አስራር ሊወሰድ የሚችል ሆኖ ድመፁ መከብሩን ግን የምናዉቅበት መንገድ የለም። የምክር ቤት አባሎች ለህገ-መንገሰቱ ና ለህሊናቸው ተገዥ መሆንና የመረጣቸው ህዝብና የፓርቲያቸው መመረያ በሚጋጭበት ሁኔታ የሚከተሉት አቅጣጨ ምን እንደሆነ የሚታወቅበት ሁኔታ የለም፡፡ እንደ ተቛም እለይ በተቀመጡት መስፍርቶች ሲመዘንም መልሱ ያው ነው፡፡እጅ እያወጡ ከማፅደቅ የዘለለ ከፍተኛ ትርጉም ያለው ሚና ነበረው ለማለት ያስቸግራል፡፡ በቅርብ ግዜ ት ዝታችን የተባበሩት የአሜሪካ መንግስታት ኮንግሬስ የኢራን ኑክሌር ስምምነት እነ እከሌ የሚባሉት ዴሞክራቶች ተቃወሙት ሲባል እንስማልን፡፡ የተባበሩት ኪነግደም ገዢው ኮነስረቫቲቭ ፓርቲ አውሮፓ ሕብረት ሪፈረነደም አካሄድ እሚመለከት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ የተወሰኑ አባሎቹ ስላልደገፉት ውድቅ ሆነ እነስማልን ወ.ዘ.ተ። እኛ አገር ዝምታ ነው ምናወቀው ነገር የለም:: የመረጥነዉን ወኪል እምንመዝንበት መረጃ የለንም፤ ለፓርቲ ነው የመረጣቹሁት ካልተባለን በስተቀር!! ድበቅነት በዛ ከልክ ያለፈ ሆነ!!!

ከዴሞክራሲ አኳያ ፓርላማው በ GTP 1 የነበረው ሚና ካነሳን ግን ምንም ሚና አልነበረውም ለማለት ያስደፍራል፡፡ እጅግ ብዙ ችግሮች እያሉ ሁሉም ነገር ሰላም እንደሆነ በሚያስመስል መልኩ “ዝምተኛ” ሆኖ አልፎታል፡፡ ፍትህ ሲጠፋ፣ ዜጎች ሲበደሉ፣ አስፃሚውን ደፍሮ የታገለበት አግባብ ስላልነበረ በዚህ ረገድ “የሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱ” ሳያረጋግጥ እንዳለፈ ይቆጠራል፡፡

የህዝቡ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጣቸውን መራጭ ህዝብ ንቁና ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ እሚያደርጉበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለበት፡፡ አሁን ባብዛኛው እንደምታዘበው የመራጭ ህዝብ እና የተመራጭ ግለሰብ ግንኙነት ጎልቶ የሚታየው በምርጫ ሰአት ግዜ ነው፡፡ መራጮች ተወካዮውን በቀጣይነት እያገኝ ወቅታዊ ሁኔታቸውን ፍላጎታቸውንና ስጋቶቻቸውን እሚያስረዱበት አሰራር እና ሁኔታ መፈጠር ተገቢ ነው፡፡ ሲጀምር የህዝብ ተወካዮች እንደመሆናቸው መጠን የህዝቡን የልብ ትርታ ተቋማዊ በሆነ መልኩ በቀጣይነት እንዲገነዘቡ መራጩ ህዝብ ለተሳትፎ እና ቁጥጥር እሚመች ሁናቴ ማግኘት መቻል አለበት፡፡ አለበለዝያ በየአምስት አመቱ ምርጫ በመጣ ቁጥር ብቻ እየተገናኘ ትክክለኛ የመራጩን ህዝብ ተወካይ ናቸው ለማለት ያስቸግራል፡፡

ያገሪትዋን ከፍተኛ ስልጣን በህገ መንግስት የተረጋገጠለት ተቋም አሁን ያሉት አማራጮች ሁለት ናቸው፡፡ አንደኛው አማራጭ ህገ መንግስታዊ ስልጣኑን ተጠቅሞ የዜጎችን ጥቅም ማስከበር ሁለተኛው አማራጭ ህገ መንግስታዊ ስልጣኑን መጠቀም እማይቻል እና የህዝባችን አደራ መሸከም ካልቻለ ያገሪትዋን ሃብት ያላግባብ ከሚባክን ህዝበ ውሳኔ አዘጋጅቶ አይረቤነቱን ህጋዊ ድጋፍ ሰጥቶ ተቋሙን ማፍረስ፡፡ ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስትነት ነው እሚከተለው በሚል ሃገር በልማቱም በዴሞክራሲውም ላይ የጎላ ሚና መጫወት እማይችል ፓርላማ ትርፉ ሃብትን፣ ጉልበትን እና ግዜን ማባከን ነው፤ በዚህ ምክንያትም ነው “እውን ኢትዮጵያ ፓርላማ አላትን?” ብለው ብዙዎች የሚጠይቁት፡፡ ምክርቤቱ ህገ መንግስታዊ ሃላፊነቱ እየተወጣ መሆን ያለበትን እየሆነ ከሄደ የዴሞክራታይዜሽን ሃይል መሆኑ አይቀርም፤ ይህን ችላ ካለ ግን መሃል ላይ መስፈር ብሎ ነገር ስለማይኖር ሃብት አባካኝ ተቛም ከመሆን አልፎ የኢ-ዴሞክራታይዜሽን ሃይል ነው ሊሆን እሚችለው።

የኢትዮጵያ መንግስት በ 1994 ዓ.ም ባሳተመው ፁሁፍ ላይ የሚከተለዉን ይላል “በመጀመርያ መቀመጥ ያለብት ችግር የአባላቱ (የምክር ቤቱ) ብቃት ነው። የምክር ቤቶቹ ስልጣንና ተግባር ምን ያህል ሰፊና ወሳኝ እንደሆነ፤ ምክር ቤቶቹ ሃላፊነታቸዉን በሚገባ መወጣታቸው ለዴሞክራስያዊ ስርአታችን ማበብ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ በመገንዘብ ረገድ በምክር ቤት አባላትም ሆነ በሌላው የህብረተሰብ ክፍል፣ በየደረጃው ባሉ የህግ አስፈፃሚ አካላት ወዘተ በቂ ግንዛቤ የተያዘበት ጉዳይ አይደለም።” አሁንስ ከ 14 ዓመት በኃላ የተለየ ሁኔታ አለ ወይ? ለዚህም ነው ተቛማቱ ስለ ተግባር እና ሃላፊነታቸው ጠንከር ያለ ግምገማ እና ራስን መፈተሽ አስፈላጊ ሆኖ የሚገኝው።
5.3 የመገናኛ ብዙሃን

የመገናኛ ብዙሃን በመንግሰት፤ በድርጅት እና የግል በሚል ለያይቶ ማየት ይበጃል:: የመገናኛ ብዙሃን ህዝቡን ለልማት ባመዘጋጀት እና በማንቀሳቀስ እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ ከባቢው እንዲሰፋ እና እንዲጠናከር የሚጨወቱት ሚና ላቅ ያለ ነው፡፡ በህዝብ እና በመንግስት መሃል ክፍተት እንዳይሰፋ፣ መንግስትም የህብዝን ነባራዊ ችግር ለመገንዘብ እሚረዳው መረጃ እሚያገኝበት፣ ህዝብም መንግስት እያደረገ ስላለው እንቅስቃ እሚገነዘብበት መሳርያ ነው ሚድያ፡፡ ከህግ አውጪው፣ ህግ ተርጓሚው እና ህግ አስፈፃሚው አካል ጎን ለጎን አራተኛው አምድ እየተባለ እሚጠቀሰው ሚድያ በመንግስት አሰራር ግልፅነት፣ ተጠያቂነት፣ ፍትሕ፣ ህገ መንስታዊ ሚዛን እንዲኖር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ በሃገራችን ትላልቅ የሚድያ ተቋማት በመንግስት ስር ያሉ የመገናኛ ብዙሃን ናቸው፡፡

እነዚህስ ቢሆኑ ከልማት እና ከዴሞክራሲ አኳያ የነበራቸው ሚና ምን ይመስላል? በኢኮኖሚያዊ ልማቱ ዙሪያ ምልአተ ህዝቡን በሚፈለገው መንገድ አንቅተዋል፣ ተአማኒ ሆነው ህዝብን አንቀሳቅሰዋል ለማለት ቢከብድም የተወሰነም ቢሆን አስተዋፅኦ ነበረው ማለት ይቻላል፡፡ ከዴሞክራሲ አኳያ ግን ሚናቸው አግላይ ነበር፡፡ እነዚህ “የህዝብ” መገናኛ ብዙሃን ከፓርቲ የፕሮፓጋንዳ መሳርያነት ያለፈ ማንነት መላበስ ሳይችሉ ስልጣን ላይ ያለውን ግንባር በግልፅ አድልዎ እያገለገሉ GTP 1ን ጨርሰውታል::

በልማቱ ዙርያ ፈጠራ በታከለበት መንገድ ምልአተ ህዝቡን በሚፈልገው መንገድ አንቅቷል፣ ተአማኒ ሆነው ህዝቡን አንቀሳቅሷል ለማለት ሙሉ ለሙሉ ቢከብድም አስተዋፅአቸው ቀላል ሊባል አይችልም። ሆኖም ከላይ ወደ ታች በሚፈስ የድጋፍ ማሰባሰብና አፅድቅልኝ ስራ ካልሆነ ህዝቡ መስማት እና መደገፍ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ልማት አስተያየት እየሰጠ፣ እያስተካከለ፣ እየጨመረ ልማቱን የሚያሳልጥበት፤ መንግስትም ግብረ መልስ (feedback) የሚያገኝበት ከታች ወደላይ የሚንሸራሸር ሓቀኛ እንቅስቃሴ አልነበረም ማለት ነው።

ከዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር አዃያ ግን ሚናቸው አሉታዊ ነበር። ህዝቡ በብልሹ አስተዳደር ሲለበለብ የህዝቡ አለኝታ ብሎም የመንግስት አለኝታ ሆነው ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ከመፈለግ ይልቅ አበረታች፣ አመርቂ፣ተስፋ ሰጪ የሚሉ አድበስባሽ ቃላቶችን በመጠቀም የብልሹ አስተዳደር ተባባሪ ሁነዋል። አንዱ እንደሚለው አበረታች፣ አመርቂ፣ተስፋ ሰጪ እና የመሳሰሉት ቃላት የኢህአዴግ ማደንዠዣ ቃላት ከሆኑ ሰነባብቷል።

ከዚህ ባሻገር ብዙሃነትን የተረዱበት መንገድ ጠብብ እና አግላይ ነበር፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ የተከበረዉን የዘመን መለወጫ በዓል እንዃን ብንመለከት አቀራረቡ እና የፕሮግራሙ ይዘት ቅዱስ ዩሃንስን እና የዘመን መለወጫ በዓልን በማይለይ ጠላ፣ ጠጅና ዶሮ ወጥ ማእከል ያደረገ ከእንዲህ አይነት ባህል እና ልማድ የተለዩት ኢትዮጵያውያንን የማያካትት ሆኖ እናገኘዋለን። ብዙሃነት ሲባል የጭፈራ፣ የመጠጥና እና ያልባሳት ብቻ አድርገው በመቁጠር በተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ያለ የግጭት አፈታት እና የእርቅ ዘይቤዎች፣ የተለያዩ የአስተዳደር መንገዶች፣ ውብ ባህላዊ አደረጃጀቶች እና አገር በቀል እውቀቶች አይዳስሱም፡፡ ስለ መተካካት ሲወራ ከኮንሶው ካራ ወይም ከኦሮሞው ገዳ ከመማር ይልቅ ከዉጭ ብቻ መማር እንደሚገባን እምናስበው የራሳችን አገር በደምብ ስለማናውቅ ጭምር ነው፡፡

አረ ለመሆኑ እንደነ ሪፖተር ያሉ ኃላፊነት የሚሰማቸው ጥቂት የግል ሚዲያዎች ለአመታት የፍትህ ያለህ፣ የመልካም አስተዳደር ያለህ፣ ሙስና በዛ ብለው ሲጮሁ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ አዲስ ዘመን እና ሌሎች የመንግስትና የህዝብ የመገናኛ ብዙሃን የት ነበራችሁ? ዴሞክራሲ ቀጨጨ፣ የጉልበተኞች ዘመን እየሆነ ነው፣ ሰዎች በስልጣን እየባለጉ ነው፣ ፣ ውሃ፣ መብራት እና ስልክ እየተቆራረጠ ነው እያሉ እነ ሪፖተር ሲጮሁ የመንግስት /የህዝብ ሚድያዎች የት ነበሩ? እነ ሪፖተር የህግ የበላይነት ይከበር ዜጎቹ ኑሮ ከበዳቸው ሲሉ የመንግስት ሚድዎችሆይ የት ነበራችሁ? ደግ የሆነውና ያልሆነውን ደግ አድርጎ በማቅረብ ኢትዮጵያ ፍትህ የነገሰባት፣ መልካም አስተዳደር ሞልቶ የተረፈባት ከሙስና የፀዳች አገር አርጋችሁ ስታቀርቡ ግዜ እኔም “እነዚህ ሚድያዎች ውግንናቸው ከማን ጋር ነው ከማለት አልፌ ምን ያህል ጠባብ የዴሞክራሲ ከባቢ የባሰ እያጠበባቹህ እንደሆነ ስታዘብ አዝናለሁ፡፡ የመንግስት ሚድያዎች ምርመራዊ ጋዜጠኝነት እንደ አንድ ዘይቤ በመቁጠር መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን፣ ሙስና እንዲቀንስ እና ፍትህ እንዲነግስ የበኩላቸው አስተዋፅኦ ማበርከት አለባቸው።

እንደኔ ሃሳብ፣ ሚድያዎችን የመንግስት፣ የድርጀት እና የግል ብየ ፈርጄ ትዝብቴን ለመፃፍ ነበር ሃሳቤ። ነገር ግን የድርጅት ሚድያ ላይ ያለኝ ትዝብት ደካማ በመሆኑ የግል እና የመንግስት ሚድያ ማእከል አድርጌ ይህንን ፅሁፋ በማጠቃለል እያለሁ አንዱ ጏደኛየ “ምስጋና ነቲ ተጋዲሉን አጋዲሉን ናብ ዓወት ዘብፀሐና ህዝቢ ትግራይ” (ትርጉም:ምስጋና ታግሎ ላታገለን የትግራይ ህዝብ) በሚል ርእስ በኔ ተፅፎ በብቸኛዋ የትግርኛ መፅሄት ዉራይና ከወራት በፊት የታተመዉን ፅሁፍ መሰረት አድርጎ የተፃፈ ነገር ስላለ እየው ብሎ ላከልኝ። አየሁትም፤ ገና የዉስጥ ይዘቱ ሳላይ ደነገጥኩኝ፤ እዉነት መሆኑ ለማረጋገጥ ደጋግሜ ሳየም ቅዠት አለመሆኑን አረጋገጥኩ :: ይህ ሳይ አንድ ነገር ብለጭ አለብኝ፡፡

በህወሓት ጉባኤ ወቅት የተወሰኑ ጄኔራሎች መቐለ አካባቢ ያንዣብቡ ነበር ብለው አንድ ሁለት እዛ የነበሩ ሰዎች ገለፁልኝ፤ ታድያ ምን አለበት ለራሳቸው ጉዳይ ሂደው ከጉባኤው ጋር ተገጣጥሞ ሊሆን ይችላል አልኳቸው። አንደኛው “አይ ማታ ማታ ከፖለቲካዊ መሪዎች ጋር ይገናኙ ነበር “ አለኝ። እኔም የድሮ ጏደኞቻቸው በአጋጣሚ አግኝተው እየተጫወቱ ይሆናል አልኳቸው። “አይ ብዙ ሰው የተለያየ ትርጉም ነው የሚሰጠው” አሉኝ። በነገሩ ግራ ገባኝ እና አይ ጉባኤዉን በቀጥታ ተፅእኖ እያሳደሩበት ነው እያልክ ከሆነ እንዲህ የሚያደርጉ አይመስለኝም፤ ህገ መንግስቱን ጠንቅቀው ያዉቁታል፤ በኮርት ማርሻል (ወታሃደራዊ ፍርድ ቤት) የሚያስቀጣቸዉና በቀጥታ ከሰራዊት የሚያባርራቸው መሆኑን በሚገባ ስለሚያውቁት አይሞክሩትም አልኩኝ። አይ እኔ እንጃ ብዙም አላውቅም አለኝ::

በሌላ በኩል ግን ብታየዉስ ህወሓት የመከላከያ ጄኔራሎች በፖለቲካው ገብተው እንዲዘባርቁ የምትፈቅድ አይመስለኝም አልኩት። ፖለቲካዊ ትርጉሙ መሰረታዊ ነው። ብዙ አንፀባራቂ ታሪክ ስርታ እዚህ የደረሰች ድርጅት ይህን ከፈቀደች ሞታለች ወይም አንድ እግሯ ጉድጏድ ዉስጥ አስገብታለች ማለት ነው አልኩት። ከሌሎች የአህአዴግ ድርጅቶች ጋር በመሆን መንግስት ተመስሮቶ እንዴ ሌላው ተቛም ፖሊሲ በማውጣት ብቻ ሳይሆን የሲቪል አስፈፃሚው ወታደራዊ ክፍሉን መቆጣጠር የሚያጠናክርበት ሆኖ እያለ እንዴት የተገላቢጦሽ ይሆናል ስል አግራሞቴን ገለፅኩለት። በተጨማሪም የድርጅቱ ሊቀመንበር የጄኔራሎቹ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት የሚቀበሉ አይመስለኝም አልኩት፤ ሳዋራው የነበረው ሰዉየም የሊቀመንበሩ አፍቃሪ ስለነበር “ይሄስ እዉነጥን ነው” አለኝ።

ወይን መፅሄት በ ሃምሳኛ እትሙ ህገ መንግስቱን በግላጭ የጣሰና አሁን ተፍጥሮ ያለዉን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ኢ-ዴሞክራስያዊ ሃይሎች ምን ማድረግ እንደሚችሉ እሚያሳይ ደንበኛ ምሳሌ በመሆኑ ስፋ አድረርጌ ለማየት ተገድጅያለሁ። የ “ወይን” ስፖንሰሮች የፌዴራል ሚኒስቴር መስርያ ቤቶች፣ መከላከያ ሚኒስቴር ሳይቀር፣ የአዲስ አበባ ቢሮዎች፣ የዞን ፅህፈት ቤቶች፣ ከትግራይም ከክልል ቢሮዎች እስከ ወረዳ ድረስ ያሉ የመንግስት መዋቅሮች ናቸው። ጥያቄዉም የመንግስት መስርያ ቤቶች የአንድን ፖለቲካዊ ድርጅት ልሳን የሆነን መፅሄት ስፓንሰር ማድረግ ይችላል ወይ? ቢሆንም የግል ድርጅቶች ተጨምረውበት በማስታወቅያ የታጨቀ ሃምሳ ብር የሚሸጥ ሃምሳኛ እትም መፅሄት ነው ሊባል እሚችል ሁኖ አግኝቼዋለሁ።

እነዚህ የመንግስት ተቛሞች የአንድ ፖለቲካዊ ድርጅት ልሳን እንዲደጉሙ ዓቅም እንዲፈጥሩ ሕገ መንግስቱ ወይም ሌሎች ህጎች ይፈቅዳሉ ወይ? በተለይ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 87/5 መሰረት ከፖለቲካዊ ወገናዊነት ነፃ በሆነ መንገድ ስራዉን ማከናወን ያለበት መከላከያ ስፖንሰር ሆኖ ማየት አስገራሚ ነው። ዕብሪት ነው!!! መንግስት ከህግ ዉጪ አንድን ፓርቲ መደጎም የለበትም። አይ… ህገ መንግስቱ አይከለክልም ከተባለም እንግዲህ ህጋዊ ሆነው ተመዝግበው እሚንቀሳቀሱ እንደነ የመድረክ፣ የዓረና እና የመኢአድ ልሳኖችን ስፖንሰር ቢያደርጉ ደካማ የፋይናንስ አቅም ስላላቸው ለዴሞክራስያዊ ስርዓት ግንባታ ድጋፍ ይሆን ነበር። ከዲያስፖራ ጥገኝነትም ያላቅቃቸው ነበር።

ወደ ዝርዝር ይዞታው ከመሄዳችን በፊት ግን የኤርትራ ጦርነት በአብዛኛው ትግራይ ዉስጥ የተካሄደ በመሆኑና አገራችንም በድል ብትወጣውም አሁንም ለአስራ አምስት ዓመታት የ No War No Peace ድባብ በሃገር ደረጃ ያለው ተፅእኖ እንዳለ ሆኖ ለትግራይ ህዝብ ግን ጫናው ከፍተኛ ነው። ግንባሩ ያለበትና አብዛኛው ሰራዊትም እዛ ስላለ ትርጉም ከፍተኛ ነው። የኢትዮጵያ ሰራዊት ልጆቹ ስለሆኑ በሙሉ ልቡ ተቀብሎ የሚቻለዉን እያደረገ እንደሆነ ስለማዉቅ የትግራይ ህዝብን ማመስገን ተገቢ ነው። የፌዴራል መንግስት ይህ ሁኔታ የሚፈጥረው አሉታዊ ተፅእኖ በሚገባ አጥንቶ ተገቢ ፍትሃዊ እርምጃ እንዲወስድ ይጠበቅበታል። ይህ ለወይን መፅሄት የተደረገው ድጎማ ህጋዊነት የሌለው ከመሆኑም አዃያ ለማይረባ ፖለቲካ ከሚዉል በ No War No Peace ድባብ የበለጠ የተጎዳዉን ህዝብ ለመደገፍ እና ሁኔታው የፈጠረው ኢኮኖምያዊ፣ ስነ ምህዳራዊ፣ ስነልቦናዊና ማህበራው አሉታዊ ተፅእኖ ለማጥናት ቢዉል በአገሪቱ ሞራላዊ ግዴታ ለመወጣት የመጀመርያው እርምጃ በሆነ ነበር።

የመፅሄቱ ዝርዝር ይዞታ ሳይ ደግሞ በእውነት የህወሓት ልሳን ነው ወይ? የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አስገድዶኛል። ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ በኢህአዴግ ዉስጥ የተፈጠረው መነቃቃት፤ የህወሓት ጉባኤ ደግሞ ከሌሎች የግንባሩ ድርጅቶች የሰላ እንደነበር፤ የዚህ የሰላ ጉባኤ ምልክት ተደርገው በህዝቡ ክብር ያገኙት ቄስ ገብረገርግስ ገብረማርያምም የጉባኤዉን ሂደት ሲገልፁ “ፊት ንፊት ገጢምና እንተወሐደ ንለባም ክርደኦ ገይርና አለና! ቀይናን እዉን ሰንቢዱ አሎ” ትርጉም፥ “ቢያንስ ፊት ለፊት ገጥመን ልባሙን እንዲረዳ አድርገናን! ጠማማው ደግሞ ደንግጥዎል” ነበር ያሉት ከ ዉራይና መፅሄት ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ። ሁኔታው ይህ ሆኖ ሳለ ትግራይ ዉስጥ የተፈጠረው ማዕበል ከወይን ሳልሰማ ስቀር ግን ግርምት ፈጥሮብኛል። በኔ አመለካከት ወይን ቁጥር ሃምሳ (ሌሎች እትሞችን ስላላነበብኩ አስተያየት ለመስጠት ያስቸግረኛል) የዴሞክራሲ ማዕበሉን ያስፈራቸው የድርጅቱ አመራር ወይም ከበስተጀርባቸው የሚደጉምዋቸው ሃይል ልሳን ነው እንጂ የህወሓት 12ኛ ጉባኤ መንፈስ የሚያንፀባርቅ አይደለም።

ህወሓትም እንደሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ስለ GTP 1 አፈፃፀም ጠንካራ እና ደካማ ጎን በአንድ በኩል፤ GTP 2 የሚጀምርበት ውቅትም በመሆኑ የህዝቡን አስተያየት አካቶ ህዝቡን በዙርያው እንዲሰለፍ ለማድረግ ይሞክራል ተብሎ ሲጠበቅ አጀንዳው ሌላ ሆነ፤ በዚህም ይህ እትም የወደቀ እና የሚያሳፍር ይመስለኛል። ትልቅ ፖለቲካዊ ትርጉም ግን አለው:: ማዕበሉ ሲጀምር ከሁሉም በላይ ለማደናቀፍ የሚሞክሩት በፓርቲ/በመንግስት ያሉ የተወሰኑ ሹማምንት መሆኑን ያሳያል። የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ዴሞክራስያዊ ምህዳር ለማስፋት የሚታገል ህዝብ፣ ፓርቲ እና መንግስት የመጀመርያው ምልክት ነው። እንደ ማስጠንቀቅያ መወሰድ ይኖርበታል፤ ትግሉም ከዚህ መጀመር ይኖርበታል። ወይን ቁጥር ሃምሳ ህገ መንግስቱን በግላጭ የደፈረ ሲሆን ከወቅቱ ፖለቲካም የ ኢ-ዴሞክራስያዊ ሃይሎች መሳርያ ሆኗል።

ወደ ይዘቱ ስንመጣ የሚያስገርም ነው። “አብ ቅድሚ መለስን ስዉአትን ዝተአተወ ረዚን ቃል” ትርጉሙ “በመለስ እና በሰማእታት ፊት የተገባ ከባድ ቃል” በሚል የህወሓት ሊቀመንበር ሰፋና ሁሉኑም ያቀፈ ቃለ መጠይቅ እንዲሁም በተመሳሳይ የቀድሞ የትግራይ ሲቨል ስርቪስ ሃላፊ የነበሩት የተደረገ ቃለ መጠይቅ እናገኛለን። ካሉት ሌሎች ፁሁፎች አንዱ በአቶ ገብሩ አስራት የተፃፈውን “ሉእላዊነት እና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ” የሚለው መፅሃፍ ላይ እኔ ለፃፍኩት ፅሁፍ ‘ሂስ’ የሚያቀርብ ሲሆን ሌሎቹ ግን ከ 24 ዓመት በፊት በትጥቅ ትግል የነበረው ሁኔታ ነው የሚያትቱት። ከቃለ መጠይቁ ዉጭ ስለ GTP 1፣ GTP 2፣ ስለተፈጠረው ማዕበልና ስለ አዲሶቹ አመራሮች ምንም እሚለው ነገር የለም። የጀግኖቻችን (በሂወት ያሉትም የተሰዉትም) ደማቅ ታሪክ መሰነድ አለበት፤ በየግዜዉም ከተሞክሮቻቸው መላው የኢትዩጵያ ህዝቦች እንዲማርበት ይገባል። እኔም እኮራባቸዋለሁ። የወቅቱ ፖለቲካዊ ትኩሳት (ማዕበል) ለማቀዝቀዝና አጀንዳ ለማስቀየር ሲዉል ግን ያሳዝናል። ወይን ባሉትም በተሰዉትም ጀግኖቻችን ስም መሸቀጥ የለባትም እላለሁ።

በጥቅሉ በህጋዊ መንገድ በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን የመድረክ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር፣ የዓረና የቀድሞ ሊቀመንበር፣ በፓርላማው ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪል የነበሩትን ሰዎች በፎቶግራፍ አስደግፈው “በጥፋትና በሁከት መንገድ የሚደረግ የስልጣን እሽቅድድም ላሁንም ለዘላለሙም ተቀባይነት የለዉም” ብለው ወይን እንዲፅፉ እንዴት እነዛ መስርያ ቤቶች ስፖንሰር ያደርጋሉ? እነዚህ መሪዎች ከህግ ዉጪ ከሄዱ የሚጠይቃቸው መንግስት እያለ፤ ይህ እስካልሆነ ድረስ ግን የትኛዉም ፖለቲካዊ ዓላማ ይያዝ የመንግስት መስርያ ቤቶች በተለይም መከላከያ ስፖንሰር ማድረጉ ወይንን “እዉነትህ ነው” እንደማለት አይቆጠርም ወይ?

“ሸፈጥን አነነትን እንትሓብሩ” ትርጉም “ሸፈጥና እኔነት ሲያብሩ” የሚለው ፅሁፉ ጠቅላላ ይዘቱ በስልጣን ያሉትን ኢታማዦር ሹምን ለማሞገስ እና በጡሮታ የተገለሉትን የቀድሞ ኢታማዦር ሹምን የሚያንኳስስ ‘የማን ይበልጣል?’ ዓይነት ፁሁፍ ነው። የትግራይ ህዝብ እየለበለበው ያለዉን የብልሹ አስተዳደር ችግር እያለ እንደ ድሮ መሳፍንት ‘ራስ እገሌ ከ እገሌ ይበልጣል’ ዓይነት ፅሁፍ ይዞ መዉጣቱ በጣም የሚያሳፍር ነው። መወየን ተራማጅነትን የሚገልፅ ቢሆንም እየተደረገ ያለው ግን የ አድሃርያን ተግባር ነው፤ ወያነነቱም የት ሄደ? ያስብላል። ለመሆኑ ወይን በስራ ላይ ካሉት ኢታማዦር ሹም ምን ቢፈልግ ነው የህዝቡን ድምፅ ማሰማት ሲገባው ወደ ወረደ መሳርያነት ራሱን ያሸጋገረው? ፖለቲካዊ ዘመቻም ከሆነ ጡረታ ሲወጡ ያደርግላቸዋል። ሁለቱም ኢታማዦር ሹሞች የየራሳቸው እና የጋራ የሚያኮራ ታሪክ እያላቸው የ ‘አንዱ ይበልጣል’ ንፅፅር ምን አመጣው?

ወይን መፅሄት “አብ መከላኸሊ ሓይሊ እዉን ክግበር ዝኽእል ዘይሕጋዊ መማረፂታት እንተልዩ ምሕሳብን ምፍታንን ጀሚሮም” ይላል። ትርጉም “በመከላከያ ሃይል ዉስጥም ማድረግ እሚቻል ህጋዊ ያልሆነ አማራጭ ካለ ብለው ማሳብና መሞከር ጀመሩ” ይላል። ለሌተናል ጄኔራል ፃድቃን እና እኔ ባለፉት ወራት አንዳንድ ከትጥቅ ትግሉ ጋር የተያያዘ የምናውቀዉን ፅፈን ነበር፤ ሰው ሊስማማ ላይስማማ ይችላል። የሚገርመው ግን ወይን ወይም ስፖንሰሮቹ “ህገ ወጥ ድርጊት በማስብ እና በመሞከር” ብለው ለማስፈራራት የሞከሩት ነገር ነው። ከ አስራ አምስት ዓመት በኃላ ይህ ማስፈራርያ ለምን መጣ? አርፋቹህ ተቀመጡ ለማለት ነው? ወይንና ‘እማይታወቀው’ መሐመድ በወቅቱ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ (ነብሳቸው ይማርልን) እያወቁ “ምህረት” አድርገዋል፤ አሁን ግን የሚምራቹህ ሰው የለም እያሉን ይሆን እንዴ ?

‘ቁም ነገር’ ማስፈራራቱ ነው፤ ‘የምናውቀው ሚስጢር ስላለ ተጠንቀቁ’ እንደማለት ነው። ይህ ጉዳይ የአንድ መፅሄት ነገር ቢመስልም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የጠቅላይ ሚኒስቴሩ ቢሮ እና መስርያ ቤቶቻቸውን ሊመረምሩት እና ማስተካከያ ሊያደርጉበት ይገባል እላለሁ። ይህ የጥቂት ሰዎች ድርጊት የጀግናው መከላከያ ስራዊታችንን አጠቃላይ ስብእናው እንዳይጎዳዉም ጭምር እሰጋለሁ፤ በመፅሄቱ የተንፀባረቀው ሃሳብም ሁሉም የመከላከያ የበላይ አመራሮች እንደማይቀበሉት አውቃለሁ። ወይን አብዮታዊ (ወያናይ) ስብእናዉን መጠበቅ ካለበት የማንም መፈንጫ መሆን የለበትም::

በተለይ የመከላከያ ጉዳይ አሳሳቢ ነው። በታዳጊ አገር ሰለምንገኝ እና ዴሞክራቲክ ተቛሞቻችን ደካማ በሆኑበት ግዜ የታጠቀው ሃይል ወይ ራሱ ንጉስ (King) ወይም እንጋሽና አፍራሽ (King Maker and breaker) ለመሆን ይዳዳዋል። አሁን የታየው ምልክት እንዳይሰፋ ከወዲሁ መጠናት አለበት፤ የሲቪልያን ቁጥጥሩም ጠበቅ ማለት አለበት። ጠንካራ የሃገር መከላከያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን ዘበኛ ቢሆንም፤ ከልክ በላይ ካበጠ ግን የ ኢ-ዴሞክራስያዊ ሃይሎች መሳርያ ስለሚሆን በዚህ ረገድ የተሰማሩ ሙሁራን ወታሃደራዊ ክፍሉ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ወይ ቅልበሳ (democratization and de-democratization) ላይ የሚኖረዉን ሚና እንዲያጠኑት መንግስት ሁኔታዎችን ማመቻቸት አለበት፤ እኔ እስከምናውቀው በዚ ዙርያ ኢትዮጵያን ማእከል አድርጎ የተጠና ጥናት አላገኘሁም።

በተያያዘ መልኩም የግል ሚድያው እንደነ ሪፖርተር፣ዉራይና፣ አዲስ አድማስ እና ሰንደቅ የመሳሰሉ ሃላፊነት የሚሰማቸው ጥቂት ሚድያዎች ቢኖሩም አብዛኞቹ ግን መልካም አስተዳደር ለማስፈን፣ሙስናን ለመታገል እና ፍትህን ለማንገስ ይቅርና በግላጭ መካድ እማይቻለዉን ማህበረ-ኢኮኖምያዊ ለውጦችን እሚክዱ መሆናቸው ስታዘብ ራሳቸዉን ማስተካከል እንዳለባቸው እረዳለሁ። በነጋ በጠባ ቁጥር አመፅን እና ሁከትን እሚሰብኩ፤ ዘመናዊ የሰለጠነ ፖለቲካ አለርጂክ የሆነባቸው የግል ሚድያዎች የሞያዊ ስነ ምግባር ጉድለት እና ህገ-ወጥነት ሲታከልበት ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው እየጎላ ይሄዳል። ሃላፊነት እሚሰማቸው ሚድያዎች እሚያደርጉት ጥረት መደገፍ ያለበትና ለሌሎቹም ትምህርት የሚሆን ስለሆነ በርቱ መባል መቻል አለባቸው።

በስራ ላይ ያሉት የመንግስት እና የህዝብ የሚባሉት የመገናኛ ብዙሃን የኢትዮጵያ ህዝብ መረጃ እና አማራጭ ሃሳቦች ማግኘት እንደሚገባው የተገነዘቡ ሳይሆን የኢህአዴግ ልሳኖች መሆናቸው በተግባር ያረጋገጡ ሚድያዎች ናቸው፡፡ ያገሪትዋ መገናኛ ብዙሃን በአድልዎ የተሞላና ህጋዊ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ከገዢው ፓርቲ የተለየ አቛም ያላቸዉን ሰዎች የሚያገል አሰራር እና ባህሪ ያለው ተቛም ነው። በጅምር ዴሞክራሲ በብዙ ጫና እና ድካም እሚንቀሳቀሱትን ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንደማገዝ ፈንታ ስህተቶቻቸውን እየፈለጉ እና እየለቃቀሙ ለህዝቡ በማቅረብ የኢህአዴግን ጠንካራነት እና አይበገሬነት ሲሰብኩ ማየት የተለመደ ተግባራቸው ከሆነ ብዙ ግዜ ቆጥረናል፡፡

የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ትዕቢትና ህግ መንግስትና ሌሎች ያገሪትዎን ህጎች ከቁብ እንደማይቆጥሩት በተግባር እያሳዩን ነው፡፡ የህወሓት 40ኛ አመት በትግራይ ቴሌቪዥን የወራት ሙሉ ሽፋን እንዲሁም በኢቢሲ (EBC) ላቅ ያለ ሽፋን የተሰጠው የምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ትንፋሽ ለመተንፈስ እንኳ የማትበቃ ጥቂት ደቂቃ በተመደበላቸው የምርጫ ወቅት መሆኑ ስንገነዘብ ነው የመንግስትና የህዝብ የመገናኛ ብዙሃን ባህሪ እና ማንነት መረዳት እምንችለው፡፡ እስኪ ህወሓት በትግራይ ቴሌቪዥን እና EBC ላሰራጨው የወራት ፕሮግራም ክፍያ ፈፅመዋል? ቢፈፅምስ ይህ ተገቢ ተግባር ነውን?

ከመንግስት ዉጪ የሆነ በግል ድርጅት ባለቤትነት ስር የሚገኝ የቴሌቭዥን ጣብያ እስካሁን አገራችን ላይ አለመኖሩ እሚገርም ነገር ነው። የዚህ ዋና ምክንያት ምንድን ነው? ብሎ መጠየቅ መቻል አለብን። ሲጀመር ፍቃድ የሚሰጠዉስ ግልፅነት፣ ተጠያቂነት እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ነው? መንግስትስ ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ አስተሳሰብ የተለየ ሃሳብ ያላቸዉን ዜጎች የቴሌቭዥን ፍቃድ ቢጠይቁ የመስጠት ድፍረት አለዉን? ወይስ ለመንግስት እማያጎበድድ ከሆነ ፍቃድ አያገኝም? አልያም ለ “ጨዋዎቹ” ብቻ ነው ‘ሊራራ’ እያሰበ ያለው?

የዚህ ፅሁፍ ፀሃፊ የካቲት 11 መከበር ያለበት በዚህች አገር ታሪክ የዴሞክራሲ እና የልማት የማዕዘን ድንጋይ የተቀመጠበት ቀን ነው ብሎ ያምናል፡፡ ሆኖም ቀኑን ለርካሽ ግዝያዊ ፕሮፓጋንዳ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን በመጣስ ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ለማፈን መዋል የለበትም ብሎ ያምናል፡፡ የምንወደው እና የምናከበርው በዓልም ህገ መንግስትን ባከበረና ለዴሞክራያዊ ስርኣት ግንባታ አስተዋፅኦ በሚያደረርግ መልኩ መከበር አለበት፡፡ የካቲት 11 ሁሌም መከበር እና መዘከር ያለበት በዓል ነው። ይህ ስል ግን በሰማእታት ደም እየነገዱ ለመኖር ባለመ ሁኔታ መከበር እንደሌለበትም በማሳሰብ ነው። አንዳንዴ ለበዓሉ እሚወጣወ የገንዘብ እና ሌሎች ሃብቶች ሳስስተዉል ግን ምናለ በንዲህ ከሚጠፋ ለጥናት እና ምርምር ፈሰስ ተደርጎ ባይ እሚል ጥያቄ ይጭርብኛል።

ከዚህ ጋር በተመሳሳይ መልኩ በትግራይ ቴሌቭዥን ‘አንጃ’ ‘የበሰበሰ’ ወዘተ ማለትን ይዘወተራል፤ አንዱን የፓርቲው ወገን ደግፎ ሌላዉን መዘርጠጥ የተለመደ ስለሆነ ብዙ ሀተታ አያስፈልገዉም። የዴሞክራሲ ስርዓት ለሚያውቅ ግን አሳፋሪ ነው። በሆነ ዴሞክራስያዊ ስርዓት የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች የተለያዩ ብሄር /ብሄሮች ሃይማኖት፣ ፆታ፣ የተለያዩ መደቦች (እንደ ገበሬ) እና ሌሎች ያሉበት ስለሆነ የተለያዩ ፍላጎቶች ማንፀባረቃቸው አይቀርም። የፍላጎትና የእሴት ጉዳይ ስለሆነ ባብዛኛው ፖለቲካዊ ገፅታው የተወሰኑ ሰዎች ባቛቛሙት ድርጅት ሊገለፅ ይችላል። ለምሳሌ በአሜሪካ ኮንግረሰ የቀኝ አክራሪዎች ቀጣይነት ባለው ወጣ-ገባ ነው እሚካሄደው። በቅርብ የ ኮንግረሱ አፈ ጉባኤ ስራ ለመልቀቅ የቻሉት በነዚህ ግፊት ነው። አንጃ (Faction) መፍጠር የተለመደ እና ፓርቲው አቻችሎ እሚሄደው ነገር ነው። የተለያዩ ፍላጎቶች በፓርቲው ዉስጥ መንሸራሸራቸው ባህርያዊ ነው። ይሄም በቛሚነት የሚታይ ባህሪ/ permanent ternd ነው። በአንድ ጉዳይ ላይ በአንድ ፓርቲ የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያየ ፍላጎት እና አዝማሚያ ሊያንፀባርቁ ይችላሉ፤ ዴሞክራስያዊ አካሄድ ደግሞ ይህን አቻችሎ መሄድን ይጠይቃል። አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሊበራል ዴሞክራሲን መድረስ ወደ ሚገባው ጫፍ ለማድረስ እሚንቀሳሰ ከሆነ የተለየ ሃሳብ ያራመዱትን ለምን እያሳደደ እንደሚኖር አይገባኝም። ከዴሞክራሲ አኳያ ስብሰባን ረግጦ መዉጣት አገርን እንደመሸጥ ተደርጎ ሊቆጠርበት የሚችል ሁኔታ ኢ-ዴሞክራስያዊ ሁኔታ ብቻ ነው።

አንድ ጏደኛየ አንጃ ምንድን ነው? ብየ ስጠይቀው ማስፈራርያ በትር ነው አለኝ። ልክ ደርግ ወያነን መግለፅ ሲይቅተው “ወያኔ በጣም ትላልቅ ጆሮዎች ያላቸው ጭራቆች ሲሆኑ፤ አንደኛው ይነጠፉታል፣ አንደኛው ይለብሱታል” ሲል እንደነበረው መሆኑ ነው። ከዴሞክራስያዊ ባህል አዃያ ሲታይ የተለየ አቛም ያለው “በሰበሰ” ማለት ከራስ የተለየን ሃሳብ የማክበርን ዴሞክራስያዊ መርህ ይፃረራል።

በተመሳሳይ መንፈስ ህዳር 11 መከብር መዘከር ያልበት ታሪካዊ ቀን ነው ነገር ግን የክብረ በዓሉ አጀማመሩ ልክ እንደ ህወሓት ይመስላል። ጋዜጠኞች ወደ ትግል ቦታ ተወስደዋል፤ በማን በጀት? የክልል ፓርላማ ግልፅ በሆነ መንገድ ከወሰነም የክልሉ መንግስት ይህ ለማድረግ ህገ መንግስቱ ይፍቅድለታል ወይ? በጀቱስ ስንት ነው? ብአዴን በአማራ ክልል ቴሌቭዥን እና በ EBC ለሚያሰራጨው ፕሮግራም ክፍያው ማን ይከፍለዋል? አሁንም የበዓሉ አከባበር ህገ መንግስቱ እና ሌሎች ህጎች የተከተለ ነው ወይ? እስከ ምንድረስስ አሳታፊ፣ ግልፅ እና ተጠያቂነት በሚያረጋግጥ አዃሃን እየተሰራ ነው? እስከ ምን ድረስ ሚዛናዊ መረጃስ ለህዝብ ያቀርባል? እሚሉት ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው።

ይህ ሃቅ ኦህዴድንም ደኢህድንንም የሚመለከት ነው፡፡ በቅርቡ ካየነው እንኳን ከዜና አንባቢው ጀርባ እምናየው ሽፋን የኢህአዴግ 10ኛ ጉባኤ መፈክር ነበር፡፡ ይህ ምን ማለት መሆኑ በራሱ እሚነግረን ብዙ ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ዓረና መድረክ ወይም አብኮ ድርጅታዊ ጉባኤ ቢያካሂዱ EBC እንዲህ ያደርጋል? ሲጀምርስ በተሟላ አኳሃን ይዘግበዋል? መምቻ ይሆናል ብሎ ካሰበ ግን መልሱ አዎ “በደምብ ነው እንጂ” ነው እሚሆነው፡፡ይህ ግላጭ ፀረ ህገ መንግስትነት በግዜ መታረም አለበት።

መሬት ላይ ያለው እውነታ ከላይ እንደተገለፀው ቢሆንም፤ ኢህአዴግ በ1992 ለውይይት ያቀረበው ሰነድ ግን እንደሚከተለው ይላል፡ “ህዝቡ ነፃና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መወሰንና መሳተፍ አለበት ሲባል ቅንና ሳይንሳዊ የሆኑ ሃሳቦችን ብቻ መስማት አለበት ማለት አይደለም፤ የተሳሳተና ኋላቀር ሃሳብንም በነፃ መስማት አለበት፡፡ ሰምቶ ከተከተለው መከተል ይችላል፡፡ በሂደት በተግባር ከስህተቱ ተምሮ ወደ አብዮታዊ ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ይመለሳል፡፡ ካልተቀበለው ደግሞ ይበልጥ በነፃ ፍላጎቱና በሚያስተማምን አግባብ ቅን ወደሆነው ሃሳብ ይገባል፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራያዊ የአስተሳሰብ ልዕልናውን የሚጣረጋግጠው የተሳሳቱ ሃሳቦችን በማፈን አይደለም፡፡ የተሳሳቱ ሃሳቦን ማፈን ማለት የሚያጋልጣቸውና የሚታገላቸው ሳይኖር ውስጥ ለውስጥ እንዲጎለብቱና እንዲጠነክሩ በር መክፈት ማለት ነው” ይላል በገፅ 65 ላይ፡፡

ይህ የተጠቀሰው ዶክመንት በገፅ 123 ላይም እንዲህ ይላል “መላውን ህዝብ /አብዛኛው ክፍል/ ለአመታት ለአንድ ፓርቲ አመለካከት በማጋለጥ፣ ሌሎችን በመከላከል የሚደረግ አሰራር መከተል በሃሳቦች መካከል ነፃ ውድድር እንዳይኖር የሚያደርግ ነው የሃይለስላሴና የደርግ መንግስታት ይህም ማድረጋቸው የሚያመላክተው ፀረ ዴሞክራስያዊ ባህርያቸው ነው” (ኢህአዴግ፣ 1992 ዓ.ም ገጽ 123) ። ምን ዋጋ አለው ሰነድ ሌላ እዉነታ ሌላ ሁነ እንጂ!!!

የነፃ ሚዲያ እድገት ሃሳብን ከመግለጽ መብት ጋር የተቆራኘ ነገር ነው፤ ሃሳብን የመግለጽ መብት ደግሞ መሰረታዊ ሰዎች ሰብአዊ መብት ነው፡፡ የዚህ መብት በሰው ሂወት ያለውን እርባና ሰፋ አርገን መገንዘብ አለብን ይላሉ የዘርፉ ባለሞያዎች (ቢአታ ሩዞሚሎቪችስ) እንደሚለው የሰው ልጅ ያለበትን ሁኔታ፣ስጋቶቹ እና ፍላጎቶቹን መግለፅ እና ለሌሎች ማስተላለፍ እስካልቻለ ድረስ ሂወቱ ሙሉ ነው ማለት አይቻልም ይላል ቢአታ።

ከዚህ መረዳት እምንችለው ሃሳብን በነጻ የመግለፅ እና ተያያዥ መብቶች ሰው መሆንን ሙሉ እሚያደርጉ እና ለሂወት አስፈላጊ አምዶች እንደሆኑ ነው፡፡ ዴሞክራሲ ሰዎች ሙሉእነታቸው በሚያረጋግጡበት ክብሮች /values/ የታጀበ ነው ሲባልም ለዚህ ነው:: ሂወት የመማማር ሂደት የምትሆነው ሃሳባችንን በነፃ መግለፅ ስንችል እና የሌሎችን ሃሳብ በነፃነት ማግኘት ስንችል ጭምር ነው ይላል ቢአታ (2002:13)፡፡ መገናኛ ብዙሃንም እውነተኛ መገናኛ ብዙሃን የሚሆኑት በህብረተሰቡ ያሉትን የተለያዩ ሃሳቦች አቅማቸው በፈቀደ መጠን በእኩልነት ሲያስተናግዱ ነው፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ የመገናኛ ብዙሃን “ደግ ደጉን” ብቻ እሚያወሩ የአንድ ፓርቲ አፈ-ቀላጤ ከሆኑ ህዝቡን እና የፖለቲካ ሃይሎች ወደ ፅንፉ እየገፋ አውዳሚ ሊሆኑ ለሚችሉ የሚድያ ተቋማት በር መክፈታቸው አይቀርም ፤እየሆነ ያለዉም ይሄው ነው፡፡ የህዝብ እምነት ያጡ ሚዲያዎች ለልማቱም ለዴሞክራሲውም እሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ላይኖር ይችላል፡፡ ሚድያ በገበያ ሃይሎችም ይሁን በመንግስት በብቸኝነት በቁጥጥር ስር ሲውል ከዴሞክራሲ አኳያ አደገኛ የስጋት ምንጭ ነው እሚሆነው፡፡የግል የመንግስት እና የድርጅት ሚድያዎች ተገቢ ሚናቸዉን በተገቢ አዃሃን ከተጫወቱ የዴሞክራታይዜሽን ሃይል ሆነው የላቀ ጥቅም ይሮራቸዋል፤ ይህ ሳይሆን ሲቀር ግን አጥፊ እና የኢ-ዴሞክራታይዜሽን ሃይል መሆናቸው አይቀርም።

5.4 የአንድ ለአምስት ተቋም

አንድ የቆየ ዋዛ ከቁም ነገር ነው፤ ሴትየዋ መልካም የሚባል ትዳር አንዳላትና መሰረቱም ከባልዋ ጋር ያላቸው የስራ ክፍፍል እንደሆነ በደስታ እንዲህ ስትል ትመሰክራለች “ባሌ ትላልቅ ውሳኔዎችን ይወስናል፤ እኔ ደግሞ በትናንሽ ነገሮች ላይ እወስናለሁ፡፡ ባሌ እሚወስናቸው ነገሮች ልክ እንደ ‘ቻይና የተባበሩት መንግስታት አባል ያድርጋት? አያድርጋት?’ እሚሉት ነገሮች ላይ ሲወሰን፤ እኔ ግን የት አካባቢ መኖር እንዳለብን እና ልጆቻችን የት ይማሩ እሚሉትን ጉዳዮች ላይ እወስናለሁ” አለች፡፡ የዚህ ተረት መልእክቱ ባልየው ውጤታማ ሳይሆን ቅዠታም ወይም ብቸኛ እና አማራሪ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ፍላጎት ያለው እና የሆነ የጥናት መስክ “የፖለቲካ ተሳትፎ” ያደርጋል ብሎ ሊፈርጀው እሚችል ዓይነት ሰው ሲሆን፤ ሚስቱ ግን የምትወስነው ውሳኔ ተፅዕኖ የሚፈጥር እና የተፈፃሚነት መጠኑም ከፍ ያለ ነው፡፡ በእርባና አኳያም የሚስትየው ተሳትፎ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡

አንድ ለአምስት አደረጃጀትም ለህዝቡ የቀረበና የሚወስዱት እርምጃዎችም ቀጥተኛ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ በመሆናቸው ሊጠኑ እና በጥልቀት ሊዳሰሱ ይገባቸዋል፡፡ ይህ አደረጃጀት እታች ወርዶ የተፈጠረ ተቋም ሲሆን አጠቃላይ ህዝቡን ለልማት አነቃንቆ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊ እና ፖለቲካዊ አወንታዊ ለውጦችን በማስመዝገብ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ሊያግዝ እሚችል ፈጠራ የታከለበት አደረጃጀት ነው፡፡ በአግባቡ ካልተያዘ ግን የድህንነት ተቋም ተቀጥያ ሊሆን ይችላል፡፡ ለጠባብ የፓርቲ ፖለቲካዊ መሳርያነት ከተጠቀምንበትም ጉዳቱ የከፋ ይሆናል፡፡ በቤተሰብ ዉስጥ ስለላን እና ጥራጣሬን ሊተክል ይችላል፤ አለን እምንለው የቆየ ማህበራዊ እሴትንም ድምጥማጡ ሊያጠፋው ይችላል።

ኢህአዴግ እሚመራው መንግስት ወደ ህዝቡ ወርዶ ለማገልገል እና ድህነትን ለመቅረፍ እሚያደርገው ትግል ላቅ ያለ ምስጋና ይገባዋል፡፡ ማዳበርያ፣ ምርጥ ዘር፣ የእርሻ ቴክኖሎጂዎች እና አስተምህሮዎች፣ ለገበያ እሚያበቁ ምርቶች እንዲያመርቱ እሚደረገው ማበረታቻ፣ ውሃ፣ የጤና እና የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ ገበሬው ለማድረስ እሚደረገው ጥረትም ይበል እሚያስብል ነው፡፡ እንዲሁ በስመ ነፃ ገበያ እና ሊበራል ዴሞክራሲ ከላይ የተጠቀሱት አገልግሎቶች እና ግብአቶች መንግስት አይመለከተኝም በገበያ ህግ ይመራ ቢል ምን ሊከሰት እንደሚችል እስኪ አስቡት? በአስር ሺዎች እሚቆጠሩ የጤና እና የግብርና ባለሞያዎች አሰልጥኖ፣ አሰማርቶ እና ደሞዝ ከፍሎ ወደ ገበሬው ማሰማራት ምን እንደሆነ እስቲ አጢኑት? በተጨማሪም ከጎጥ እስከ ፌዴራል መንግስት እሚገኝ ባለስልጣናት ይህን እንዲመሩ ሲደረግ ትርጉሙ ምን እንደሆነ አስቡት? ይህ ሁሉ ኢንቨስትመንት በግዜ፣ በገንዘብ፣ በእውቀት እና በጉልበት ተምኑት፣ ወደድንም ጠላንም ይህ ጥረት አስገራሚ ለውጦችን ማስመዝገብ ችለዋል፤ በትንሹ ከአጭር ግዜ አኳያ፡፡

ሆኖም ይህ ዘላቂ ነውን? ብለን መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ ዘላቂነት የሚረጋገጠው መሰረታዊ የተቋሙን (አንድ ለአምስት) ችግር ሲፈታ ነው፤ መሰረታዊ ችግሩ ደግሞ ሌላ ሳይሆን የዴሞክራሲ እጥረት (democratic deficiency) ነው:: በዚህ ዙርያ ብዙ ነገሮች ይነሳሉ፡፡ ጥልቅ ጥናት እሚፈልግና ከቦታ ወደ ቦታ ሊለያይ የሚችል ነገር መሆኑ ሳንዘነጋ ካጠቃላይ ከባቢው (General environment) እና ከምታዘባቸው ነገሮች ተነስቼ ስለ ጉዳዩ ጥያቄ ማንሳት ግን ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ በትንሹ የገጠርን እንኳን ብንወስድ ከኢትዮጵያ ህዝብ ከ 80% የሚሆነውን ህዝብ እሚያንቀሳቅስ አደረጃጀት መሆኑ ስንገነዘብ በዚህ ጉዳይ መፃፉ ምን ያህል ጠቃሚ እንደሚሆን እንረዳለን፡፡

አንድ ለአምስት እሚባለው ተቋም /አደረጃጀት/ ሰዎች በራሳቸው ተነሳሽነት እሚመሰርቱት ተቋም ተደርጎ ሊታይ ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት አባላት ያጭር እና የረጅም ግዜ ፍላጎታቸው እሚወስኑበት እና እንዴት እና በማን ያላቸውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ሃብታቸውን አንቀሳቅሰው አሳታፊ በሆነ መንገድ ውሳኔ ላይ የሚደርሱበት አደረጃጀት ተደርጎ ሊታይ ይችላል፡፡ የተቋሙ አባላት ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የተደራጁ ናቸው ብንል እንኳ ከውጭ እሚሰጥ አመራርም ቁልፉ ነገር ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው ብንል ከዴሞክራሲ አኳያ ግን መመለስ ያለብን ጥያቄዎች አሉ፤ መሬት ላይ ያለውን ሃቅን መሰረት አድርገን በመነሳት፡፡

እውን አሁን ያለን አንድ ለአምስት አደረጃጀት በአባላት በጎ ፍቃድ የተመሰረቱ ናቸው? ፍላጎታቸውን መሰረት አድርገው በነፃነት ራሳቸው ይወስናሉ? የቀረበላቸው ግብአት መርጠው የመቀበል እና እምቢ የማለት መብት አላቸው? “ህዝብ ከራሱ ተሞክሮ ይማራል” እምትል ዴሞክራስያዊ መፈክር ተግባር ላይ እየዋለ ነው? ግምገማውስ ምን ይመስላል? አንድ ሰው በተለያየ ምክንያት ማዳበርያ ወይም ምርጥ ዘር አልገዛም ቢል ሰውዬው ላይ ምን ይከተላል? ይሄስ እንዴት ነው ሪፖርት የሚደረገው? ባለስልጣናት በቅጣት ሊታጀብ እሚችል ማስገደድ እያከናወኑ አይደለምን? የኔ ቅኝት በጣም አሉታዊ እና የተፈጠረውን በጎ ውጤት ሊያቀጭጭ ይችላል የሚል ድምዳሜ ነው ያለኝ ፡፡ ዘላቂነቱ መረጋገጥ ካለበት መሰረታዊ የተቋሙ በዲሞክራሲ ዙሪያ የሚታይ እጥረቶች መታከም መቻል አለባቸው፡፡ ይህ አገር ሙሉ እሚያንቀሳቅስ ተቋም በፀረ ዴሞክራሲ አሰራር እና ባህል ከተተበተበ ኢትዮጵያ ላይ የሚያስከትለው ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ኪሳራ ለመገመት እሚያስቸግር ቀውስ ነው እሚፈጥረው፡፡

ባጭሩ ተቛሙ ቀና ለሆነ ልማታዊና ዴሞክራስያዊ ተግባር እንዲዉል ከተደረገ የዴሞክራታይዜሽን ሂደቱ ዋና መዋቅራዊ መሰረት ይሆናል፤ ምክንያቱም ከስማንያ ፐርሰንት የሚሆነው ህዝባችንን እሚያንቀሳቅስ ተቛም ስለሆነ ነው። በተቃራኒው ይህ ተቛም ወይም አደረጃጀት ከታለመለት አላማ አፍትልኮ የጠባብ ፖለቲካዊ ፍላጎት እና የቁጥጥርና ስለላ መዋቅር ተቀጥያ ከሆነ ግን የኢ-ዴሞክራታይዜሽን ሃይል ነው እሚሆነው።

6. ንቅናቄው እንዴት ይቀጣጠል?

እንደ መፍትሄ የሚደረገው እንቅስቃሴ አጠቃላይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሽግግሩን መሰረት ያደረገ አስተሳሰብ ፤ ያደረጃጀት እና የአሰራር ለውጥ ሲሆን ነው የተጠቀሱት ሶስት በሽታወዎች ተፅእኖአቸውን ደካማ ማድረግ የሚቻለው፡፡ እነዚህ ሶስት አደገኛ በሽታዎችን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና በተወሰነ ደረጃ ለማከም (ለማምከን) አዳገች ወይም የማይቻል የሚያደርጋቸው ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉትን ዲሞክራሲያዊ ተቋማት ማእከል አድርገው የሚካሄዱ ዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች ሲቀዛቀዙ ወይም ሙሉ በሙሉ ሲጠፉ ነው፡፡

የቻለ ይሩጥ ያልቻለ ያዝግም፣ የተቸከለ ይወገድ! የተፈጥሮ መረጣ ሂደትን አስቀጥሎ ህዝብን ማእከል ያደረገ ንቅናቄን መምራት እና እመርታ ማስመዝገብ!

ኢትዮጵያ በዚህ ሰዓት በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች:: በኢኮኖሚ መስክ መሃከለኛ ገቢ ያላቸውን አገራት ለመቀላቀል ውጤታማ ስራ እየሰራች ሲሆን በዲሞክራሲ ረገድ ግን ፖለቲካዊ ስርዓቱ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ሃላ እያሽቆለቆለ እየነጎደ ይገኛል፡፡ ይህ ተጨባጭ ሁኔታ ማህበራዊ ንቅናቄ (Social Movement) የግድ አስፈለጊ ያደርገዋል፡፡ ሳራሞጎ እንደሚለው ሁኔታዎች ፈላጎትን ይፈጥራሉ፤ ፍላጎቶችም በበቂ ደረጃ ሲጎለብቱ ሁኔታዉን ይፈጥሩታል “The circumstances create the need, and the need, when it is great enough creates the circumstances”. ያለው ሁኔታ ማህበራዊ ንቅናቄን የግድ እሚል ሲሆን ይህ ፍላጎት በብዙዎች ዘንድ ሲስፋፋ ሁኔታውን ሊፈጥር ይችላል። ይህ ማህበራዊ ንቅናቄ ጎላ ያለ ዲሞክራሳዊ ምህዳር ፈጥሮ GTP 2ን ለላቀ የአፈፃፀም ደረጃ እያስኬደ አያይዞም የዲሞክራሲ ተቋማት ተገቢ ሚናቸው እንዲጫወቱ እሚያስችል ይሆናል፡፡

በህወሓት ታሪክ የቻለ ይሩጥ ያልቻለ ያዝግም፣ የተቸከለ ይወገድ (ዝኸአለ ይጉየ፣ ዘይኸአለ ይሳለ ዝተሸኸለ ይታአለ!) በሚል መፈክር ስር የተደረገው ንቅናቄ ህወሓት ትንሽ እና ድሃ ህዝብ ይዞ መላው ህብረተሰብ ያነገበውን አላማ ይዞ እንደየ አቅሙ እንዲሰለፍና የተቸከሉት ደግሞ እንቅፋት እንዳይሆኑ በመከላከል ይህ ንቅናቄ ደርግን ለመጣል በተደረገው ትግል ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው፡፡ ይህ በእሳት ተፈትኖ ውጤታማነቱ በተግባር ያረጋገጠ የንቅናቄ ሂደት ኢህአዴግና መላው ህዝብ ካለንበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር አዛምደው ሊጠቀሙበት ይገባል ብየ አስባለሁ፡፡ በአንድ ማህበረሰብ የነበረ ወይም ያለ ልምድ ወደ ሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል መዘርጋት የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እሴቶች ወደ ሁሉም መዘርጋት ስለሚሆን ጥንካሬያችንን ነው እሚገልፀው፡፡ ከምዕራባውያን፣ አሁን ደግሞ ከምስራቁ አለም ብቻ ሳይሆን የሚጠቅመንን አገራዊ ተሞክሮ ሲገኝም ካንዱ የኢትዮጵያ ጫፉ ወደ ሌላው ማስፋፋት ጠቃሚ ተግባር ነው፡፡

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1915 አንድ የተከፋ ቻይናዊ ሙሁር ወጣቶቹ ወግ አጥባዊ ከመሆን ተላቀው ተራማጅ እንዲሆኑ እንዲህ ሲል መከራቸው “የምድራችን እድገት ወደ ፊት ብቻ እንደሚዘሉ እንደ ሸምጥ ጋላቢ የፈረስ መንጋ ነው፤ ብልሃተኛ ሆኖ ራሱን ከዓለም ጋር መቀየር ያልቻለ ራሱን እሚያገኘው ከዓለም ተወግዶ ነው” (ቴንግ እና ፌየር ባንክ, 1967:242):: ይህ ሙሁር እያረጋገጠል ያለው የሰው ልጅ በጋራ ድርጊት ማድረግ እንዳለበትና ይህም ካደረገ ድርጊቱ የማህበራዊ ለዉጥን እሚያስከትል ተራማጅነት እንደሚፈጥር ነው። ያለንበት ሁኔታ ደግሞ ስር የሰደደ ብልሹ አስተዳደር ያለበትና ይህም ካልተገታ እና መታረም ካልቻለ የከፋ ሰፊ አድጋ ማስከተሉ ስለማይቀር፤ እንዲሁም መላው ኢትዮጵያዉን እያሳመመ ያለ በሽታ በመሆኑ ስፊ ማህበራዊ እንቅስቓሴ ነው እሚያስፈልገው። ለመሆኑ ማህበራዊ ንቅናቄ ምንድን ነው?

ማህበራዊ ንቅናቄ (Social Movement) ምንድን ነው?

ተርነር እና ኪልያን እንደሚሉት በዉን የተመራ ይሁን አይሁን የሆነ ማህበራዊ ንቅናቄ የተፈጥሮ መረጣ ችሮታ ማሳየቱ የተለመደ ነው ይላሉ፡፡ ቀጥለውም ማህበራዊ ንቅናቄ ሰዎች በሚኖሩበት ማህበረሰብ ለውጥን ለማምጣት ወይም ለዉጥን ለመቃወም እሚያደርጉት የጋር ድርጊት ነው ይላሉ።

ላንግስ (1961፡507) በሚገባ እንዳስቀመጠው ማህበራዊ ንቅናቄ ራሱ በማህበረሰቡ ወስጥ ለውጥ ለማምጣት እሚደረግ የጋራ ጥረት ቢሆንም ከንቅናቄው ዉጪ ከሆነው የማህበራዊ ሁኔታዎች መለዎጥን ተከትሎ የሚመጣ ክስተት ነው። ማህበራዊ ለውጥ ማህበራዊ ንቅናቄን ይወልዳል ማህበራዊ ንቅናቄ ደግሞ ማህበራዊ ለውጥ ያስከትላል፡፡ ባጠቃላይ ማህበረሰቡ ላይ የሚታዩ ለውጦች የንቅናቄዎቹን እድገት ላይ የራሳቸው ተፅእኖ ያሳድራሉ፡፡ ሮበርት ላቨር እንደሚለው በትልቅ ማህበረሰብ ዉስጥ ማህበራዊ ንቅናቄን ማጥናት በተረጋጋ ማእቀፍ ዉስጥ እንቅስቃሴን ማጥናት ማለት አይደለም። ይልቁንስ በንቅስቃሴ ዉስጥ ያለን እንቅስቃሴ ማጥናት ማለት ነው። ማህበራዊ ንቅናቄን ስናነሳ ሁለት የተቆራኙና የሚገኛኑ ሂደቶችን ነው እምናየም፤ እነዚህም አንደኛው የንቅናቄው ሂደት ራሱ ሲሆን፣ ሁለተኛ ደግሞ ንቅናቄው በሚንቀሳቀስበት ማህበረሰብ ዉስጥ ያለን እንቅስቃሴ ነው።

በዚህ መረዳት አንፃር ስናየው የጠራ የንቅናቄ አላማ እና ስትራቴጂዎች ተነድፈው ሁሉም ዜጋ እንደየ ፍላጎቱና አቅሙ የበኩሉን ድርሻ እሚወጣበት የዴሞክራሲ ንቅናቄ ማድረግ የ GTP2 ወሳኝ አካል ማድረግ የግድ የሚልበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን፡፡ የተቸከለና ያልቻለ በጣም በመቀነስ መሮጥ የቻለውንና እሚችለውን በማብዛት የተማረ ቁርጠኛ ወጣት መሪነቱ እሚያረጋግጥበት እቅስቃሴ መሆን ይገባዋል፡፡ የንቅናቄው አላማም ይህ መሆን አለበት፡፡የተማረ ቁርጠኛ ወጣት ስል የህብረተሰቡን ሁኔታ መቀየር አለበት ብሎ የሚያምን እና ለዚህም የበኩሉን ለማበርከት በፅናት እሚተጋ ማለቴ ነው። ተቋም ማእከል ሳያደርግ የሚካሄድ ንቅናቄ ግን ግዜያዊ የቅሬታ ማስተንፈሻ እንቅስቃሴ ከመሆን ስለማያልፉ ቁልፉ ተግባር መሆን ያለበት ተቋም ማእከል ያደረገ የንቅናቄ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው፡፡

ለዚህም ሲባል

1. ዴሞክራስያዊው ንቅናቄ ማሳካት የሚፈልገው አላማ ህዝባዊ አላማ በመሆኑና ያለ ህዝቡ ተሳትፎ እሚሳካ አንዳችም ነገር ስለማይኖር ንቅናቄው ትርጉም ያለው መሆን ካለበት ምልአተ ህዝቡን በሰፊው ማሳተፍ ንቅናቄዉን ለመለኮስ ወሳኝ ድርጊት ነው።ፈጠራ በታከለበት አሰራር የህዝቡን ቀጥተኛ ተሳትፎ ማረጋገጥ ለነገ የሚባል ስራ አይደለም። ህዝቡም ያለበትን ሁኔታ ለማስተካከል ያለው ቁርጠኝነት በተለያየ መንገድ እየገለፀ ስለሚገኝ እሚያሳትፍ መድረክ ካገኝ ለመሳተፍ ዝግጅ ነው። ቼማ (2005) የተባለ ተመራማሪ እንደሚለው ህዝቦች በፖለቲካዊ ሂደቱ ለመሳተፍና በሃገራዊና አካበብያዊ ፖሊሲዎች እና ፕሮግራሞች ተፅእኖ ለማሳደር ሲሉ እሚያደርጉት መደራጀት ብቸኛዉና የላቀ የሰዉን ልጅ ሁኔታ ሊያሻሽል እሚችል ነገር ነው ይለዋል። ሁለም የህበረተሰብ አደራጃጀተች ስምንቱን የመልካም አስተዳድር ባህርያት ከሁኔታቸው አጣጥመው አስተሳሰበቸው አሰራራቸው አስተካክለው ሁነኛ ኣመራሮች መርጠው ክፉኛ የኢ-ዴሞከራሲ ተከታዮች አስወግደው መንቀሳቀስ ይኖረባቸዋለ፡፡ ከላይኛው አካል ጀምሮ በየደረጃው እንቅስቃሴዉን የሚደግፍ ብቃት ባላቸው ኮሚቴዎች እንዲመሩ አጠቃላይ ትላን ወጥቶለት በየግዜው እየተገመገመ የሚሄድ እንቅስቃሴ አመራር ያስፈልገዋል።

2. መንግስት፣ ያገሪትዋ የፖለቲካ ተዋንያን እና ሊሂቃን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች መዋቅሮች ከ ስድሳዎቹ “የኔ መንገድ ብቻ ነው የእዉነት መንገድ” ከሚለው ኃላ ቀር አስተሳሰብ ተላቀው ዘመኑ እና ህገ መንግስታችን የሚፈልጉትን ዴሞክራስያዊ የመቻቻል ባህል ማዳበር እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል። ይህ ለማከናወን እነዚህ አካላት ራሳቸዉን መገምገምና ተጨባጭ ቁመናቸው ትውልዱን እሚመጥን እና እማይመጥኑ መሆናቸው መገንዘብ ይኖራቸዋል። በተለይ ገዢው ፓርቲ ከኢህአዴግ ዉጪ ያሉት ሁሉም አማራጮች የጥፋት መንገድ ናቸው እሚለው አመለካከቱ ማስተካከያ እሚፈልግ መሆኑ ተገንዝቦ አመራሩን እና አባላቱን ወደ ዴሞክራስያዊ ቅኝት ማስገባት መቻል አለበት። ይህ ሃላ ቀር አስተሳሰብ በቅርቡ ገዢው ፓርቲ ‘ከተቃዋሚዎች ጋር አብሬ መስራት እፈልጋለሁ’ ከሚለው ዉሳኔው ጋር ስለሚጋጭ አፋጣኝ እርምት ያስፈልገዋል።

3. ዴሞክራሲ በአንድ ጀምበር እሚዳብር ነገር አይደለም፤ የትውልዶች መወራረስ እሚገነባው ሂደት በመሆኑ መንግስት ቲንክ ታንኮችንና ሙሁራንን ድጋፍ በመስጠት ሰፋፊ የጥናት እና ምርምር ስራዎች እንዲሰሩ ማድረግ። ያለንበት የዴሞክራሲ ሁኔታ፣ መሆን ያለበት እና ሊኖሩን የሚችሉ አማራጮች እንዲሁም ምን በጎ እና አደናቃፊ ሆኔታዎች እንደተጋረጡብን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መጠናት ስላለበት መንግስት አገር ዉስጥም ካገር ዉጭም ያለውን ሙሁራዊ አቅም መጠቀም መቻል አለበት።

4. ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (Democratic movement) የሚለውን ሀሳብ በአግባቡ መረዳት፡፡ ይሄ መረዳት ከከፍተኛ አመራር ጭምር ንቅናቄውን ለመግታት ከባድ ጥረት ሊደረግ እንደሚችል መገንዘብ፡፡ በዋናነት እየተመዘገበ ያለውን ኢኮኖሚያዊ ድል ዘላቂ እንዲሆን እና ዴሞክራሲም ለአገራችን የህልውና ጥያቄ በመሆኑ ነው ይህ የታለመው የዴሞክራሲ ንቅናቄ ያስፈለገው፡፡ ሁሉም ተቋማት ራዕይና ተልእኳቸውን እንዲሁም የስነ ምግባር ደንባቸው ላይ ትርጉም ያለው ውይይት እንዲያካሄዱ ማድረግ ህገ መንግስታዊ ተቋማት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን እና ተጨባጭ ተግባሮቻቸውን በማነፃፀር መገምገም፡: ስራ አስፈፃሚ እና ህግ አውጪው (ምክር ቤቶች) የተቋሞቻቸውን ሁኔታ ስርአት እና መስፈርት ያለው ግዜውን የጠበቀ እና ጥርስ ያለው የግምገማ ስርአት ማበጀት፡፡

ምክር ቤቶች በተመቻቸው አካሄድ፤ ማለት በተለያዩ ኮሚቴዎች ወይም አንድ ላይ ወይም በደረጃው የሚካሄድ ግምገም በማድረግ ከሀገ መንግስቱ ጋር የሚፃረሩ አስተሳሰቦች ለመቀነስ ፣ አሰራሮች በማስወገድ ከንግዲህ የህዝቡን እዉነተኛ ፍላጎቶች እና ቅሬታዎች ትክረት ስጥተው የሚወያዩበት አሰራር መዘርጋት አለባቸው። ህጉች የሚወጡበት የ ማህተም መቺ አዝማምያ (Rubber Stamp) የሚያስወግዱበት ፤ስራ አስፈፃሚው የመከታተል እና የመቆጣጠር ሃላፊነቱ በኩል የታዩትን ድክመቶች ገምግሞ እንዴት ብለው ተጠናክረው ህገ መንግስታዊ ግዴታቸዉን እንደሚወጡ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል። በተለይ በስራቸው ያሉትን ኮሚሽኖችንና ሌሎች እንደ መንግስት ማስ ሚድያ ያሉ ተቛማትን እነሱ በገመገሙበት መንፈስ እንዲያስተካክሉ መምራት ይጠበቅበታል። ዴሞክራሲያዊ ድባብን የሚያጠቡ ህጎችን ለማሻሻል በቁርጠኝነት መነሳት ይኖርባቸዋል።

ህግ አስፈፃሚው በገንዘብ ታጭቆ፣ ጠበንጃ ታጥቆ፣ ዓለም አቀፍ ፋይናንስ እና ሌሎች ተንተርሶ በመዋቅሩ ደግሞ ሁሉን የህብረተሰብ ክፍል የሚያዳርስ በመሆኑ በዚህ እንቅስቃሴ ልዩ ትኩረት ያስፈልገዋል። ህግ አስፈፃሚው በአገራችን መልካም አስተዳደርን በማንገስና ዴሞክራሲን በማስፈን ልዩ ሚና የሚኖረው ያህል ኢ-ዴሞክራስያዊ ድባብ እንዲያብብ አስተዳደርን በማበላሸት ረገድም ዋና ተዋናይ ይሆናል። ከህግ አዉጪዉም ከህግ ተርጏሚዉም ሲነፃፀር እጅግ ፈርጣማ ነው። ልጏም ካላበጁለት እንደ አባይ ፈረስ ደፍጥጧዋቸው መሄድ እንደሚችል መገንዘብ ያስፈልጋል።

ስራ አስፈፃሚው እጅግ ግዙፍ በመሆኑ ከዋናዎቹ ዘርፎች (Sectors) የተወሰኑትን መርጦ እንደ ሞዴል በመውሰድ በማእከል ገምግሞ ሌሎች ሚኒስቴር መስርያ ቤቶችም በላይኛው ኮሚቴ መሪነት በህገ መንግስቱ እና በሌሎች ህጎች ካላቸው ራዕይ እና ተልእኮ እንዲሁም ከስምንቱ የመልካም አስተዳደር መርሆች አዃያ መገምገም አስፈላጊ ነው።

5. የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞችን ሞራላዊ እና ቁሳዊ ፍላጎታቸውን እንደ አዲስ በማጤን አስፈላጊ ማሻሻያ ማድረግ፡፡የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች የህዳሴው ግድብ ዓይነት ፕሮጀግቶች የአገራችን የወደፊት ተስፋ እና የኢኮኖሚ ሃያልነታችን ምልክቶች ቢሆኑም፤ ከአጠቃላይ የሰው ሃይል ልማታችን በንፅፅር ሲታዩ አሁንም ፕሮጀክቶቹ በሁለተኛ ደረጃ የሚታዩ ናቸው። ዋናው አቅማችን የሰው ሃይል ስለሆነ።

ከሰው ሃይላችን መሃከል መልካም አስተዳደር በማንገስ ቁልፍ ሚና ሊጫወት የሚችለዉን በንሮ ዉድነት እየተጎሳቆለ፣ በሚረባና በማይረባ ስልጠናና ግምገማ እየተንገላታ፣ እንዲሁም ራሱ ጭምር የመልካም አስተዳደር እጦት ተጠቂ የሆነበት ሁኔታ ይታያል። አገራችን ገና እያደገች በመሆንዋ የልጆችዋን ቁሳዊ ፍላጎት በሚፈለገው መጠን ለሟሟላት እንደሚቸግራት የታወቀ ነው። ለወደፊቱ እድገት ሲባል ሲቪል ሰርቪሱም ጭምር በንሮው መስዋእትነት መክፈሉ የግድ ቢሆንም እና ከፈተኛ መንገዋለል (Dillema)ቢኖርም፤ መንግስት የሲቪል ሰርቪሱ ኑሮ ለመቀየር ስር ነቀል መዉሰድ ይጠበቅበታል።

ሰማንያ ቢልዩን ብር አካባቢ የሚፈልገዉን የህዳሴ ግድብ መስራት ይሻላል ወይስ የሲቪል ሰርቪሱ ቁሳዊ ፍላጎት በመጠኑም ቢሆን ሟሟላት ይሻላል” እሚል የዕብድ የሚመስል (Crazy Idea) ሃሳብ ቢቀርብ የሚያስገርም አይሆንም። “መንግስት ደሞዝ እንደከፈለ ያስመስላል፤ እኛ ሰራተኞችም ስራ እንደ ሰራን እናስመስላለን” እምትለዋ በየስብሰባው እምትነሳ ነገር በመጠኑም ቢሆን መሰረት አለው። እላይኛው አመራር ቢሆንም በቢልየኖች ብር ላይ እየወሰነና እያሰማራ ተገቢ (Decent) የሆነ ኑሮ የሚያስኖረው ገቢ ከሌለው “እኔ ዓይኔን ጨፍኝያለሁ አንተ እንደፈለግከው አድርግ” እንደ ማለት ነው። የታችኛው ሰራተኛ ቢሆንም ከያንዳንዱ ተገልጋይ “ግብር” እንዲያስከፈል “መመርያ” እንደተሰጠው በሚያስመስል መንገድ ሲንቀሳቀስ ማየት የተለመደ ክስተት ሁኗል። ለልማታዊ መንግስት ስኬት አንዱ ወሳኝ ሁኔታም ብቁ እና ቀልጣፋ የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት መሆኑን መርሳት የለብንም።

በአጠቃላይ እየታየ ያለው ዴሞክራስያዊ ድባብ ዉስጥ ሆነው መብታቸው በሚገባ ያልተከበረላቸው የ ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች በማይረባ ስልጠና እና ግምገማ ሕብረተሰቡን ከማገልገል ተገለው፤ ፍትሃዊ ባልሆነ ግምገማ እና እርምጃ መወሰን የማይችል ፈሪ በሆነበት እና ከብቃት ይልቅ የፓርቲ ታማኝነት ቅድምያ የተሰጠበት ሆኔታ ነው እምንታዘበው። ቁሳዊ እና ሞራላዊ ፍላጎቱ የማይሟላለት የሲቪል ስርቪስ ሰራተኛ ይዞ መሄድ ማለት “መልካም አስተዳደር እንጦርጦስ ግባ” እንደ ማለት ነው እሚቆጠረው።

6. ሚድያዉም መሰረታዊ እሚባሉ የመልካም አስተዳደር እሴቶችን መሰረት አድርገን መገምገም አለብን። ኢቢሲ እና ሌሎች የመንግስት እና የህዝብ ብቻ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ፤ ከኢህአዴግ የፕሮፖጋንዳ መሳርያነት የሚያላቅቅ አሰራር እና የህግ አውጪው ክትትልና ቁጥጥር ያስፈልጋል። ኢቢሲን ብንመለከት ሙሁራን እንዃን ሲጋብዝ በተጠየቁበት ጉዳይ የተናገሩት ደካማ እና ጠንካራ ጎን ሳይሆን፤ ለገዢው ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ በሚጥም መልክ ተቆራርጦ እና በፓርቲው ፍላጎት ልክ ተሰፍቶ ነው እሚቀርበው። ጣብያው የተለየ ሃሳብ ሳይሆን የገዢው ፓርቲ ሃሳብ እና ግምገማ እሚያጠናክር ብቻ እየመረጠ በርካታ ሙሁራን ደግመው እማይሳተፉበት ተቛም ለመሆን በቅቷል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንደኔ ብቻ አስብ ወይም ከኔ ሃሳብ ዉጪ መስማት የለብህም ዓይነት እንደምታ ካለው የ መገናኛ ብዙሃኖቻችን አሰራር ተላቀው በሀገሪትዋ ያሉት የተለያዩ ድምፆች መሰማት መቻል አለባቸው። ከነዚህም የተቃዋሚ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸዉን አማራጭ ለህዝቡ እሚያቀርቡበት ሁኔታ መመቻቸት መቻል አለበት። በተጨማሪም ከቡር የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በአዲሱ ምክርቤት መክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንዳሳሰቡት የመንግስት እና የህዝቡ መገናኛ ብዙሃን የምርመራዊ ጋዜጠኝነትን መርህ በመተግበር መጥፎ አስተዳደርን በመዋጋት ጂቲፒ 2 በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበር የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ ማበርከት አለባቸው። በአጠቃላይ ሚድያዉ በአስተሳሰብ እና በአደረጃጀት እንደገና እንዳዲስ መሰራት አለበት፡፡

የግል መልእክት

በቅርብ ግዜ አንድ ሶስት አርቲክል በመፃፌ የተለያዩ አስተያየት ሳሰባስብ ነበር። ለዚህም ሲባል የተወሰኑ ሰዎችን አሰማርቼ ነበር። ሁለቱም አርቲክሎች የትግራይ ህዝብ እንደሌላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ለአገሩ ለዓላዊነት የከፈለው መስዋእትነት እጅግ ከፍተኛ ሆኖ ሳለ፤ የደርግን ስርዓት በመደምሰሱ እንደ ከዳተኛ ከሚከሱት ሃይሎች ጥቃት ለመከላከል ያለሙ ሲሆኑ ሌላኛው ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ደህንነትና የዉጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ የምደግፈዉን በመደገፍ ድክመቶችን ለመጠቆም የሞከርኩበት ፁሁፌ ነበር።

የብዙዎቹ ሰዎች ምላሽ ታድያ አወንታዊ እንደነበርና፤ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ጆቤ አቶ ገብሩ አስራትን አስበልቶ ከባለስልጣናቱ ጋር ለመታረቅ ፍልጎ ይሆን እንዴ? የሚሉ ሃሳቦችም እንደ ነበሩ ለዳሰሳ ያሰማሩሃቸው ሰዎች ነገሩኝ። የትግራይ ብሎም የኢትዮጵያ ታሪክ በሚጎድፍበት ግዜ ይህን የመከላከል ሞራላዊ ግዴታ እንዳለኝ እንደሚሰማኝ እና ዋናው ፁሁፌ የአቶ ገብሩ መፅሃፍ ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም በኢህአዴግ ያለን የሚታየኝን መሰረታዊ ጉድለቶች ዓቅሜ የቻለዉን ያህል ለመጠቆም መሞከሬን ገለፅኩላቸው። በተጠቀሰው ያለፈው ፁሁፌ አቶ መለስን (ነብሳቸው ያማርና) እና ጄኔራል ሳሞራን መከላከል ያስፈለገዉም የዚሁ የጥቃት ሰለባ በመሆናቸው እና ተነጥለው ስለተጠቁም ጭምር ነው።

ከጄኔራል ሳሞራ በአንጃ ግራንጃ ጉዳይ ብንለያይም፤ አብረን ብዙ ስለሰራን ብንታረቅ ነውር እንደሌለውና ጡረታ ከወጡ በኃላ ቡና ለመጠጣት እና ስላለፈው ጥሩ ግዜ እንድናወራ ብጋብዛቸው ደስ እንደሚለኝ ለዳሰሳ ያሰማሩሃቸው ሰዎችን ነገርኳቸው። ስልጣን ለማግኝት የምሞዳሞድበት ምክንያት እንደሌለኝና ፖለቲካዊነት የህይወቴ አካል ቢሆንም ፕሮፌሽናል ፖለቲከኛ ለመሆን ፍላጎቱም ብቃቱም እንደሌለኝ እንዲሁም ባለኝ ግዜ ለወጣቱ ትውልድ ያለኝ ተሞክሮ በጥናት እየደገፍኩ ማስተላለፍ ከፍተኛ እርካታ እንደሚሰጠኝና ህገ መንግስቱም የታገልኩለት ዓላማ ማሰርያ በመሆኑ እና ካሁን በፊት ከነበረኝ እምነት አሁን ትንሽ ባወቅኩኝ ቁጥር የበለጠ የሚያረካኝ እንደሆነም ገለፅኩላቸው። ህገ መንግስቱ በተገቢ መንፈሱ ሲተረጎም የዓቅሜን ድጋፍ የምሰጠዉን ያህል ሲያኮላሹትም (ከኢህአዴግ ይሁን ከሌላ) የመከላከል ሞራላዊ ግዴታ እንዳለብኝ እንደሚሰማኝም ገለፅኩላቸው።

አመሰግናለሁ

አበበ ተክለሃይማኖት/ጆቤ (ሜ/ጄ)

መስከረም 29, 2008 ዓ. ም

Source HORN AFFAIRS

ዘውዴ ረታ –የታሪኩ ቀንድ ስብራት (1927 – 2008)

$
0
0

2b0b49d35d3eb6f6df3dcb784b6e701d_L
‹‹… ዘውዴ! ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ከሆነው ትውልድ መካከል እንደ አንተ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መንግሥት አመራር በቅርብ የማየትና የመረዳት ዕድል ያገኘ ብዙ ሰው የለም፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ያየውንና የተረዳውን፣ ጣዕም ባለው ጽሑፍ

አብራርቶ ለመግለጽ ተሰጥኦ ያለው እንደ አንተ የመሰለ ጸሐፊ ብዙ የለም፡፡ ስለዚህ በእኔ አመለካከት ሁለት የተጣመሩ ዕድሎች በአንተ እጅ ተይዘው ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ታሪኩን የማወቅና የጽሕፈት ችሎታህ ናቸው፡፡ ስለዚህ እኔ አጥብቄ አደራ የምልህ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መንግሥት ጉዳይ አንተ ዕድል አጋጥሞህ ያየኸውንና ከአዋቂዎች ዘንድ ቀርበህ ያጠናኸውን እውነተኛውን ታሪክ ገልጠህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጻፍለት፡፡ ለዚህ ሕዝብ ከአንተ በኩል ከዚህ የበለጠ የምታደርግለት ሊኖር አይችልም፡፡ አንተም አስበህ የጀመርከውን ለመፈጸም እግዚአብሔር ይርዳህ፡፡ … እኛም ወዳጆችህ፣ ዕድሜና ጤና አግኝተን የምትደክምበትን ለማንበብ ያብቃን…››

ከአሥራ ሁለት ዓመታት በፊት ነበር ታዋቂው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር መርዕድ ወልደ አረጋይ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት አመራርን በቅርቡ የማወቅ ዕድል ለነበራቸው፣ ከእልፍኝ እስከ አደባባይ ከንጉሠ ነገሥቱ ያልተለዩትን ዘውዴ ረታን እውነተኛው ታሪክ ገልጠህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጻፍለት ብለው የተማፀኗቸው፡፡

ይህን የማበረታቻ ምክር መቼም ያልረሱት ዘውዴ ረታ አምና እጅግ ግዙፍ የሆነውን ‹‹የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት›› አንደኛ መጽሐፍ ከነገሡበት 1923 እስከ 1948 ዓ.ም. ድረስ የሚሸፍነውን ታሪክ ለንባብ አደባባይ ያዋሉት፡፡

የአዲሱ መጽሐፋቸውንም የተለየ ፋይዳም እንዲህ አስቀምጠውታል፡፡ ‹‹እንግዲህ ማንም ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው ኢትዮጵያ የነፃነት ችግር ያጋጠማት በሁለት ኮሎኒያሊስት በሆኑ አገሮች ነው፡፡ የመጀመሪያው የፋሽስቱ የሙሶሊኒ የግፍ ወረራ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ነፃ አውጪዎች ነን ብለው በመጡት ወዳጆቻችን በምንላቸው በእንግሊዞች ወታደራዊ የሞግዚት አስተዳደር የተፈጸመብን በደል ነው፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱም ኮሎኒያሊስቶች የኢትዮጵያን ነፃነት ለማስመለስ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት የደረሰበት መከራና ፈተና በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ ይህን ሁሉ በተለይ አዲሱ ትውልድ እንዲያውቀው ስለሚያስፈልግ፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ታሪኩ በተቻለ መጠን ተዘርዝሮ ቀርቦለታል፡፡››

ጋዜጠኛ፣ ዲፕሎማትና ስመጥር የታሪክ ጸሐፊ (ሦስት ዓይና) የነበሩት አምባሳደር ዘውዴ ረታ በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ከዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዕረፍት በኋላ የነበረውን የልጅ ኢያሱን፣ የንግሥት ዘውዲቱ፣ ብሎም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ታሪክ ትክክለኛውን ሒደት የዘመኑም ሆነ መጪው ትውልድ ማወቅ ያስፈልጋል በሚል ነበር የታሪክ መጽሐፋቸውን ‹‹ተፈሪ መኰንን ረዥሙ የሥልጣን ጉዞ›› ለኅትመት ያበቁት፡፡ ‹‹በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኤርትራ ጉዳይ 1941-1963›› ሌላው በመረጃና በማስረጃ የተደገፈ ታሪካዊ መጽሐፍንም እነሆ ብለዋል፡፡

የኤርትራን ጉዳይ የተመለከተው መጽሐፋቸው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገነዘበው በዶ/ር ኃይሉ ሃብቱ አማካይነት “THE ERITREAN QUESTION” በሚል ተተርጉሞ ለሕትመት ዝግጁ መሆኑም ይነገራል፡፡

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ሕገ መንግሥቱ ከተሻሻለበት ከ1948 ዓ.ም. በኋላ የነበረውን በለውጥ የታጀበው ዓቢይ ዘመን የሚያወሳውን መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ ነበሩ አምባሳደር ዘውዴ ረታ፡፡ በተለይ በለንደን (እንግሊዝ)፣ ፓሪስ (ፈረንሣይ) እና ሮም (ኢጣሊያ) ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ስለ ዘመነ ኃይለ ሥላሴ የሚያወሱ ሚስጥራዊ ሰነዶች በቅርቡ ክፍት መሆናቸውን ተከትሎ፣ ጥናትና ምርምር ለማድረግ ነበር መስከረም 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ ባሕር ማዶ ያቀኑት፡፡ ያለሙት የዘመናት ሕልም እውን ሳያደርጉት ተቀጨ እንጂ፡፡ ሞት ቀደማቸው፡፡ የጥናታቸው ቀዳሚ መነሻ ባደረጉት ለንደን ከተማ መስከረም 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በድንገት አርፈዋል፡፡

በኢጣሊያና በቱኒዚያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት አቶ ዘውዴ ረት የተወለዱት በአዲስ አበባ ከተማ በ1927 ዓ.ም. ነው፡፡ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት በፊት ደጃዝማች ገብረ ማርያም የአርበኞች ትምህርት ቤት በሚባለው፣ ከዚያም ሊሴ ገብረ ማርያም በተባለው ትምህርት ቤት ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ሬዲዮ አንባቢነትና በቤተ መንግሥት ዜና አቅራቢነት ተቀጥረው ያገለገሉ ሲሆን፣ በፈረንሣይም በጋዜጠኝነት ተመርቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ ድምፅ ዕለታዊ ጋዜጣና ወርኃዊው መነን መጽሔት ዳይሬክተርም ነበሩ፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የፓን አፍሪካን ኒውስ ኤጀንሲ ፕሬዚዳንት፣ የማስታወቂያ ረዳት ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርም ነበሩ፡፡ በዘመነ ደርግ የስደት ዘመናቸውም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ በዓለም አቀፍ የእርሻ ልማት ፈንድ የመንግሥታት ግንኙነትና የፖለቲካ ኃላፊ ሆነው ለ13 ዓመታት አገልግለዋል፡፡

ሦስት ዓይናው ዘውዴ ረታ በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ለሃያ ሁለት ዓመት በላይ ላበረከቱት ውጤታማ ተግባር ከንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የምኒልክ የመኰንን ደረጃና የኢትዮጵያ የክብር ኮከብ አዛዥ መኰንን ኒሻን ተሸልመዋል፡፡ ከተለያዩ አገሮችም ኒሻኖችን የተሸለሙ ሲሆን፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህም በባሕር ማዶና በአገር ውስጥም ልዩ ልዩ ሽልማቶች ተበርክተውላቸዋል፡፡

ከ49 ዓመት በፊት ከወይዘሮ ገሊላ ተፈራ ጋር ጋብቻ መሥርተው ሦስት ልጆች ያፈሩት አምባሳደር ዘውዴ አስከሬን፣ በሳምንቱ መገባደጃ ከእንግሊዝ መጥቶ ሥርዓተ ቀብራቸው በአዲስ አበባ እንደሚፈጸም ከቤተሰቦቻቸው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ ሪፖርተር ተጻፈ በ ሔኖክ ያሬድ

Did ISIS chief survive iraqi airforce attack today ?Nobody knows yet.-(ALEMNEH WASSE NEWS)

$
0
0

Did ISIS chief survive iraqi airforce attack today ?Nobody knows yet.,,,,የኢራቅ አየር ኃይል ዛሬ ስሙን አይ ኤስ አይ ኤስ በማለት በሚጠራው ታጣቂ ቡድን ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን የሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ገለፀ። የጦር ኃይሉ በዚሁ ርምጃ የቡድኑ መሪ አቡ ባክር አል ባግዳዲ ስለመገደላቸው ርግጠኛ ባይሆንም አል ባግዳዲ ከሌሎች የቡድኑ ባለስልጣናት ጋር ወደ ካራብላ ከተማ በጉዞ ላይ እንዳሉ አስታውቆ ነበር። በርካታ የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በቦምቡ ጥቃት መገደላቸውን የህክምና ባለሙያዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የኢራቅ ጦር ዛሬ የአየር ጥቃት የፈፀመው አንባር በሚባለው የሶርያ ድንበር የሚገኝ አውራጃ ነው። የዚህን ዜና ዝርዝር አለምነህ ዋሴ የተለያዩ ዜና ምንጮችን ጥቅሶ “የአይ ኤስ አይ ኤስ መሪ አልባግዳዲ ከኢራቅ ኃየር ኃይል ጥቃት ተርፎ ይሆን? ሲል የሰራውን ዘገባ ፤ ሊንኩን ተጭነው ያድምጡ።


አሰልጣኙ እንዳሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን “ተነጣጥሏል?”( ኢብራሂም ሻፊ )

$
0
0

12132542_10207769307781322_5283566971429856451_o (1)
እግርኳስ እስከተከወነ እንቅስቃሴ (Movement) አለ፤ እንቅስቃሴ ካለ ደግሞ ቦታ/ክፍተት (Space) መፈጠሩ አይቀርም፡፡ በእግርኳስ እንቅስቃሴ ትልቅ ትኩረት ያገኘው 1953 እ.ኤ.አ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በሀንጋሪ አቻው 6-3 ከተረታ በኋላ እንደሆነ ታክቲክን በተመለከተ ጥልቅ ትንታኔዎችን በማቅረብ የሚታወቀው ፀሐፊ ጆናታን ዊልሰን ይነግረናል፡፡ ጆናታን እግርኳስን በተመለከተ ከቀረቡት ድንቅ መፅሐፎች አንዱ በሚባለው “Inverting The Pyramid” የሀንጋሪ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከተፈጥሯዊ ቦታቸው ውጪ ቶሎ ቶሎ መገኘታቸው እና ሳይሰለቹ እንዲሁም ሳያቋርጡ ቦታ መቀያየራቸውን ተንትኖ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ፍፁም መወናበዱን ይነግረናል፡፡ ከእዚህ ጨዋታም በኋላ በእግርኳስ ስለ እንቅስቃሴ (Movement) ልዩ ትኩረት እንደተሠጠው ሀሳቡን ያስቀምጣል፡፡ ጆናታን እንቅስቃሴን በተመለከተ እዚህ ላይ አያበቃም፤ ዘመናዊ እግርኳስ ደግሞ መልካም እንቅስቃሴ (Good Movement) ይዞልን መጥቷል ይላል፡፡ መልካም እንቅስቃሴን የሚተነትነው የተጋጣሚ ተጨዋቾችን ያለ ኳስ በእንቅስቃሴ ከቦታቸው ውጪ ከመሳብ ጋር አያይዞ ሲሆን፤ ዋነኛ አላማውም በቁልፍ ቦታ ክፍተት (Space) መፍጠር ነው፡፡
ቁጣ ከተሞላበት የአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መግለጫ ብዙ ነገሮችን መዞ መተቸት፣ ስህተቶችን መጠቆም፣ ማስተካከያ ማቅረብ ወይም ሀሳቤን ስሙልኝ ብሎ መወትወት ይቻላል፡፡ ሆኖም ጋዜጣዊ መግለጫው በተለይ ቡድኑ እና ዋና አሰልጣኙ ከተመረጡበት አስተዳደራዊ ማዕዘን ተነስተን መስመር በመስመር የሚተች በመሆኑ የተጨበጠ እና የማያወላዳ ማስረጃ ሲገኝ ብለን ብናቆየው መልካም ነው፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዛሬው ጨዋታ እንቅስቃሴ በአሰልጣኙ ሲገለፅ ጥያቄ ያጫሩብንን ነጥቦች አሉ እና እነሱን እናንሳ፡፡
“የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማጥቃት እንቅስቃሴ የተነጣጠለ እና በአምስት ተጨዋቾች ብቻ የሚደረግ ነው፤ አምስቱ ተጨዋቾች ማጥቃቱን አያግዙም፡፡ ተነጥለው ሜዳቸው ላይ ይቀራሉ (ጥያቄው ቃልበቃል አልተተየበም)” ለሚለው የመንሱር አብዱልቀኒ ጥያቄ የዮሐንስ ምላሽ ” ሆን ብለን ያደረግነው ነው፡፡ ፈጣን እና ጎልበተኛ ስለሆኑ አንድ ባንድ ስለማንችላቸው እና መረዳዳት ስላለብን ተከላካዮቹ መቅረት ነበረባቻው፡፡ ከጨዋታ በፊት ለሁለት አጥቂ አራት ተከላካይ የሚል ዕቅድ ይዘን ነበር፡፡ ከእነሱ ሁለት አጥቂ ጀርባ የእኛ አራት ተከላካዮች መኖር አለባቸው የሚል፡፡ ስለዚህ መነጣጠላችን የታቀደበት ነበር (ምላሹም ቃልበቃል አልተተየበም)” የሚል ነበር፡፡
ለእኔ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሁለት ነገሮችን ስተዋል፡፡ የመጀመሪያው በእግርኳስ መሰረታዊ የሆነውን ሁሉም የዘመናዊ እግርኳስ አሰልጣኞች ያውቁታል የሚባለውን “ሜዳ ላይ ከሚታዩት ሁለቱ ቡድኖች ደካማው የተነጣጠለው ነው” የሚለውን ነው፡፡ ዘመናዊ እግርኳስ በግለሰቦች እና ክፍሎች (Band) [ ክፍሎች ወይም (Band) የሚለውን ቃል ለመፍታት አሰላለፍን ማምጣት አለብን፡፡ ለምሳሌ 4-4-2 አሰላለፍ ዘይቤ የመረጠ ቡድን አንዱ አራት ክፍል ወይም (Band) ነው፡፡] መካከል መጠጋጋትን እጅግ ይፈልጋል፡፡ የአንድ ቡድን በመጨረሻው የመከላከያ ቀጠና እና በመጨረሻው የማጥቂያ ክልል ባለ አጥቂ መካከል ያለው ቦታ/ክፍተት (Space) ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበበ መጥቷል፡፡ እግርኳስም በግለሰቦች ጉልበት፣ ፍጥነት እና የግል ክህሎት ብቻ የምናሸንፈው ስፖርት መሆኑ ከቀረ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ እግርኳስ ከማይረሳቸው ምርጡ ተከላካዮች አንዱ የሆነው ፓውሎ ማልዲኒ ” (አሪጎ) ሳኪ ወደ ኤሲ ሚላን ከመምጣታቸው በፊት ቁልፉ ነገር በሁለት ተጨዋቾች መካከል የሚደረግ ፍጥጫ ነበር፡፡ ሆኖም እርሳቸው ከኳስ ውጪ በሚደረግ እንቅስቃሴ ቀየሩት፤ ጨዋታውን የምናሸንፈው እዛ ጋር ነበር” ይላል፡፡ ሳኪ በኤሲ ሚላን በግለሰቦችም ሆነ ክፍሎች (Band) መካከል ያለውን ቦታ/ክፍተት ጥብብ አድርገው (Pressing) የማይረሳ ቡድን እንደገነቡ ያስረዳናል፡፡ ዮሐንስ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተነጣጠለ እና “ደካማ” እንደነበር በራሱ አንደበት ያስረዳናል፡፡ ወይም የእምነት ቃሉን ይሰጠናል፡፡
ሆኖም የኢትዮጵያ ቡድን ማሸነፉን ስንመዝን ደግሞ “እንዴት ሜዳ ላይ ከታዩት ሁለቱ ቡድኖች ደካማው” ይባላል? ብለን እንጠይቃለን፡፡ መንሱርም ሆነ ዮሐንስ ተስማምተውበት ተከላካዩ እና አማካዩ “የተነጣጠለ” ብለውስ እንዴት ፈረዱበት ብለን እንመዝናለን፡፡ ለእኔ አሁንም አቶ ዮሐንስ እዚህ ጋርም ስህተት ላይ ወድቀዋል፡፡ ጋዜጠኛው “የተነጣጠለ” ሲላቸው ከይሞግተኛል ፍራቻ በመነጨ “አቅደንበት ነው” ብለው ያላቸውን ተቀብለው አልፈውታል፡፡ ሆኖም ከሳዖ ቶሚ ንፅፅር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን “የተነጣጠለ” አልነበረም፡፡
የመጀመሪያውን ግማሽ በ 4-4-2 አሰላለፍ የቀረበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሁለቱ የፊት አጥቂዎቹ (በረከት ይስሃቅ እና ዳዊት ፍቃዱ) አንዱ ወደ ኋላ ተመልሶ በጥልቀት ለመጫወት ባለመፍቀዱ የመስመር ተጨዋቾቹ ( ራምኬል ሎክ እና ኤፍሬም አሻሞ) የመስመር አማካይነትን ብቻ እንዲወጡ፤ እዛው ተገድበው መስመሩን ሸፍነው እንዲከላከሉ እና አደጋ ክልል ኳስን እንዲያሻሙ ተገደው ነበር፡፡ አደጋ ክልል ውስጥ ገብተው ማጥቃቱን እንዳያግዙ በእንቅስቃሴ የተፈጠረ ቦታ/ክፍተት (Space) አልነበረም፡፡ አንዱ አጥቂ በጥልቀት ወደ ውስጥ በመግባቱም ከቀሪው አጥቂ የሚመጣ የጎንዮሽ (Lateral) ቦታ/ክፍተት ፍለጋ እንቅስቃሴ አልነበረም፡፡ የመሀል አማካዮቹም ሽመልስ በቀለ እና ጋቶች ፓኖም ረጅም (Long) እና በቀዳዳ መካከል (Through) ኳሶችን ለማቀበል እና ወደ ጎል ለመምታት ጥረትን ያደርጉ ነበር እንጂ የማጥቃቱ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች አልነበሩም፡፡ በሁለትዮሽ ቅብብል (Double Pass) እና ክፍተትን ተመልክቶ በሚደረግ ሩጫ (Run) አደጋ ክልል መግባት አልቻሉምም ነበር፡፡ ይሄ ሁሉ የተፈጠረው ከበረከት እና ዳዊት አንዱ በጥልቀት ወደ መሀል በመግባት ራሱን ነፃ አድርጎ ኳስን ለመቀበል ፍቃደኛ ባለመሆናቸው፣ የሳዖ ቶሚ የመሀል ተከላካይን ይዘው በጥልቀት ወደ መሀል ባለመግባታቸው እና እዚህ ጋርም የሚፈጠረውን ቦታ/ክፍተት ሽመልስ፣ ጋቶች፣ ኤፍሬም እና ራምኬል ባለማግኘታቸው ነው፡፡ የመስመር ተከላካዮቹ ተካልኝ ደጀኔ (እስኪወጣ ድረስ) እና ስዩም ተስፋዬ ተደጋጋሚ ድራቢ ሩጫዎች (Overlap) አድርገው ማጥቃቱን ለማገዝ በመጣራቸው ቡድኑን “የተነጣጠለ” እንዳንለው ያደርገናል፡፡ ሳዖ ቶሚ ደካማ ቡድን በመሆኑም የሁለቱ የመሀል ተከላካዮች (አስቻለው ታመነ እና አንተነህ ተስፋዬ) አቋቋም ለመሀሉ የተጠጋ እና ከመጨረሻው አጥቂ ተጨዋቾች ብዙም ያልራቀ ነበር፡፡ ይህም ቡድኑ “አልተነጣጠለም” ለሚለው ማሰሪያ ማስረጃ መሆን ይችላል፡፡
ቡድኑ “ላለመነጣጠሉ” ሁነኛ ማስረጃ ከፈለግን ደግሞ ሁለተኛውን አጋማሽ ማየት አለብን፡፡ በክለቡ በተለያዩ የአማካይ ስፋራዎች የሚጫወተው ብሩክ ቃልቦሬ የግራ መስመር ተከላካይነት ሚናን ይዞ መግባቱ እና በረከት ወጥቶ አስቻለው ግርማ ቦታውን መያዙ ብዙ ነገሮችን አስተካክሏል፡፡ የብሩክ መግባት ለአማካዮቹ ኳስን ተቀብሎ ሊያቀብላቸው የሚችል (ወይም አማካዮቹ ኳሱን ለመስጠት እምነት የሚጥሉበት) ተከላካይ ተጨዋችን የሰጣቸው ሲሆን አስቻለው ደግሞ ከቅርፅ ጀምሮ ቡድኑን በሁሉም መስክ ቀይሮታል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዚህ አጋማሽ ለ4-2-3-1 የቀረበ ጨዋታን አሳይቶናል፡፡ በአራት ክፍል (Band) የአሰላለፍ ዘይቤ መቅረብ ደግሞ ጥቅጥቅ ብሎ እና ቦታን እየተቀያየሩ ለመጫወት አመቺ ከመሆኑም በላይ አጥቂው የመሀል ተከላካዩን ይዞ ወደ ኋላ ሲመለስ ቢያንስ ለሦስት ተጨዋቾች በቁልፍ አካባቢ ቦታ/ክፍተትን የሚፈጥር በመሆኑ ኢትዮጵያ በርካታ የጎል ዕድሎችን አግኝታለች፤ አምክናቸዋለችም፡፡ በኢትዮጵያ የመጨረሻ ተከላካይ እና በመጨረሻው አጥቂ መካከል ክፍተቱ የበለጠ በማነሱ እና ዳዊትም ወደ አማካዩ በጥልቀት እየመጣ ለመጫወት ፈቃደኛ በመሆኑ ቦታ/ክፍተት እንደልብ ሲገኝ ነበር፡፡ እዚህ ላይ ግን የሳዖ ቶሚን ደካማ መሆን እና 2-0 ሲመሩ ታክቲካል ስርዐታቸውን ለመጠበቅ ያሳዩትን ዝቅተኛተነሳሽነት መረሳት የለበትም፡፡ በዚህ አጋማሽ የአራት ክፍሉ (Band) አጨዋወት የመስመር አማካዮችን ወደ ጎል በደንብ ስለሚያቀርብ፤ አማካዮችም ክፍተት እያዩ እና የሁለትዮሽ ጨዋታ እየተጫወቱ ወደ አደጋ ክልል እንዲገቡ ስለሚያስችል በርካታ ተጨዋቾች የጎል ዕድል አግኝተዋል፡፡ ዳዊት፣ ራምኬል፣ ኤፍሬም፣ አስቻለው ግርማ፣ ቢኒያም በላይ እና ሽመልስ ለጎል የቀረቡ ኳሶችን አባክነዋል፡፡ ሽመልስ እና ጋቶች መሀሉን በሚገባ በመቆጣጠራቸው በአጥቂ መስመር የሚደረገውን እንቅስቃሴ እና ክፍተት የማግኘት ሂደትን የላቀ ቦታ ሰጥቶታል፡፡ አራት ክፍል (Band) የአሰላለፍ ዘይቤ በተፈጥሮው ከሌሎች አሰላለፎች አንፃር የበለጠ ዋላይ (Fluid) በመሆኑ ሽመልስ፣ ራምኬል፣ አስቻለው፣ ኤፍሬም እና ዳዊት ቦታን እየተቀያየሩ ሳዖ ቶሚዎችን በልጠዋል፡፡ ብሩክ፣ ስዩም፣ አንተነህ፣ አስቻለው ታመነ እና ጋቶችም ከአጥቂዎቹ በቅርብ ርቀት ስለነበሩ ጨዋታውን አሳክተውታል፡፡ የሳዖ ቶሚ ተጨዋቾች ተመቻችተው ወደ ጎል ከርቀት የመምቻ ክፍተትን እንኳን አሳጥተዋቸዋል፡፡ የላቀ ጥራት ያለው ቡድን ሲመጣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አቀራረብ እና የጨዋታ አቀባበልን ማመን ቢከብድም ቢያንስ በዚህ ጨዋታ ቡድኑ “አልተነጣጠለም”፡፡

ተመስገን ደሳለኝ በግፍ ከታሰረ አንድ አመት ሞላው! ( አቻምየለህ ታምሩ )

$
0
0

ፈላጭ ቆራጭ አምባገነኖች ባሉበት ሁሉ የጀግና ማደሪያው እስር ቤት ነው። ተመስገን ደሳለኝም የአዕምሮው የበላይነት በቀሰቀሰው ፍርሀት ሳቢያ ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስትነት በተሰየመው ሽፍታ ቡድን በግፍ ከታሰረ ይሄው አንድ አመት ሞላው።
12095999_1066212580079492_5489674840184367941_n
በመሰረቱ የወያኔ ፖለቲካ የጀግኖች የአዕምሮ የበላይነት የቀሰቀሰው ፍርሀትና ጥላቻ ነው። በመንግስትነት የተሰየሙት እነዚህ ሽፍቶች የአዕምሮ የበላይነት ያለውን ሰው ሁሉ መታሰቢያው ከምድር እንዲጠፋና በዓለም እንዳይኖር በማድረግ ድምፅ ያልነበረው ህዝብ ድምጹ እንዲጠፋ በማድረግ ከብርሃን ወደ ጨለማ ይመልሱታል። ለወያኔዎች ፖለቲካ ማለት ከተቻለ ሁሉን ወደ ዞምቢነት መቀየር፤ካልተቻለ ደግሞ አሳዶ ማሳደድ ነው፤ ምክንያቱም እነሱ የእድገት ተስፋቸውን ያቆራኙት የአዕምሮ የበላይነት ካላቸው ሰዎች ውድቀት ጋር ነውና!
ስለ ተመስገን ደሳለኝ ስጽፍ ውዬ ስጽፍ ባድር ተመስገንን በሚገባው መጠን የገለጽሁት መስሎ አይሰማኝም። ተመስገንን ሳስበው ሁልጊዜ አስቀድሞ ወደ ህሊናየ የመሚጣው ግን እንደ ሰው ተፈጥሮ፣ እንደ ሰው ማሰብና እንደ ሰው መኖር ያልተሳነው የዘመናችን ጀግና መሆኑ፤በቁሳዊ አለም ውስጥ እየኖረ በጎ ሰውነቱ ግን ሞልቶ የተትረፈረፈ አይበገሬና ቆስቋሽ ብዕረኛቱ ነው።
እንደ አንድ አገር ወዳድ ዜጋ ተሜ ለአገሩ የሚጠበቅበትን በማድረጉና ለህሊናው ተገዢ በመሆኑ ያልተደሰቱበት ዞምቢዎቹ ወያኔዎች በግፍ ዘብጥያ አውርደውት ሰቆቃ እየፈጸሙበት የጭካኔያቸው ማርኪያ በማድረግ፤ በፍቅር የሚሳሱለት አሮጌ እናቱ እንኳ አይኑን እንዳያዩት አርቀው ማሰራቸው ሳያንሳቸው እንዳይጠይቁት ከልክለው ሁለት ትውልድ ያስለቅሳሉ።
ተመስገን ደሳለኝን በቅርብ የማውቀው ወንድሜ ነው፤ እንደ ጽሁፉ አንባቢም አብሮት እንደሰራም ሰው የማደንቀው ጎልማሳ ነው። ተሜ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን አሰልፎ «ተራሮችን በነፍጥ እንዳንቀጠቀጠ» የሚደሰኩረውን የወያኔ ቡድን ብቻውን በብዕሩ ያንቀጠቀጠ የዘመናችን ትንታግ ብዕረኛ ነው። ተመስገን ደሳለኝ ከምርጫ 97 በኋላ በተፈጠረው የለውጥ ስሜት መጨናገፍ ሳቢያ «ተስፋ ቆርጦ አንድ ላይ ከመቆም፡ ይሻላል በተስፋ ሲጓዙ መክረም» የሚል መንፈስ በሰላማዊ ትግሉ ጎራ እንዲያንሰራራ ታላቅ ስራ የሰራ የህዝብ ልጅ ነው ብዬ አምናለሁ።
12048561_1027416840626506_244110668_n
ተመስገን ደሳላኝ ዘርፈ ብዙ ስብዕና የተላበሰ የቀለም ቀንዲል ነው። ተመስገንን በወዳጅነት ለመጎዳኘት ለቀረበው ሰው፡ እሱ ግንኙነቱን ወደ ወንድማዊ/ እህታዊ መተሳሰር ለውጦት ያገኘዋል። እኔ ግን ከተሜ ወንድማዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊና ሞያዊ በረከትም የተቋደስሁ ሰው ነኝ። ይህንንም እሱ ያሳትማት በነበረች መጽሄት ለመጀመሪያ ጊዜ ባሳተምሁት ጽሁፌ ገልጨዋለሁ። ተሜን አንድ ሰው አዲሳባ ለሆነ ጉዳይ ማግኘት ፈልጎ ለቀጠረውም ሆነ በእንግድነት ሊጎበኝ ወጣ ባለባቸው ያገራችን ክፍሎች ሁሉ፤ በእግድነት የሚያስተናግደውን ሰው እንግዳ ያደርገውና ራሱን እንግዳ ተቀባይ አድርጎ የሚያስተናግድ ሰው ነው። ከዚህም አልፎ ተመስገን፣ ሌሎች ጓደኞቹም እንደሚመሰክሩለት፣ እጁን ዘርሮ የማይታክትና የማይነጥፍ ምንጭ ነው።
ተመስገን ከዘመን ተጋሪዎቹ አልፎ በመሄድ፣ በተባ ብዕሩ፣ ባዲስ አቀራረብ፣ የፖለቲካና የሲቪል ነጻነት ሐሳቦችን ለወገኖቹ ኢትዮጵያውያን ለማሳወቅ የተጋ፣ ሌት ተቀን ታግሎ ያገሩ ልጆች የመንፈስ ግዛታቸውን ለማስፋት የጣረ ምርጥ ሰው ነው። እንደ ተሳለ ካራ በምታበራው ብዕሩ ሀሳብ አፍልቆ የወቅቱን አስገባሪ ቡድን ድብቅ ድርጊት ባደባባይ ለህብረተሰባችን እያጋለጠ ለኋላ ቀር ገዢዎቻችን የእግር እሳት፣ ለኢትዮጵያውያን ደግሞ የንቃተ ህሊና መብራት የሆነ የእናት አገሩ የስለት ልጅ ነው።
ለተሜ ፖላቲካ በእውቀት የተሻሉ ሰዎች ህዝብን ለማገልገል ያስተሳሰብና የተግባር ፉክክር የሚያደርጉበት እንጂ ልክበር፣ ልሰር፣ ልግደል፣ ልበድል፣ ባይ ልቦናን ድል ሳያደርግ ዳግማዊ ሚኒልክ ቤተ መንግስትን መቆጣጠር ስላልሆነ፤ የመንግስትነት ጠባይ ሳያሳይ 24 ዓመታትን አገባድዶ 25ተኛውን የግፍ ዘመን ለማክበር ተፍ ተፍ እያለ ያለውን ቡድንም ፣ «መለስ ሆይ፡―ክልምኖም ይስምዑኒ» እያለ አደብ እንዲገዛ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል።
ፍርሀትና ጥላቻ ሆደ ጠባብ እንዲሆን ያደረገውን ይህን በመንግስትነት የተሰየመ የባሪያ አሳዳሪዎች ቡድን፤ ከሩብ ክፍለ ዘመን የመንግስትነት ቆይታ በኋላም በዕውቀትና በጥበብ ከፍ ያለ አእምሮ ያላቸውን ሰዎች እያሳደደ፣ ከሰውነት ጠባይ ወጥተው ሲሰሩ ያገኛቸው ይመስል የሃጢያት ክስ እየደረደረ፣ እልቆ መሳፍርት ምርጦችን አሳጥቶ ዛሬ ራቁታችንን አቁሞን ይገኛል።
የተሜ የሀጢያት ክስ ሲገለጥ እንደ ሌሎች የህሊና እስረኞች ሁሉ «ጥፋቶቹ» ተመሳሳዮች ናቸው። ከጥፋቶቹ መካከል እንደ ገዢው ቡድን የተወለዱበትን አካባቢና የተዛመዳቸውን ብቻ አገሬና ወገኖቼ ብሎ አለመለየቱ፤ በሰፊው አስተያየት ገምቶ የሰውን ዘር ሁሉ እንደ ወንድም ባለማስተዋል ወገኔ ዘሬ ባለማለቱ፤ልቦናውንና አእምሮውን በጥበብና በስልጣኔ ያለሰለሰ ሰው ሆኖ መገኘቱ፤ አገሩን በጠባቡ ክልላዊ ጠረፍ ወስኖ ሰው ያለበትንና ተሰርቶ የሚታደርበትን ሁሉ አገሬ ነው በማለቱ የተነሳ እና ሌሎች ዝባዝንኪ ሰበቦችም ተደርድረውበታል።
እውነቱ ግን ተመስገን፡ ሁሌ በሚጽፋቸው ጽሁፎቹ ለጆሮ የሚቀርቡ ጉዳዮችን እያነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ ከገዢዎቹ ተላቆ በህሊናው መሪነት የገዛ ራሱ አስተዳዳሪ ወደሚሆንበት ምድረ ርስት ለማድረስ የታተረ ጀግና ነው። ይህ ጠቢብ ባሁኑ ወቅት ያለው አገዛዝ እጅግ አጥቦት ካለው የህይወት መስክ ኢትዮጵያውያን ወጥተው፡ እውቀት ከሚያስገኘው የነጻነት ሰፊ ሜዳ ገብተው እንደልባቸው ተዝናንተው እንዲራመዱ፡ ብርቱ የሆነ የሰለጠነ ትግል እንደሚያስፈልግ በመምከሩ እንደ ጨካኝ ነፍሰ ገዳይ በጨለማ እስር ሆኖ በተፈጸመበት ግፍ ምክንያት ጀርባው አብጦ፤ግራ ጆሮው ሙሉ ለሙሉ መስማት አቁሞ ስለእኛ እጅግ ብዙ መስዕዋትነትን እየከፈለ ይገኛል። በዘመነኞች ተዓብዮ እንዲህ የህዝብ ልጆች ስቃይና ግፍ ሞልቶ ሲፈስ ሰሚ ቢጠፋም መጪው ትውልድ ይፋረድበት ዘንድ የነተሜን ስቃይና ግፍ የኢትዮጵያ አፈርና ቅጠል ሰምቶ በታሪክ መዝገብነት ቀርጾ አስቀምጦታል።
ተሜ የዘመናችን አቤ ጉበኛ ነው። በችሎታው ስለሚመካ፣ ስለሚጽፈው ጽሁፍ ብዙ አይጨነቅም፤ ለሱ እንደማንኛውም ነገር የሚሰራው ስራ ለህትመት ሲበቃ ብዙ አንባቢን ያነጋግራል። ተመስገን፡ የብእር ትሩፋትን፡ እንደ ቅኔ መምህሩ ስብረ አብ፡ ሁለት ቤት ቅኔ፡ እንዲነበብ አድርጎ ያስተዋወቀ ታላቅ ብእረኛ ነው። ተሜ በteam work የሚያምን፣ ፈገግታ የማይለየው፣ ሞያውን የሚያከብር፣ በስሩ አብረውት የሚሰሩትን የሞያ ጓደኞቹን ችሎታ የማይጋፋ፡ይልቁንም የሚያከብር፣አድናቆትና ምስጋናውን ያላንዳች ስስት የሚቸር፣ መታበይና ትክሻን መስበቅ የማያውቅ፣ መስሪያ ቢሮውና መኖሪያ ቤቱ ሳይቀር ለሁሉም ክፍት የሆኑ፣ በህትመት መገናኛ ብዙሀን አዲስ አሰራር ፈር የቀደደ የህዝብ ድምጽ ነው። ይህንን አንደበት እስር ቤት ቆልፎ እንዲሰቃይ ማድረግ የሚያም ትልቅ አገራዊ ጉዳት ቢሆንም ቅሉ፤ የእርሱ መታሰርና መሰቃየት ለሀገሩ የሚገባውን ሰርቶ ነውና እኛ ያልታሰርነውና ከእስር ያመለጥነው እርም አንልም! ተሜ ሆይ ተመልሰን የምንገናኝበት ቀን ግን ሩቅ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለሁ። እስከዚያው ባለህበት ሰላም ሁን!

ኢህዴግ በሚጠራው መድረክ አለመገኘት ማንን ይጠቅማል? (ግርማ ሠይፉ ማሩ )

$
0
0

ቅጥ አንባሩ የጠፋው የኢትዮጵያችን ፖለቲካ በዋነኝነት የሚጎድለው ልክ ያልሆነን ነገር ልክ አይደለም ማለት ያለመቻል ነው፡፡ በግል አስተያየት ልክ አይደለም ብሎ መቆም ደግሞ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ የተሳሳተ ውሳኔ ባለቤቶች በድጋሚ ጥፋታቸውን በጥፋት ለማረም ሌላ ስህተት ይደግማሉ፡፡ አሰተያየትን በአሰተያየት ለመመለስ ይከብዳቸዋል፡፡ የዚህ ደግሞ ዋነኛው ሰለባ የተቃዋሚው ጎራ ነው፡፡ ለነገሩ አሁን ይህ ነው የሚባል ተቃዋሚ አለ ባይባልም፤ ያሉትም ቢሆኑ ከልምድ የሚማሩ ዓይነት ሆነው አልተገኙም፡፡
1780811_751873094830908_1867964153_n
ለዛሬ ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ አንድ ሰሙ “የአንዳርጋቸው ፅጌ ብርሃን” በሚል የብዕር ሰም የሚከተለውን መልዕክት በፌስ ቡክ ገፄ የውስጥ መልዕክት ማስቀመጫ
“ግርማ ካሳ (ልብ በሉ እኔ ግርማ ሠይፉ ነኝ) ወረድክብኝ በጣም። ተፈጭቶ ተቦክቶ ተጋግሮ ሊበላ የቀረበውን ነገር ድጋሚ ወፍጮ ቤት ይሂድ ብለክ እየተከራከርክ ነው። 24 አመት ሲያታልል የኖርን መንግስት ዛሬ 25ኛው አመት ላይ ሆነክም እንዴት አልገባክም? ስንት አመት ነው የሚፈጀው እንዳንት አይነት ሰዎችን ለማብሰል? ተወያየተክ ምን ታተርፋለክ ? ወያኔ ተቃዋሚዎችን የሚፈልገው ለተራ ፕሮፖጋንዳው ሊጠቀምባቸው እንጂ ለነሱ ሀሳብ ጆሮ ለመስጠት አደለም። መንግስት እራሱ ያወጣውን ህግ ጥሶ ያሰራቸውን የፓርቲ አባሎችን ለማስፈታት ከወያኔ ጋር ስብሰባ መቀመጥ አያስፈልግም። እንዲ የምታስብ ከሆነ ከአልም ሁሉ ተለይተክ ከሀይለማርያም ደሳለኝ ብቻ የተሻልክ ጅላጅል ነክ ማለት ነው። ወያኔ ለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጻፈውን ድብዳቤ ልብ ብለክ አንብበከዋል ? እንዲ የሚል አርፍተ ነገር አለበት። “በሀገራችን የሚገኙ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች “እንደ መላው የሀገራችን ህዝቦች ” እያለ ይቀጥላል። ሲጀመር ወያኔ እነዚ ፓርቲ ብሎ የሚያውቃቸው ድርጅቶች ከህዝብ ተለይተው ያሉ እና የህዝብ ድጋፍ የሌላቸው አርጎ ነው የጠራቸው። ፀረ ህዝብ አርጎ ነው የሚስላቸው። አንደ ህዝብ አካል አርጎ አይቆጥራቸውም አያከብራቸውም። አንዳንተ ዓይነት አሟሟቂ ሰው ነው ወያኔ የሚፈልገው።ኢቢሲን አሟሟቂ”
የሚል መልዕክት አስቀመጠልኝ፡፡
መልዕክቱ የተፃፋው በዚህ ጉዳይ አስተያየት ለሰጠው ወዳጄ ግርማ ካሣ ይመስላል ነገር ግን የተላከው ለእኔ በእኔ አድርሻ እና እኔን በዓይነ ልቦናው እየሳለ እንደሆነ ያስታውቃል፡፡ በእኔ እይታ ደግሞ የግርማ ካሣን ሃሳብ መደገፍ ብቻ ሳይሆን በግል ለደወሉሉኝ አቋሜን ገልጬ ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ ግን ሚዲያ ላይ ወጥቶ አስተያየት መስጠት ብፈልግም፤ ብዙ ምቾት አልተሰማኝም ነበር፡፡ ለማነኛው የዚህ አሰተያየት ሰጪን ሃሳብ መነሻ አድርጌ የግሌን አስተያየት ላቅርብ፡፡
በመጀመሪያ ማነኛውም ግብዣ ላይ የተጠራ ሰው ግብዣ የሚሄደው በመከባበር ሰሜት መሆን አለበት፡፡ ጠሪ አክባሪ በሚል እንጂ ግብዣው ላይ ምን ድግስ አለ በሚል መሆን የለበትም፡፡ በእኔ እምነት ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራዊ አጀንዳ ላይ ከዚህ በፊት ጥሪ ተደርጎላቸው የማያውቁ የፖለቲካ ፓርቲውች መድረክ፣ ሰማያዊ እና መኢህአድ ግብዣ ተደርጎላቸዋል፡፡ ለምሳሌ በመጀመሪያው የአምስት ዓመት ዕድገትና ትራንሰፎርሜሸን ዕቅድ እና በአባይ ግድብ ወቅት ጥሪ ስለ አልተደረገላቸው አልተጠራንም ሃሳባችንን መስጠት እና የጋራ ማድረግ አልቻልንም ሲባል ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የፖለቲካ ምዕዳሩም ሆነ አጠቃላይ ሀገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ተመሳሳይ ነበር፡፡ በዛን ጊዜ ተቃዋሚዎች አልተጠራንም ሲሉ የነበረው ተጠርተው ለመቅረት አይመስለኝም፡፡ ተገኝተው ሃሳባቸውን ለማካፈል ይመስለኛል፡፡
በእኔ እምነት አሁን በተደረገው ጥሪ መስረት ከላይ ሰማቸውን የጠቀስኩት ፓርቲዎች ተገኝተው የሚከተለውን ማከናወን ይችሉ ነበር፡፡ መጀመሪያ ያለፈው አምስት ዓመት ክንውን ሲቀርብ ከመነሻው ጀምሮ በጋራ ከተቃዋሚዎች ጋር በጋራ ለመስራት መንግሰት እርምጃ ባለመውሰዱ የእቅዱ ዋና ዋና ምሶሶ የሆኑት ተግባራት ያለመሳካታቸውን በተጨባጭ ማስረጃ ለማስረዳት እድሉን ሊጠቀሙበት ይችሉ ነበር፡፡ ለምሳሌ የባቡር ዝርጋታ ከታቀደው 30 ከመቶ ያለመሰራቱ፣ በኤሌትሪክ ሀይል በተመሳሳይ 20 ከመቶ እንኳን ያለመሳካቱ፤ በመንገድ በውጭ ንግድ፣ በዋጋ ማረጋጋት፣ በግብርና በተለይ በሰፋፊ እርሻ ወዘተ.. ያሉትን መሰረታዊ ችግሮች በማሳየት ለዚህ ዋነኛው ችግር በጋራ በመስራት ሊገኝ የሚችለውን ሀገራዊ ሀይል ወደ ጎን ማድረጋቸውን ለህዝብ ይፋ ማድረጊያ መድረክ ይሆን ነበር፡፡ በተለይ የአባይ ግድብን ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ መጠቀሚያ እንዲሆን በማድረጉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሊያደርጉ የሚችሉት ከፍተኛ አሰተዋፅኦ መገደቡን ለመናገር ከዚህ የተሻለ ትክክለኛ መድረክ የሚያገኙ አይመስለኝም፡፡ ይህንን መድረክ ለመጠቀም ባለመቻላቸው ትልቅ የፖለቲካ ኪሣራ ይመስለኛል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ገዢው ፓርቲ እራሱ ያመነውን የመልካም አስተዳደር መፍቻው ቁልፍ መንገድ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ እና በተለይ ደግሞ የሚዲያዎች ተሳትፎ መኖር ተዓማኒነት የሚጣልባቸው የፍትህ ስርዓት መሆኑን በሰብሰባው በሚፈጠሩ አጋጣሚዎች ሁሉ በማንሳት ዕቅዱ ያልተሳካው ይልቁንም ሙስና የተንሰራፋው ስርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኘኞችና አምደኞች በመታሰራቸው፣ እምነት የሚጣልበት የፍትህ ስርዓት ባለመኖሩ እንደሆነ አጋጣሚውን መጠቅም ይቻል ነበር፡፡ ለዚህ ደግሞ ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዝግጅት አድርገው መሳተፍ እንጂ አድማ አድርጎ ከግብዣ በመቅረት ውጤት የሚገኝ አይመስለኝም፡፡ ይህ ትልቅ ሰህተት ይመስለኛል፡፡
ከዚህ ውይይት በማስከተል “የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም” በሚል ተረት ከገዢው ፓርቲ ጋር ተመራርቆ ለመውጣት ሳይሆን በቀጣይ ዕቅድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለያዩ ሀገራዊ አጀንዳዎች በምን መልክና ደረጃ ስንሳተፍ ይህ ዕቅድ ተግባራዊ ይሆናል በሚል መነሻነት የድርጊት መርዓ ግብር በመንደፍ የጋራ ኮሚቴ አቋቈሞ መውጣት፣ በተለይ የፖለቲካ ምዕዳሩ ለማስፋት የሚቻልበት መንገድ መቀየስ ሊሞከር የሚገባው ትልቅ ስራ ነበር፡፡ ይህ ከገዢው ፓርቲ ባህሪ አንፃር ተቀባይነት ባያገኝ እንኳን እንቢተኝነቱን ለማጋለጥ ይረዳ ነበር፡፡ እንደ ፓርቲ ሰርተፊኬት ይዞ ዓመት ከመቁጠር በዘለለ መንግሰት በተገኘበት ሁሉ እየተገኙ ድምፅ ማሰማት (ባይሰሙም መጮኽ) ግዴታቸው ነበር የሚል የግል አቋም አለኝ፡፡
እውነቱን ለመናገር በቁጥር እስከ ሃያ የሚደርሱ የፓርቲ አባላትን (ለምሳሌ ሶስቱ ፓርቲዎች 60 አባላትን) በአንድ መድረክ ላይ እንዲገኙ የተሰጠን እድል ያለመጠቀምን ያክል ደካማ ውሳኔ አይታየኝም፡፡ እያንዳንዳቸው ሁለት ደቂቃ መልእክት ቢያስተላልፉ የሁለት ሰዓት መልዕክት በመንግሰት ጆሮ ላይ ማስቀመጥ ይቻል ነበር፡፡ እነዚህን አጋጣሚዎች በእስር የሚማቅቁ ጓዶቻችንን በማንሳት ልንዘክራቸው ይገባ ነበር፡፡ አሸባሪ ያሏቸውን “ጀግኖች” ብለን ልናወደስ የምንችልበት መድረክ ያለመጠቀም በምን መመዘኛ ልክ እንደሚሆን አይታየኝም፡፡
ገዢው ፓርቲ ከአሁን በኋላ ለማነኛውም ዓይነት ውይይት ሳይጠራ ዳተኛ ቢሆን ሰበብ አግኝቷል፡፡ ቢጠሩም አይገኙም ይልቁንም በሚጠሩበት መድረክ ከመገኘት ይልቅ ውጪ ሆነው መግለጫ በማውጣት ላይ ይገኛሉ ብሎ ለሀጋሮቹ ማስረጃ ያቀርባል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከኢህዴግ መንግስት ባልተናነሰ ካድሬ የሆኑ የአሜሪካን እና አውሮፓ ህብረት ድጋፍ ሰጪዎች ይህን ለመስማት እና ለማመን ብዙ አይቸገሩም፡፡
በእኔ አረዳድ ፓርቲዎቹ በግብዣው ላይ ተገኝተው በምን ጉዳይ አተኩረው እንደሚናገሩ እንዴት አድርገው የፖለቲካ ጥቅም እንደሚያገኙበት መካሪ አላገኙም፣ በውስጥም በቅጡ አልመከሩበትም፡፡ የሚያሳዝነው እነዚህ ፓርቲዎች የአሜሪካ ኤምባሲ ለስዕል ኤግዚቢሽን ምረቃ ቢጠራቸው በግብዣው ላይ ይገኛሉ፡፡ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባል ሊያነጋግራችሁ ይፈልጋል ቢባሉ ይገኛሉ፡፡ መገኘት ብቻ ሳይሆን አነጋገሩን ብለው ዜና ይሰራሉ፡፡ እንግዲህ አንባገነኑ ኢህአዴግ ዲሞክራት እሰኪሆን ጠብቀው ለመወያየት ከሆነ ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡ ባለፈው ፕሬዝዳንት ኦባማ ጉብኝት ሲያደርጉ ለግንኙነት በሚመቸው የእራት ግብዣ ላይ ላለመገኝት ወስነው በብዙ ሜትር ርቀት በቴሌቪዥን በተሻለ ለመከታተል በሚቻልበት የአዳራሽ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ሲወስኑ ዝም ማለታችን አበጃችሁ ያልን የመሰላቸው መሪዎች፤ ይህንንም ግብዣ ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል አለመቻላቸውን ዝም ማለት ተገቢ አይደለም ለማለት ሲባል የቀረበ አስተያየት ነው፡፡ በእኔ እምነት በሰላማዊ ትግል በሀገር ውስጥ ለመንቀሳቀስ የወሰነ ማንኛውም አካል መንግሰትን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እያገኙ መልዕክት ማስተላለፍ ተገቢ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው፡፡ ገዢው ፓርቲ እና መንግሰት በሚጠሩት ማንኛውም ስብሰባ ላይ ላለመገኘት መወሰን የሚጠቅመው ገዢውን ፓርቲ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ሃሣብ ያለው በመቅረት የሚገኘውን ጥቅም ቢያስረዳኝ፣ በተለይ አሁን በተደረገው የሁለተኛው የእድገት እና ትራነስፎርሜሽን እቅድ ለመወያየት በተደረገው ጥሪ ላይ ያለመሳተፍ ያስገኘውን ጥቅም ለሚያስረዳኝ ለመማር ዝግጁ መሆኔን እገልፃለሁ፡፡ በደፈናው ገዢውን ፓርቲ እውቅና መንፈግ የሚል መልስ ግን አልቀበልም፡፡ በሀገር ውስጥ ሆኖ በዚሁ መንግሰት ስር እየተዳደሩ እውቅና መንፈግ የሚባል ፖለቲካ አይገባኝም፡፡
ቸር ይግጠመን!!!!
girmaseifu32@yahoo.com, www:girmaseifu.blogspot.com

አራቱ የዞን ዘጠኝ አባላት ነፃ ተባሉ፤ በፍቃዱ ሀይሉ በወንጀል ህጉ እንዲከላከል ተወሰነ

$
0
0

12107780_1512167905763406_2572413332814840742_n
በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው አንድ አመት ከአምስት ወር በላይ ፍርድ ቤት ሲመላለሱ የቆዩት የዞን ዘጠኝ አባላት ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ተወስኗል፡፡ የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥቅምት 5/2008 በዋለው ችሎት ከዞን ዘጠኝ አባላት መካከል 1ኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ፣ 3ኛ ተከሳሽ ናትናኤል ፈለቀ፣ 5ኛ ተከሳሽ አጥናፍ ብርሃኔና 7ኛ ተከሳሽ አቤል ዋበላን መከላከል ሳያስፈልጋቸው ተከሰውበት ከነበረው የሽብር ወንጀል ነፃ በመሆናቸው ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡
በሌላ በኩል 2ኛ ተከሳሽ በፍቃዱ ሀይሉ በብሎግ ወጥተው በማስረጃነት ከቀረቡበት የፅሁፍ ማስረጃዎች መካከል አመፅ ቀስቃሽ ናቸው በተባሉት ፅሁፎች ከሽብርተኛ ወንጀል ወጥቶ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 557/ሀ እንዲከላከል ተወስኗል፡፡ በፍቃዱ ሀይሉ በዋስ እንዲወጣ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን የዋስትናውን ጉዳይ ለማየት ለጥቅምት 10/2008 ዓ.ም ተቀጥረሯል፡፡
የዞን ዘጠኝ አባላት ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ ለአንድ አመት ከአምስት ወር ያህል ብይን ሲጠባበቁ የቆዩ ሲሆን ለብይን 5 ጊዜ እንዲሁም በአጠቃላይ ለ38 ጊዜ ፍርድ ቤት ተመላልሰዋል፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ

ከዞን ዘጠኝ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

12106870_888646904557136_8673514626248909683_n
በዛሬው ዕለት የልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ፩ኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ ፪ተኛ ተከሳሽ በፍቃዱ ሃይሉ ፫ተኛ ተከሳሽ ናትናኤል ፈለቀ ፭ተኛ ተከሳሽ አጥናፍ ብርሃኔ እና ፯ተኛ ተከሳሽ አቤል ዋበላ ተጠርጥረው ከነበረበት የሽብርተኝነትና የኅብረተሰቡን ደህንነት አደጋ ላይ የመጣል ክስ ነጻ መውጣታቸውን በበጎ መልኩ የምንቀበለው ቢሆንም
1. ፪ተኛ ተከሳሽ በፍቃዱ ሃይሉ በሃይል ተገዶ ማዕከላዊ ምርመራ ውስጥ በማሰቃየት ስር የሰጠው ቃል ተቆጥሮ አመጽን በማነሳሳት ወንጀል በወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀጽ 257 መሰረት አንዲከላከል መባሉን አጥብቀን እንቃወማለን ፡፡
2. ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ከአንድ አመት ከአምስት ወር በላይ በእስር የቆዬት የዞን9 ጦማርያን የመፈቻ ወረቀት ከችሎቱ መጠናቀቅ በኋላ በአስቸኳይ በፍርድ ቤቱ አማካኝነት ተጽፎ ለማረሚያ ቤቱ ተወካይ ቢሰጥም ማረሚያ ቤቱ እስከ አርብ የስራ ሰዓት መጠናቀቂያ ድረስ መፈቻው አልደረሰኝም በሚል ሰበብ ሶስቱን ጦማርያን በእስር ማቆየቱን አስጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
ይህ ተግባር ከዚህ በፊት እንደታየው ሁሉ አቃቤ ህግ ለይግባኝ ጊዜ አንዲገዛ ከማረሚያ ቤቱ የሚደረግለት የጓሮ ትብብር አንዳይሆን እጅግ ከፍተኛ ስጋት አለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተለመደው የፍርድ ቤቶችን ስልጣን ዝቅ አድጎ የማየት እና የማረሚያ ቤቶች የእጅ አዙር ፍርድ ሰጪነት ማሳያም ነው ፡፡ በመሆኑም ከዚህ በፊት አንደታየው በአደባባይ በሕግ አግባብ የተሰጠን ነጻነት በጓሮ ከሕግ ውጪ ሊነጠቅ የሚችልበት ከፍተኛ ስጋት አሁንም የዞን9 ጦማርያን ፊት ተጋርጧል ፡፡
539 ቀናት ያለአግባብ እስር መቆየታችን ሳያንስ በራሱ መቆም የማይችል እና ምንም ማስረጃ ያልቀረበበትን ክስ አቃቤ ሕግ በጓሮ ከማረሚያ ቤት ጋር በመመሳጠር የመንፈግ ሌላ ተጨማሪ ግፍ አንዳይሰራብን አጥብቀን እንጠይቃለን ፡፡

ስለሚያገባን አንጦምራን!
ዞን9

Viewing all 212 articles
Browse latest View live