Quantcast
Channel: Kalkidan Amharic – Kal Tube
Viewing all 212 articles
Browse latest View live

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን የጠለፈው ረዳት ፓይለት መኪና ለጨረታ ቀረበች

$
0
0

በጥር 2006 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ጣሊያን ሲበር የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 767 አውሮፕላን ጠልፎ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ያሳረፈው ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን አበራ ንብረት የሆነች የቤት መኪና በሐራጅ ለጨረታ ቀረበች፡፡
66db0da56aa2ffdb291f9af3242f4601_L

የሰሌዳ ቁጥር አአ 2-A32521 መኪና ጨረታ ያቀረበው ዘመን ባንክ ነው፡፡ ረዳት አብራሪው ለመኪና ግዢ ከዘመን ባንክ የተበደረው ብድር ስላልተከፈለው ባንኩ ተሽከርካሪዋን በጨረታ ለመሸጥ መገደዱን አስታውቋል፡፡

ባንኩ ተሽከርካሪዋን ለጨረታ ያቀረበው በሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 261,503.37 ነው፡፡ ጨረታው የሚካሄደው በመስከረም ወር 2008 ዓ.ም. ነው፡፡ ረዳት አብራሪ ኃይለ መድኅን መኪናዋን የገዛው ከአውሮፕላን መጥለፉ ጥቂት ወራት ቀደም ብሎ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኃይለ መድኅን ስዊዘርላንድ ውስጥ የፖለቲካ ጥገኝነት ቢጠይቅም የአገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎት ፍርድ ቤት አንድ ጊዜ የቀረበ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ጉዳዩ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ አይታወቅም፡፡ ለስዊዘርላንድ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በግለሰቡ ላይ ክስ መሥርቶ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሌለበት 19 ዓመት ፅኑ እስራት እንደተፈረደበት ይታወሳል፡፡
ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ


መስከረም 03/2004 ዓ.ምን ሳስታውሳት… አንዷለም -ወ- እስክንድር -(ኤልያስ ገብሩ)

$
0
0

መስከረም 03 ቀን 2004 ዓ.ም እኔና ጓደኛዬ አናንያ ሶሪ በወቅቱ እንሰራባት ለነበረው አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ፣ በከፍተኛ ትምህርት ጉዳይ ዙሪያ ፊቸር ጽሑፍ በጋራ ለማዘጋጀት አቅደን፤ ለመረጃ ግብዓት መቅረፀ ድምጻችንን ይዘን በቀድሞ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ቢሮ በጥዋት ደረስን፡፡ ለተወሰኑ ጥያቄዎቻችን መረጃ እንዲሰጡን ቀድመን ጥያቄ በማቅረብ ቀጠሮ ይዘን የነበረው ከአቶ አስራት ጣሴ ጋር ነበር፡፡ እሳቸውም ከቀጠሯችን ቀደም ብለው በቢሯቸው ተገኝተዋል፡፡ ከሰላምታ ቀጥለን ወደዋናው ጉዳያችን ዘለቅን፡፡ በዚህ መካከል የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የፓርቲው ፀሐፊ አቶ አንዷለም አራጌና በአሁን ወቅት የዘነጋሁት አንድ ሰው አቶ አስራት ቢሮ ድረስ በሩን በማንኳኳት ገቡ፡፡

12002823_885053151580709_1952369173699994291_n
ከሰዓት ከሁሉም ጋር ሰላምታ ተሰጣጠን፡፡ የእነአንዷለም አመጣጥ አቶ አስራትን ጠርተው አጠር ያለች ኢ-መደበኛ ስብሰባ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ከንግግራቸው ተረድተናል፡፡ ‹‹አስቸኳይ ነው›› ስለተባለ አቶ አስራት እኛን ይቅርታ በመጠየቅ ቀጠሯችንን ከሰዓት በኋላ ማድረግ እንችል እንደሆነ በትህትና ጠየቁን፡፡ እኔ እና አናንያም ሁኔታውን በመረዳት 10፡00 ሰዓት ላይ በድጋሚ ቀጠሮ ይዘን ወጣን፡፡ በወቅቱም አንዷለም አንድ ቀልድ ፈገግ እያለ በመናገር አስቆን እንደነበረም አስታውሳለሁ፡፡
እኔና አናንያም ጊዜውን ለመጠቀም በሚል፣ ሽሮሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ወደሚገኘውና በዶ/ር ተስፋዬ ተሾመ ዋና ዳይሬክተርነት ወደሚመራው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አግባብነትና የጥራት ኤጀንሲ (Higher Education Relevance and Quality Agency) መ/ቤት በመሄድ ከህዝብ ግንኙነት ባለሙያው የምንፈልገውን የሰነድ እና የድምጽ መረጃ አገኘን፡፡ ከቀጠሯችን ቀደም ብለንም አቶ አስራት ቢሮ ደረስን፡፡ የአቶ አስራት ፊት ግን ጥዋት እንዳየነው አልነበረም፡፡ ደስ የማይል ስሜት አረብቦባቸዋል፡፡ ‹‹አንዷለምን እኮ ፖሊሶች አሁን ወሰዱት›› ብለው የሚያውቁትን ያህል ዘርዝረው ነበሩን፡፡ ‹‹ጥዋት ህጻን ልጁ ለመጀመሪያ ጊዜ ት/ቤት ገብቶለት ከሰዓት በኋላ ደስ ብሎት ከት/ቤት ሊያመጣው አቅዶ እንደነበረ ነግሮኝ፣ በጣም ያሳዝናል›› አሉ፡፡ እኛም በአቶ አስራት ቢሮ በጋራ አዘንን፡፡ በዚህ ደስ በማይልና ባልተረጋጋ ስሜት ውስጥ ቃለ-መጠይቁን ማድረግ በድጋሚ ሳንችል ቀረንና ከፓርቲው ቅጥር ግቢ ወጣን፡፡ ከቢሮው ጀምሮ እስከዋናው አስፋልት ድረስ ፊታቸውን ከስክሰው፣ ፈንጥር ፈንጠር ብለው በመቆም አካባቢውን በአይነ ቁራኛ የሚመለከቱ፣ በእኔ አጠራር ‹‹ተከታትሎ አደሮች›› ነበሩ፡፡ በዋናው የአራት ኪሎ መገናኛ መንገድ ዳር በሚገኘው ‹‹ፍሮስቲ ባርና ሬስቶራንት›› መግቢያ በር ጋር ቆሞ ከፓርቲው ቢሮ መውጣታችንን ያወቀው አንድ ጠቆር ያለ ‹‹ተከታትሎ አደር›› አፈጠጠብን፤ እኛም አፍጥጠን አጸፋውን መለስንለት፡፡ እርሱም ወዲያው አንገቱን ለማቀርቀር ጥረት አደረገ፡፡ [ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሰዎች ይገርሙኛል፤ ልባቸው በፍርሃት ውስጥ ሆኖ፣ ሰው እንዲፈራቸው የሚያደርጉት የደካማ ሥነ-ልቦና የትግበራ ሙከራቸው በጣም ያናድደኛል]
የእኔና አናንያ ቢሮ እዚያው ቤል-ኤር አከባቢ ስለነበረ ወዲያው ገባን፡፡ ሁሉም የጋዜጣዋ ባልደረቦች እስሩን ሰምተዋል፡፡ አቤል ዓለማየሁ፣ በዚሁ ቀን፤ ቀትር ላይ የዛሚዋን ሚሚ ስብሐቱ ‹‹እነአንዷለም ይታሰሩ›› የሚል ይዘት ያለው ‹‹የእስር ዋረንት›› ዘመቻዋን ካደመጠ በኋላ ከሰዓታት በፊት ለአንዷለም ስልክ ደውሎለት እንደነበረ በቁጭት ሲናገር አደመጥነው፡፡ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን መታሰርም በዚሁ ቢሮ ውስጥ ተረዳን፡፡ ሀዘን …ዝምታ …ቁጭት …ድጋሚ የሀዘን ስሜት ….ተፈራረቁ፡፡
የጋዜጣዋ ባልደረቦች፣ ኢ-መደበኛ ኤዲቶሪያል ስብሰባ አድርገን፣ በቀጣይ ዕትም ላይ ንጹሕ ወገኖቻችንን ዋጋ እያስከፈለ ስለሚገኘው የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ፊቸር ጽሑፉ እንዲደረግ ተስማማን፣ በቅዳሜ ዕትምም ተደረገ፡፡ ምሽት በሁለት ሰዓት ላይ፣ በቀድሞ የኢቴቪ ዜና እወጃ የአንዷለምንና የእስክንድርን የእስር ሁኔታ በፎቶ ግራፍ ተደግፎ ተመለከትን፡፡ ….
በነሐሴ ወር 2003 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር የወቅቱን የዓረብ ሀገራት አብዮት አስመልክቶ ሙያዊ ትንታኔ እንዲሰጠን እና ከዚህም አኳያ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ በእርሱ አተያይ ምን እንደሚመስልና ተያያዥ ሀገራዊ ጥያቄዎችን በማንሳት ከእኔ ጋር ሰፊ ቃለ ምልልስ አደርግን – በአራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል፡፡

12011337_885053174914040_8644077110975029211_n
እስክንድርን ቃለ-መጠይቅ እያደረኩለት ባለሁበት ወቅት፣ በዓለም ሀገራት ላይ ስለተደረጉ አብዮቶች አነሳስና ውልደት ታሪካዊ የዓ.ም ፍሰታቸውን ሳያዛንፍ ሲተነትን መስማቴ አስደምሞኝ ነበር፡፡ ቃለ-ምልልሱ አልቆ ቢሮ ገባሁና ወደወረቀት ላይ ልገለብጠው ስል የቃለ ምልልሱ ድምጽ የለም፡፡ በጣም ግራ ተጋባሁ፣ ከባልደረቦቼ ጋር ደጋመን ሞከርነው ግን ምንም የእስክንድር ድምጽ የለም፡፡ ለካ በስህተት ከባልደረባዬ ናፍቆት ዮሴፍ ጋር የማይሰራ መቅረፀ-ድምጽ መቀያየሬን ዘንግቼው ነበር፡፡ በጣም ተናደድኩ – መሰል ነገር በጋዜጠኝነት ሕይወት የሚገጥም ነገር መሆኑን ባውቅም፡፡ ከቢሮ ወጥቼ ተረጋግቼ አሰብኩ፡፡ ያን የመሰለ ቃለ-ምልልስ መቅረት የለበትምና በድፍረት ለእስክንድር እውነቱን ልነግረው ወስኜ ፡፡ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ቃለ-ምልልስ ካደረጉ በኋላ ድንገት መሰል ነገር መፈጠሩ ሲነገራቸው በጣም ይናደዳሉ፤ በድጋሚ ቃላቸውን ለመስጠት ፍቃደኛም ላይሆኑ እንደሚችሉ አውቃለሁ፡፡ እስክንድር ግን በጣም በሚገርም ደወልኩለትሁኔታ ሁኔታውን ተረድቶ በትህትና ‹‹መቼ ይመችሃል›› አለኝ፡፡ በጣም ደስ ብሎኝ በነጋታው ከሰዓት በኋላ እዚያው ቱሪስት ሆቴል ተቀጣጠርን፡፡
ቃለ-ምልልሱን ከመጀመራችን በፊት ወደእኔ ጠጋ አለና ‹‹ከጀርባህ ደህንነቶች አሉ፤ እነሱ መኖራቸውን ሳታስብ ጥያቄህን ጠይቀኝ›› አለኝ፡፡ ዞሬ አየኋቸው፤ ሁለት ናቸው፡፡ ሁለመናቸው እኛ ጋር ነው፤ እየታወቁም ፍጥጥ ብለው ሲያዩና ጆሯቸውን ሲቀርሱ ምንም እፍረት አይነበብባቸውም፡፡
ቃለ-ምልልሱ ሲጀመር ግን ረሳኋቸው፤ የእስክንድር ተመስጧዊ ትንታኔ ብዙ ነገር ያስረሳ ነበር፡፡ በመጨረሻም ደስ የሚል ቃለ-ምልልስ ከእስክንድር ጋር አደረግን፡፡ ‹‹በግሌ፣ ትንታኔህ በጣም ማርኮኛል፤ ከአንተ ጋር አንድ ቀን ተገናኝተን ካንተ ብዙ መማር የምፈልጋቸው ነገሮች አሉኝ›› አልኩት፡፡ ‹‹ኤልያስ እኔ ራሴ ካንተ ብዙ ነገር መማር እፈልጋለሁ፤ ደስ ይለኛል፤ ከአዲስ ዓመት በኋላ እንገናኛለን›› አለኝ በሚያስገርም ትህትና፡፡
መስከረም 02 ቀን 2004 ዓ.ም ለእስክንድር ደወልኩለት፡፡ ለመስከረም 05 ቀን ልንገናኝ ቀጠሮ ያዝን፡፡ ‹‹እንዲያውም አንተ ከፌዴራል የሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሊ ሱሌይማን ጋር ያደረከውን ሰፊ ቃለ-ምልልስ አንብቤ በአንድ ጉዳይ ላይ ጽሑፍ አዘጋጅቻለሁ፡፡ በባለፈው ዕትም ቃለ-ምልልሴ ስለወጣ ጋዜጣው ላይ በተደጋጋሚ ቦታ እንዳልይዝ ለቀጣይ እትም አደርሳለሁ›› አለኝ፡፡
ለኮሚሽነር አሊ ‹‹አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ከኢትዮጵያ የተመዘበረ 8.4 ቢሊየን ዶላር ገንዘብ ከውጪ ባንክ መገኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ስለዚህ ምን ምላሽ አለዎት? …ብሩ በኢትዮጵያ አቅም በቃላሉ የሚታይ ነው እንዴ?!›› የሚሉ ተከታታይ ጥያቄዎችን አቅርቤላቸው ነበር፡፡ ኮሚሽነሩም ‹‹ግድ የለህም …ይ…ሄ…ን…ን ከጥያቄህ ብታወጣ? ሌላ ዓላማ ስላለው ነው፡፡ ከሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (Money Laundry) ጋር አብሮ ተያይዞ የሚመጣ ነገር አለ፡፡ ለእናንተ ለሚዲያ የማይጠቅም ነገር ነው፡፡›› በማለትና ተጨማሪ ነገር መግለጽ ሳይፈልጉ የተዳፈነና የተድበሰበሰ መልስ ሰጥተውኝ ነበር፡፡ እስክንድር እንደነገረኝ ከሆነም፣ ከዚህ ጥያቄና መልስ በመነሳት፣ ይህ የተመዘበረ ገንዘብን በተመለከተ እና ኮሚሽነር አሊ ይህህን አስመልክቶ ለምን ለመመለስ እንደከበዳቸው የራሱን ምልከታ ለመግለጽ ነበር ጽሑፉን ያዘጋጀው፡፡ ግን ምን ያደርጋል በቀጠሯችን መሰረት ከእስክንድር ጋር ተገናንተን ሳንወያይ እና ጋዜጣዋ ላይ ሙስናን አስመልክቶ እንዲታተም ያዘጋጀውን ጽሑፍ ሳይሰጠኝ ነበር ልክ የዛሬ አራት ዓመት የበኩር ልጁን ከት/ቤት አውጥቶ ወደቤታቸው ሊሄዱ ሲሉ ነበር በግፍ በፖሊሶች የተያዘው! ልክ የዛሬ አራት ዓመት ነበር፣ ውድ ልጁን ከእጁ መንጭቀው በህጻን ልጁ ፊት የብረት ካቴና ያጠለቁለት! የአብራኩ ክፋይ የሆነው ናፍቆት እያለቀሰ ነበር ይዘውት ወደቤቱ ለብርበራ ያመሩት፡፡ አንዷለምም ቢሆን ት/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የገባለትን ልጁን እንደአባት ከትምህርት ቤት በደስታ ሊያወጣው እንደናፈቀ ነበር ወደማዕከላዊ የተላከው፡፡
እንግዲህ እንዲህ ነች ኢትዮጵያ ሀገራችን!!!
…..እናንተ የህሊና እስረኞች፡- አንድ ቀን ከእስር የምትፈቱበትንና ከውድ ቤተሰቦቻችሁ እና ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የምትገናኙበትን ቀን እሻለሁ!!!
በእስራችሁ ሳቢያ ከባድ ዋጋን በመክፈል ላይ ለሚገኙት ውድ ቤተሰቦቻችሁም በሙሉ፣ ፈጣሪ ይበልጥ ውስጣዊ ጥንካሬን ይስጣቸው፤ ተስፈኛም ሁኑ እላለሁ!!!

ምኞትና ተግባር ምንና ምን ናቸው? (ርዕዮት አለሙ)

$
0
0

በአዲሱ አመት ዋዜማ የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ ወደ ቂሊንጦ እስርቤት ከእህቴ ጋር ሄጄ ነበር፡፡ ስማችንን እና የምንጠይቃቸዉን እስረኞች ስም ካስመዘገብን በኋላ መታወቂያችን አሳይተን ወደዉስጥ ልንገባ ስንል መታወቂያዉን የምትመለከተዉ ፖሊስ ስማችንን ካነበበች በኋላ “ቆይ ቆይ የእናንተማ መጠየቅ አለበት” አለችንና መታወቂያችንን ይዛ ከበር መለሰችን፡፡ ከበሩ አጠገብ በሚገኝ ጎብኝዎች ወረፋ በሚጠብቁበት የእንጨት መቀመጫ ላይ አረፍ እንዳልን በሃሳብ ላይ ታቹን ማለት ጀመርኩ፡፡

1959250_629681597105784_1036270970_n
እንድንገባ ይፈቅዱልን ይሆን ወይስ የቃሊቲዎቹ እንዳደረጉት “ፍቃድ የላችሁም” የሚል አስቂኝና አናዳጅ መልስ በመስጠት ይመልሱን ይሆን? ለሚለዉ ጥያቄ መልሱ እኔዉ ጋር ያለ ይመስል አጎንብሼ ማሰቤን ቀጠልኩ፡፡ ቀና ስል ከፊት ለፊቴ “ማረሚያ ቤቱ” ለእስረኛ ቤተሰቦች መልካም ምኞቱን የገለፀበት ወረቀት ተለጥፎ ተመለከትኩ፡፡ ከአራት አመታት በላይ በመኖር የእስርቤቶቹን አሰራር አዉቀዋለሁና ተመሳሳይ የመልካም ምኞት መግለጫ የያዘ ወረቀት ለእስረኛዉም ተለጥፎ እንደሚሆን አልተጠራጠርኩም፡፡
ሰላም እየነሳ ሰላም “የሚመኝ”፣ ህክምና እየከለከለ ጤንነትን “የሚመኝ”፣ የሚዋደዱ ሰዎችን ከሽቦ ወዲያና ወዲህ ሆነዉ እንኳን እንዳይተያዩ እየከለከለ ፍቅርን “የሚመኝ” . . .ተቋም ! አንድ ፖሊስ ወደኛ እየቀረበ ሲመጣ ሀሳቤ ተቋረጠ፡፡ መታወቂያዬን እየመለሰልኝ መግባት እንደማልችል ነገረኝ በኋላ ለእህቴም ተቀራራቢ መልስ በመስጠት መታወቂያዋን መለሰላት፡፡ ለምን ለሚለዉ ጥያቄያችን “አላዉቅም፡፡ የተወሰነውን ንገር ተብዬ ነው” የሚል ምላሽ ሰጠን፡፡ ምን አይነት አምባገነንነት ነው? እስር ቤት እያለሁ በሌሎች የመጎብኘት መብቴን የነፈገው ስርዐት ዛሬ ደግሞ የጠያቂነት መብቴን እየነፈገው ነው፡፡ ሙሉውን ቀን ሊባል በሚችል መልኩ ስለፖለቲካ አሳሪዎቻችን ጉዳይ እያሰብኩ ስብሰለሰል ዋልኩ፡፡ የእኔና የሌሎች በርካቶች መብሰልሰል ምክንያት የሆኑት የኢህአዴግ ባለስልጣናት ደግሞ በአሉን ምክንያት በማድረግ ፍትህ እያዛቡበተ፣ እያሰሩትና እየገደሉት ላሉት ህዝብ የመልካም ምኞት መግለጫቸዉን ሲያዥጎደጉዱለት ዋሉ፡፡ ይህንን የኢህአዴግ ምኞትና ተግባር መራራቅ እያሰብኩ እያለሁ “ኢህአዲግን ለመለወጥ የምንፈልግ ሰዎች ምኞትና ተግባርስ ምን ይመስላል? ” የሚል ጥያቄ ሽው አለብኝ፡፡ ጥያቄው በርካታ መልሶች ቢኖሩትም በዚህ ጽሁፍ ለማቅረብ የመረጥኳቸው ግን ሁለቱን ብቻ ነው፡፡
አጉል ህልመኞች በዚህ ስርዓት ተጠቃሚ በመሆናቸው ብቻ የሌሎችን ወገኖቻቸውንና የሀገርን ጉዳት ማየት ካልቻሉ ወይም ካልፈለጉ ሆዳሞችና በህወሓት የዘረኝነት መርዝ ከተበከሉ ጥቂቶች በቀር የኢህአዴግን መሰንበት የሚፈልግ ዜጋ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች የማገኛቸዉ ሰዎች ምኞትም የስርዓት ለውጥን ማየት ነው፡፡ ነገር ግን “እነዚህ ሁሉ ሰዎች የሚፈልጉትን ለውጥ ለማየት ምን አይነት አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው?” ብለን ብንጠይቅ የምናገኘው ምላሽ አስደሳች አይደለም፡፡
አንዳንድ ለዉጥ ፈላጊዎች ቁጭ ብሎ ከመመኘት በቀር ለለዉጡ መምጣት የሚያደርጉት ምንም ነገር የለም፡፡ ለምን አንዳች ነገር እንደማያደርጉ ስትጠይቋቸው ከምታገኟቸዉ መልሶች መሃከል “እነዚህን መዥገሮች እሱ ይንቀላቸዉ እንጂ በሰው ሃይልማ የሚሆን አይደለም፤ ህዝቡን ከፋፍለውታል እኮ ምን ማድረግ ይቻላል? . . .” የሚሉት ይገኙበታል፡፡ እነዚህ ሰዎች ምንም እንዳይሰሩ ያደረጋቸዉ ትልቁን ምክንያት ጠጋ ብላችሁ ስትመረምሩ ግን ፍርሃት ሆኖ ታገኙታላችሁ፡፡ ፕ/ር መሳይ ከበደ “The Impasse of Fear in Ethiopia and the Necessity of Comprehensive struggle ” በተሰኘ ፅሑፋቸዉ እንዳስቀመጡት ፍርሃት የጨመደደው ህዝብ ሁሌም ምንም ላለማድረጉ የሚያቀርባቸው በርካታ ምክንያቶች ይኖሩታል፡፡
ሌሎቹ ለዉጥ ፈላጊዎች ደግሞ ለዉጥ ሊያመጡ የሚችሉ እንቅስቃሴዎቸን በማድረግ ረገድ ከላይኞቹ የተሻሉ ቢሆኑም የጀመሩትን መጨረስ ግን የማይሆንላቸው ናቸው፡፡ እያደረጉ በነበረዉ እንቅስቃሴ ሳቢያ አንዳች ችግር ሲደርስባቸው ከመንገዳቸው ይወጣሉ፡፡ “በዚህኛው አመተምህረት በተደረገው ምርጫ ሳቢያ ለእስር ተዳርጌ ነበር፤ በዛኛው ወቅት በተደረገው ሰልፍ ላይ ተገኝቼ ተደብድቤያለሁ” ማለት ይቀናቸዋል፡፡ አሁንስ? ስትሏቸው ግን መልሳቸው “ጎመን በጤና” ነው፡፡ እንደነዚህ አይነቶቹ ሰዎች መጀመሪያዉኑ እየታገሉት የነበረውን መንግስት ግፈኝነት በሚገባ ያወቁት አይመስሉም፡፡
የቆረጡ ለዉጥ ፈላጊዎች እነዚህኞቹ አስቀድሞ ከተጠቀሱት ጋር የለዉጥ ፍላጎታቸው ቢያመሳስላቸውም ለውጥን ለማምጣት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መኖሩና ቁርጠኝነታቸው ደግሞ የተለዩ ያደርጋቸዋል፡፡ “እሱ ያመጣዉን እሱ እስኪመልሰው” በማለት እጃቸውን አጣጥፈው አይቀመጡም፡፡ ለለውጡ እዉን መሆን የሚችሉትን ሁሉ ያዋጣሉ፡፡ ከነዚህ ሰዎች መሀከል በግንባር ቀደምትነት ሊጠቀስ የሚገባው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን መዉሰድ ይቻላል፡፡ እስክንድር ለለዉጡ ያለውን ሁሉ እየከፈለ ያለ ሰው ነው፡፡ ወደስምንት ጊዜ ያህል ሲታሰርና ሲፈታ፣ የመፃፍ መብቱን ሲገፈፍ፣ ሲደበደብ፣ ንብረቱ ሲወረስና ከሚወዳት ባለቤቱና ልጁ ጋር በአካል መለያየት ግድ ሲለዉ ሁሉ በአላማው ከመጽናት ውጭ ለአፍታ እንኳን ሸብረክ ሲል አልታየም፡፡ እስክንድርና መሰሎቹ ዲሞክራሲ እንዲሰፍንና ነፃነት እንዲገኝ ካስፈለገ ከምኞት ባለፈ ስራና መስዕዋትነት እንደሚጠይቅ ገብቷቸዋል፡፡ ለገባቸው እውነት ደግሞ እየኖሩ ነው፡፡ እነ እስክንድር ይሄን ሁሉ መስዕዋትነት ሲከፍሉ ታዲያ ሁኔታው ያማያማቸው ሆኖ አይደለም፡፡ ህመሙን ጥርሳቸውን ነክሰው እየቻሉ እንጂ!
አቶ ኤፍሬም ማዴቦ “ከዊሃ እስከ ኦምሃጀር-አንድ ሰሞን ከአርበኞች ጋር” በሚል ርዕስ በቅርቡ ባስነበቡን ጽሑፋቸዉ የአርበኞች ግንቦት 7 ጦርን ለመቀላቀል ከአሜሪካን ሀገር ከተደላደለ ኑሮዋቸው ተነስተው ሲሄዱ ይሰማቸው የነበረዉን ከሚወዱት ልጃቸው የመለየት ህመም በዉብ አገላላፅ ተርከዉልናል፡፡ አቶ ኤፍሬም አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ ሊሸኛቸው የመጣዉን የ17 አመት ልጃቸውን ሲሰናበቱ “ልጄ ይሄን ማድረግ አልፈልግም ነገር ግን ማድረግ አለብኝ” ያሉት ፊታቸው በእንባ እየታጠበ ነበር፡፡ የማይፈልጉትን ነገር ለማድረግ እራሳቸዉን ያስገደዱበትን ምክንያት የገለጹት “የምወደውን አንድ ልጄንና ጥሩ ስራዬን ደህና ሁኑ ብዬ በረሃ የገባሁት ሃገሬ ዉስጥ ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ አብቦ ለማየት ነው” በማለት ነው፡፡
ጋዜጠኛ እስክንድርና አቶ ኤፍሬም ምንም እንኳን ለውጥን ለማምጣት የሚሄዱበት መንገድ ለየቅል ቢሆንም ሁለቱም ግን ለለውጡ ያላቸውን ሁሉ ለመስጠት ተዘጋጅተዋል፡፡ አንደኛቸው ለውጡ ግድ ብሎአቸው ቤታቸው እስርቤት ሲሆን ሌላኛቸው ዱርቤቴ ብለዋል፡፡ ሁለቱም ከሚወዷቸው ወንዶች ልጆቻቸው ጋር ተለያይተዋል፡፡ ሁለቱም ለውጥ በምኞት ብቻ እንደማይመጣ ያውቃሉና እራሳቸው ሄደው ይገናኙት ዘንድ በተለያየ መንገድም ቢሆን በጉዞ ላይ ናቸው፡፡
በመጨረሻም
በኢትዮጵያ እኩልነት ዴሞክራሲ ነፃነትና ፍትህ እንዲሰፍን የምንመኝ ሁላችን ከቀን ህልማችን መንቃትና ምኞቶቻችንን ወደ ተግባር ለመለወጥ መንቀሳቀስ ያስፈልገናል፡፡ ከመንቀሳቀስ ያገደን ፍርሃታችን ከሆነ በቀደመው ንዑስርዕስ ስር የጠቀስኩት የፕ/ር መሳይ ጽሑፍ ፍርሃትን ለመዋጋት የሚያስቀምጠው አንድ መፍትሄ አለ፡፡ ድርጊት! ራሳችንን ለፈሪነት የተመደብን አድርገን የምንቆጥርና በሌሎች ደፋርነት መንፈሳዊ ቅናት የሚያድርብን ሰዎች ካለን ፕ/ሩ የጠቀሱት የፈላስፋው አርስቶትል ሃሳብ ሳይጠቅመን አይቀርም፡፡ አርስቶትል “ጀግና ለመሆን ጀግንነትን መለማመድ ያስፈልጋል” ይለናል፡፡ ለአርስቶትል ድፍረት እንደሌሎቹ የሞራል እሴቶች ሁሉ አብሮን የሚወለድ እምቅ ሃይል ሲሆን እውን ለመሆንና ለመዳበር እንዴሎቹ እሴቶች ሁሉ ልምምድ ያስፈልገዋል፡፡ አስፈላጊዉ ጥንቃቄ እንደዳለ ሆኖ እስኪ እስከዛሬ ያላደረግነዉን አንድ ድፍረት የተሞላበት ድርጊት እናድርግ፡፡ ፕ/ሩ እንደሚሉንና እኔም እንደማምነው ድርጊት ስኬትን ያመጣል፡፡ ስኬቱ የቱንም ያህል ትንሽ ቢሆን በራስ መተማመንን ይወልዳል፡፡ በራስ በተማመን ሲኖር ደግሞ ፍርሃት ይጠፋል ወይም ችግር ሊሆን በማይችልበት ደረጃ ዝቅ ይላል፡፡
ከፍርሃታችን ወጥተን እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ሳለን ከኢህአዴግ በሚወረወርብን ዱላ ተሰብረን ከመንገዳችን ላለመውጣት ደግሞ የገዢዉን ፓርቲ ማንነት ጠንቅቆ ማወቅና ቢያንስ የስነልቦና ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለማንጠብቀው ነገር አንዘጋጅም፡፡ ያልተዘጋጀንበት ነገር ደግሞ ሁሌም ይጥለናል፡፡ በመሆኑም የምንታገለው ስርዓት ስልጣኑን ላለማጣት የቱንም አይነት ጭካኔ የተሞላው እርምጃ እንደሚወስድ ማወቅና ለዛም እራስን ማዘጋጀት ግድ ይላል፡፡ ደግሞስ ኢህአዴግ ምን ሊያደርገን ይችላል? ሊያደርግብን የሚችለው ሁሉ አስቀድሞም ከአፈር በታች እንዲዉል የተወሰነበት ስጋችን ላይ አይደለምን?
መልካም አዲስ አመት!
መስከረም 3/ 2008

ላምብ፤ የበግ ለምድ ለብሶ የመጣው ተኩላ ፊልም (ከሕይወት እምሻው)

$
0
0

ዘ ጋርዲያን <<ያሬድ ዘለቀ የሀገሩን ባህልና ወግ በሚያስደንቅ ሁኔታ አይቶ ያሳየበት ድንቅ ፊልም›› ብሎ ያወደሰው ላምብ ወይም ዳንግሌ በካን ፊልም ፌስቲቫል የ 68 አመት ጉዞ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ተመርጦ የታየ የኢትዮጵያ ፊልም ነው፡፡ ትላንት ፊልሙ በኤድና ሞል ሲኒማ እየታየ መሆኑን ስሰማ ሄጄ እስካየው ቸኮልኩ፡፡ ማታ ሄጄ ከማየቴ በፊት ስለፊልሙ በተለያዩ ድረ ገፆች ላይ በአመዛኙ በፈረንጆች የተፃፉ እጅግ ብዙ ሙገሳዎችን ሳነብ ቆይቼ ጉጉቴ ከፍ ባለበት ሰአት እዚሁ አዲስ አበባ ከእኔ በፊት ያዩት ጓደኞቼ የተሰማቸውን ያሉባቸውን ፅሁፎች ፌስቡክ ላይ አገኘሁ፡፡ የፊልም ባለሙያ የሆነው ዳዊት የተባለ ወዳጄ ፊልሙን <<….ግራ የሚያጋባ፣ አሰልቺ ….. ገፀባህሪያቱ ከአከባቢያቸው ጋር ክፉኛ የተነጠሉ ከመሆናቸው የተነሳ ‹‹ካንጋሮዎችን ሰሜን ተራራ ላይ እንደማየት›› ሆኖብኛል ….›› ብሎ ባነበብኩት ጊዜ ‹‹ምነው ጨከነበት›› ባሰኙኝ ቃላት የታጨቀ አስተያየቱን ፅፏል፡፡ ሌሎች ጓደኞቼ ያሉትን አየሁ፡፡ ሁሉም ‹‹እኔ አልወደድኩትም፣ አንቺ ግን ሂጂና ለራስሽ እይው›› አሉኝ፡፡ እናም ሄድኩ፡፡ ፊልሙን ላላያችሁትና ለምታዩት ሰዎች ክብር ሲባል የታሪክ ዝርዝር ውስጥ አልገባም ግን የተሰማኝ ይሄ ነው፡፡ [caption id="attachment_3636" align="aligncenter" width="325"]Yared Zeleke Yared Zeleke[/caption]
1. ‹‹በእንግሊዝኛ አምሳል የተፈጠረ አማርኛ››
ከዚህ በፊት እንዳየነው፣ እንደውም ትንሽ ባስ ባለ ሁኔታ- ውጪ ሀገር አድገውና ኖረው በሚመጡ ‹‹ኢትዮጵያውያን›› ፀሃፊዎችና አዘጋጆች እንደተጻፉና እንደተዘጋጁ ፊልሞች ሁሉ ፊልሙ ላይ ያሉ ምልልሶች እጅግ ይቀፋሉ፡፡ አርቴፊሻል ናቸው፡፡ ምክንያቱም ፊልሙ በእንግሊዝኛ ታስቦና ተፅፎ ወደ አማርኛ የተመለሰ ምልልሶችና እና ንግግሮች ድሪቶ ነውና፡፡
በእንግሊዝኛ አምሳል የተፈጠረ አማርኛ የሚያወሩት በገጠር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ልቋቋመው የማልችለው ህመም ፈጥረውብኛል፡፡ እስቲ በፈጠራችሁ የትኛው የገጠር ልጅ ነው በጉን ‹‹አዝናለሁ እዚህ በማደርሽ …›› ብሎ የሚናገር? ‹‹የነጻነት ትኬታችንን ለማግኘት የሚያስፈልገን 120 ብር ብቻ ነው ›› የሚል? ‹‹የትኛዋ የገጠር ልጃገረድ ናት እናቷን ‹<እንዲህ ልትናገሪኝ መብት የለሽም ›› የምትል? የትኛዋስ ገጠር የምትኖር እናት ናት ልጇን ‹‹‹ደሞ ብለሽ ብለሽ እንደ ሴተኛ አዳሪ በዚህ ሰአት ገባሽ!›› የምትል….? ያማል፡፡ እጅግ ያማል፡፡ — ይሄ ሁሉ ሲሆን ሃይ ባይ ሲጠፋ ደግሞ የበለጠ ያማል! እንዴት በፊልሙ ላይ የተሳተፉ አንጋፋ የሚባሉ እዚሁ ተወልደው፣ እዚሁ አድገው ፣እዚሁ ሲተውኑ የኖሩ ተዋንያን ‹‹የለም የእኛ ሰው እንዲህ አያወራም›› ብለው ለመናገር አይዳዳቸውም! እንዴትስ ፀኃፊ እና አዘጋጁ ከአስር አመት እድሜው ጀምሮ በባእድ ሀገር እንደመኖሩ ‹‹እንዴት ነው…ይሄ ነገር ልክ ነው…?ይሄ አባባል በአማርኛ ስሜት ይሰጣል…?››ብሎ ደህና ሰው ሊያማክር፣ ብሎም ቀጥሮ ሊያሳይ አያስብም? ያሬድ ከካን ፊልም ፌስቲቫል ይልቅ ፊልሙን አዲስ አበባ ማሳየቱ ፍርሃት እንዳሳደረበት ተናግሯል ሲባል አንብቤያለሁ፡፡ ልክ ነው፡፡ እዚህ ያለነው ቋንቋውን እና ባህሉን የምንረዳ ሰዎች ስለሆንን ሊፈራ ይገባ ነበር! ከቋንቋው አኞነት በተጨማሪ ሲያሳቅቀኝ ያመሸው በፊልሙ ላይ የገቡ ፍፁም ስሜት የማይሰጡና እጅግ ግራ የሚያጋቡ አንዳንድ ንግግሮች ናቸው፡፡ ከብዙ ነገር አንድ ምሳሌ ብቻ ላምጣ፡፤ የፊልሙ ዋና ገፀ ባህሪ የሆነው ትንሹ ልጅ ኤፍሬም ከዘመዶቹ ጋር ለመኖር አዲስ ቤት ሲመጣ ያገኛትን የስጋ ዘመዱን ሴት ልጅ ‹‹መቀነትሽ ያምራል›› ሲላት መስማት እጅግ ይረብሻል፡፡ ከዚያ በላይ የሚረብሸው ግን ኤፍሬምና ይህች ዘመዱ ሲለያዩ በመኪና መስኮት መቀነቷን ፈትታ መስጠቷ ነው፡፡ በሀገራችን ‹‹መቀነት መፍታት›› ምን ማለት እንደሆን ያሬድ ያውቅ ይሆን! 2. ህዘቡ ተኩላ ሆኖ ተስሏል በትንሹ ኤፍሬምና በሚወዳት በጉ ጩኒ ዙሪያ በሚያጠነጥነው ፊልም ላይ ከ ጅማሬ እስከ ፍፃሜ ኤፍሬም በጉ እንዳትታረድበት መላ ሲቀይስና ‹‹መከራውን ሲያይ›› የፊልሙ ፀሃፊና አዘጋጅ በኤፍሬም ዙሪያ ያለውን ማህበረሰብ፣ በተለይም ቤተሰቡን የኤፍሬምን በግ ለመብላት ያሰፈሰፈ ተኩላ ብቻ አድርጎ ስሎታል፡፡ ቤተሰቡ ፍቅር የሌለው፣ ለሆዱ ብቻ የሚያስብ፣ እንግዳን የሚንቅና ለጥቅም ብቻ የቆመ አድርጎ ያሳየናል፡፡ በተለይም በረሃብ የሞተች እናቱን ትዝታ ተሸክሞ ለመጣ ምስኪን የአደራ ዘመድ ልጅ አንድ የገጠር ቤተሰብ ሊሰጥ የሚችለው ነገር ይሄ ብቻ ነው ተብሎ መሳሉ የደራሲና አዘጋጁን ጠባብ እይታ የሚሳይ እና የሚያሸማቅቅ ነው፡፡ በድህነት ውስጥ ፍቅር የሚመግበውን፣ በረሃብ ውስጥ ፍቅርና ለልጅ መሳሳትን የሚያሳየንን፣ በከፋ ረሃብ ጊዜ እንኳን ‹‹ከብቶቼን አላርድም›› ብሎ ከእንሳሶቹ በፊት የሚረግፈውን ማህበረሰብ በእንዲህ ያለው ‹‹ለፊልሙ ሲባል በግድ በተፈጠረ›› ቤተሰብ መወከል ወንጀል ሆኖ ታይቶኛል፡፡ 3. በመጨረሻም….ፊልሙ በፈረንጆች የተወደደበት ምክንያት ገብቶኛል! ሆሊውድ ኬንያዊቷ ሉፒታ ኒዮንጎን ኦስካር የሸለማት የሚፈልጋት ቦታ ስላገኛት ነው፡፡ ባሪያ ሆና ስለሰራች፡፡ ሆሊውድ ዴንዘል ዋሽንትተንን በሙስና የተዘፈቀ ጥቁር ፖሊስ ሆኖ ሲሰራ ኦስካር የሸለመው የሚፈልገው ቦታ ስላገኘው ነው፡፡ ሆሊውድ ሆቴል ርዋንዳን መታየት ያለባቸው የምንጊዜም 250 ምርጥ ፊልሞች መካከል ያስቀመጠው የሚፈልገው ቦታ ስላገኘው ነው፡፡ የአፍሪካን ሰቆቃ የሚተርክ ስለሆነ፡፡ ቋንቋውን እና ባህሉን ለማያውቅ ሰው ላምብ ግሩም ፊልም ሆኖ ሊታይ ይችላል፡፡ በተለይም አፍሪካን እና ኢትዮጵያን አንድ ሳጥን ውስጥ አስቀምጦ ከዚያ የወጣ ነገር ለማየት ፈቃደኛ ባልሆነ ምእራባዊ አይን ላምብ ግሩም ፊልም ነው፡፡ የሚፈለገውን ሁሉ ያሟላል፡፡ ከምእራቡ አለም በዘመናት ወደ ኋላ ቀርተው ሳሎናቸው ውስጥ በእንጨት ማገዶ የሚያበስሉ ሰዎችን ያሳያል፡፡ የአፈር ወለል ያለው ደሳሳ ጎጆ ውስጥ የሚኖሩ ችጋራም ኢትዮጵያውያንን ያሳያል፡፡ በረሃብ የሞተች እናትን ታሪክ ይናገራል፡፡ በግ አርደው ለመብላት ያሰፈሰፉ ረሃብተኛ ኢትዮጵያውያንን አጉልቶ እንካችሁ ይላል፡፡ ይሄ ለእነሱ አውነት ነው፡፡ ይህ ለእነሱ ልክ ነው፡፡ ስለዚህም ወደውታል፡፡ ምእራባውያን ስለ እኛ የሚሰሩትን ፊልም መቆጣጠር አንችል ይሆናል፡፡ ‹‹የእናንተ ነኝ›› የሚል ሰው ግን እነሱን ሆኖ ፣በእነሱ አይን አይቶን፣ እንደነሱ ሲፅፈን እና ሲያበጀን ማየት ያሸማቅቃል፡፡ ያሳቅቃል፡፡ እናውቃለን- ደሃ ነን፡፡ እናውቃለን – ረሃብተኞች ነን፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን ደሃ እና ረሃብተኞች ብቻ አይደለንም፡፡ በድህነታችን እና ረሃባችን ውስጥ እሴት ያለን ሰዎች ነን፡፡ ራበን ብለን አደራ የምንሰለቅጥ ህዝቦች አይደለንም፡፡ ስለ ረሃብና ድህነት በሚተርክ ፊልም ውሰጥ ስብእናችን፣መተሳሰብና እንደ ህዝብ ያለንን ማንንት ለማሳየት የሚያስፈልገው ችሎታ ብቻ ነው፡፡ ያሬድ እና አጃቢዎች ያንን ለማድረግ የሚያስችል የፊልም ጥበብን እንደ ተካኑ ማየት አይከብድም፡፡ ግን አያውቁትም ወይም የሚያውቁን አልጠየቁም፡፡ እናም፤ ዘ ጋርዲያን <<ያሬድ ዘለቀ የሀገሩን ባህልና ወግ በሚያስደንቅ ሁኔታ አይቶ ያሳየበት ድንቅ ፊልም›› ብሎ ያወደሰው ላምብ ወይም ዳንግሌ ፊልም በካን ፊልም ፌስቲቫል ታይቶ የተወደደው ለእነሱ የሚፈልጉትን ኢትዮጵያ ስላቀረበ ይሆናል፡፡ እኔ እና መሰሎቼ ግን ታመንበታል፡፡ ያሬድ ዘለቀ ተወድሶበታል፡፡ እኛ ግን አፍረንበታል፡፡

ሰኞ ምሽት ወጣቷን በጥይት የገደለው የፌዴራል ፖሊስ አባል በራሱ ላይ የግድያ ሙከራ አደረገ

$
0
0

አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ለቡ አካባቢ በሚገኝ መዝናኛ ቤት ውስጥ ሰኞ ምሽት አንዲት ወጣት መግደሉ ተሰማ፡፡ ግለሰቡ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ተርፎ በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡

ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ከጓደኛዋ ጋር በመሆን በለቡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች አካባቢ በሚገኝ የጓደኛቸው መዝናኛ ውስጥ በመዝናናት ላይ እያሉ ነው ከተጠርጣሪው ገዳይ ጋር የተገናኙት፡፡

87a16f70d957081bb7afbd21ff2124bc_L

ለጊዜው ስሟን መናገር ካልፈለገችው ጓደኛዋ መረዳት እንደተቻለው፣ የፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሰው ግለሰብ ከዚህ ቀደም ሰሎሜን አስቸግሮ ከሚያውቅ ግለሰብ ጋር በሚዝናኑበት ባር ውስጥ እንደነበር ትናገራለች፡፡ ሁለቱ ሴት ጓደኛሞች መዝናኛ ባሩ ውስጥ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ከመውጣታቸው በፊት፣ ወደ መፀዳጃ ቤት ለመግባት ተስማምተው መሄዳቸውን ታስታውሳለች፡፡ ክፍሉ ራሱን የቻለ መዝጊያ ኖሮት መፀዳጃ ክፍሎቹም ራሳቸውን የቻሉ መሆናቸውን የገለጸችው የዓይን እማኟ፣ አንዱን ክፍል በሚከፍቱበት ወቅት ዩኒፎርም የለበሰው ፖሊስ ውስጥ ሆኖ ስላዩት ይቅርታ መጠየቃቸውን ትገልጻለች፡፡

ይቅርታቸውን ተቀብሎ እንደወጣ እነሱ ወደ መፀዳጃ ክፍሎቹ ገብተው ከደቂቃ በኋላ ሲወጡ የዋና ክፍሉን በር ቆልፎ ፖሊሱ መፀዳጃ ክፍል ውስጥ እንደጠበቃቸው አስረድታለች፡፡ ወደ ሰሎሜ ተጠግቶ ‹‹አንቺ ሰው የማታናግሪው ለምንድነው?›› ብሎ በጥፊ እንደመታትና እንደወደቀች የገለጸችው የሟች ጓደኛ፣ እሷ በሁኔታው ተደናግጣ ወደ መፀዳጃ ክፍሉ ገብታ መቆለፏን ትናገራለች፡፡ በክፍሉ ውስጥ እንዳለች የተኩስ ድምፅ መሰማቱን፣ የማቃሰት ድምፅ ስትሰማ መውጣቷን ገልጻለች፡፡

ጓደኛዋ ሰሎሜም ሆነች ፖሊሱ ወድቀው እንዳየቻቸው ሰው እንዲደርስላት ብትጮህም፣ ለደቂቃዎች ያህል ማንም እንዳልደረሰ ትናገራለች፡፡

በኋላ ከደረሰችላት አንዲት እንስት ጋር በመሆን እስትንፋሷ የነበረውን ጓደኛዋን ለመርዳት እየሞከረች ሳለ፣ ፖሊሶች እንደደረሱና በሥፍራው ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ በፒክ አፕ መኪና ይዘዋት መሄዳቸውን፣ ነገር ግን የጓደኛዋ ሕይወት ማለፉን ገልጻለች፡፡

ተጠርጣሪው የፖሊስ ባልደረባ ጭንቅላቱን በጥይት መትቶ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም ሕይወቱ ባለማለፉ የሕክምና ዕርዳታ እየተደረገለት ነው፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ ይሁን እንጂ ተጠርጣሪው ገና በሕክምና ላይ በመሆኑ ፖሊስ ቃሉን እንዳልተቀበለ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የወጣት ሰሎሜ የቀብር ሥነ ሥርዓት ማክሰኞ መስከረም 4 ቀን 2008 ዓ.ም. በለቡ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡
ምንጭ ሪፖርተር ጋዜጣ

በፍቅር ሰበብ; ሴት ስለሚገድሉ ወንዶች….. (በእውቀቱ ስዩም)

$
0
0

በፍቅር ሰበብ; ሴት ስለሚገድሉ ወንዶች የሚወጡ ዜናዎችን እንሰማለን፡፡ በወጣትነታቸው የተቀጠፉ ጽጌሬዳዎች ያሳዝናሉ፡፡
ነፍስ ይማር!!
በፍቅር ሰበብ መግደል በተለይ የወንዶች ችግር ይመስለኛል ፡፡ ሴቶች በወደዱት ሰው መገፋትን በእንባቸው ያጥቡታል፡፡ ለወንድ ግን ደም ካልፈሰሰ ስርየት የለም፡፡

12032218_1084709661564406_2931683630599249631_n
ለብዙ ወንዶች ከሴት ጋር የሚደረግ ግኑኝነት የፍቅር ጉዳይ ብቻ ኣይደለም፤ የክብር ጉዳይ ጭምር ነው፡፡ ኣንድ ሴት ፈልገው እምቢ ስትላቸው ሰማይ እንደ ብረት ቁና የሚደፋባቸው ወንዶች ጥቂት ኣይደሉም፡፡ ኣልፈልግህም መባል ተንቄ ነው የሚል ስሜት ያሳድራል፡፡ ሰው መገፋቱን ለብቻው ይዞ እንዳያስታምም ማህበረሰብ ኣስተያየት ከባድ ቀንበር ሆኖ ይወድቅበታል፡፡ ” ጠይቋት ጥምብ ርኩሱን ኣውጥታ ”ኣባረረችው የሚል ሽሙጥ ኣርፈህ እንድተኛ ኣያደርግም፡፡ ኣብዛኛው ያለም ህብረተሰብ ኣሸናፊውን የሚቀድስ ተሸናፊውን የሚያራክስ ነው፡፡ እኛም“ የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል” ብለን ዘግተነዋል ፡፡ ኣንድ ሰው እምቢ ያለችውን ሴት ሲቀጥፍ ብቻውን ኣይደለም፡፡ ሽንፈትን የሚያጋንን ማህበረሰብም ኣባላትም የሆንነው እኛም በስውር ተባብረነዋል፡፡
ኣፍቅራችሁ የተገፋችሁ ወንዶች መገፋታችሁን በጸጋ የምትቀበሉበት ጽናቱን ይስጣችሁ፡፡“ንቃኝ ነው፡፡” ከማለት“ እኔ ምርጫዋ ስላልሆንኩ ነው፡፡ እኔን የምትፈልገኝ ሴት ደግሞ የሆነ ቦታ ኣለች ፤የሆነ ጊዜ ላይ ትመጣለች” ብሎ ማሰብን ተለማመዱ፡፡ በርግጥ ሰዎች በተቆጡበት ወቅት በቀልን እንጅ ጠቃሚ ምክር የሚያስታውስ ልቦና እንደሌላቸው ይገባኛል፤ እንዲያው ቢቸግረኝ ነው፡፡
የዛሬ ኣበባዎች የነገ ሰለባዎች ሴቶች ሆይ ! ልባችሁ ያልፈቀደውን ሰው በይሉኝታ ወይም ለእናት ኣገራችሁ ስትሉ የማቀፍ ግዴታ የለባችሁም፡፡ ለእናት ኣገራችሁ ስል ኣንድ የሰነበተ ወግ ትዝ ኣለኝ፡፡ በመንጌ ጊዜ ኣንዲት ቆንጆ ሴተኛ ኣዳሪ ነበረች፡፡ የኣፍሪካ ኅብረት ስብሰባ በተደረገ ጊዜ ካፍሪካ ኣምባገነኖች ኣንዱ ከጀላት፡፡ ይህን ያወቁ የመንጌ ቦዲጋርዶች መኖርያዋ ድረስ መጥተው “የሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ስለወደዱሽ ተኝላቸው ” ብለው ኣባበሏት፡፡ እሷም እሺ ብላ የፕሬዚዳንቱን ወቀጣ ጥርሷን ነክሳ ስትቀበል ኣደረችና ማለዳ እያነከሰች ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ በማግስቱ ምሽት እንደገና ልኡካኑ መጥተው ሊወስዷት ሲያግባቧት“ ኧረ ምን በወጣኝ !! ትናንትም ለእናት ኣገሬ ስል ነው የተረዳሁ ”በማለት መለሰች፡፡(” የተረዳሁ“ የሚለው ቃል የዋናው ቃል ምትክ ሆኖ ገብቷል፡፡ )
እና ቆነጃጅት ለእናት ኣገራችሁ ሲባልም ቢሆን የማትፈልጉት ወንድን እሺ የማለት ግዴታ የለባችሁም፡፡
ግን በተቻላችሁ መጠን ኣለመፈለጋችሁን በተለሳለሰና በተሽሞነሞነ ቃል ለመግለጽ ሞክሩ፡፡“ እኔ ደግሞ የሚገጥመኝ ሙጀሊያም ሙጀሊያሙ ነው ”ኣይነት መልክት ያለው ፊት ላለማሳየት ተጠንቀቁ፡፡ በለሰለሰ ቃል የተገለጸ እምቢታ ከእሽታ ልተናነሰ በጎ ስሜት ይፈጥራል፡፡
የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለን ሴት ተማሪዎችን ኣስቁመን ባንድ እጃችን በላብ ያደፈ ደብተራችንን፤ በሌላ እጃችን የተፈቃሪዋን እጅ ጨብጠን “ ኣበባው ግሮሰሪ ገብተን ብንጫወት ምን ይመስልሻል?” ስንል የሚመለስልን መልስ ኣይረሳኝም፡፡“ ይቅርታ ! እኔ ኣላማ ኣለኝ፤ በእህትና በወንድምነት ከሆነ ግን ችግር የለውም” ይሉን ነበር፡፡ በጊዜው ኣላማ የሚለው ቃል ትልቅ ክብደት ያለው ቃል ነበር፡፡ ህብረተሰብን ከመሃይምናትና ከኋላቀርነት የማውጣት ኣላማ፤የኣገር ኣንድነት ኣላማ ምናምን የሚባሉ ግዙፍ ቃሎች ጋር የተያያዘ ነበር፡፡እና ከልጅቷ ኣላማ ጋር ሲነጻጸር የኛ ሽፍደት ኢምንት ሆኖ ይታየናል፡፡ በዚያ ላይ፤ ያችን በመሰለች ልጅ በወንድምነት መታጨታችን ያጽናናል፡፡ እናም በመጣንበት እግራችን በሰላም እንመለሳለን፡፡
ከላይ ያስቀመጥኳቸው የግጭት መፍቻ ሀሳቦች ከችግሩ ትልቅነት ኣንጻር ኣቅመቢስ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እንግዲህ በተረፈ “ ኣይድረስ” ማለት ነው፡

ጠቅላይ ቤተ ክህነት: በሕግ የሚጠየቁ ሙሰኛ ሓላፊዎች በስም ዝርዝር ተለይተው እንዲቀርቡለት አዘዘ

$
0
0

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማት እና አድባራት፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን ተጠቃሚ በማያደርጉ የመሬት እና የገቢ ማስገኛ ተቋማት የኪራይ ውሎች፣ የተጧጧፈ ዘረፋ እና ምዝበራ መፈጸሙን በጥናት ያረጋገጠው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት÷ በጥምርና በተናጠል በሕግ ተጠያቂ የሚኾኑ የሥራ ሓላፊዎች እና ሠራተኞች በስም ዝርዝር ተለይተው እንዲቀርቡለት ለአጥኚ ኮሚቴው ትእዛዝ ሰጠ፤ በመሬት፣ በሕንጻዎች፣ በሱቆች፣ በመቃብር ቦታዎች፣ በመኪና ሽልማት እና በመሳሰሉት የልማት ሥራዎች ዙሪያ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው ስለሚገቡ ነጥቦች፣ ለሀገረ ስብከቱ ጥብቅ መመሪያም አስተላልፏል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ የሥራ አስፈጻሚ እና የአስተዳደር አካል የኾነው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ መመሪያውንና ትእዛዙን የሰጠው÷ የሀገረ ስብከቱን 48 ገዳማት እና አድባራት ያካተተውን የመሬት፣ የሕንጻዎችና የገቢ ማስገኛ ተቋማት የኪራይ ተመንና የመኪና ሽልማት ጉዳዮች ጥናታዊ ሪፖርት ቋሚ ሲኖዶሱ ተቀብሎ ያሳለፈውን ውሳኔ መሠረት በማድረግ ነው፡፡

quwami-synod-decision

ቋሚ ሲኖዶሱ፣ ነሐሴ ፳፰ እና ፳፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ባካሔዳቸው ስብሰባዎች፣ አጥኚ ኮሚቴው በ33 ገጾች በማካተት በአንድ ጥራዝ ካቀረባቸው 48 አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ÷ 15ቱ በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኙ፤ ኹለቱ በመካከለኛ ደረጃ የተቀሩት ስድስቱ ደግሞ በደኅና ኹኔታ ላይ እንዳሉ ተገንዝቧል፡፡

ከፍተኛ ችግር ያለባቸው 15ቱ አብያተ ክርስቲያናት÷ የቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም፣ የቦሌ ገርጂ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅዱስ ገብርኤል፣ የጃቲ መካነ ሕይወት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፣ የደብረ ኢዮር ቅዱስ ሚካኤል፣ የመካኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል፣ የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ፣ የመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ፣ የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል፣ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል፣ የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል፣ የሰሚት ኆኅተ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፣ የደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል፣ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም፣ የብሔረ ጽጌ ቅድስት ማርያም፣ የደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል እና የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል እንደኾኑ በውሳኔ ቃለ ጉባኤው ተዘርዝረዋል፡፡

በተዘረዘሩት ገዳማት እና አድባራት፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ መገልገያ ከመንግሥት የተሰጡ መሬቶች እና በይዞታዎቹ ላይ ለገቢ ማስገኛ በሚል የተሠሩ ሕንጻዎች እና ሱቆች፣ የ“ልማት አርበኛ” እየተባሉ በካህናቱ እና ምእመናኑ ስም የሚሸለሙ ሓላፊዎች እና ሠራተኞች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለምዝበራ እንዳጋለጧቸውና አላግባብ ሀብት እንዳፈሩባቸው በጥናቱ ሒደት በማስረጃ በመረጋገጡ ጉዳያቸው በሕግ አግባብ እየታየ ክሥ እንዲመሠረትባቸው በጠቅላይ ጽ/ቤቱ አስተዳደር ጉባኤ ቀደም ሲል ተወስኗል፡፡
የጠቅላይ ጽ/ቤቱን ውሳኔ የተቀበለው ቋሚ ሲኖዶሱ፣ ለሕጋዊ ጥያቄ እና አካሔድ አመቺነት መሟላት ይገባቸዋል ያላቸውን ነጥቦች በመለየት ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ በዝርዝር አስታውቋል፡፡

በቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት፣ በጥምር እና በተናጠል በሕግ ተጠያቂ የሚኾኑ የሥራ ሓላፊዎች እና ሠራተኞች ስም ዝርዝር ከተሰበሰቡት ማስረጃዎች ጋር እየተነጻጸረ በሰነድ ተደግፎ እንዲቀርብለት ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ለአጥኚ ኮሚቴው ጳጉሜን ፲፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም፣ በተጠቀሱት ገዳማት እና አድባራት የአካባቢ የመሬት ዋጋ በካሬ ሜትር ስንት እንደኾነ፣ የተሰጠው የኪራይ ውል ዓመት ከስንት እስከ ስንት ዓመት እንደኾነ በአሐዝ እንዲገለጽ፣ የቤት እና የመኪና ሽልማት የተሰጣቸው አለቆች እና የስጦታው ምክንያት ተብራርቶ እንዲቀርብ፤ በአጠቃላይ በጥናቱ ሒደት የተሰበሰቡት 1500 ማስረጃዎች ለሕጋዊ ጥያቄ አመቺ በሚኾንበት አኳኋን በሚገባ ተጣርተው እንዲዘጋጁ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ አጥኚ ኮሚቴውን አዟል፡፡

ገዳማቱንና አድባራቱን በበላይነት በሚቆጣጠረው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም፤ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያንን የመሬት አጠቃቀም እና የገቢ ማስገኛ ተቋማት አጠቃቀምበተመለከተ ትኩረት ሊሰጣቸውና በአግባቡ ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባቸው ነጥቦች በቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ የተመለከቱ ሲኾኑ፤ ጠቅላይ ጽ/ቤቱም በውሳኔዎቹ ላይ በመመርኮዝ ለሀገረ ስብከቱ በጻፈው ደብዳቤ ጥብቅ መመሪያ ሰጥቶባቸዋል፡፡

በዚኽም መሠረት፣ በገዳማቱ እና በአድባራቱ የመሬት እና የሱቅ እንዲኹም የልማት ይዞታዎች የኪራይ ውላቸው ለአንድ ዓመት ብቻ ይኾናል፤ የተለየ ችግር ካጋጠመም ውሉ በሕግ እንዲቋረጥ ታዟል፡፡

የመቃብር ቦታዎች አጠቃቀም፤ የቦታዎች እና የሱቆች ኪራይ አፈጻጸም በአጠቃላይ የልማት ነክ ጉዳዮች ኮሚቴ ተቋቁሞ እና ውስጠ ደንብ ወጥቶላቸው እንዲሠሩ፤ ውሎቻቸውም በየደረጃው ተጠንተው ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቀርበው ተቀባይነት ካገኙ በኋላ ተግባራዊ እንዲኾኑ ተወስኗል፡፡

የቤት እና የመኪና ሽልማት በቢሮ ደረጃ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቀርቦ ሳይታይና በቋሚ ሲኖዶስ ሳይጸድቅ እንዳይፈጸም ታዟል፡፡ ከሦስተኛ ወገን ጋር ቤተ ክርስቲያኒቱ መዋዋል እንደምትችል የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ቋሚ ሲኖዶሱ አጽድቋል፤ የመንበረ ፓትርያርክ የሕግ አገልግሎትም፣ ውሎች ወጥ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን መብቶች የሚያስከብሩና የሚያስቀድሙ መኾናቸውን በማረጋገጥ ውሳኔውን ለውጤት እንዲያበቃ በቋሚ ሲኖዶሱ ተወስኗል፡፡

በመሬት፣ በሕንጻዎች፣ በሱቆች እና በመሰል የገቢ ማስገኛ ተቋማት ዙሪያ በተጨባጭ ጥናት እንደተረጋገጠው ኹሉ ቤተ ክርስቲያናችን በእጅጉ ተጎጂ እና የበይ ተመልካች የኾነችበት ኹኔታ በመፈጠሩ የሚከተሉት የመፍትሔ ሐሳቦች ቀርበዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱን በማይጠቅሙና ለግለሰብ ነጋዴዎች በሚያመዝኑ መልኩ የተገቡ ውሎች በሙሉ ለአንድ ወገን ጥቅም የሚያመዝኑ መኾናቸው እየተገለጸ እንዲፈርሱና በሌላ ውል እንዲተኩ እንዲደረግ በማድረግ አዲስ ውል በመዋዋል የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥቅም ማረጋገጥ፡፡

በጥናቱ ወቅት እንደተመለከትነው÷ የአንዱ ደብር ውል አንድ ዓመት፣ የሌላኛው 10 ዓመት እንዲኾን ስለተደረገና አንዳንድ ውሎችም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሳይኾን የተከራዮችን መብት የሚያስከብሩ ኾነው በመገኘታቸው ውሎቹ ወጥ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥቅም የሚያስከብሩ መኾን ይገባቸዋል፡፡ ስለኾነም በሕግ ዐዋቂዎች የሚዘጋጅና ወጥነት ያለው ውል በማእከል ደረጃ እንዲዘጋጅ በማድረግ ኹሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት አንድ ወጥ በኾነ ውል የሚሠሩበትን ኹኔታ ማመቻቸት፡፡

በቃለ ዐዋዲው አንቀጽ ፲፪ ንኡስ አንቀጽ ፰ መሠረት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የጨረታውን ሒደት ተመልክተው ሲያጸድቁት እንዲፈጸም በማድረግ ሥራዎችን በሕግና በሥርዐት ማከናወን፡፡

ማንኛውም ዐይነት የሽልማት ሥነ ሥርዐት መኪናን ጨምሮ የሥራ አፈጻጸም ተገምግሞ በሀገረ ስብከቱ በኩል ታምኖበት በሊቀ ጳጳሱ እና በቅዱስ ፓትርያርኩ ሲፈቀድ ከሚፈጸም በስተቀር ምንም ዐይነት ሽልማት እንዳይከናወን ማድረግ፡፡

በየአድባራቱ በሰንበቴ ማኅበራት ስም የሚሠሩ የመካነ መቃብር ፉካዎች የሕዝበ ክርስቲያኑን በቤተ ክርስቲያን እኩል አገልግሎት የማግኘት መብት የሚገድቡ በመኾኑ አዳዲስ የሰንበቴ ማኅበራት ፉካዎችን እንዳይገነቡ ማድረግ፡፡

የመሬት እና የቦታ ኪራይ ጥያቄን ለማስተናገድ፡-

አጥቢያዎች መሬትም ኾነ ሱቅ በሚያከራዩበት ወቅት የየክፍለ ከተማቸውን የመንግሥት የሊዝ ኪራይ ዋጋን ባገናዘበና የየአካባቢያቸውን የንግድ ማእከላት የገበያ ኹኔታ መሠረት ባደረገ አግባብ ቤተ ክርስቲያንን ተጠቃሚ ሊያደርግ ይቻል ዘንድ፣ ጨረታውን በግልጽ እንዲያካሒዱ በሀገረ ስብከቱ በኩል ጥብቅ መመሪያ እንዲሰጣቸው ማድረግ፡፡

አድባራቱ መሬትም ይኹን ሱቅ ሲያከራዩ፣ የሚያከራዩትን ቦታ፣ የሚያከራዩትን ሱቅ ብዛት፣ ቦታውን ወይም ሱቁን ለማከራየት የፈለጉበትን ዝርዝር ኹኔታ እና የሚከራዩት ቦታዎችም ኾኑ ሱቆች በገበያው ያላቸው አዋጭነት ተጠንቶ በመዘርዘር ለሀገረ ስብከቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሀገረ ስብከቱም የቀረበለትን የኪራይ ጥያቄ ተገቢና ትክክለኛ መኾኑን በማጥናት በአስተዳደር ጉባኤ ወስኖ እንዲያከራዩ መፍቀድ ወይመው መከልከል ይችላል፡፡

አጥቢያዎች ቦታም ኾነ ሱቅ እንዲከራዩ ሲፈቀድላቸው በግልጽ ጨረታ ያከራያሉ፤ ጨረታውም የሀገረ ስብከት፣ የምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት መካሔድ ይኖርበታል፡፡

በአጥቢያ እንዲከራይ የተፈቀደው ቦታና ሱቅ በሕጋዊ መልኩ ግልጽ ጨረታ ከተካሔደ በኋላ ውጤቱ ለሀገረ ስብከቱ እንዲደርሰው ይደረጋል፡፡ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ የተከራየው ቦታ ወይም ሱቅ፣ በሕጋዊ መንገድ የአካባቢ ዋጋና የመንግሥት የሊዝ ኪራይ ዋጋ ባማከለ መልኩ በይበልጥም ቤተ ክርስቲያንን ተጠቃሚ በሚያደርግ አግባብ ማከራየታቸውን በአስተዳደር ጉባኤው ካረጋገጠ በኋላ የኪራይ ውሉ እንዲፈጸም ያደርጋል፡፡

በአጥቢያ የሚከራይ መሬት ይኹን ሱቅ የኪራይ ውል የሚሰጠው ለአንድ ዓመት ብቻ ኾኖ ውሉ ወጥና ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚጠቅም በኾነ መልኩ በሕግ ባለሞያዎች ተጠንቶ በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ከታመነበት በኋላ አድባራቱ በአዲሱ ውል ተከራዮቻቸውን እንዲያዋውሉ ማድረግና የውላቸው ግልባጭ ለሀገረ ስብከቱ እንዲላክ መደረግ ይኖርበታል፡፡

ሀገረ ስብከቱም ቦታዎቹ እና ሱቆቹ በሕጉ መሠረት እየተከራዩ መኾናቸውን በማረጋገጥ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ማሳወቅና ማስፈቀድ ይኖርበታል፡፡

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤትም ሀገረ ስብከቱ በመሬት፣ በሕንጻዎችና በመሰል የገቢ ማስገኛ ተቋማት ዙሪያ ለሚያከናውነው ሕጋዊ የሥራ አፈጻጸም በሙሉ ተገቢውን ድጋፍና ትብብር በማድረግ ለሥራው ውጤታማነት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት ይጠበቅበታል፡፡

ማንኛውም ተከራይ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የተከራየውን ሱቅ ወይም ቦታ ለሦስተኛ ወገን ማከራየት አይችልም፡፡ አከራይቶ ቢገኝ ያለምንም ቅድመ ኹኔታ የተከራየውን ሱቅ ወይም መሬት እንዲለቅ ይደረጋል፡፡

ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱን ይዞታ በውል የተከራየ ሰው በተከራየው ባዶ ቦታ ላይ ሱቅ ሠርቶ ወይም ቦታውን ሸንሽኖ ለሦስተኛ ወገን ማከራየት አይችልም፡፡

ማንኛውም የንግድ ቤት ወይም ቦታ ተከራይ የንግድ ስያሜ ለወንድሜ፣ ለእኅቴ፣ ለጓደኛዬ…ወዘተ እንዲዞር ይደረግልኝ የሚል ጥያቄ፣ ከውስጥ ለውስጥ የቁልፍ ወይም የቦታ ሽያጭ ጋር የሚካሔድ በመኾኑ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ /ጥናታዊ ሪፖርት፤ የመፍትሔ ሐሳቦች፤ ከገጽ 31 – 33/

በጥናቱ ያልተካተቱት ገዳማት እና አድባራት ችግር እንደሌሎቹ ተጠንቶ እንዲቀርብም በቋሚ ሲኖዶሱ በተወሰነው መሠረት ጠቅላይ ጽ/ቤቱ መመሪያ በመስጠቱ፣ ጥናቱ በቀሪዎቹ ከመቶ በላይ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ላይም ቀጣይነት እንደሚኖረው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይህም ኾኖ የጥናቱን ሒደቱ እና ፋይዳ በየመድረኩ በማጥላላት እና በማንቋሸሽ የተጠመዱት ቀንደኛ አማሳኞች እና ግብረ አበሮቻቸው የኮሚቴውን አባላት በጎጠኝነት እና በጥቅም ኔትወርክ ለመደለል ከመሞከር ጀምሮ ከስም ማጥፋት፣ ከዛቻ እና ከማስፈራራት ባለፈ የጥቃት ውጥኖች ለማሰናከል እየሞከሩ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

“አጥፍተናችኹ አገራችን እንገባለን” የሚለው የቀንደኛ እና ልማደኛ አማሳኞች ፉከራ ለጥቃት ውጥኑ በማሳያነት እንደሚጠቀስ ለኮሚቴው አባላት ቅርበት ያላቸው የዜናው ምንጮች ተናግረዋል፡፡
ሐራ ዘተዋሕዶ

የግብጹ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ ለመስቀል በዓል አዲስ አበባ ይመጣሉ

$
0
0

የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፻፲፰ኛ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ፣ በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ ለመታደም እና የአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ፣ መስከረም ፲፭ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከቤተ ክርስቲያኒቱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር በመኾን አዲስ አበባ ይገባሉ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የእስክንድርያ ፻፲፰ኛ ፖፕ እና ፓትርያርክ ዘመንበረ ማርቆስ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የእስክንድርያ ፻፲፰ኛ ፖፕ እና ፓትርያርክ ዘመንበረ ማርቆስ


ፓትርያርክ አቡነ ቴዎድሮስ አራት ቀናት በሚወስደው ቆይታቸው፣ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ከመታደማቸው በተጨማሪ፣ ወደ አኵስም እና ላሊበላ አቅንተው ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ሥፍራዎችን እንደሚጎበኙም ታውቋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሚኖራቸው ቆይታ፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትን፣ እንዲኹም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከታዋቂ ግለሰቦች ጋር እንደሚነጋገሩ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ጉዟቸውን አስመልክቶ ቅዱስነታቸው ከሳምንት በፊት ከግብጽ የውኃ ሀብት ሚኒስትር ሆሳም አል ሞጋሃዚ ጋር መነጋገራቸው የተዘገበ ሲኾን፣ በውይይታቸውም ወቅት ግብጽ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ላይ ያላትን ጥያቄዎች አንሥተው ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጋር ውይይት እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ መጠየቃቸውና የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ተዘግቧል፡፡

ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስ በበኩላቸው ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ኹለቱ አብያተ ክርስቲያናት ባላቸው ታሪካዊ ግንኙነት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እየተባበሯቸው እንደኾነና አስተዋፅኦዋቸውም ከፍተኛ እንደኾነ ገልጸዋል፤ በማለት ስታር አፍሪካ በተሰኘ ድረ ገጽ ላይ የወጣ ዘገባ ያትታል፡፡

የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ግብጽን ለስድስት ቀናት በይፋ በጎበኙበትና በካይሮ ፕሬዝዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከፕሬዚዳንት አልሲሲ ጋር በተወያዩበት ወቅት ፕሬዚዳንቱ፣ የዓባይ ወንዝ ለኢትዮጵያውያን የልማት ምንጭ ቢኾንም ለግብጽ ግን ልማት ብቻ ሳይኾን የደም ሥር መኾኑንም መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስም በበኩላቸው፣ በጠንካራ ትስስር ላይ ለተመሠረተው የኹለቱ አገሮች ግንኙነት፣ ከዓባይ የሚመነጭ ውኃ የማያቋርጥ የጋራ ሀብት በመኾኑ በፍትሐዊነትና በእኩልነት ተጠቃሚ የሚኮንበት ይኾናል ማለታቸውም አይዘነጋም፡፡

ፖፕ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ፣ እ.ኤ.አ. በ፲፱፻፶፪ ማንሱራ በተሰኘ የግብጽ ከተማ የተወለዱ ሲኾን፣ በ፲፱፻፸፭ ከኤሌክሳንደርያ ዩኒቨርሲቲ በፋርማሲ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ ለጥቂት ዓመታት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኝ መድኃኒት ፋብሪካን ከአስተዳደሩ በኋላ፣ ቅዱስ ፒስሆግ የተባለ ገዳም ገብተው የሥነ መለኰት ትምህርት በማጥናት እ.ኤ.አ. በ፲፱፻፹፱ ተመርቀዋል፡፡

ከሦስት ዓመት በፊት ያረፉትን የቀድሞውን ፓትርያርክ አቡነ ሺኖዳን በመተካት በአኹኑ ወቅት ፻፲፰ኛው የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ በመኾን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን ታሪካዊው የቅዱስነታቸው ጉብኝት የተሳካ ይኾን ዘንድ፣ በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የሚመራ ዘጠኝ አባላት ያሉት ኮሚቴ በማቋቋም ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡
ምንጭ ሐራ ዘተዋሕዶ


ሸራተን አዲስ ከ5 ኮከብ በላይ ይገባኛል ሲል ቅሬታ አቀረበ

$
0
0

በቅርቡ ይፋ በተደረገው የአዲስ አበባ ሆቴሎች የኮከብ ደረጃ ምደባ ሸራተን አዲስ፣ ኢሊሊ ዓለም አቀፍ ሆቴልና ካፒታል ሆቴልና ስፓ፤ 5 ኮከብ የተሰጣቸው ሲሆን ሸራተን አዲስን ጨምሮ 20 ሆቴሎች በኮከብ አሰጣጡ ላይ ቅሬታ አቅርበው ምላሽ እየተጣበበቁ ነው፡፡
ባለ 5 ኮከብ ደረጃ ይሰጣቸዋል ተብሎ የተጠበቁት ሂልተን አዲስና ራዲሰን ብሉ ሆቴል ባለ 4 ኮከብ ሆነዋል፡፡
kalkidan1090
5 ኮከብ የተቀዳጁት ኢሊሊ እና ካፒታል ሆቴል በተሰጣቸው ደረጃ ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ሸራተን አዲስ ግን ከ5 ኮከብ በላይ ይገባኛል የሚል ጥያቄ አቅርቧል፡፡
ካፒታል ሆቴል 12 በሚደርሱ መስፈርቶች መመዘኑን የጠቆሙት የሆቴሉ ሴልስና ማርኬቲንግ ማናጀር አቶ ሚካኤል ተካ፤ ከመቶ 85.68 በማግኘትም ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ለመሆን መብቃቱን ገልፀዋል፡፡ ሆቴላችን የ5 ኮከብ ባለቤት መሆኑ በአለማቀፍ ደረጃ ያለው ተቀባይነት እንዲጨምርና ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲዘልቅ ይረዳዋል ያሉት ማናጀሩ፤ ሆቴሉ ወደፊት ሊጀምር ያቀዳቸው ሌሎች አገልግሎቶች ሲሟሉ፣ ወደ “ግራንድ ሌግዠሪ” ደረጃ ማደግ እንደሚችል መዛኞቹ መጠቆማቸውን ተናግረዋል፡፡
ሆቴላቸው 5 ኮከብ ማግኘቱ እንዳስደሰታቸው የተናገሩት የኢሊሊ ዓለም አቀፍ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ ፕሮፌሰር አብዱሰላም ባሬንቶ በበኩላቸው፤ የተሰጠው ደረጃ ሆቴሉ በእንግዶች ዘንድ ይበልጥ ተመራጭ እንዲሆን እንደሚረዳና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለማቅረብ እንደሚያተጋቸው ገልፀዋል፡፡ የሸራተን አዲስ ሆቴል አንድ የስራ ሃላፊ በስልክ በሰጡን አስተያየት፤ ሆቴሉ በኮከብ ደረጃ አሰጣጡ ላይ ያሉትን ቅሬታዎች ለሚመለከታቸው አካላት አቅርቦ ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን ጠቅሰው ጉዳዩ፣ እልባት ሲያገኝ ውጤቱ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የባህልና ቱሪዝም የህዝብ አለማቀፍ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው፤ በኮከብ ደረጃ ምደባው ላይ 20 ሆቴሎች ቅሬታ ማቅረባቸውን ጠቁመው፤ ቅሬታቸው ምላሽ ማግኘቱንና በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ እንደሚደረግ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ ሆቴሎች 95 ያህሉ ለምዘና ተመርጠው የነበረ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ፣ 38ቱ ከ 1 ኮከብ እስከ 5 ኮከብ ደረጃ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት፤ ከ5 ኮከብ በላይ “ግራንድ ሌግዠሪ” ያገኘ ሆቴል የለም፡፡ የኮከብ ደረጃ ከተሰጣቸው መካከልም 3ቱ ባለ 5 ኮከብ 11ዱ ባለ 4፣ 13ቱ ባለ 3፣ 10ሩ ባለ 2 ኮከብ ደረጃ ሲያገኙ አንድ ሆቴል ባለ 1 ኮከብ ደረጃ ተሰጥቶታል፡፡ ለሁሉም ሆቴሎች ተመሳሳይ 12 የመመዘኛ ነጥቦች የተዘጋጁ ሲሆን ባገኙት የመቶኛ ውጤት መሠረት ደረጃው ተሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡ የሆቴሎች የኮከብ ደረጃ ምዘናው ከተጀመረ 5 ወራት ገደማ ያስቆጠረ ሲሆን በአሁን ወቅት በክልል ከተሞች ለሚገኙ ሆቴሎች ተመሳሳይ የምዘና ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የሆቴል ምዘናው የሚከናወነው በተባበሩት መንግስታት የአለም ቱሪዝም ድርጅት ሲሆን ለስራው የሚውለው በጀት የተገኘው ከአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እንደሆነም ታውቋል፡
ምንጭ፦ አዲስ አድማስ

ደርግ ተራማጅ ነው! (አፈንዲ ሙተቂ)

$
0
0

አዎን! ብዙ ጊዜ “ደርግ ጨፍጫፊ ነው” ስንል ነበረ አይደል…? ዛሬ ደግሞ ደርግ ተራማጅ ነው እንል ዘንድ ሁኔታዎች አስገድደውናል፡፡ ታዲያ ሁለቱም ትክክል መሆኑን ልብ በሉ፡፡ ደርግ እስከ አፍንጫ ድረስ በታጠቀው የጦር ሰራዊቱ እልፍ አዕላፍ የሚሆን ህዝብ ጨርሷል፡፡ ዜጎች ቀይ ሽብር በተባለው የቀይ ደም ትርኢት እየተገደሉ አስከሬናቸው ሜዳ ላይ ከተሰጣ በኋላ የሽብሩ ዘገባ በግልጽ በህዝብ ሚዲያ ይለፈፍ ነበር፡፡ ጋዜጣና መጽሔቱም ሁሉንም ሳያስቀሩ በሰፊው ይጽፉ ነበር፡፡ በአንድ ጊዜ ብዙዎችን እየፈጁ ግዳዩን በሚዲያ ማወጁ ከ1971 በኋላ የቀረ ቢሆንም እስከ ስርዓቱ መጨረሻ ድረስ ህገ ወጥ ግድያዎችና ጭፍጨፋዎች ነበሩ፡፡

12033171_898432963556028_995053122576680975_n
በአንጻሩ ደግሞ ደርግ የተራማጅነት ባህሪዎች እንደነበሩት ማንም አያስተባብልም፡፡ አጼዎቹ በብዙ ገመዶች የተበተቧቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየበጣጠሰ በመጣል ሀገሪቷ በስር-ነቀል ጎዳና እንድትጓዝ ጥርጊያውን መደልደል የጀመረው ደርግ ነው፡፡ የመሬት ጥያቄውን ተመልከቱት!! ከ80 በመቶ የሚልቀው የኢትዮጵያ ገበሬ የመሬት ባለቤት መሆኑ የተረጋገጠለት ደርግ በየካቲት 25/1967 ባወጀው አዋጅ አማካኝነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ የብዙ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች እና ሃይማኖቶች ሀገር መሆኗን በአዋጅ የተቀበለው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ መንግሥት ደርግ ነው፡፡ ፊውዳሎች በዘፈቀደ መንገድ ህዝብን የሚገዙበትን ያረጀ ያፈጀ አስተዳደር መንግሎ በመጣል ሀገሪቱን በእቅድና በፕሮግራም የመምራትን ፍልስፍና ያመጣው ደርግ ነው (የማዕከላዊ ፕላን ኮሚሽንን ያስታውሱት)፡፡ በደርግ ዘመን የተወሰዱ ሌሎች ስር-ነቀል እርምጃዎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡

በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን ዘገባ ደግሞ እዩት!! “የአረፋ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ ብሄራዊ በዓል ሆኖ ተከበረ” ይላል፡፡ ይህም በ1967 የተፈጸመ ክስተት ነው፡፡ ከዚያ በፊት የፓርላማ አባል የሆኑ ጥቂት ባላባቶች፣ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ አንዳንድ ታዋቂ ነጋዴዎች እና ጥቂት የሃይማኖት መሪዎች ወደ ቤተ መንግሥት እየተጠሩ ጋብዣ ቢጤ ይደረግላቸውና በማግስቱ “በኢትዮጵያ የሚኖሩ እስላሞች በዓላቸውን አከበሩ” እየተባለ በአዲስ ዘመን እና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ይጻፋል፡፡ በኢትዮጵያ የሚኖሩ እስላሞች!! ለአንድ ሺህ አራት መቶ ዓመታት እዚሁ የነበሩት ሙስሊሞች በአጼዎቹ ዘመን “በኢትዮጵያ የሚኖሩ እስላሞች” እየተባሉ ነበር የሚጠሩት፡፡ እስልምናም ሆነ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ከሌላ ሀገር ነው፡፡ አጼዎቹ ግን አንዱን መጤ አንዱን የሀገሩ ዜጋ ይሉት ነበረ፡፡ ሀገሪቱም የአንዱ ብቻ እንደሆነች ነው በአዋጅ ያሰፈሩት፡፡ በትምህርት ገበታም ይህንኑ ነበር የሚያስተምሩት፡፡
ደርግ ግን የአጼዎቹን ድንቁርና በመሻር ሙስሊሞቹን “ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች” በማለት መጥራት ጀመረ፡፡ በዚህም ሳይገደብ የኢድ-አልፈጥር፣ አረፋ እና መውሊድ በዓላት ብሄራዊ በዓል ሆነው እንዲከበሩ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ በዚህም መሰረት ደርግ መስከረም 1967 ስልጣን ከያዘ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በብሄራዊ ደረጃ የመከበር እድል ያገኘው የአረፋ በዓል ነው፡፡ ይህ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ እትም በዓሉ በተከበረበት ማግስት የወጣ ነው፡፡
—-
የአጼዎቹን ዘመን እከን የለሽ የብልጽግና፣ የእኩልነት እና የኩሩ ኢትዮጵያዊነት ተምሳሌት አድርገው የሚነዘንዙን ሰዎች ይህንን ታሪክ አያውቁትም አይባልም፡፡ ነገር ግን ሐቅን ላለማየት የወሰኑ አውቆ አበዶች በመሆናቸው ከእብደታቸው ጋር ልንተዋቸው እንገደዳለን፡፡ (በበኩሌ ከእንደነዚህ ዓይነቶቹ ጋር የውይይት አጀንዳ አልከፍትም)፡፡
የአሁኑ መንግሥት ደግሞ ይገርማል፡፡ በስልጣኑ የመጀመሪያ ዓመታት ጥሩ የሚባሉ ጅምሮችን አሳይቶን ለዘመናት የነበርንበት የመቻቻልና የመተሳሳብ ባህላችን የበለጠ እንዲጠናከር ከሚደረግበት ደረጃ ላይ ልንደርስ ነው አስብሎን ነበር፡፡ እያደር ግን እውቅና የሰጣቸውን ህዝባዊ መብቶች መገደብ ጀመረ፡፡
ለምሳሌ ሙስሊም ሴት ተማሪዎችና ሰራተኞች በትምህርት ቤትና በስራ መስክ ላይ ሆነው “ሂጃብ” መልበስ እንዲችሉ የፈቀደው የአሁኑ መንግሥት ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የመንግሥት ባለስልጣናት ይህንን መብት ለማገድ እንቅስቃሴ መጀመራቸውን እየሰማን ነው፡፡ ይህ የሂጃብ ጉዳይ ደግሞ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ “የታገልንለት መብት ስለሆነ ማንም ሊያግደው አይችልም” ያሉለት መሆኑን ልብ በሉ፡፡
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ጉባኤ እንዲመሰረት የፈቀደው ደርግ ነው፡፡ በደርግ ዘመን የጉባኤው እንቅስቃሴዎች ውስን እንደነበሩ ማንም አያስተባብልም፡፡ ኢህአዴግ ሲመጣ ደግሞ “ጉባኤ” የሚለው እና ተቋሙ የራሱ ስልጣን ያለው መሆኑን የሚያስረዳው ስያሜው ተቀይሮ “የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት” የሚል ግራ የተጋባ አጠራር መጣ፡፡ “ጉባኤ” ሲባል እላይ ካልኩት በተጨማሪ ተቋሙ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ንብረት መሆኑን ነው የሚገልጸው፡፡ “ምክር ቤት” ሲባል ግን አንዳንዶች በውክልና የሰየሙት ተቋም ዓይነት እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡
ታዲያ ምክር ቤቱ በአሰራሩም ነው የተለወጠው፡፡ በደርግ ዘመን የነበረው የእስልምና ጉባኤ ህልውናውን ለማንም አስደፍሮ አያውቅም፡፡ ደርግ ለጉባኤው “ይህንን ስራ፤ ይህንን ተው” የሚል ትዕዛዝ ሰጥቶት አያውቅም፡፡ በዘመናችን ግን ጽንፈኝነትና አሸባሪነትን በመዋጋት ስም የብዙዎችን ልብ ያደሙ በርካታ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ እነዚህን እርምጃዎች በበላይነት ያስፈጽም የነበረው የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሚባለው ተቋም መሆኑ ደግሞ በግልጽ ይታወቃል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ እንዲህ ዓይነቱ አካሄድ ትክክል እንዳልሆነ ለመንግሥትና ለሌሎች አካላት እንዲያስረዱለት የወከላቸው የሃይማኖት አባቶችና መምህሮች በጅምላ ታስረውበታል፡፡
እና ምን እንበል? “ጨፍጫፊ” እየተባለ የሚወገዘው ደርግ እንኳ ያላደረገው ነገር በኢህአዴግ ዘመን ሲፈጸም አባላቱና ደጋፊዎቹ ለምን ዝም ይላሉ?….. ይህ ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነው፡፡ የወደፊቷ ኢትዮጵያ የተጣመመውን እያስተካከሉ፣ የጎደለውን እያሟሉ መጓዝን ነው የምትፈልገው፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግሥት ከህዝበ ሙስሊሙ የተነሱትን ቀላል ጥያቄዎች እንዲመልስና በንትርኩ ሳቢያ የታሰሩብንን ንጹሐን ዜጎች እንዲለቅልን አሁንም በድጋሚ እንጠይቀዋለን፡፡
አፈንዲ ሙተቂ
መስከረም 7/2008

ማስታወሻ፤ በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን የጋዜጣ ቅጅ ካለበት ቦታ አምጥቶ በፌስቡክ ግድግዳችን ላይ ያዋለው ታዋቂው የፊልም አክተርና ፕሮዲዩሰር ሁሴን ከድር ነው!! ይገርማል!! ዘመኑ በጣም ይሮጣል!! ሑሴን ከድርን ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅኩት በ1991 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች የአረፋ በዓልን በማስመልከት በሰሜን ሆቴል ባዘጋጀነው አንድ ፕሮግራም ላይ ነው፡፡ በወቅቱ እርሱ፣ ጅላሉ አወል፣ ፈትሒያ ተመስገን እና ሌሎችም … ባቀረቡት ድራማ መድረኩን አድምቀውልን ነበረ፡፡ ከዚያ በኋላ ሁሴንን በአካል ያየሁት አምና በኢግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀ የመጻሕፍት አውደ ርእይ ላይ ከደራሲ አስፋው ዳምጤ ጋር ተያይዘው ሲሄዱ ነው፡፡ ሁሴን በፊልሞቹና በቲቪ አፍሪቃ እያየሁት በአካል ማየቱ ከባድ ሆኖብኛል፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥም ተሁኖ እንዲህ መራራቅም አለ፡፡ ለሁሉም ግን ሁሴንን “ጀዘከላህ” ብለነዋል፡፡

አቤል ተስፋዬ”ዘ ዊኬንድ”የሙዚቃ ስኬት (ከተመስገን ባዴሶ)

$
0
0

ኑሮዋቸውን በባህር ማዶ ያደረጉና_ ኢትዮጵያዊ ዝርያ ያላቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተሰማሩበት የሙያ መስክ ስኬታማ ሆነው ይታያሉ።ከእነዚህም መካከል በሙዚቃው ኢንዱስትሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ ተፅህኖ ፈጣሪ ሆኖ ከእውቅና ሰገነት እየወጣ ያለው የአር ኤንድ ቢ ሙዚቃ አቀንቃኙ አቤል_ተስፋዬ ይጠቀሳል። ኢትዮጵያኖቹ የአቤል ወላጆች በጎርጎሮሲያኑ የጊዜ ቀመር በ1980ዎቹ ገደማ የተሻለ ህይወት ፍለጋ ጓዛቸውን ሸክፈው ከባለፀጋዋ ሀገር ካናዳ ከተሙ።

12033389_1502689746711766_1168063890_n

በዚያም ኑሮዋቸውን ሲያደራጁ ቆይተው፣ እ,ኤ,አ የካቲት 16 ቀን 1990 በካናዳዋ የኦንታሪዮ ከተማ አቤልን ወልደው ለመሳም በቁ። አቤል የልጅነት ጊዜውን በሞግዚትነት እየጠበቁና እየተንከባከቡ ያሳደጉት አያቱ ስለነበሩ አማርኛ ቋንቋን ቅኔ ሳይቀር ቀላቅሎ አቀላጥፎ ይናገራል። ኸንዳውም አማርኛ የአፍ መፍቻዬና የመጀመሪያ ቋንቋዬ ነው ሲል አቤል ደጋግሞ በኩራት ይናገራል!!……የሙዚቃ ክህሎት እንዳለው ከተረዳ በኋላና በፍቅር ከተቆራኘ ወዲህ ራሱን የተሻለ መሰላል ላይ ለመስቀል ሲፍጨረጨር ኖሮ “ዘ ዊኬንድ” የተሰኘ ኦፊሻል የመድረክ መጠሪያ ለራሱ በማውጣት መንቀሳቀስ ጀመረ። ይሄን የመድረክ መጠሪያ የመረጠበት በ17 አመቱ ከትምህርት ቤት አቋርጦ በሳምንቱ መገባደጃ…(weekend) ቤቱን ጥሎ ከወጣ በኋላ ባለመመለሱ የተነሳ እንደሆነ ይናገራል። አቤል የሙዚቃ ስራውን……” ሀ” ብሎ የጀመረው እ,ኤ,አ በ2010 ጀርሚ_ሮስ የተባለውን ፕሮዲዩሰር ካገኘ በኋላ ነበር። አቤል በወቅቱ ከጀርሚ ጋር…” what you need”: ” loft music” እና ” the morning” የተባሉ ሙዚቃዎችን አብረው ለመስራት ቻሉ። ምንም እንኳን በእነዚህ ስራዎቹ አቤል ባይታወቅበትም በታህሳስ ወር 2010 ላይ እነዚህን ሙዚቃዎቹን በዩቲዩብ (you tube) ላይ በመልቀቅ ራሱን ለማስተዋወቅ ሞከረ። በወርሃ መጋቢት 2011 ላይ ዘጠኝ ሚክስ ቴፕ( mix tape) ሙዚቃዎችን ” ሃውስ ኦፍ ባሎን” በሚል መጠሪያ በድረ_ገጹ ለቀቀ! በዚያው አመት ሐምሌ ወር ላይ አቤል የመጀመሪያው የሆነውንና ህዝብ ፊት ቆሞ ያቀነቀነበትን የመድረክ ስራው በካናዳ ሞድ ክለብ ውስጥ አቀረበ። አቤል አከታትሎም በዚያው አመት ሁለተኛና ሦስተኛውን ሚክስ ቴፑን…” thursday” እና “echoes of silence” በሚል መጠሪያ በድረ_ገጹ ለቀቀ። እነዚህ ስራዎቹ ከ8 ሚሊየን ጊዜ በላይ ታይተውለታል። አቤል በሚያዚያ 2012 ላይ ከባንድ ጓደኞቹ ጋር በመሆን በአሜሪካ፣ በስፔን፣ በፖርቱጋል፣ በለንደን፣ በፓሪስና በብራስልስ ከተሞች ተዘዋውሮ የሙዚቃ ኮንሰርቱን አቅርቦዋል። አቤል ከዚህ የሙዚቃ ቱር በኋላ ብዙም ሳይቆይ በመስከረም ወር 2012 ከ…” republic records” ጋር አብሮ ለመስራት ተፈራረመ። ቀጥሎም ከዚህ በፊት የሰራቸውን ሚክስ ቴፖችና ሶስት አዲስ ተጨማሪ ዘፈኖችን በመጨመር…” trilogy” የተሰኘ አልበሙን ለጆሮ አደረሰ። ” ትሪሎጅ” አልበሙ በካናዳ የአልበም ሰንጠረዥ አምስተኛ፣ በአሜሪካ የቢልቦርድ…” ምርጥ 200″ ሰንጠረዥ ላይ ደግሞ አራተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ በቃ!!…እንዲሁም አልበሙ በተለቀቀ በመጀመሪያው ሳምንት ብቻ 86 ሺ ቅጂዎችን ለመሸጥ ችሏል። ይሄው ትሪሎጅ በግንቦት 2012 ከአሜሪካው የሪከርድ ኢንዱስትሪ ( recording industry association of america) የፕላቲንየም እና ከካናዳው ” music canada” የደብል ፕላቲንየም ሰርተፊኬት ለማግኘት በቅቷል። አቤል በግንቦት 2013 ላይ “kiss land” የተሰኘውን የስቱዲዮ አልበሙን አስመረቀ። በዚህ አልበም አቤል ከዝነኛው ካናዳዊ የራፕ አቀንቃኝ ድሬክ ጋር በጋራ ያቀነቀነው “live for” የተባለውን ዜማ አካቶ ነበር። “ኪስ_ላንድ” በሙዚቃ ሂስ ሰጪዎች አዎንታዊ ምላሽ ለማግኘት የቻለ ሲሆን፣ 96 ሺ ቅጂዎችም ሽጧል። አቤል…”the hunger games catching fire” ለተባለው ታዋቂ ፊልም ከሌሎች አርቲስቶች ጋር በመሆን የፊልሙ ማጀቢያ የሆነውን “devil may cry” የተሰኘ ሙዚቃን አቀንቅኗል። በወርሃ የካቲት 2014 የቢዮንሴን “drunk in love” የተባለ ዘፈኗን በራሱ የሙዚቃ ስልትና ምት በማቀንቀን የበርካቶችን አድናቆት አገኘ። ሰኔ 2014 “often”; ሐምሌ 2014 “king of the fall”; መስከረም 2014 ደግሞ ከአሜሪካዊቷ ድምፃዊ “አሪያና_ግራንዴ” ጋር ” love me harder” የተባሉ ተወዳጅ ሙዚቃዎችን ለአድማጭ አድርሷል። አቤል ነሀሴ 28 2015 ላይ ” beauty behind the madness” የተሰኘ ሁለተኛ የስቱዲዮ አልበሙን ለቀቀ። አቤል በአር ኤንድ ቢ ሙዚቃ ሰንጠረዥ ላይ ሳምንቱን ሙሉ ” can’t feel my face”; “the hills” እና “earned it” የተሰኙት ዘፈኖቹ ከአንድ እስከ ሶስት በመሆን በቢልቦርድ ሰንጠረዥ ላይ የመጀመሪያው አርቲስት በመሆን ታሪክ ሰርቷል። አቤል ድምፃዊ ብቻ ሳይሆን የሙዚቃ ግጥምና ደራሲ እንዲሁም የሙዚቃ አቀናባሪም ነው። አቤል ሲናገር……” ማይክል ጃክሰን፣ አር ኬሊና ፕሪንስ” ተፅህኖ አሳድረውብኛል ይላል። ከኢትዮጵያ ድምፃዊያን አስቴር_አወቀ ” ነብሴ ናት የሚለው አቤል የሙላቱ አስታጥቄም አድናቂ ነው። የወላጆቼ ሀገር የሆነቸው ኢትዮጵያን ማየትም የወደፊት ፕሮግራሜ ነው የሚለው አቤል ብዙ መስራት የሚችል ክህሎት ውስጡ እንዳመቀ ብዙዎች ይመሰክሩለታል። ይሳካለት!!!!

የተናገሩት ከሚጠፋ… (ኤፍሬም ማዴቦ – ከአርበኞች መንደር)

$
0
0

ባለፈዉ መጣጥፌ “ቃል የእምነት ዕዳ ነዉ” ብዬ ጀምሬ “ቃላችን አይለወጥ” ብዬ ነበር የተለየኋችሁ። አለምክንያት አልነበረም እንዲህ ያልኳችሁ፤ በአንድ በኩለ ቃል መከበርም መከፈልም ያለበት ዕዳ ስለሆነ በሌላ በኩል ደግሞ ቀትር ላይ የገባዉን ቃል ሳይመሽ እንደ ጴጥሮስ ሦስቴ የሚክድ ብዙ ቃላ አባይ ሰላለ ነዉ። አገሬን ከወያኔ አጸዳለሁ ብሎ ቃል የሚገባ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዕዳ አለበት። ዕዳዉ ደግሞ ገንዘብ ወይም ንብረት አይደለም። ቃሉን መጠበቅ ወይም ቃሉን ማክበር ነዉ።

Ephrem Madebo with Patriotic Ginbot 7 fighters

Ephrem Madebo with Patriotic Ginbot 7 fighters


ደግሞም አንድ ሰዉ የተናገርዉን ቃል ሰብሮ የእምነት ባለዕዳ ከሚሆን ዕድሜ ልኩን የገንዘብ ባለዕዳ ቢሆን ይሻለዋል። የገንዘብ ዕዳ ቆይቶም ቢሆን ይከፈላል ወይም አበዳሪዉ ሊምረን ይችላል፤ የዕምነት ዕዳ ግን የማይሽር ጠባሳዉ እየቆረቆረን አብሮን ይኖራል እንጂ አይጠፋም። ማንም ሰዉ ለአገሬ ህይወቴን እሰጣለሁ ብሎ ቃል ሲገባ መሃላዉ ከህዝብና ከአገር ጋር ብቻ አይደለም፤ እንዳዉም የሰዉ ልጅ ቃል የሚገባዉ መጀመሪያ ከራሱ ጋር ነዉ። ለራሱ የገባዉን ቃል የማያከብርና ቃሌ ቃል ነዉ ብሎ የገዛ ራሱን የእምነት ዕዳ ያልከፈለ ሰዉ ለህዝብና ለአገር ቃል መግባት አይችልም። ዛሬ ወያኔን እናጥፋ ብሎ ካራ ጨብጦ አብሮኝ የቆመ ሰዉ ነገ ከወያኔ ጋር ሆኖ ካራዉን እኔዉ ላይ አዙሮ ባየዉ እሱ ቀድሞዉንም ካራ የጨበጠዉ ወያኔን ለማጥፋት ሳይሆን ስጋ ሊቆርጥብት ነዉና ብዙ አይገርመኝም። እንዲህ አይነቱን ለቁም ነገር ሲፈልጉት አልሰማ ብሎ ሆዱ ሲሞላለት ግን ሳይጠሩት አቤት የሚል ስጋ ወዳድ ሆዳም ደግሞ ኢትዮጵያ በየዘመኑ አፍርታለችና ብዙ ሊገርመን አይገባም። ከሰሞኑ ከምድረ ኤርትራ የነፈሰዉ ነፋስ ያስተማረን አንድ ትልቅ ቁም ነገር ቢኖር እንዲህ አይነቱን ሞላ ጎደለ የሚባል የካራና የስጋ ጨዋታ ነዉ። አዎ! የካራ ጨወታ – ወዲህ ማዶ ስጋ ሊቆርጡበት ወዲያ ማዶም ስጋ ሊቆርጡበት።
“የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” . . . ገዢዎቻችን በተለይ የዛሬዎቹ ቃል አባዮች እንደቆሻሻ ዕቃ መሬት ላይ ጣሉት እንጂ ቃል የዕምነት ዕዳ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ዘመን አይሽሬ የአገራችን አባባል ነዉ። አባቶቻችን የተናገሩትን ወይም ቃል ገብተዉ የተማማሉትን ነገር ከሚያጥፉ የወለዱትን ማጣት ይቀላቸዋል። እኛ ልጆቻቸዉ ግን ከዬት የመጣን ጉዶች አንደሆንን አላዉቅም ቃል አባይነታችን እኛን፤ ልጆቻቸንና አገራችንን ሲያጠፋ በአይናችን እያየን ቅር እንኳን አይለንም። “እመጣለሁ ብሎ ሰዉ እንዴት ይዋሻል፤ ማበል እንኳን አንቺን ምድር ያበላሻል” መሬት ላይ ጠብ የማይል ትክክለኛ አባባል ነዉ። አገራችን ኢትዮጵያ ትናንት እንሞትልሻለን ብለዉ ዛሬ በሚገድሏት ቃል አባይ ልጆቿ እየተበላሸች ነዉ። እነዚህ ቃልአባዮች የኢትዮጵያን የምድር ላይና የምድር ዉስጥ ኋብቷን አንጂ የገረጣዉን ፊቷን ማየት አይፈልጉም- አዎ ወያኔ የሚያየዉ ኃብትሽን፤ የሳዑዲዉ ሰዉ ወርቅሽን፤ ባዕድ ከበርቴዉ ለምለም መሬትሽን . . . ወይኔ ኢትዮጵያ ማን ይሆን የሚያየዉ የጠቆረዉ ፊትሽን፤ ማን ይሆን የሚያብሰዉ እምባሽን፤ እኮ ማን ይሆን የሚያቆመዉ መከራሺን . . . ማን ይሆን?. . . ማን ይሆን?
የዛሬዋ ኢትዮጵያ አንድ ትዉልድ ዉሸት ብቻ እየሰማ ያደገባት የዉሸት መዲና ሆናለች። ጳጳሱ፤ ቄሱና ፓስተሩ “እኔ መንገድ፤ አዉነትና ህይወትና ነኝ” ያለዉን የሰማዩን አምላካቸዉን ረስተዉ ለምድር ዉሸታሞች አደሩ። ሂዱና ዋሹ ሲባሉ ሄደዉ ዋሹ፤ እዉነትን በዉሸት አስተባብሉ ሲባሉ አስተባበሉ፤ በሀሰት መስክሩ ሲባሉ አፋቸዉን ሞልተዉ በሀሰት መሰከሩ። “ታላቁ መሪ” እየዋሸን ኖሮ እየዋሸን ሞተ። መታወቂያዉ ዉሸት ነዉና ሞቶም አልሞተም ተብሎ ተዋሸለት። ከአህያ ጋር የዋለች ጊደር ምን ለምዳ ትመጣለች እንዲሉ ሌላ ሁሉ ቢቀር ዉሸትን ይፀየፋል ተብሎ የተነገረለት የዛሬዉ ጠ/ሚኒስቴር ጭራሽ “ታላቁን መሪ” እንደዋቢ እየጠቀሰ ስራዉ ሁሉ ዉሸት፤ ዉሸት፤ ዉሸት ብቻ ሆኖ ቀረ። የኢትዮጵያ ሬድዮ ሲከፈት ዉሸት ይናገራል፤ ሲዘጋ ደግሞ ነገ ስለሚዋሸዉ ዉሸት ያስባል። ጋዜጦች በስህተት አንኳን እዉነት አይጻፍባቸዉም። የኢቲቪ ዜና አንባቢ ተመስገን በየነ ግማሽ ሰዐት የዋሸዉን ዉሸት ለማካካስ ዜናዉን አንብቦ ሲጨርስ ለ15 ደቂቃ ጎንበስ ብሎ ይሰግዳል።
ለረጂም ግዜ ተማምነን ጀርባችንን የሰጠነዉ ሰዉ ለጠላት እጁን ሰጥቶ ጦርነት ሲያዉጅብን አንዳንዴ በትግሉ ዉስጥ ማንን አምነን ጀርባችንን እንደምንሰጠዉ ግራ ሊገባን ይችላል። ከሰሞኑ የሰማነዉ ዜና እንዲህ ግራ የሚያጋባ ዜና ነዉ። ሆኖም ሳንተማመን ትግል ብሎ ነገር የለምና የትግል ጓዶቻችንን ማመን ብርታት እንጂ ደካሞች እንደሚሉት ሞኝነት ወይም የዋህነት አይደለም። በጓዶቻችን ላይ ክህደት ፈጽመን ከምናሰቃያቸዉ እኛ ብንሰቃይ ይሻላል፤ ደግሞም ጓዶቻችንን ማመን አቅቶን በጥርጣሬ ተፋጥጠን ባለንበት ከምንረግጥ አንዳንዴ አዉቀንም ቢሆን ብንታለል ብዙ መንገድ መጓዝ እንችላለን። ትግል በተለይ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ከሚያስተምረን ትምህርቶች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ሌሎች በኛ ላይ እምነት እንዲኖራቸዉ ከፈለግን እኛ አስቀድመን ልናምናቸዉ አንደሚገባን ነዉ። አለዚያ ሁለታችንም አንተማመንም። አለመተማመን ደግሞ ያጠፋፋናል እንጂ አንድ ቤት ዉስጥ አብሮ አያኖረንም። እንደኔ እንደኔ የወያኔን ስርዐት ደምስሰን ኢትዮጵያን የእኩሎች አገር የምናደርጋት እያንዳንዳችን ለትግል ጓዶቻችን የገባነዉን ቃል ሰብረን ረጂም ህይወት ከመኖር ቃላችንን አክብረን ዛሬዉኑ መሞትን ስንመርጥ ብቻ ነዉ። ወያኔ አንደ እሳት የሚፈራዉና በፍጹም የማያሸንፈዉ አንዲህ አይነቱን ከብረት የጠነከረ ጽኑ አቋማችንን ብቻ ነዉ። ለዚህ ነዉ እንዲህ አይነት ጽናት የሌላቸዉን ደካማ ግለሰቦች ፈልጎ እያማለለ ጽናታችንን የሚፈታተነዉ። ከሰሞኑ ለህዝብ ከመታገል ህዝብን መታገል መርጦ ከለየላቸዉ የህዝብ ጠላቶች ጋር የተቀላቀለዉ ሞላ አስገዶም ለዚህ ዉሳኔ የበቃዉ ህዝባዊዉ ትግል የሚፈልገዉ የአለማ ጽናት የሌለዉ ደካማ ግለሰብ ስለሆነ ብቻ ነዉ። ዉድ ኢትዮጵያዉያን ክህደት ትናንት ነበር፤ ዛሬ አለ፤ ነገም ይኖራል። ስለዚህ ክህደት ሊያስተምረን እንጂ በፍጹም ሊያስበረግገንና አንገታችንን ሊያሰደፋን አይገባም። ክህደትና ከሀዲዎችን እያሰላሰልን የምንኖር ከሆነ የበለጠ እንዲጎዱን ተጨማሪ ዕድል እንሰጣቸዋለን እንጂ ሌላ ምንም የምንፈይደዉ ፋይዳ የለም።
ሞላ አስገዶም እሱን የመሰሉ ደካማ ጓደኞቹን ከተቀላቀለ በኋላ መቀሌ፤ አዲስ አበባና አዳማ ዉስጥ ክህደቱን አስመልክቶ እርስ በርሳቸዉ የሚጣረሱ ሦስት ጋዜጣዊ መግለጫዎችን ሰጥቷል። እርግጠኛ ነኝ ይህ ቁርስ ላይ የተናገረዉን ምሳ ላይ የማያስታዉስ ግለሰብ በተያዘለት የጉብኝት ሰሌዳ መሠረት ዘጠኙን ክልሎች የሚዞር ከሆነ ዘጠኝ የተለያዩና እርስ በርሳቸዉ የሚጣረሱ ምክንያቶችን መደርደሩ አይቀርም። የወያኔ የመረጃና የደህንነት መ/ቤት ተብዬዉም ቢሆን ምን ያህል የዉሸትና የጉራ ቤት ለመሆኑ መረጃ ብሎ የለቀቃቸዉን ዉሸቶችና ቱልቱላዎች መጥቀሱ ይበቃል። ለምሳሌ የመረጃና ስለላ ድርጅቱ ከአንድ አመት በላይ ከሞላ አስገዶም ጋር በሚስጢር ይሰራ እንደነበር ተናግሯል። ይህ እዉነት ከሆነ የደምህት ታጋዮች በዚህ አንድ አመት ግዜ ዉስጥ በወያኔ ታጣቂዎችና ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ለወሰዷቸዉ እርምጃዎች በተለይ እግር ኳስ ጨዋታ በመከታተል ላይ እንዳሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር እንዳለ ለተደመሰሱት የኢትዮጵያ ወታደሮች ተጠያቂዉ ከሞላ አስገዶም ጋር ይሰራ የነበረዉ የወያኔ የመረጃና የስለላ ድርጅት ነዉ ማለት ነዉ።
ሞላ አስገዶም ትናንት ከኛ ጋር ሆኖ እኛ ሲል ነበር፤ ዛሬ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጠለቶች ጋር ሆኖ እኛ ይላል። ይህ ሰዉ “እኛ” ሲል የሱ እኛ እነማንን እንደሚያጠቃልል አይታወቅም፤ እሱ እራሱም የሚያዉቀዉ አይመስለኝም። ሞላ አስገዶም ወያኔን እንደተቀላቀለ አፉን ሞልቶ ጥምረቱን የፈጠርነዉ “እኛ” ነን ብሎ ሲናገር በተደጋጋሚ ተደምጧል። ጥምረቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎትና ህዝባዊ ትግሉ የደረሰበት የዕድገት ደረጃ ዉጤት ነዉ እንጂ ሞላ አስገዶም ስለፈለገዉ የሚፈጠር አለዚያ የሚቀር የሞላ አስገዶም የቤት ዉስጥ ዕቃ አይደለም። ደግሞም እንደ ሞላ አስገዶም ፍላጎት ቢሆን ኖሮ የደምህት ጥምረቱ ዉስጥ መግባት ለግዜዉም ቢሆን ሊዘገይ ይችል ነበር። ደምህት ጥምረቱ ዉስጥ ገብቶ አገር አድን የጋራ ንቅናቄዉ የተፈጠረዉ የደምህት ሠራዊትና ከሞላ አስገዶም ዉጭ ሁሉም የደምህት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ከሌሎች ኢትዮጳያዉያን ወገኖቻቸዉ ጋር ሆነዉ በጋራ ለመታገል በመወሰናቸዉ ነዉ። የሞላ አስገዶም ፈርጥጦ ወያኔ ጉያ ዉስጥ የመሸጎጡ ዋነኛዉ ምክንያትም የዚህ ዉሳኔ ዉጤት ነዉ እንጂ የወያኔ መረጃና ስለላ ድርጀት ሚስጥራዊ ግንኙነት ዉጤት አይደለም። ሌላዉ እርስ በርሱ የሚጋጭ የወያኔ ዉሸት – በአንድ በኩል ሞላ አስገዶምና የደምህት ሠራዊት ሙሉ ትጥቃቸዉን እንደታጠቁ ጠቅልለዉ ወደ አገራቸዉ ተመለሱ የሚለዉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ቁጥሩ ወደ 700 የሚጠጋ የደምህት ሠራዊት ወደ አገሩ ተመለሰ የሚለዉ የተምታታ ዘገባ ነዉ። እዚህ ላይ የደምህትን ሠራዊት ብዛት መናገሩ አስፈላጊ ባይሆንም ግንዛቤ ማግኘት የፈለገ ሰዉ ግን ተመድ ያወጣቸዉን ሪፖርቶች መመልከቱ የሚበቃ ይመስለኛል። ደግሞም ሞላ አስገዶም አታልሎ መንገድ ካስጀመረዉ ሠራዊት ዉስጥ ገሚሱ ወደ ትግሉ ሜዳ ተመልሷል፤ የተቀረዉ ደግሞ ወደ ትግሉ ሜዳ ካልተመለስኩ እያለ ከሱዳን ባልስልጣኖች ጋር እየተደራደረ ነዉ። በነገራችን ላይ የዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ ሞላ አስገዶም አታልሎ ሀምዳይት ከወሰዳቸዉ በኋላ ትግል ወይም ሞት ብለዉ ተመልሰዉ ከትግል ጓዶቻቸዉ ጋር ከተቀላቀሉ ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን ጋር አብሮ ቡና ጠጥቷል።
ጓዜን ጠቅልዬ ትግሎ ሜዳ ከመግባቴ በፊትም ሆነ ከገባሁ በኋላ የደምህት ስም በተነሳ ቁጥር አብረዉ የሚነሱ ሁለት መላምቶች አሉ። አንደኛዉ መላምት ደምህት የኤርትራ መንግስት ሆን ብሎ የፈጠረዉና ጭራሽ ኤርትራ ዉስጥ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎችን ተክቶ በመንግስታዊ ተቋሞች ጥበቃና ደህንነት ስራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ነዉ የሚል መላምት ሲሆን ሁለተኛዉ መላምት ደግሞ ሞላ አስገዶም በኤርትራ መንግስት ድጋፍ ሁለተኛዉ መለስ ዜናዊ ሆኖ ህወሃትን ተክቶ አትዮጵያን ይመራል የሚለዉ መላምት ነዉ። ደግነቱ የነዚህ መላምቶች የማዕዝን ራስ የሆነዉ ሞላ አስገዶም ኮብልሎ ወያኔን መቀላቀሉና ከተቀላቀለ በኋላ የሰጣቸዉ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ሁለቱንም መላምቶች እንዳልነበሩ አድርጓቸዋል። እኔን አልገባ ያለኝና በጣም የሚገርመኝ ግን በአንድ በኩል የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ትብብር እንዲፈጥሩ አይፈልግም ይባላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ጥምረቱ የተፈጠረዉ በሻዕቢያ ግፊት ነዉ ይባላል። መቼም ገና በልጅነቴ ካልጃጀሁ በቀር ሻዕቢያና የኤርትራ መንግስት መሃል ልዩነት ያለ አይመስለኝም። ሌላዉ የሰሞኑ አስቂኝ ድራማ ደግሞ ሞላ አስገዶም ጥምረቱን የፈጠርነዉ እኛ ነን ሲል የሱን መኮብለል አስመልክቶ የሚሰጠዉ አስተያያት ደግሞ ሞላ አስገዶም ጨርቁን ጠቅልሎ ወያኔን የተቀላቀለዉ ብርሀኑ ነጋ በኤርትራ መንግስት ግፊት የጥምረቱ ሊ/መንበር መሆኑ አልዋጥ ብሎት ነዉ ይባላል።
ሌላዉ አሁን በቅርቡ ወይም ከሞላ አስገዶም መኮብለል በኋላ የተጠነሰሰዉ መላምት ደግሞ ደምህቶች እራሳቸዉ ኤርትራ ዉስጥ የሚገኙ ተቃዋሚ ድርጅቶች በወያኔ ስርዐት ላይ ወታደራዊ እርምጃ መዉሰድ እንዳይችሉ ሆን ተብለዉ በወያኔ የተፈጠሩ እንቅፋቶች ናቸዉ የሚለዉ መላምት ነዉ። በኔ ግምት ይህኛዉ መላምት ከሁሉም መላምቶች የከፋና እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ጽንፈኛ መላምት ነዉ። እንደዚህ መላምት ፈጣሪዎች አባባል የትግራይ ህዝብ በህወሃት አመራር በደል አይደርስበትም ወይም የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር ሆኖ የህወሃትን ግፈኛ ስርዐት አይታገልም ማለት ነዉ። እንዲህ አይነቱ ጭፍንነትና ጠባብነት የሚመነጨዉ ደግሞ ሞላ አስገዶምንና ደምህትን ወይም ህወሃትንና የትግራይን ህዝብ ለያይቶ ማየት ካለመቻል አባዜ ነዉ። በደርግ ስርዐት ዉስጥ ጭቆናዉና በደሉ በዛብኝ ብሎ ጠመንጃ ያነሳዉ ጀግናዉ የትግራይ ህዝብ ህወሃት ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹ ተነጥሎ እንዲታይ ለማድርግ የሚሸርብበትን ሤራና የሚያደርስበትን ግፍና መከራ አፉን ዘግቶ የሚቀበልበት ምንም ምክንያት የለም። ስለዚህ ደምህት የትግራይ ህዝብ ብሶትና ምሬት አምጦ የወለደዉ ፀረ ህወሃት ንቅናቄ ነዉ እንጂ ወያኔ የፈጠረዉ ድርጅት አይደለም፤ሊሆንም አይችልም። ሞላ አስገዶምም ቢሆን የራሱ የተጠረቃቀመ ድክመት ከንቅናቄዉ ሊ/መንበርነቱ እንደሚያስነሳዉ ሲያዉቅ የፈረጠጠ ፈርጣጭ እንጂ እሱና ወያኔ እንደሚሉት የአንድ አመት ቀርቶ የአንድ ወርም ተከታታይ ግንኙነት አልነበራቸዉም።
ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረከ ብቅ ብለዉ የጠፉትንም ሆነ ዛሬም ድረስ ያሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች ባህልና ድርጅታዊ አሰራር ስንመለከት የድርጅቶች ህልዉና መመዘኛና የማንነታቸዉ መለኪያ ቆምንለት የሚሉት አላማ ሳይሆን የመሪዎቻቸዉ በተለይ የዋናዉ መሪ ተክለሰዉነት ነበር። የድርጅት ወይም የፓርቲ ሊ/መንበር ከድርጅቱ ባለይ ነዉ፤ እሱ ይሁን ያለዉ ይሆናል፤አይሁን ያለዉ አይሆንም። ብዙ ግዜ የድርጅት/ፓርቲ ሊ/መንበር ድርጅቱን የማፍረስ አቅም ጭምር አለዉ። ይህንን ደግሞ በቅርብ ግዜ ታሪካችን በተደጋጋሚ አይተናል። አንድን ድርጅት ወይም ፓርቲ አባላት ሲቀላቀሉ የሚመለከቱት የፓርቲዉን ሊ/መንበር እንጂ የፓርቲዉን የፖለቲካና የኤኮኖሚ ፕሮግራም አይደለም። የፓርቲ ሊ/መንበርም ቢሆን የኔ የሚላቸዉን ሰዎች ነበር እየመረጠ የሚያሰባስበዉ። እንደዚህ አይነቱ የፓርቲ አደረጃጀትና አሰራር አሁን እየተቀየረ የመጣ ቢሆንም ለረጂም ግዜ የፖለቲካ ትግላችን ችግር ሆኖ ቆይቷል። ሞላ አስገዶም በቅርቡ የደምህትን ሠራዊት ከነሙሉ ትጥቁ ይዤ ኢትዮጵያ ገባሁ ብሎ በድፍረት የተናገረዉ ንግግር ይሄዉ የድርጅት ሊ/መንበር ያሰኘዉን ሁሉ ማድረግ ይችላል የሚለዉ የቆየ የፖለቲካ ባህላችን በሽታ ተጠናዉቶት ነዉ። “ዝንጀሮዉን ከጫካ ያዉጡታል እንጂ ጫካዉን ከዝንጀሮዉ ዉስጥ አያወጡትም” የሚል ብህል አለ፤ ትክክለኛ ብህል ነዉ። ሞላ አስገዶም ህወሃት/ወያኔ የኢትዮጵን ህዝብ በአጥር እየለያየ በትናናንሽ ጎጆዎች ዉስጥ ማኖሩ አልዋጥ ብሎት ሁሉንም የሚያቅፍ ሰፊ ቤት ሰርተን ኢትዮጵያን የዲሞክራሲ አገር እናደርጋለን ብሎ ለብዙ አመታት የታገለ ሰዉ ነዉ። ችግሩ ሞላ አስገዶም ነዉ ከነዚያ ትናንሽ የወያኔ ጎጆዎች የወጣዉ እንጂ ትናንሽ ጎጆዎቹ ከሞላ አስገዶም ዉስጥ ስላልወጡ እንደ ማግኔት እየሳቡት ወደነበረበት ቦታ መልሰዉታል። ለሁሉም የሞላ አስገዶም ታሪክ ሲጻፍ – መጣና ሄደ ከሚሉ አምስት ሆሄያት የዘለለ ምንም ቁም ነገር የለዉም። እየመጡ መሄድና እየሄዱ መምጣት ደግሞ ትናንሽ ቤት የሚናፍቃቸዉ ትናንሽ ሰዎች እስካሉ ድረስ ይቀጥላል።
ሁለት ሺ ሰባት ሊጠናቀቅ ሦስት ቀን ሲቀረዉ አንድ የብዙ ኢትዮጵያዉያንን ጆሮ የሳበ ዜና ቴሌቪዥኑን፤ ሬድዮኑን፤ ጋዜጣዉንና ድረገጹን ተቆጣጠረዉ። ዜናዉ የወያኔ/ህወሃትን ስርዐት በመሳሪያ ኃይል የሚታገሉ አራት ድርጅቶች አገር አድን የጋራ ንቅናቄ ፈጠሩ የሚል የአዲስ አመት የምስራች ነበር። የኢትዮጵያ ህዝብ ለረጂም ዘመን የናፈቀዉ የምስራች ነበር። ግን ምን ያደርጋል – በጥባጭ እያለ ንጹህ ዉኃ አይጠጣምና ይሀንን የአዲስ አመት የምስራች ሰምተን ሳናጣጥም ነበር የሞላ አስገዶምን ዜና ክህደት የሰማነዉ። አስደንጋጭ ዜና ነበር። በእርግጥም የአራት ድርጅቶች ጥምረት ተፈጠረ የሚል ዜና በተሰማ ማግስት የጥምረቱ ምክትል ሊ/መንበር ሠራዊት እየመራ ሄዶ ወያኔን ተቀላቀለ የሚል ዜና መስማት የሚያስደነግጥና በመጀመሪያዉ ዜና ላይ ቀዝቃዛ ዉኃ የቸለሰ ልብ ሰባሪ ዜና ነዉ። ደግነቱ ሁሉም ነገር ለበጎ ነዉ። የሞላ አስገዶም መክዳት ተራ ዜና ነዉ ማለቴ አይደለም። ግን ሞላ አስገዶምና የወያኔ መረጃ ድርጅት በትብብር ሠራነዉ ያሉት አዲስ ድራማ ተዉኔቱ ሳይጻፍ አየር በአየር የተከወነ ምናቡ ያልተባ ድራማ በመሆኑ ድራማዉ ከያኒዉን ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝብና ለአንድነቱና ለነጻነቱ የሚታገሉ ልጆቹን በከፍተኛ ደረጃ የጠቀመ መሆኑን ማሳዉቁ አስፈላጊ ይመስለኛል።
ደምህት በዚህ የወያኔ ድራማ ዉስጥ በእሳት ተፈትኖ ወርቅነቱን አረጋግጧል። ሞላ አስገዶም የደምህትን ሠራዊት ለወያኔ አስረከብኩ ብሎ በተናገረ ማግስት የደምህት መሪዎች የሰጡት አርቆ አስተዋይነት የታየበት አመራርና ያሳዩት ቆራጥነት የፖለቲካ ድርጅቶቻችን የደረሱበትን የዕድገት ደረጃ በግልጽ አሳይቷል። ደምህት እራሱም እንደ አንድ የትግል ድርጅት የተደቀነበትን አደጋና ፈተና በጣጥሶ በመዉጣት በትናንሾችና በደካሞች ሴራ በፍጹም የማይናጋ ጠንካራ ድርጅት መሆኑን በተግባር አሳይቷል። የዛሬዉ ደምህት ዉስጡን ከአድርባዮች ያፀዳ ሁለትና ሦስት እርምጃዎች ወደፊት የተራመደ ጠንካራ ድርጅት ነዉ። እርግጠኛ ነኝ ይህ የደምህት መሪዎች ያሳዩት አስተዋይነት፤ ጽናትና ቆራጥነት እኔ የምፈልገዉ ነገር ካልሆነ ድርጅቱን በአፍጢሙ እደፋዋለሁ ብለዉ ለሚያስቡ ዕብሪተኛ መሪዎች ጥሩ ትምህርት ነዉ። ሌላዉ የሞላ አስገዶም ክህደት በግልጽ ያሳየን ነገር ቢኖር የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ የሀዝብ መብትና ነጻነት ይከበር በሚሉ የነጻነት ሀይሎችና ህዝብን ረግጠን እንገዛለን በሚሉ ፀረ ህዘብ ሀይሎች ለሁለት መከፈሉን ነዉ። ወደድንም ጣላን ካሁን በኋላ ያለን አማራጭ ሁለት ብቻ ነዉ፤ ወይ ወያኔ ሆኖ ከህዝብ ጋራ መዋጋት ወይም ከህዘብ ጋር ሆኖ ወያኔንና ስርዐቱን መዋጋት። ሞላ አስገዶም ጎራዉን ለይቷል፤ እኛም ጎራችንን እንለይ። መኃል ቆሞ መመልከት አብቅቷል።
ጠላቴን አግዝፌ መመልከት አልወድም፤ ትንሽ ነዉ ብዬም ጠላቴን በፍጹም አልንቅም። በቅርቡ የወያኔ የመረጃና ደህንነት መ/ቤትና ሞላ አስገዶም ከአንድ አመት በላይ አብረን ሠራን ያሉትን የጀማሪዎች ስራ ስምለከት ግን ወያኔ/ህወሃት “የምትሰሩትን ብቻ ሳይሆን የምታስቡትን ጭምር የሚያይ አይን አለኝ” እያለ የኢትዮጵያን ህዝብ ከማስፈራራት ዉጭ የረቀቀ የመረጃ ስራ መስራት ቀርቶ አረፍተነገሮችን አገጣጥሞ ለጆሮ የሚጥም ንግግር ማድረግ የሚችል አዋቂ የሌለበት የባዶዎች ድርጅት መሆኑን ነዉ የተረዳሁት። ሞላ አስገዶምም በወዶገባነት ሄዶ የተቀላቀለዉ ይህንኑ አዋቂ የሌለበትን እሱን የመሰለ ድርጅት ነዉ። ይህንን ደግሞ እስከዛሬ በሰጣቸዉ ቃለመጠይቆች በግልጽ አይተናል። ህወሃት/ወያኔን እስከዛሬ በሥልጣን ላይ ያቆዩት ሁለት ነገሮች ቢኖሩ አንዱ ጠመንጃ ሁለተኛዉ የኛ የነጻነት ኃይሎች መበታተን ብቻ ነዉ።
ነገ የምንፈልጋት ኢትዮጵያ እንደ መኪና ተገጣጥማ አትጠብቀንም – የዛሬዉ ጥረታችንና ድካማችን ዉጤት ናት። ኢትዮጵያና ህዝቧ ከወያኔ ሲፀዱ የሚነፍሰዉ የነጻነት አየር ሁላችንንም ቢያስደስትም ደስታዉ የሚገለጸዉ በግለሰብ ደረጃ ነዉ። ዛሬ ከጠላት ጋር ተፋልመን የተቀማነዉን ነፃነት ማስመለስና እንደገና እንዳንቀማ ነቅቶ መጠበቅ ግን የሁላችንም የጋራ ሀላፊነት ነዉ። እንግዲህ ወገን ወገባችንን ጠበቅ የምናደርግበት ግዜ አሁን ነዉና ሁላችንም በየተሰለፍንበት መስክ እንበርታ። ጠላታችን ጠንካራ መስሎ የሚታየዉና ያለ የሌለ ጡንቻዉን የሚያሳርፍብን የማይቀረዉን ድል ማሽተት ስንጀምር ነዉ። የድል መአዛችንን የምናሸትበት ግዜ ደግሞ ሩቅ እንዳይመስለን ነገና ከነገ ወዲያ ነዉ። ከወላዋይና እዚህም እዚያም እየዘለለ ከሚያዘናጋን አጉል ጓደኛ አንዱኑ የለየለት ጠላት ይሻላልና የሞላ አስገዶም ክህደት ትግላችንን ሊያጠራዉና መንገዳችንንም ሊያሳጥረዉ ይገባል እንጂ በፍጹም ግራ ሊያጋባን አይገባም። አይዞን. . . ሞኝ ከዘመዱ ከሚያገኝዉ ጥቅም አዋቂ ከጠላቱ የሚያገኘዉ ጥቅም ይበልጣልና ጠላቶቻችን የፈጠሩልንን አጋጣሚዎች ሁሉ በሚገባ እንጠቀምባቸዉ እንጂ ለጠላት አንመቻች። ጠላታችን እየተሳሳተልን ነዉ፤ ጠላት ሲሳሳት ማቋረጥ ነዉር ነዉ። ቸር ይግጠመን!!!
አፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር ebini23@yahoo.com

አሜሪካ ሙስሊም መሪ “አያስፈልጋትም “ ያሉ እጩ ፕ/ታዊ ተወዳዳሪ ተቃውሞ ገጠማቸው (ታምሩ ገዳ)

$
0
0

በመካሄድ ላይ ያለው የ አሜሪካዊያን የእጩ ፕሬዚዳንት ምረጡኝ ቅስቀሳ የተለያዩ ጉዶችን እና ግርምቶችን እያሰማን ነው። በሰሞኑ ቅስቀሳ ላይ ብቅ ያሉት ሪፐብሊካኑ እጩ ቤን ካርሰን ባለፈው እሁድ ከኢን ቢሲ ቴሌቭዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ “አሜሪካ ከእሴቶቿ (values) እና ከ ህጎቿ ጋር የማይሄድ የእስልምና ሐይማኖት የሚከተል ፕ/ት በጭራሽ አያስፈልጋትም ፣ነገር ግን በተቃራኔው ከቆመ ችግር የለውም” በማለት መልሰዋል።

12048539_1503226689991405_305454164_n
ጥያቄው በዚህ ብቻ አልተቋጨም ወረድ ሲልም “ታዲያ የእስልምና ሐይማኖት ከአሜሪካ ሕገ መንግሰት ጋር ይጣጣማል ብለው ያምናሉ?” የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው። የቤን ካርሰን ምላሽ”ነው ብዩ በፍጹም ነው ብዩአላስብም ። አገሪቱን ሙስሊም ፕ/ት ይምራ ብዮ አልቀሰቅስም፣ በዚህ ሃሳብ በጭራሽም አልስማማም” የሚል ነበር ። የ64 አመቱ ጸሃፊው፣ፖለቲከኛው ፣ ጡረተኛው የእንጎል ቀዶ ጥገና ስፐሻሊስቱ(እዚህ ላይ የእርሳቸውም የእንጎል ሰራስር ትንሽ ላላ ያለ ይመሰላል) እና ወግ አጥባቂ ክርስቲያን የሆኑት ቤን ካርሰን ወዲያውኑ ከተለያዩ ወገኖች ተቃውሞዎች የገጠማቸው ሲሆን በተለይ የአሜሪካ የሙስሊም ካውንስልዳይሬክተር የሆኑት ኒሃድ አዋድ “ካርሰን በዚህ አንጋገራቸው ብቻ ብቁ ፕ/ት መሆን አይችሉም፣ከውድድር በቅድሚያ ሊባረሩ ይገባል፣ለእጩ ፕ/ታዊ ተወዳዳሪዎች የምመክራቸው ነገር ቢኖር የአሜሪካ ህገ መንግስት ምን እንደሚል በቅድሚያ አንዲያነቡት ነው ።”በማለት ተችተዋል፣መክረዋል።
የካርሰን የምረጡኝ ቅስቀሳ ቡደን በበኩሉ” የ እጩ ፕ/ታዊው የ ካርሰን አስተያየት ተጣሟል /ተጋንኖ ነው የቀረበው” ሲል መላሽ በመሰጠት የካርሰን አስተያየት የነበረው”አሜሪካ በአሁኑ ወቅት ሙስሊም ፕ/ት ለመቀበል ዝግጁ አይደለችም የሚል ነበር ፣ካርሰን በቅርቡ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ለማነጋገር ዝግጁ ናቸው።” በማለት አልሸሹም ዞር አሉ አይነት ምልሹን ሰጥቷል። ዛሬ ማክሰኞ የምረጡኝ ዘመቻውን ኦሃዮ ውስጥ ያካሄዱት ካርሰን ከቀደመው አቋማቸው ፈቀቅ እንዳላሉ “ይልቁንም ሃይማኖታዊ ተጽእኖ ለማሳደር የሚሻ ክርሰቲያናዊ መሪም ቢሆን ቦታ የለውም።”ሲሉ ተደምጠዋል።ካርሰን በአሁኑ ወቅት 20% ቅደመ ምርጫ ደጋፍ በማግኝት በረፖብሊካኑ ጎራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ከዚህ ቀደም “ ፕ/ት ኦባማ ትውልዳቸው አሜሪካ አይደለም ፣የልደት ካርዳቸውም ቢሆን አሜሪካዊነታቸውን ሰለ መጠቆሙ እጠራጠራለሁ ።”ያሉት (የሪፐብሊካኖችን እጩዎች እየመሩ ያሉት) ቱጃሩ ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ሰሞን ደግሞ “ከተመረጥኩ የሜክሲኮ ሰደተኞች ወደ ግዛታችን (አሜሪካ ) ዝር እንዳይሉ በአለም ትልቁ የሆነ አጥር በድንበራችን ላይ እገነባለሁ፣ፕ/ት ኦባማ የክርስትና እምነትን እያጠፉ ነው። “ በማለታችው ከዲሞክራቶች ታላቅ ተቃውሞ ገጥሟቸው ሰንብተዋል።

በውቤ በረሃ የሚገኙ ነጋዴዎች የንግድ ቦታቸውን በግዳጅ ሊነጠቁ ነው

$
0
0

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፣ በተለምዶ ውቤ በረሃ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን (አራዳ ጊዮርጊስ) አዲሱ የባቡር ተርሚናል እስከ አፍንጮ በር የሚገኙ ነጋዴዎች፣ ምትክ

የንግድ ቦታ ሳይሰጣቸው የንግድ ቤቶቻቸውን በግዳጅ ለማፍረስ ወረው እያሸገ መሆኑን ገለጹ፡፡

12048818_1503700773277330_369759090_n
ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር እኩል ሊባል የሚችል ዕድሜ ያስቆጠሩ ንግድ ቤቶች በአንድ ሳምንት ማስጠንቀቂያ ማፍረስ ተገቢ አለመሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ፣ አስተዳደሩ የገባላቸውን ቃል በማጠፍ፣ ‹‹ተለዋጭ ቦታ የምሰጣችሁ አሁን ያላችሁበትን የንግድ ቦታ አፅድቼ ስጨርስ ነው›› ማለቱ፣ ከሕግም ሆነ ከመንግሥት ፖሊሲ አንፃር የዜጐችን መብት የማያስከብር በመሆኑ አግባብነት የለውም ብለዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ነጋዴዎቹን ከዓመት በፊት ሰብስቦ በአክሲዮን እንዲደራጁና እያንዳንዳቸው 25,000 ብር በማዋጣት በባንክ እንዲያስቀምጡ፣ እንዲሁም በየወሩ ከ2000 ብር በላይ ገቢ እንዲያደርጉ ያቀረበውን ሐሳብ መቀበላቸውንና ተግባራዊ ማድረጋቸውን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ፣ በንግድ ቦታቸው ላይ ግንባታ ተካሂዶ እያንዳንዳቸው 25 ካሬ ሜትር ቦታ እንደሚሰጣቸው የተነገራቸው ሁሉ ታጥፎ፣ በቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ መወሰኑ እንዳስደነገጣቸው ተናግረዋል፡፡

መንግሥት ከወሰነ በኋላ የገባውን ቃል ተላልፎ በአስቸኳይ እንዲለቁ የሚያደርግ ከሆነ፣ ለሌሎች የልማት ተነሺ ነጋዴዎች የተሰጠው ዕድል ለእነሱም መነፈግ ስለሌለበት፣ ተለዋጭ የኮንዶሚኒየም የንግድ ቦታዎች እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

ቤተሰቦቻቸውንና ቀደምት ነጋዴዎችን በመተካት ሥራቸውን በንግድ ላይ በማድረግ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩት፣ የሚመግቡትና ራሳቸውንም እያኖሩ የሚገኙት በያዙት ንግድ ቤት እየነገዱ በሚያገኙት ገቢ መሆኑን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ፣ በሕገወጥ መንገድ በ‹‹አፍራሽ ግብረ ኃይል›› አማካይነት ወደ ጎዳና ተገፍተው ከመጣላቸው በፊት መንግሥት ሊደርስላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ዕድሜ ጠገብ የንግድ ቤቶች ከሆኑት መካከል የታዋቂው ክራር ተጫዋች ከተማ መኰንን ቤት የነበረው አሁን ብሔራዊ ሆቴል በቅጽል ስሟ ‹‹ጭራ ቀረሽ›› በሚል መጠሪያ የምትታወቀው የዘነበች ታደሰ የነበረውና አሁን ግሪን ባርና ሬስቶራንት፣ መዲና በመባል የሚታወቀው አሁን ያሲን ሱፐር ማርኬት፣ ድምፃዊት አበበች ደራራ የነበረችበት አሁን ሰላም ልኳንዳ፣ ዘመናት ያስቆጠረው አባ ገዳ ማተሚያ ቤት፣ አርቲስት አሰለፈች አላምረው ትሠራበት የነበረው ሆቴል፣ ኤፍሬም ግሮሰሪና ሌሎችም ታዋቂ የንግድ ቤቶች የሚፈርሱ መሆናቸውንም ነጋዴዎቹ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ለልማት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን እነሱም የሚደግፉት ተግባር እንደሆነ የገለጹት ነጋዴዎቹ፣ ከሁሉም በፊት የዜጐች መብትና ክብር መቅደም ስላለበት፣ እንዲሁም መንግሥት ዜጐቹን የመንከባከብና እንደየሥራ ዘርፋቸው ማሰማራት የሚጠበቅበት በመሆኑ ምትክ ቦታ ሰጥቶ እንዲታደጋቸው ጠይቀዋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ የቀድሞ ቀበሌ 03/09 (ወረዳ 5) አስተዳደር፣ በደል ሊፈጽምባቸው መሆኑን እየገለጹ ስለሚገኙት የውቤ በረሃ ነጋዴዎች ጉዳይ ለማነጋገር ሪፖርተር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

በተመሳሳይ ከአራዳ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደርና ከተማ ማደስ ጽሕፈት ቤቶችም በተመሳሳይ ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
ምንጭ ሪፖርተር

ዮ ..ሀ.. ማስቃላ!! ….አደይ ሲፈንዳ!! (አስፋ ጫቦ Corpus Christi, Texas USA)

$
0
0

መስከረም ሲጠባ ፤አደይ ሲፈንዳ፤
እንኳን ሰው ዘመዱን ፤
ይፈልጋል ባዳ ማለት እውነት ነው!ለኔ፣የኔ እወነት ነው!
ዳዊት “..ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ …፤ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ምድርም ሐሴት ታደርግ“ ያለው መሆኑ ነው።ዘፈን ዘፈን !ዝፈን ዝፈን! ብሎኛል እንደማለት ።ዳዊት የተናገረው በምናቡ ኢትዮጵያን እያየ መሆን አለበት። እንጅማ የሱ አገር በአበባ ሠምሮ፥ደምቆ፥ ሰውም፤ምድሪቱም የሚዘፍኑበት አይመስለኝም:: የሰሐራ በረሀ ቅጣይ መሆኑ አይደል!! “ማርና ወተት የሚፈስባትን ቅድስት ሀገር” ለመሳለም ሔዶ የተመለሰው ኢትዮጵያዊ “ቅድስትነቱ እንኳን ይሁን ማርና ወተት የሚፈስባትስ የኔይቱ አገር ነች” አለ። አለ ብሏል ብሎ ዶናልድ ለቪን (Donald Levin Greater Ethiopia) እንደሚጽፈው ለማለት ነው።እንዲያ ብሎ ጽፎ ያነበብኩ ይመስለኛል
መስከረም በጠባ፤አደይ በፈንዳ ቁጥር ያለፈውን ስንትስ አመት በመንፈስ ትዝታ ወደጥንት፤ወደልጅነቴተ ይዞኝ ጭልጥ ይላል።ከዚህ ውስጥ ሶስቱ ጎልተው፤ፍክተው ፤ፋፍተው ይመጡብኛል። የመጀመሪያው የዕንቁጣጣሽ ለት ጎህ ሲቀድ የጨንቻ ገብርኤል ቅዳሴ ማሕሌትና የትንሣኤ(ፉሲካ)ሌሊት ሲሆን ሁለተኛው የጋሞ ማስቃላ፤በተለይም የዶርዜ ማስቃላ፤በተለይም ዶርዜ ላካ የሚከበረው ነው።
መስከረም 1 ጥዋት ድርቡጭ ያለች ጎጆ የሚያክል ስንዴ ይከመርና በዚያ ላይ ካህኑ ወይ መርጌታው የዚያን አመት በአላቱና አጽዋማቱ የሚውሉበትን ቀን ያውጃል። በአዋጁ ውስጥ የዘመን አመጣጥን፤የዘመን አቆጣጠርን ከአዳም አስከዚያ ለት የተርተራል::የዘክራል። በአላቱና አጽዋማቱ የሚዉሉበትን ቀንና ምክንያትም ሲደረደር አብቅቴና መጥቅ የሚለውምአለው። “አብቅቴ ሲበዛ መስከርምን ንዛ ፤አብቅቴ ሲያንናስ ጥቅምትን ዳስ!” የሚለው አለው። አብቅቴ ፤መጥቅ ፤ንዛ፤ዳስ ምን እንደሆነ ያኔም አሁንም አልገባኝም። ስለዘመናት አቆጣጠር ዶክተር ጌታቸው ኃይሌ የተረጎመውን መጽሐፍ ያነበብኩ ይመስለኛል። ማንበብ ማለት መረዳት ማለት አይመስለኝም። ያም ሆኑ ትእይንቱ የሚፈጥረው፣የራሱ፣ ነፍስን ፣ መንፈስን ወደላይ አውጥቶ የማንሳፈፍ ባሕርይ ስለአለው ያው ከኔው ጋር ቀርቶ ትዝታ የሚሉትን ሆኗል።

12021807_1020182711346731_1490198286_n
እኔው እኔን ከሆንኩ ወዲህ (ቶሎ ይመስለኛል እኔ እኔን የሆንኩት) አስገዳጅ ምክንያት ካልተገኘ በስተቀር ቤተክርስቲያን ሔጄ የማውቅ አይመስለኝም።ከዚያ ውስጥ ለሁለት ይሁን ሶስት አመት ለፋሲካ ያደርግነውን አሁን ይህንን መጻፍ ስጀምር አስታወስኩት። ህግ ትምህርት ቤት ( Faculty of Law)እያለሁ፤መልአከ ድንግል እንግዳየሁ የሚባል፤ ጎንደሬ፤ የቤተ መንግስቱ ቅዱስ ገብርኤል ይሁን ባህታ ዲያቆን የነበረ ጓደኛ ነበረኝ። መልአከ አሁን ከኛ ተለይቷል። ቅዳሜ ስሁር፤አራት ኪሎ፤አልማዝ ክፍሌ ቡና ቤት የሚደረገውን ሁሉ እያደርግን እናመሽና ወደአራት ሰአት ተኩል ቤተክርስቲያን ሔደን ስነስረአቱ ከተፈጸመ በኋላ ወደምንሔድበት እንሔድ ነበር። ከአልማዝ ቡና ቤት በእገር የ10 ደቂቃ መንገድ ቢሆን ነው።
በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፤የትንሳኤ በአል ትናንትንና ዛሬ ቁልጭ ብለው የሚለየበት በአል( ቀን)ይመስለኛል።ለ56 ቀናት ጾም ነው። ጾም ማለት ደግሞ ከማንናቸውም የእንስሳትና አእዋፋት አስተውጸኦ መታቀብ ማለት ነው።ከዚህም ሌላ አድማቂ የሚሆኑት ከበሮ፤መቋሚያ ፤ጽናጽል የመሳሰሉት ሁሉ እርፍት ይወስዳሉ።ድምጻቸው አይሰማም።ይጾማሉ እንደማለት!! ከሶስቱ ዜማ አይነቶች፤ግዕዝ፤እዝልና ራራይ ግእዝ ብቻ ነው የሚዘመረው። የሆነ የትካዜ ቅላጼ( Subdued) አለው ተብሎ ይሆናል። ልክ ከለሊቱ 6 ሲሆን፤” ክርስቶስ ተንሰአ እሙታን ፤በአቢይ ኃይል ወስልጣን፤አስሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም” ከተባለ በኋላ ምስባኩም “ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፤ሞተ ወኬዶ ለሞት…” የሚለው ነው:: እኒያ ሲጾሙ የሰነበቱት ማድመቂያ መሳሪያዎች ስራቸውን ሲጀምሩ እውነትም ፋሲካ፣እውነትም ትንሳኤ በል! በል! የሚያሰኝ መንፈስ ይሰፍናል።ያንን መካፈል መንፈሴንም ስጋዬንም የሚያድሰው ይመስለኛል። የእርካታ ምንጫ ብዙ ነው። ሁሉንም በቅጡ ለየተን የምናውቅ አይመስለኝም። ሲመጣ ግን መለየት መቻሉ መታደል ይመስለኛል።
ሌላው አደይ ሲፈንዳ የሚታውሰኝ ጨንቻ ነው።አሁን ሳስበው እንደ ጨንቻ የአደይ አበባ ፍንዳታ ገኖሮ፣ አጥለቅልቆ፣ሠምሮ፣ፈክቶ የሚታይበት የትም ወደየትምም ያለ አይመስለኝም:: Perception is Reality ይላሉና በልጅነት አንዴ የታተመው ምናልባት ሌላ አላይም ብሎም ሊህን ይችላል ብሎ መጠርጠርም የሚቻል ይመስለኛል።
አራዳ ሲቀር (አራዳማ አራዳ! ነውና ) የቀረው፣ነፍጠኛ ፤አየለ፤ ማርያም፤ ገብርኤል፤ መድኃኔ ዓለም ሠፈር፤ካቡራ፣ጥቅጥቅ፣ችምችም ያለ የአደይ አበባ ጫካ ይሆናል።ለኔ ከአበባነቱ ይልቅ አስቸጋሪነቱ ነበር ጎልቶ የሚታየኝ። ጎሮቤት ተልኮ መሔድ፤ውሐ ለመቅዳት ጨፌ መውረድ፤በየእሁዱና በአላት የሆኑ ለት ገብርኤል ሰፈር መሔድ ራሱን የቻለ ጤዛ -በጤዛ የሆነ የሳር፤የአበባ ጫካ ወይ እያባበሉ ወይ እየራሱ መጓዝ ራሱን የቻለ ፈተና እንደነበረ ፍንትው ብሎ ዛሬም ይታየኛል። ልጃገርዶች ከዶኮ መጥተው ለከብቶቻቸው ያጨዱ እንደሁ እስኪተካ ትንሽ ትንፋሽ ይገኛል። ጨንቻ የትና- የት ሰፊ ከተማ ስለሆነ ሁሉን አይዳርሱት ነገር! የኛ ቤት ለዶኮ ቀረብ ስልሚል ከዚህ እድል በመጠኑ የኛ ሰፈር ተጠቃሚ ነበር። ዶኮ ማለት ከጨንቻ ወደምእራብ ያለው አገር ነው። ዶርዜ ወደደቡብ ነው። ዶርዜዎች ግን መጥተው ሲያጭዱ አላየሁም::

A Thousand Suns | Global Oneness Project
አሁን ወደ ሌላው የልጅነት ትዝታዬ፣ወደጋሞ ማስቃላ እሔዳለሁ።የጋሞ ማስቃላ አናቱ መስከረም 16 ወይም 17 ወይም ያው የቀረው የኢትዮጵያ የመስቀል በአል (ደመራ) ሲከበረ ነው።የጋሞ ማስቃላ ምንደነው? ጋሞ፣ ማስቃላ በሚለው፣ ምንን ፣ ማንን ነው የሚያከበረው? የጋሞ አዲስ አመት መሆኑ ነው? የጋሞ አዲስ መንግስት ሥልጣን የሚረከብበት ቀን ነው? በጋሞ በዚያ አመት የተጋቡ ሙሹሮች፤የወጣትነት ዘመናቸው አልፎ ወደ ሙሉ ሰውነት የተሸጋገሩበትን ቀን የሚያስመርቁበት፣የሚያዉጁበትን ቀን ነው? በዚያ አመት የተገረዘ ሁሉ የተገረዘ መሆኑ ባደባባይ የሚነግርበት ቀን ነው? ሌላም ሌላም!
ለመሆኑ የጋሞ ማስቃላ ወይ አዲስ አመት ወይም አዲስ መንግስት ወይም በሆነ ሌላ ስም የሚታወቅበት ቀን ነው? የተጠና፤ቢያንስ እኔ የማውቀው ጥናት ስለሌለ በልጅነት ያስተዋልኩትንና ከዚያም ሊሆን ይችላል የምለውን ነዉ እዚህ ለማቅረብ የምሞክረው።
የጋሞ አዲስ አመት ዝግጅት የሚጀመረው(ለዚህ ውይይት እንዲረዳን አዲስ አመት እንበለውና) ወይ በሰኔ ወይም ሐምሌ ነው። ለዚያ ምልክቱ የግጦሽ ምሬት እንዳለ ይከለልና (ካሎ ነው የሚባለው) መሐሉ አንድ ረዥም አንጨት ይተከላል። ይህ “እዚህ ከበት ድርሽ እንዳይል!” የሚል አዋጅ መሆኑ ነው። ድርሽም አይልም!! ለጋሞ እረኛ አስቸጋሪው ወቅት ይሕ ይመስለኛል። ባንድ በኩል የምህር እርሻ ይጀመራል።በሌላ በኩል የተለመደው የከብቶች የግጦሽ ቦታ ተከልክሏል። ከብቶች ደግሞ በልተው ጠገበው መመለስ አለባቸው። ያንን ሟሟላት የረኛው እጣው ፋንታው ይሆነል።ማለት የፈለኩት በመጠኑ ግልጽ የሆነ ይመስለኛል።
የጋሞ መንግሥስት በየአመቱ በምርጫ የሚመጣ ነው። ተመራጩ ሁዱጋ ወይም ሐላቃ ይባላል።ወደ አርባ የሚደርስ አገር( ደሬ)ስለአለ አንዱ ጋ ባንዱ ሌላው ጋ በሌላው ይጠራል። የልዩነቱን ምክንያት አላውቅም።የዶርዜው ሐላቃ ነው የሚባለው። የሥልጣን ዘመኑም በአብዛኛው አንድ አመት ሲሆን ሁለት አመት የሚሆንበትም ደሬዎችም አሉ።ጋሞ የነገስታት (ካዎ) አገር ነው። ካዎው (ንጉስ)ምልክት እንጅ ስልጣን የለውም።አልነበረውም ማለት የሚሻል ይመስለናኛል! ከምንሊክ ወዲህ ባላባት የሚል ስም ተስጥቷው ከግራዝማች እስከ ፊታውራሪ ደርሰው የአጼው መንግስት በዝቅተኛው ደርጃ አካልና አስፈጻሚ ሆነዋል። በዚህ ሳቢያ በባህሉ ያልነበራቸውን ስልጣን ያገኙ ይመስለኛል።

ይኸ ነገር ካሰብኩት በላይ የተንዛዛብኝ መሰለኝ። አንድ በደንብ ያላጠናሁት ግን የሚከነክነኝ ነገር አለና ትንሽ ልሞክረው። ጋሞ በአመት ውስጥ የሚያከብረው አንድ፣ብቸኛ፣ ሁለገብ፤ ሁለነክ በአል አለዉ።ይህም ማስቃላ ነው። ለመሆኑ የማስቃላ አከባበር ጊዜውወቅቱ ከመቼ እስከመቼ ነው? ከፍ ብዬ መጥቀስ እንደሞከርኩት ካሎ (ግጡሽ መሬት ላይ ማእቀብ) በሰኔ ወይም ሐምሌ የሚጀምር ይመስለኛል። የሚደመደመው ወደመስከረም መጨረሻ ገደማ ነው። አናንቱን፣ጣሪያዉን የሚነካው መስከረም 16 ወይም17 ነው። በዚህ የ3 ወራት ጊዜ ድምቀቱ እንደ^ ይሆናል።በሰኔ ወይም ሐህምሌ ከአንደኛው ጫፍ በወጣቶች የየሰአት በኋላ ዘፍን ታጅቦ ይጀምርና ቁጥሩም እድሜዉም እየጨመረ ይሔድና ጣሪያውን የማስቃላ ለት ይረግጣል። ልክ ጅምሩ ላይ እያሻቀብ እንደሔደው ሁሉ እያሽቆለቆለ ይሔድና መስከረም ሲገባደድ ያጠናቀቃል።
የክረምቱ ወራት የእርሻ፤የመዝራት፤የኩትኳቶ፣ ጥቢው ደግሞ የእሸት ወራት ነው። በጥንት የመካከለናኛው ምስራቅ ታሪክ ይህንን ወራት የአምልኮ ወራት ያደርጉታል። የምርት አማል ክትን (Gods of Fertility) የሚያመልኩበት፤ከደረሰው አዝመራ መስዋእት የሚያቀርቡበት ነው።ሁለመናው ሲታይ የጋሞ ማስቃላም የምርት አምላክን ማወደሻ ይመስለኛል። ከሆነ ደግሞ ይህንን የሚከተል የተረፈ ቢኖር ጋሞ ብቻ ሊሆን ነው። መካከለናኛው ምስራቅ በክርስትናና እስልምና በአብዛኛው ተተክቷል። አሁን ኦሪትን ጠጋ ብለን ብናነበው አብዛኛናው በአላትና መስዋእት ከምርት ወጤት ጋር የተገናኙ ናቸው። ማስቃላ መስቀል ከሚለው ከክርስቲያኑ ነው የመጣው? ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። ከሆነ ደግሞ ማን ከመን ወሰደው የሚለው ለአጥኒዎች የሚተው ይመስለኛል።
በመጨረሻም ከሶስቱ የልጅነት ትዝታዬ አንዱ ወደሆነው ወደጋሞ ማስቃላ፤በተለይም የዶርዜው ማስቃላ፤በተለይም ወደዶርዜ ላካ ማስቃላ አከባበር እሔዳለሁ። ዶርዜ ላካ ከጨንቻ፤በልጅ እግር ከ30 እስከ 45 ደቂቃ ቢወስድ ነው። ማንኛውም የጋሞ ደሬ የሕዝብ አደባባዮች አሉት። ከዚህ ዋንኛው በሁዱጋው ወይም በሐላቃው ሰብሳቢነት(ሊቀመነበርነት) የሚስበሰቡበት ታላቁ ነው። ከትልልቅ ዋርካዎችና ሌሎችም ዛፎች ስር ነው።ጥርብም ከሚመሳስሉ ደንጊያዎች የተሰራ፣መደገፊያ ጭምር ያላቸው መቀመጫዎች አሉት። ሁሌም ሜዳማ ቦታ ላይ ነው። ብዙ ጊዜ ሜዳው ገበያና የባሌ (ሙሾ ማወረጃ)ማረገጃ ጭምር ነው። ላካ ይኸ ሁሉ አለው። ለባሌው (ሙሾዉ) የጸጋዬ ገብረ መድሕንን ሞትም ይሙት ማንበብ ድምቀቱን የተሻለ የሚገልጸው ይመስለኛል።
አዲስ አበባ፤ጃን ሜዳን የጥምቀት ለት በአይነ ሒሊና ማየት የማስቃላ ለት ዶርዜ ላካን የተሻለ የሚገልጸው ይመስለኛል። የክብር እንግዶቹ፤ለክብራቸው በተዘጋጀው ስፍራ (መቀመጫ) የሰየማሉ። ያለፈው አመት ሁዱጋ ወይም ሐላቃና አዲሱ ተመራጭ ጎን ለጎን ይሰየማሉ። ባለፈው አመት የተዳሩ ሙሹሮች፤ባለፈው አመት የተገረዙ ወንዶችም እንዲሁ በተመደበላቸው የክብር ቦታ ይሰየማሉ። ዘፈን፤ጭፍራ ቀኑንሙሉይወርዳል። ይቀልጣል! ማለት ይሻላል። ቀን ሙሉ ከሚውል የዘፈን ድግስ በኋላ ለዘመኑ የተመረጡት ሥልጣናቸውን ይረከባሉኩ።አዲሱ የዶርዜ መንግስት ተቋቋመ፤ስራውንም ጀመረ ማለት ነው።ይኸው ትእይነት ጋሞ ደሬዎች ሁሉ ይፈጸማል። ሙሹሮቹ ተመርቀው ወደ ሙሉ፤
የሕብረተሰቡ አባልነት ተሸጋገሩ ማለት ነው። እኔም ቀኑ፤ ሰአቱ ሳይታወቀኝ በኖ-ተኖ፤ረክቼ ወደጨንቻ የመልስ ጉዞ እጀምራለሁ። ሁለት ሰአት ያክል የሚወስድብን ይመስለኛል። የምናውቀው ጨንቻ ስለሆነ ለመድረስ የሚያጣድፍ ነገር ይለምና!!
እንኳን ሰው ዘመዱን ይፈልጋል ባዳ !!ነው የተባለው? ተርፎን ለባእድ ጭምር የምንቸረው ምርት የሚሰጥ አመት ያድርግልን
ዮ….ሐ ማስቃላ!! መስከረም ጠባዬ!!


የ5 አመቷ ሶፊያ አለም አቀፍዊ መልእክተኛ እና ጀግና ሆነች (ታምሩ ገዳ)

$
0
0

የሮማው ካቶሊክ ቤ/ክ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ፍራንሲስ በአሜሪካ የሚያደረጉትን የ 6 ቀናት ጉብኝታቸውን ለማደረግ እሮብ እለት ከቀትር በሁዋላ ወደ ዋሽንገተን ዲሲ ጎራ ሲሉ ከተቀበሏቸው ታላላቅ መሪዎች (ፕ/ት ኦባማን እና ቤተሰቦቻቸው ጨምሮ) ይልቅ 11ሚለዮን ሰዎችን በመወከል ከካሊፎርኒያ /ሎሳንጀለስ ከተማ ድረስ ተጉዛ ፓፓውን በግንባር ያገኘችው የ 5 አመቷ ሶፊያ ክሩዝ ትልቅ አለም አቀፍዊ የዜና ሽፋን ለማግኘት እና ታሪካዊት ልጃገረድም ለመሆን ችላለች።

12038290_10154343013379298_5638655577720123207_n
ስፊያ አሜሪካ ውስጥ በመወለዷ ሙሉ የአሜሪካ ዜግነት ያላት ሲሆን ከጎረቤት ሜክሲኮ በህገወጥ መንገድ የመጡት ወላጆቿ ግን ህጋዊ ሰንድ የላቸውም። ታዲያ በአሜሪካ ህግ መሰረት በማነኛውም ጊዜ ሊባረሩ የሚችሉት ወላጆቿ እና መሰል 11 ሜሊዮን ሰደተኞች ጉዳይ እንቅልፍ የሚነሳት ሶፊያ አባቷን ጨምሮ ከጥቂት አክቲቪስቶች ጋር በመሆን ለአቡነ ፈራንሲስ ደህንነት ሲባል ልዩ እና እጅግ ጥብቅ የጸጥታ ቁጥጥር ወደ ነበረበት የ ዋሽንግተኑ ስለፍ ላይ ከተገኙት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የብጹነታቸው አፈቃሪዋች እና ምእመናን ጋር በመቀላቀል የፓፓውን መምጣት ይጠባበቁ ነበር።ታዲያ አቡኑ ወደ ሕዝቡ ሰቃረቡ ትንሿ ሶፊያ የደህነነት ጥበቃው አጥርን በማቋረጥ ወደ አቡነ ተንቀሳቃሽ መኪና መሮጧን የተመለከቱ የደህንነት ጥበቃዎች ሶፊያን ለማገድ/ለመከለከል ቢሞክሩም ሁኔታውን የተመለከቱት አቡነ ፈራንሲስ በምልክት ”ጨቅላ ህጻኑዋን ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ አትከልክሏት” በማለታቸው የተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በጽጥታ ሃይሎች የተዋከበችው እና የተገፈተረችው ሶፊያ ከጥቂት ደቂቃዎች በሁዋላ በነዚያ ባዋከቡዋት የጥበቃ ሰራተኞች በአንደኛው እቅፍ ተይዛ አቡነ ፍራንሲስ ከቆሙባት ግልጽ አውቶ ሞቢል በመቅረብ የበጹነታቸውን አባታዊ ቡራኬያቸውንም አግኝታለች።
የትንሿ ሶፊያ እና የ ፓፓው ድንገተኛ ግንኙነት በዚህ ብቻ አላበቃም ። የወላጆቿ ከአሜሪካ ምድር የመባረር ሰጋት ከልቧ የገባዋ ሶፊያ በእጇ የጻፈችው ደበዳቤ ለብጹነታቸው በግንባር ተገኝታ በእጇ ሰጥታለች። መልእክቱም በከፊል “ብጹ አቡነ ፍራንሲስ ውሰጤ በእጅጉ ማዘኑን ለገልጽሎት እፈልጋለሁ።እንደማንኛውም ሰው ከወላጆቼ ጋር የመኖር መብት እንዳለኝ አምናለሁ፣ ደስተኛ የመሆን ተፈጥሮአዊ መብት አለኝ፣ የእኔን ቤተሰቦችን ጨምሮ ሁሉም ሕገ ወጥ ሰደተኞች ለአሜሪካ ህዝብ ካሮት ፣ብርቱካን ፣ሽንኩርት ፣ጎመን እና የመሳሰሉትን በማብቀል እና ለገበያ በማቅረብ ልዩ አስተዋጽኦ በማደረጋቸው ተገቢው ክብር እና ሰብእና ሊሰጣቸው ይገባል፤ብጹነቶ ወላጆቼ በማንኛውም ጊዜ ከአሜሪካ ምድር ሊባረሩብኝ ሰለሚችሉ እባክዎትን ፕ/ት ኦባማን ሆነ ኮንግረሱን አቋማቸውን እንዲቀይሩ ተማጸኑልኝ ”ይላል። ከጽሁፉም በተጨማሪ ፓፓው በግራ እና በቀኝ እጆቻቸው የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ህጻናት “የቱንም ያህል ቀለማችን ቢለያይም እኔ እና ጓደኞቼ እንዋደዳለን” የሚል የግርጌ ማስታወሻ ተጽፎበት ይገኛል።የሶፊያ ወላጅ አባት የሆነው ራዎል ክሩዝም ከጉብኝቱ በሁዋላ “ አቡነ ፍራንሲስ የእግዜአብሔር መልክተኝእበመሆናቸው ልጄ ብጹነታቸውን በግንባር አግኝታ መባረኳ በራሱ ተአምር ነው።” ብሏል።

ትንሿ ሶፊያም የ11 ሚሊዮን ሰንድ አልባ ሰደተኞች ሰጋት እና ጭንቀት የሆነው በአሜሪካ ምድር በሰላም ሰርቶ የመኖር ሕጋዊ መብትን ለ76 አመቱ ፓፓ ከማደረሰ በተጨማሪ በዙዎች በቅርብ ርቀት ሊያዩዋቸው የሚመኙት አቡነ ፈራንሲሰን ጥምጥም ብላ ለመሳም እና በእጃቸውም ለመባረክ እድሉን አግኝታለች። የሶፊያ መልእክትን በጥሞና የተረዱት እና ሁሌም የሚያነሱት አባ ፍራንሲስ ሐሙስ እለት ከ አሜሪካ ኮንግረስ አባላት ፊት ቀረበው ባሰሙት ንግግር”እኔም የሰደተኞች ልጅ ነኝ፣ሰደተኞችን አንፍራቸው፣ አንግፋቸው። በአንድ ወቅት ሁላችንም እንግዶች/ሰደተኞች ነበረን።”በማለት መንፈሳዊ እና አባታዊ ምክራቸውን ሰጥተዋል። በመደረኩ ላይ የነበሩት በተለይ አፈጉባኤው(ካቶሊኩ) ጆን ቢይነር እንባቸው ልውረደ ፣አልውረድ እያለ ሲተናነቃቸው ተስተውለዋል።ከብዙ ሰደተኞች ቤተሰቦች እንደተገኙ የሚናገሩት አብዛኞቹ የአሜሪካ ኮንግረስ ኣባላትም “በአንድ ወቅት ሁላችንም እንግዶች ነበርን !”የሚለው የኣቡነ ፍራንሲስ አባባል ለጊዜውም ቢሆን ከልባቸው ዘልቆ የገባ የመሰላል።የሶፊያ ሆነ የብጹነታቸው ሰጋት እና መልእክትም ከምድረ አሜሪካ ውጪ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰደተኞች ወቅታዊ እና አስከፊው ሁኔታን ማመላከቱ አይቀረም።

አብዮቱና ትዝታዬ (ኮ/ል ፍሥሓ ደስታ)፣ አዲስ መጽሃፍ – አዲስ ምስጢር(ቅኝት ክንፉ አሰፋ)

$
0
0

የመጽሐፉ ርእስ፣ አብዮቱና ትዝታዬ
ደራሲ፣ ፍሥሓ ደስታ (ኮ/ል)
አሳታሚ፣ ፀሐይ አሳታሚ ድርጅት
የገጽ ብዛት፣ 598 ገጾች
ዋጋ፣ $44.95

(ቅኝት ክንፉ አሰፋ)

ፀሐይ አሳታሚ ድርጅት ከዚህ ቀደም ሁለት የአብዮቱ መጽሃፍቶችን አበርክቶልናል። የኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም – “ትግላችን” እና ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ወግደረስ – “እኛና አብዮቱ”። የኮ/ል ፍሥሓ ደስታ “አብዮቱና ትዝታዬ” ከቀድሞዎቹ ትንሽ ለየት ይላል። ኮ/ል ፍሥሓ ደስታ ተድበስብሶ የቆየውን የወታደራዊ መንግስት ውስጣዊ ገመና ብቻ ፈልፍለው አላቀረቡም። በአብዮቱ ሂደት ለተከሰቱ ጥፋቶች ከራሳቸው ጀምረው ተጠያቂው የሆነው ወገንን ከማመልከትም አልታቀቡም። ደራሲው ብዙ ምስጢሮችንም ያስነብቡናል።Fisseha Desta’s book

12025570_131112877242143_1246105835_n
መጽሃፉ ዳጎስ ያሉ ምዕራፎች ይዟል። በአምስት ክፍሎች የተመደቡ አስራ አምስት ምእራፎች ተካትተውበታል። ከቅድመ 1966 ዓ.ም. ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ፣ በደራሲው አገላለጽ – እስከ የ”መጨረሻዋ እራት” የነበሩትን ሂደቶች በስፋት ይቃኛል። ባጭሩ በአፄው መንግሥት ላይ የተነሱ ዓመፆችን በቀላል አማርኛ እያስነበበ የአብዮቱን አፈጣጠር፣ “የየካቲት አብዮት ከነገሌ እስከ መሿለኪያ” በሚል ምዕራፉ ያስነብበናል። ስለ አብዮቱ ውስብስብ ሂደት፤ ስለ ነጭና ቀይ ሽብር፣ የሶማሊያ ወረራ፣ የሕወሓት እንቅስቃሴ፣ የኤርትራ ችግር፣ የግንቦት 8 መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ … በስፋት ያወጋና በመጨረሻዎቹ ምዕራፍ ግዙፉ ሠራዊት ለምን እንወደቀ ይነግረናል።

ጸሐፊው ኮ/ል ፍሥሓ ደስታ ከ1967-1983 ኢትዮጵያን ባስተዳደረው ወታደራዊ መንግስት እስከ ምክትል ፕሬዚዳንትነት የዘለቀ ሥልጣን ነበራቸው። ከ1983 በኋላ ለሃያ ዓመታት በእስር ቆይተዋል። በመጽሐፋቸው ረጅሙ የህይወት እና የሥራ ተመክሯቸውን በመንተራስ፤ በቡድን ለስላጣን ባለቤትነት ከተደረጉ ሽኩቻዎች እስከ ሀገራዊ የመሪነት ግዴታዎችን መወጣት፣ ከግድያና የጥልፍልፎሽ ሴራዎች እስከ የሥር ነቀል አዋጆች ውጥንና አተገባበር፣ ከሙያ ጓዶቻቸው ድብቅ ስብዕና እስከ የውስጥና የውጭ ጣልቃ ገብነቶች፣ የአገርን ክብርና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የተደረጉ እልህ አስጨራሽ ትግሎችና የውድቀቶቻቸው መንስኤዎች ወዘተ በስፋት ዳስሰዋል።

አብዮት ራስዋን እየበላች በነበረበት ሰሞን የእነ ጀነራል ተፈሪ ባንቲ የአገዳደል ሁኔታ የሚገልጸው ክፍል የአንባቢን ቀልብ ከሚስቡት ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው። ኮ/ል ፍሥሓ ደስታ ሁኔታውን በዚህ መጽሃፋቸው እንዲህ በማለት ይተርኩታል።

“…ኮ/ል መንግሥቱ ጠመንጃቸውን እንዳነገቱ ብቅ ብለው በደንብ ከተመለከቱን በኋላ “ትክክል ነው” ብለው ተመለሱ። የመጡትም ቀደም ብለው ማን መቅረት ማን መገደል እንዳለበት በወሰኑት መሠረት ስህተት እንዳይፈጠር ለማረጋገጥ እንደነበር ግልፅ ነው።

ከጥቂት ቆይታ በኋላ መጀመሪያ ወደነበርንበት የስብሰባ አዳራሽ ተጠራን። ወደዚያ ስናመራ ኮ/ል ተስፋዬ ገብረኪዳንን “ባለፈው ጄኔራል አማን ተገደሉ አሁን ደግሞ ሥራቸውን ከሚሰሩበት ቦታ አምጥተን፣ ራሳችን ሾመን እንዴት እኒህ ሽማግሌ [ጄነራል ተፈሪ] ይገደላሉ? ስለዚህ ለመንግሥቱ እንንገራቸው” አልኩትና ተያይዘን ወደቢሯቸው ገባን። እኛም የመጣንበትን ስንነግራቸው “እውነታችሁን ነው” በማለት የውስጥ ስልክ አንስተው ከደወሉ በኋላ መነጋገሪያውን እያስቀመጡ “አዝናለሁ ጓዶች አልቋል” ብለው ነግረውን እያዘንን ወደ ስብሰባው አመራን። እንደገባን ኮ/ል መንግሥቱ መጥተው “ስለሁኔታው ለጦሩ ማስረዳት ስላለብኝ ኮ/ል ተስፋዬ ገብረኪዳን ከኔ ጋር እንድትሄድ” በማለት ጠየቁ። ኮ/ል ተስፋዬም “በማዛቸው ወታደሮች ፊት እጄን ሰቅዬ ወጥቼ ጦሩን ለማነጋገር ፈጽሞ ሕሊናዬ ሊቀበለው ስለማይችል አልሄድም፤ እንደውም ወደክፍሌ እመለሳለሁ” አለ። እኔም “ከእንግዲህ በዚህ ዓይነት እዚህ ግቢ ለመሥራት ፍላጐት የለኝም እኔም እንደተስፋዬ ወደክፍሌ መመለስ እፈልጋለሁ” አልኩ። መንግሥቱም ሽጉጣቸውን በማውጣት “ይህን እርምጃ ባልወስድ ኑሮ ሁላችንም አልቀን ነበር፤ በድያችሁ ከሆነ ግን ግደሉኝ” በማለት ሽጉጡን ጠረጴዛው ላይ ወረወሩት…”

በወቅቱ ከነበሩት ሁለቱ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች፤ በኢሕአፓ እና በመኢሶን ላይ ጸሃፊው የሰጡት አስተያየት ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም እና ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ወግደረስ ካስነበቡን ትንሽ ለየት ይላል። ኮ/ል ፍሰሃ፤ የሁሉንም ፓርቲዎች ብቃት ያወድሳሉ፣ የአመራሩን ችግሮች ደግሞ ይወቅሳሉ። እንዲህ በማለት፣

“…የኢሕአፓ ቆራጥነት፣ የመኢሶን የርዕዮተ-ዓለም ብስለትና የደርግ ሀገር ወዳድነት ተጣምሮ አገሪቱን ወደ ላቀ ደረጃ ሊያደርስ ይችል የነበረ ኃይል በአመራሮቹ ስህተት ያለአግባብ እርስ በርሱ ተጨራርሷል።”

ደራሲው በወታደራዊው መንግስት አመራሩ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወቱ የነበሩ በመሆናቸው በወቅቱ በነበሩ ስህተቶች ከሃላፊነት ነጻ ያለመሆናቸውንም እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል።

“… ኢትዮጵያ ትቅደም! ያለምንም ደም!’ ብለን በተነሣን ማግሥት… እነዚያ ለሀገራቸው የለፉትንና የደከሙትን አዛውንቶች መጦር ስንችል ገደልናቸው።”

ይህንን መጽሃፍ ከቀድሞዎቹ የአብዮቱ መጽሃፍት ለየት የሚያደርገው ደራሲው እንደ ጲላጦስ ከደሙ ነጻ ለመሆን የሌሎቹን ጥፋቶች ብቻ እየኮነኑ የጻፉት አለመሆኑ ነው። ራሳቸውን ከመውቀስ፣ ይቅርታ እስከመጠየቅ መድረሳቸው ደግሞ ከወገንተኝነት የራቁ መሆነቸውን ያሳየናል። ለዚህም ነው “… በማወቅ፣ በድፍረት፣ ባለማወቅና በስህተት ለተፈጸሙት ደግሞ ሙሉ ሃላፊነትን በመውሰድ በበኩሌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።…” ያሉት።

ከመጽሐፉ ድንቅ ትረካዎች መካከል የተወሰኑት ማቅረቡ ሰለ መስጽሃፉ ለአንባብያን ፍንጭ ሊሰጡ ይችላሉ። አንዳንዶቹ መረጃዎች ከዚህ ቀድመው አልተሰሙም። ፍጹም አዲስ ናቸው። ለምሳሌ የፓትሪያርኩን ማምለጥ በተመለከተ ከዚህ ቀደም የሰማነው ነገር አልነበረም። መጽሃፉ እንዲህ ይላል፣

… ፓትርያርኩ እንደሌሎቹ እስረኞች ሳይሆን ብሔራዊ ቤተመንግሥት በሚገኘው የአድሚራል እስክንድር መኖሪያ ቤት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደረገ። በታሰሩ በጥቂት ቀናት ግን ጠባቂዎቻቸው መነኩሴ ስለሆኑ የትም አይሄዱም ብለው ሲዝናኑ ቆባቸውን አውልቀው፣ ጺማቸውን ተላጭተውና ልብሳቸውን ለውጠው በግዮን ሆቴል በኩል ወጥተው ጠፉ። መጥፋታቸው እንደተነገረም በደርግ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጠረ። …

ደርግ በዓሉን በሚያከብርበት ወቅት የወቅቱ የደርጉ ሊቀመንበር ጀ/ል ተፈሪ ባንቴ በአብዮት አደባባይ ንግግር አድርገው ነበር። በንግግራቸውም ለኢሕአፓ ጥሪ አድርገዋል። አብዮት አደባባይ የነበረው አከባበር እንዳለቀ የሕዝብ ድርጅት አባላት ኮ/ል መንግስቱን እንዴ እንዳዋከቡዋቸው ሲጽፉ፣

…የሕዝብ ድርጅት አባላት መስፍን ካሡ፣ ነገደ ጐበዜ፣ እንዳርጋቸው አሰግድ፣ ሰናይ ልኬ እና ሌሎችም ወደተቀመጥንበት ቦታ እያለከለኩና እየሮጡ መጡ፤ ኃይሌ ፊዳም ተከተለ። ምነው ጓድ መንግሥቱ እርስዎን አምነን ተሰብስበን ኢሕአፓ አየገደለን አላስጣላችሁን፤ ይባስ ብላችሁ ደግሞ እኛን የበለጠ ለማስመታት ለኢሕአፓ ጥሪ እንዴት ታደርጋላችሁ ብለው ከግራ ከቀኝ ያዋክቧቸው ጀመር። መንግሥቱም አንዴ ይቅርታ አድርግልኝ ብለው ኃይሌ ፊዳንና የተቀሩትን ይዘው ቡና ቤት ውስጥ ወደምትገኘው አነስተኛ ሣሎን ገቡ። በዚያች ቀንና ሰዓት መንግሥቱ የተነጠቁትን ስልጣን ለማስመለስ መኢሶን ደግሞ ኢሕአፓን በማስመታት ለሥልጣን መንገዱን ለመጥረግ ሴራ ሳይጠነሰስ አልቀረም።…

ቀይ ሽብርን መኢሶኖች እንደጀመሩት እና የጀመሩትም ከኢሕአፓ ነጭ ሽብርና ግድያ ራሳቸውን ለመከላከል እንደሆነ ጽፈዋል። ‘ብሳና ይነቅዛል ወይ ቢሉት ለዛፎች ሁሉ ማን አስተማረና’ እንደተባለው በአብዮቱ ሰፈር ደግሞ ቀይ ሽብር የሚለውን መፈክር በቲዎሪም በተግባርም ለደርግ ያስጨበጠው መኢሶን መሆኑ አገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ሀቅ በመሆኑ ቃላትን በማውገርገርና ነገሮችን በማድበስበስ ከዚህ የታሪክ እውነታ ለማምለጥ መሞከር ትርፋ ትዝብት ነው።…’ ይላል።

ይህንን በመኢሶኖች ተጀመረ ያሉትን ቀይ ሽብር ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም እንዳስቆሙት “አብዮቱና ትዝታዬ” ይነግረናል። እንዲህ ሲል፣

… መንግሥቱ ፊታቸው ተለዋወጠ። “ግድየለም እኔ መንግሥቱ ብቻዬን አስቆመዋለሁ፤ ከእንግዲህ እኔ ሳላውቅና ሳልፈቅድ አንድም ሰው አይገደልም” በማለት ከስብሰባው ወጥተው አንድ ሁለቴ ሲጋራቸውን አቦነኑና ወደ ቢሮአቸው ሄዱ። እውነትም እንዳሉት ከመጋቢት 30፣ 1970 ጀምሮ ቀይ ሽብርም ሆነ ነፃ እርምጃ ቆመ። ኮ/ል መንግሥቱ ይህንን ማድረግ የቻሉት በኢማሌዲህ ሥራ አስፈጻሚ ሰብሳቢነታቸው እንዲሁም በርዕስ መንግሥትና የርዕሰ ብሔር ሥልጣናቸው ተጠቅመው እንደሆነ ግልፅ ነው። ዛሬ አንዳንዶች ሊመፃደቁ አንደሚሞክሩት ሳይሆን ቀይ ሽብርን ሊያስቆም የሚችል ከሳቸው ውጭ አንዳችም ኃይል አልነበረም።…

መጽሃፉ እንዲህ እያለ የአስራ ስባት አመቱን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሂደት በአዳዲስና አስገራሚ መረጃቆች እያዋዛ እስከመጨረሻዋ ሰዓት ያዘልቀናል። የመጨረሻዋ እራት በምትለው ምእራፍ ኮሎኔል መንግስቱ በሚስጥር የያዙትን ስንብትና ከሃገር ጥለው የመሄድ ምስጢር፣

… ግንቦት 10፣ 1983 ቅዳሜ ማታ በጡረታ የተገለልነውን፣ በአዲሱ ካቢኔ ያልተካተቱት፣ እንደዚሁም አዲስ የተሾሙት በተገኙበት በፕሬዚደንቱ መኖሪያ ቤት ለኛ መሸኛ ለአዲሶቹ መቀበያ የእራት ግብዣ ተደረገ። … በዚህ ግብዣ ላይ ከወትሮው በተለየ የታዘብኩት ቢኖር ፕሬዚደንቱ አምቦ ውሃ ብቻ ሲጠጡ ስላየኋቸው ለምን እንደማይጠጡ ስጠይቃቸው ጤንነት ያልተሰማቸው መሆኑን ገለፁልኝ። ወደኋላ ተመልሸ ሳስበው ግን ሆድ ያባውን ብቅል ስለሚያወጣው አገር ጥለው ስለመሄዳቸው ሚስጢር እንዳያመልጥ ለጥንቃቄ ያደረጉት ነበር። ግብዣው እንዳለቀ ቤታቸው በራፍ ላይ ቆመው አንድ በአንድ እየጨበጡ አሰናበቱን። ዳግም ላንገናኝ የመጨረሻዋን እራት በልተን ተለያየን።…

ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አብዮት ሰፊና ውስብስብ የነበረ ቢሆንም በግላቸው ተካፋይ የነበሩበትን፣ በዓይናቸው ያዩትንና በማስረጃ ያረጋገጧቸውን እውነታዎች በተቻለ መጠን ከወገናዊነት በፀዳ መልኩ በዚህ መጽሐፍ ለማቅረብ ሞክረዋለሁ።

ጸሃፊው የታሪክ ባለሞያ አይደሉም። ታሪክን፤ በተለይ ባለሙያ ያልሆኑ ሰዎች ሲጽፉ ወገንተኝነት ጉዳይ መነሳቱ አይቀርም። ከሰው ስህተት አይጠፋምና መጽሐፉን በሚገባ አንብበው በጭፍን ሳይሆን በገምቢ መልኩ የሚሰጡትን ማንኛውን ምአስተያየትና ሂስ ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውንም ኮ/ል ፍሰሃ በመግቢያው ላይ ገልጸዋል።

ጸሃይ አሳታሚ ድርጅት በኢትዮጵያ ጥንታዊ እና ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ጉዳዮች ላይ በርከት ያሉ መጽሃፍት እያሳተመ ለአንባብያን እያቀረበ ይገኛል። ይህም የታሪክ ቅርስን እየጣለልን የሚያልፍ ስራ ነው። ሊበረታታም ይገባዋል። እነሆ ዛሬም “አብዮቱና ትዝታዬ” ጀባ ብሎናል። ግንዛቤ ለመግኘት ያንብቡ – መጽሃፉ መተቸት ካለበትም ይተቹ። … በመጀመርያ ግን ያንብቡ! መልካም ንባብ!

የግብጽ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ አዲስ አበባ ገቡ

$
0
0

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ከ፻፲፰ኛው የእስክንድርያ ፖፕ እና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ዳግማዊ በተደረገላቸው ወዳጃዊ ጥሪ መሠረት ባለፈው ፳፻፯ ዓ.ም.፣ ከጥር ፩ – ፯ ቀን ድረስ በግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የስድስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ethiopia-mathias-i-egypt-pope-tawadros-ii-meet-in-cairo-2

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በጉብኝታቸው ማጠናቀቂያ ላይ ለብዙኃን መገናኛ በቀጥታ ስርጭት ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ በ፳፻፰ ዓ.ም. የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ላይ እንዲገኙ ጋብዘዋቸዋል፡፡ ግብዣውን የተቀበሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ፣ ትላንት መስከረም ፲፬ ሌሊት አዲስ አበባ የገቡ ሲኾን ከዛሬ መስከረም ፲፭ እስከ ፲፱ ቀን ድረስ የአምስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡

ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እና ከኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት እንደተገኘው፣ የቅዱስነታቸው የጉብኝት መርሐ ግብር እንደሚከተለው ነው፡፡

ቅዱስነታቸው መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሌሊቱ 9:00 ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሚደርሱበት ጊዜ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና የፕሮቶኮል ባለድርሻ አካላት አቀባበል ይደርግላቸዋል፡፡
ቅዳሜ መስከረም 15 ቀን፣ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሓላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ መዘምራንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት፣ ‹‹የእንኳን ደኅና መጣችኹ›› ፕሮግራም ይከናወናል፤ በዚኹም ዕለት ከሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ፡፡
እሑድ መስከረም 16 ቀን፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎድሮስ ካልዕ በቦሌ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ካቴድራል ተገኝተው ሥርዐተ ቅዳሴውን በመምራት ጸሎተ ቅዳሴው ይፈጸማል፡፡ ከቁርስ እና ከምሳ ዕረፍት በኋላ በመስቀል ደመራ ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት በክብር ታጅበው ወደ ዐደባባዩ ያመራሉ፤ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ጋር በመኾን በዓሉን ያከብራሉ፡፡
ሰኞ መስከረም 17 ቀን፣ በርእሰ አድባራት ወገዳማት አኵስም ጽዮንና በታሪካዊ ቦታዎች ኹሉ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ከሰዓት በኋላ ደግሞ የጎንደርን ታላላቅ አድባራት እና ታሪካዊ ቦታዎች ይጎበኛሉ፡፡
ማክሰኞ መስከረም 18 ቀን፣ በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ጉብኘት ይደረግና ወደ አዲስ አበባ መልስ ኾኖ ከተወሰነ ዕረፍት በኋላ በሒልተን ሆቴል የራት ግብዣ ይደረጋል፤ የስጦታ መርሐ ግብር ይካሔዳል፡፡
ረቡዕ መስከረም 19 ቀን፣ ወደ ታላቁ ደብረ ሊባኖስ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አምርተው ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ ከዚኹ መልስ በጌቴሰማኔ ቤተ ደናግል ወጠባባት ገዳም ከመነኰሳዪያት ጋር አጭር ውይይት ይካሔዳል፤ ከቤተ ደናግሉ የሥራ ውጤቶች ስጦታ በገዳሙ ከተበረከተ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ይደረጋል፡፡
በዚኹ ዕለት በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል፣ የሰማዕቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ኹለተኛ ፓትርያርክ መካነ መቃብር ጸሎት ይደረጋል፡፡ በመጨረሻም ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ የኹለቱም ቅዱሳት ሲኖዶሳት አባላት ዝግ የኾነ ትውውቅ እና አጭር ውይይት ያደርጋሉ፡፡
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የተወሰኑ የመንበረ ፓትርያርክ ሓላፊዎች በተገኙበት ቅዱስነታቸው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጋር በቅዱስ ሲኖዶስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከ10፡00 – 12፡00 ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ፡፡
ከጋዜጣዊ መግለጫው በኋላ የጋራ የፎቶ መርሐ ግብር ይደረጋል፡፡ በዚኹ ዕለት ምሽት 3፡00 ይፋዊ የአሸኛኘት ሥነ ሥርዐት በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ይኾናል፡፡
Source- haratewahido

የዩኒቨርስቲው በር ተሰብሯል! ዐምዶቹም ተነቃንቀዋል! –ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ (የቀድሞው የአ.አ ዩ የፍልስፍና መምህር)

$
0
0

በዚህ ጽሑፍ የማነሣቸው ርእሰ ጉዳዮች በአራት የተከፈሉ ናቸው፡፡ አንደኛው፡- ስለ ዩኒቨርስቲ አጠር ያለ መሠረታዊ ሐሳብ እና የአካዳሚያዊ ነጻነት መርሖዎች፤ ኹለተኛ፡- የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመንግሥት መዳፍ ሥር ስለ መውደቅ፤ ሦስተኛው፡- የፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬን ገጸ ሰብእና (persona) በኹለት ወጎች ሥር ማብራራት ሲኾን፣ አራተኛው፡- የርእሰ ጉዳዮቹ ማጠቃለያ ነው፡፡

10959139_809531089095868_565801363633107881_n

(ሀ) ዩኒቨርስቲ እና አካዳሚያዊ ነጻነት
ከኹሉ አስቀድሞ አንባቢ ልብ እንዲልልኝ የምፈልገው፣ በዚህ ጽሑፍ የቀረቡት አስተያየቶች እና ምልከታዎች እንደ አንድ በፍልስፍና መስክ የተሰማራ ሰው መጠየቅ ያለባቸውን ነገሮች ለመጠየቅ ያለሙ ናቸው፡፡ ይህም ሐሳቦቹ እና ምልከታዎቹ በአጠቃላይ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ከመከጀል ብቻ ሳይኾን ሳንጠይቃቸው ብናልፍ ትክክል አይኾንም ከሚል እምነት በመነሣት ነው፡፡
የዚህ ጽሑፍ አንደኛው ዓላማ የሚያጠነጥነው፣በዩኒቨርስቲ ምንነት ዙሪያ በመኾኑ ስለ ዩኒቨርስቲ ጠቅለል ያለ ዕሳቤ እና በተጨማሪም ዩኒቨርስቲን፣ “ዩኒቨርስቲ” የሚያሰኙትን ርእይ፣ ተልእኮ እና ግብ ማሳየት ነው፡፡
የዩኒቨርስቲ ዋነኛው ርእይ እና ተልእኮ፣ ዕውቀት ማፍለቅ ሲኾን፣ ያፈለቀውንም ለተማሪዎች ማስተላለፍ እና መተግበር ነው፡፡ ይህም ማለት የዩኒቨርስቲ ዋነኛው ተግባር ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ አኹን ላይ የደረሰውን ዕውቀት መጠበቅ እና መከባከብ እንዲኹም በተሟላ መልኩ ለትውልዱ ማሳወቅ እና ማስተላለፍ ነው፤ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ያልነበረውን ሐሳብ እና ዕውቀት መፍጠርም ነው፡፡
ዩኒቨርስቲ የአንድ ሀገር ምሁራዊ ህልውና እና የሥልጣኔ ዕድገት መገለጫ በመኾኑ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ከሌሎች ተቋማት በተሻለ የሕግ እና የነጻነት መብት ሊሰጠው ይገባል፡፡ እዚህ ላይ ትልቁ የጀርመን ፈላስፋ ካርል ያስፐርስ ስለ ዩኒቨርስቲ ምንነት ሲገልጹ፤ ዩኒቨርስቲ በመንግሥት ቁሳዊ እና ፋይናንሳዊ ድጎማ የሚተዳደር ቢኾንም ከሌሎች ተቋማት ለየት የሚያደርገው የራሱን ርእይ እና ተልእኮ ቀርጾ የሚተገብር እና የሚንቀሳቀስ አንጻራዊ ነጻነት ያለው በመኾኑ ነው፡፡ ለዚህም ነው፣ የዩኒቨርስቲ መምህራን የመንግሥት ደመወዝተኛ ቢኾኑም እንደ ሌሎቹ የመንግሥት ተቋማት ሠራተኞች (civil servants) የመንግሥትን ፖሊሲ ለማስፈጸም የተቀጠሩ አገልጋዮች የማይኾኑት፡፡
በተጨማሪም የዩኒቨርስቲ ዐቢይ ተልእኮ የምንለው፣ ተቋሙ እውነት ላይ ለመድረስ ማንኛውም ጉዳይ የሚጠየቅበት እና የሚመረመርበት ማእከል መኾኑ ነው፡፡ ይህንንም ተልእኮ በአግባቡ ለመወጣት ዩኒቨርስቲ በልዩ ልዩ ተቋማት ሥር ለሚያካሒደው ጥናት እና ምርምር ያልተገደበ ነጻነት እና መብት ይኖር ዘንድ ግድ ይላል፡፡ ዩኒቨርስቲ ነጻነቱን በማስቀደም ነው፣ የዕውቀት መዲና እና መፍለቂያ ኾኖ ከዘመን ዘመን እየተሸጋገረ የመጣው፡፡ የዩኒቨርስቲ ነጻነትን ባነሣን ቁጥር የአካዳሚያዊ ነጻነት ጥያቄ ቁልፍ የኾነ ድርሻ ያለው መሠረታዊ ሐሳብ እንደ ኾነ ግልጽ ነው፡፡
(ለ) አካዳሚያዊ ነጻነት
አካዳሚያዊ ነጻነት ማለት ማንኛውም መምህር በሥራ ገበታው ላይ ሊኖረው የሚገባውን ነጻነት እና መብት የሚደነግግ የሕግ መርሕ ነው፡፡ አኹን በዓለም ላይ በሰፊው ተቀባይነት ያገኙት የአካዳሚያዊ ነጻነት መርሖዎች፣ የዛሬ አንድ መቶ ዓመት ገደማ በአሜሪካን ሀገር በጉዳዩ ዙሪያ የጥናት ስብሰባ ከተደረገ በኋላ ተሳታፊዎቹ የሚከተሉትን አራት ነጥቦች አቅርበው፣ ሕጋዊ ከለላ ለማሰጠት በመቻላቸው እነሆ እስከ አኹን ድረስ ወሳኝ የኾኑ የአካዳሚያዊ ነጻነት መርሖዎች እና አዕማድ ኾነዋል፤ ፍሬ ሐሳቦቹም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
1. የመመራመር እና የማሳተም ነጻነት
ማንኛውም መምህር በፈለገው እና በመረጠው ርእስ ምርምር እና ጥናት የማካሔድ ሙሉ መብት አለው፡፡ በተጨማሪም በምርምር ያገኘውን ውጤት ያለምንም ዕንቅፋት እና ገደብ የማሳተም መብት አለው፡፡
2. መምህር በክፍል ውስጥ ስለሚኖረው ነጻነት
ማንኛውም መምህር ለሚያስተምረው ትምህርት ይኾናል የሚለውንና የሚበጀውን የማስተማርያ ጽሑፎችን የማካፈል እንዲኹም ማንኛውንም ትምህርት ነክ የኾኑ ጉዳዮችን በውይይት እና በጥያቄ ያለምንም ጫና ለተማሪዎቹ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
3. በትምህርት ተቋም ቅጽር ውስጥ የሚኖር መብት/Intramural Right)
ማንኛውም መምህር አቅሙና ችሎታው እስከ ፈቀደ ድረስ የአንድን የዩኒቨርስቲ አስተዳደር እና አመራር ሳይፈራ እና ሳይሸማቀቅ የማሔስ እና የመተቸት ሙሉ መብት አለው፡፡
4. ከትምህርት ተቋሙ ቅጽር ውጭ ስላሉ ጉዳዮች የሚኖር መብት(Extramural Right)
ማንኛውም መምህር በሥራ ገበታው ላይ እያለ የሀገሩን የአስተዳደር፣ የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ጉዳዮችን የመተቸት ሙሉ መብት አለው፡፡
እነዚህ ከላይ የተገለጹት መርሖዎች በሕግ ማህቀፍ ሥር መካተታቸው፣ በአካዳሚው ዓለም ውስጥ ለተሰማሩ መምህራን ሥራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑና እንዲኹም ለወከባና ለእንግልት እንዳይዳረጉ መከታ ይኾናቸዋል፡፡
፪.
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ለመቆጣጠር የተደረገው ሒደት
ኢሕአዴግ ስለ ፖለቲካ ስትራቴጅና አቅጣጫ በ1997 ዓ.ም. ባወጣው ሰነድ ላይ፤ ስለ ሀገሪቱ ምሁራን የሚከተለውን ግምጋሜ አቅርቧል፡፡ ግምጋሜው የታየበትን መነጽር፣ ከዚህ በታች ስለምናቀርበው የዩኒቨርስቲው በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መዋል መንደርደሪያ ይኾነናል፡፡
እንደ ኢሕአዴግ አመለካከት፣ምሁሩ ምንጊዜም ወደ ሥልጣን ማማተሩ ስለማይቀር በተቻለ መጠን የሥልጣን መወጣጫ መንገዱ ተዘግቶ መያዝ አለበት፡፡ ይህን ለማሳካት ምሁሩ የንዋይ ፍላጎቱ በተቻለ መጠን እንዲሟላለት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ በመኾኑም በሙያው ዙሪያ ባሉ ሳንካዎችና ጥቅማጥቅሞች ተጠምዶ ወደ ሀገራዊ ጥያቄዎች ሳይሻገር በእዚያው ማጥ እየዳከረ እንዲኖር ማድረግ ይኖርበታል፡፡
ከዛሬ ስድስት መቶ ዓመት በፊት፣ ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅ፣ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ ከደረሷቸው መጻሕፍት መካከል ‘መጽሐፈ ምስጢር’ ብለው በሰየሙት ድርሳናቸው ውስጥ፣ ሳይማሩ እናስተምራለን ብለው ስለተነሡ የቤተ መንግሥት ባለሟሎች የሚከተለውን ብለው ነበር፡፡ ከአባ ጊዮርጊስ የወሰድነው ጥቅስ ሊቁ ለሌላ ጉዳይ የተናገሩት ቢኾንም ለያዝነው ርእስ የመንፈስ ቅርበት አለው ብለን ስለምናምን በዚሁ አገባብ የጠቀስነው መኾኑን ለአንባብያን እያስታወስን ጥቅሱን ያጎረሱንን መሪጌታ ሳናመሰግን አናልፍም፡፡
“እሉ እሙንቱ [መነኮሳት] እለ ቀዲሙ የዐየሉ ገዳመ አድባረ ወበዐታተ ወድኅረ ይትዋሐውሑ በአዕጻዳተ ነገሥት፡፡ ቀዲሙ ከመ ኢይትመሀሩ መጻሕፍተ ነቢያት ወሐዋርያት በንኡሶሙ ወጽኡ ገዳመ ወተግኅሡ እምዐጸደ ቤተ ክርስቲያን እንተ ይእቲ እመ ኩልነ ዘኢይነጽፍ ሐሊበ አጥባቲሃ፡፡ ወድኅረኒ ኢይፈጽም ገድሎሙ በጽማዌ ውስተ ገዳም ቦኡ ውስተ አብያተ ነገሥት ወበዊኦሙ ከመ ኢያርምሙ መሀሩ ዘኢትምህሩ ወሰበኩ ዘኢያእመሩ፡፡ ይልህቅኑ ሕፃን ዘእንበለ ሐሊበ አጥባተ እሙ ይሌቡኒ መነኮስ ዘኢተምህረ መጻሕፍተ ነቢያት ወሐዋርያት ከመ ይኩን መመህረ ለሰማዕያን ፡፡ ለሀወት ገዳም በኃጢአቶሙ ወለሀዋ አድባረ ምኔታት ወኢረኪቦቶሙ፡፡
“ለሀወት ቤተ ክርስቲያን በእንተ ዘነሠቱ አናቅጺሃ ነቢያተ ወነክነኩ አዕማዲሃ ሐዋርያተ፡፡ ወሠርዑ ሎሙ ሕገ ወሥርዓተ ዘኢይወጽአ እምእስትንፋሰ አፉሁ ለእግዚአብሔር ፡፡”
ትርጉም፡-
“እነዚህ [መነኮሳትም] ቀድሞ በበርሀ በተራሮችና በዋሻዎች የሚዘዋወሩ በኋላ ግን በነገሥታት ዐፀዶች ውስጥ የሚመላለሱ ናቸው፡፡ ቀድሞ በታናሽነታቸው ጊዜ የነቢያትና የሐዋርያትን መጻሕፍት እንዳይማሩ የጡቶቿ ወተት የማይደርቅ የኹላችን እናት ከኾነች ከቤተክርስቲያን ዐፀድ ርቀው ወደ ገዳም ወጡ፡፡ ኋላም ገድላቸውን በገዳም ውስጥ ኾነው በጭምትነት እንዳይፈጽሙ ወደ ነገሥታት ቤት ይገባሉ፤ገብተውም ዝም እንዳይሉ ለራሳቸው ያልተማሩትን ያስተምራሉ፤የማያውቁትንም ይሰብካሉ፣ሕጻን ያለ እናት ጡት ያድጋልን? መነኩሴስ ለሚሰሙ ሰዎች አስተማሪ ይኾን ዘንድ ያልተማረውን የነቢያትና የሐዋርያትን መጻሕፍት ያስተውላልን?
“ቤተ ክርስቲያን ስለ ኃጢአታቸው አለቀሰች፡፡ የገዳማት ተራሮችም እነርሱን ባለማግኘታቸው አለቀሱ፤ቤተ ክርስቲያን ነቢያት በሮቿን ስላፈረሱ፣ ምሰሶዎቿ ሐዋርያትንም ስለነቀነቁ አለቀሰች፡፡ ከእግዚአብሔር አንደበት ያልወጣውንም ሕግና ሥርዓት ለራሳቸው ሠሩ፡፡”
ከላይ በጥቅስ ከተቀመጠው የአባ ጊዮርጊስ ትዝብት የሚከተሉትን ፍሬ ነገሮች ነቅሰን ማውጣት እንችላለን፡፡ የአመራረጣችን መሠረት፣ ባለንበት ወቅት አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዴት ሙሉ በሙሉ በመንግሥት መዳፍ ሥር እንደ ወደቀ የጥቅሱ መንፈስ ማሳያ ኾኖ ስላገኘነው ነው፡፡ አኹን በሥልጣን ላይ ያለው ሥርዓት፣ ከገጠር ወደ ከተማ እንደ መጣው ኹሉ፣ የአባ ጊዮርጊስም ‘ምሁራን’ ከበረሓ ወደ ቤተ መንግሥት የመጡ በመኾናቸው ተመሳሳይነታቸው ከፍ ያለ ነው፡፡
የቅዱሱን ተግሣጽ በኹለት ምድብ በመክፈል በመጀመሪያ፣ የትዝብታቸውን መነሻ ቀጥለን ደግሞ፤ ድርጊቱ ያስከተለውን አሉታዊ ዉጤት እናያለን፡፡
ሀ. የትዝብታቸው መነሻ፡-
የተወሰኑ ምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት በመፈለግ ወደ ዋሻ፣ አድባራት እና በረሓ ገቡ፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ አልኾንላቸው ሲል በረሓውንና ዋሻውን ለቀው ወደ ቤተ መንግሥት ጠጋ አሉ፤ ወደ ቤተ መንግሥቱም አዘውትረው መመላለስ ጀመሩ፡፡ ከማዘውተራቸው ብዛት የቤተ መንግሥቱን አመኔታና ይኹንታ ተቀዳጁ፡፡ የሹማምንቱን ቅቡልነት ቢያገኙም በየበረሓው ወጣትነታቸውን በከንቱ አባክነው በዘመኑ ከቤተ ክርስቲያን ብቻ ይገኝ የነበረውን ትምህርት ሳያገኙ ስለቀሩ፣ የቤተ መንግሥት ባለሟልነታቸውን ተጠቅመው፣ ያልተማረውን ምእመን እናስተምራለን ብለው ተነሡ፡፡
ለ. ድርጊቱ ያስከተለው አሉታዊ ውጤት፡-
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፤ኹኔታው ያስከተለውን አሉታዊ ውጤት በኹለት ዘይቤ (Metaphor) ያስረዳሉ፡፡ እነዚህም፡- “በሮቿ ተሰበሩ” እና “አዕማዷ ተነቃነቁ” የሚሉት ናቸው፡፡
በሮቿ ተሰበሩ፡-
“በሮቿ ተሰበሩ” ከሚለው ዘይቤ ውስጥ በዛ ያሉ ምልከታዎችን መንቀስ ይቻላል፡፡ በር ስንል የሚፈለገው የሚገባበት፣ መግባት የሌለበትን ደግሞ መቆጣጠሪያ ሥርዓት መኾኑን ነው የሚያመለክተው፡፡ በመኾኑም የተናጋና የተሰበረ በር ያለው ተቋም፤ ማንም እንዳሻው የሚገባበትና የሚወጣበት፣ ሥርዓት አልባ ጎዳና ኾኗል ማለት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን የራሷን ልዕልና አስጠብቃ መዝለቅ ተስኗታል እንደማለትም ነው፡፡
አዕማዷ ተነቃነቁ፡-
የአንድ ቤት ዐምዱ ወይም ምሶሶው ከተነቃነቀ፣ጨርሶ የመፈራረሱ ጉዳይ ተቃርቧል ማለት ነው፡፡ በአባ ጊዮርጊስ ዕይታ፤ የቤተ ክርስቲያኒቷ ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊት በአጠቃላይ አስተምህሮዋ ተናግቷል ማለታቸውን ያሳያል፡፡ በተፈጠረው አግባብ የለሽ አካሔድና ቀውስ የቤተ ክርስቲያኒቷ አበው አዘኑ፤ አለቀሱም፡፡
ወደ ጥንተ ነገራችን ስንመለስ፤የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ አቀራረብ፣ አኹን በዩኒቨርስቲው ቅጥር ውስጥ የሚካሔደውን ኹኔታ በሚገባ ለመረዳት እንደ መነጽር ይኾነናል፡፡ ከኹሉ አስቀድሞ፣ የአባ ጊዮርጊስ ‘መምህራን’ እናስተምራለን ብለው የተነሡት ራሳቸው ሳይማሩ ያልተማሩትን ሰዎች ለማስተማር ነው፡፡ በእኒህ ኹለት ዓመታት ውስጥ፣ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ እናሠልጥን ብለው የተነሡት የመንግሥት ሹመኞች ራሳቸው በሚገባ ሳይማሩ፣ አልተማሩም የሚሏቸውን ሳይኾን፣ የተማሩትን ክፍል ለማስተማር መነሣታቸው ነው፡፡ ከዚኽ አንጻር አባ ጊዮርጊስ የታዘቧቸው መምህራን ከአኹኖቹ እናስተምር ባዮች በእጅጉ የተሻሉ ኾነው እናገኛቸዋለን፡፡ ይኸውም የቀድሞዎቹ፣ ራሳቸው ባይማሩም እናስተምር ያሉት ያልተማሩትን ሲኾን የእኛዎቹ ግን እናስተምር ብለው የተነሡት የተማሩትን በመኾኑ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ በዚህ ዘመን ቢኖሩ ኀዘናቸው ምን ያኽል በበረታ ነበር!!
አባ ጊዮርጊስን በእጅጉ ያሳዘናቸውና ያስገረማቸው፣ ቤተ መንግሥት በፍጥረቷ የአስተዳደር መንገድ መቀየስ እንጂ የዕውቀት ምንጭ ወይም የምሁርነት ምኩራብ ሳትኾን፣ ዐዋቂዎች ነንና እናስተምር እያሉ የሚነሡባት ማእከል ኾና ስላገኟት ነው፡፡ አኹን ወዳለንበትም ጊዜ ስንመጣ፣ ብዙዎችን እያሳሰበ ያለው በየዩኒቨርስቲው እናሠልጥን እያሉ የሚመጡት ሰዎች አኳኋን ነው፡፡ ልክ እንደ አባ ጊዮርጊስ ‘ምሁራን’ አስቀድመው ወደ በረሓ ከወጡ በኋላ ተመልሰው ቤተ መንግሥቱን በቁጥጥራቸው ሥር አዋሉ፡፡ ከዚያም ቤተ መንግሥቱም ዩኒቨርስቲውም አይቅርብን ብለው የዩኒቨርስቲውን መምህራን እናስተምራለን ብለው ብቅ አሉ፡፡
የአባ ጊዮርጊስ ኀዘን የበረታው፣ እኒኽ ‘ምሁራን’ ቤተ ክርስቲያን እንደ በሮቿ የምታያቸውን የነቢያት አስተምህሮ ስለሰበሩና በምሰሶ የተመሰሉትን የሐዋርያትን ዶግማና ቀኖና ስላነቃነቁ ነው፡፡ ብዙዎችን ታዛቢዎች በእጅጉ እያሳሰባቸው ያለው በአስተማሪነትና በአሠልጣኝነት ስም፤ ዩኒቨርስቲው የዕውቀት፣ የጥበብ፣ የምርምርና የመሳሰሉት ዕሴቶች ገዳም ኾኖ ሳለ፤ ሊቃነ ማእምራኑ (ፕሮፌሰሮቹ) ያስቀመጧቸውን ሚዛኖች (በሮች) በመስበር አዕማዷን ስላነቃነቁት ነው፡፡የቤተ ክህነቱ በር እንደተሰበረው ኹሉ፣ የየኒቨርሲቲውም በር ተሰብሯል ስንል ዩኒቨርስቲው ተማሪዎቹንም ኾነ መምህራኑን መርጦ የመቀበል መብቱ ተገፍፎ፣ በፖለቲካ ትእዛዝ እንዲሞላ በመደረጉ፣ ማንም እንዳሻው የሚገባበትና የሚወጣበት ኾኗል ማለታችን ነው፡፡ የአዕማዷን መነቃነቅ በምናነሣበት ጊዜ በዋናነት የምናቀርበው፣ ዩኒቨርስቲው የነበረው የማስተማር ሥነ ዘዴ ተሽሮ፣ ከፖለቲካ ኃይሉ በመጣ ማዘዣ፣ እነርሱ ይበጃል የሚሉትን አካሔድ ተግባራዊ እንዲያደርግ መገደዱን ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚኾነው፣ ከቢፒአር እስከ ቢኤስሲ እና አንድ ለአምስት አደረጃጀትን መምህራኑ ሳይመክሩና ሳይዘክሩበት፣ ዩኒቨርስቲው እንዲከተል መደረጉ ነው፡፡ የአባ ጊዮርጊስ ‘ምሁራን’፣ የመንግሥትን ኃይልና ቤተ ክርስቲያንን ገና በሚገባ ያልተቆጣጠሩ ሲኾን፣ የአኹኖቹ ምሁሮች ግን ሥልጣንን ሙሉ በሙሉ ለያዙ ኃይሎች ተጠሪዎች ናቸው፡፡ በመኾኑም ከንኡሳን (ደቃቂን) ሓላፊዎች እስከ ዐቢይ አለቃው – ፕሬዝዳንቱ፣ ድረስ ለቤተ መንግሥቱ የፖለቲካ ቀኖና ተገዥና ተኣማኒ በኾኑ እሺ ባዮች እንዲያዝ ተደርጓል፡፡
እውነተኛ ዩኒቨርስቲያዊ ይትበሃል ተሽሮ፣ የበረሓ ጀግኖች እንዳፈተታቸው የሚናኙበት ኾነ፡፡ የመማር ማስተማር ሒደቱንም፣ ዩኒቨርስቲያዊ ልዕልናው ስለ ተገፈፈ ሳይንሳዊና ሞያዊ አሠራሩ ተሻረ፡፡ በቦታውም ከፖለቲካው ጽሕፈት ቤት በሚመነጭ ኢሕአዴጋዊ ትእዛዝ በሩን አፈረሱት፤ ዐምዱንም አነቃነቁት፡፡ ካርል ያስፐርስ የገለጹት ‘አማናዊው ዩኒቨርስቲ’ እና እውነተኞቹ ምሁሮቿ ስለ እነዚህ ሰዎች አድራጎት አብዝተው ያዝናሉ፡፡ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ሲቋቋም፣ ሊቁ ዶክተር እጓለ ገብረ ዮሐንስ፣ የበሩን ኹለት አዕማድ ‘በዕውቀት’ እና ‘በሠናይ’ (Virtue) በመመሰል የዘመሩለት፣ ማንም ሰው ሊያየው በሚችለው መልኩ መሠረቱ ተናጋ፤ ውድቀቱም ተቃረበ፡፡

ድምጻዊት ዘውዲ ለመጀመርያ ግዜ ወደኢትዮጵያ ልትሄድ ነው

$
0
0

በእናቷ ኢትዮጵያዊ በአባቷ ኤርትራዊ የሆነችው ድምጻዊት ዘውዲ ሓብቲ አወሎም ለመጀመርያ ግዜ ወደኢትዮጵያ ልትሄድ ነው።
ከልጅነቷ የጀመረው ሙዚቀኛ የመሆን ፍላጎቷ ድምጻዊ በሆነው አባቷ እገዛ ዛሬ የደረሰችበት ደረጃ የደረሰችው ዘውዲ የተወለደችው ኒውዮርክ ሲሆን ያደገችው ኒውጀርሲ ነው።
በዩቲዮብ ሙዚቃዋ ከ16ሚሊዮን በላይ በሚሆኑ ተመልካቾች የታየላት ሲሆን የራሷን ሙዚቃዎች በተለያዩ ቦታዎች ከማቅረቧም ሌላ ከታዋቂ ድምጻዊያን ጀርባ ተቀባይ ድምጻዊ ሆና ሰርታለች ።የ23 ዓመቷ ዘውዲ የእናት አገሯ ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ግዜ ለማየት ጉዞ መጀመሯ ልዩ ስሜት እንደተሰማት ገልጻለች ።ከሙዚቃዎቿ አንዱ የሆነውን በአማርኛና በእንግሊዝኛ የተጫወተችውን “into the night “እንጋብዛችሁ።

Viewing all 212 articles
Browse latest View live