Quantcast
Channel: Kalkidan Amharic – Kal Tube
Viewing all 212 articles
Browse latest View live

3ቱ የዞን 9 ጦማርያን ከእስር ቤት ወጡ

$
0
0

12166938_1512292605751480_2053231737_n
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ በትላንትናው ዕለት ጦማርያን ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፉ ብርሃኔና ሶልያና ሽመልስን በነፃ ማሰናበቱ የሚታወስ ሲሆን ማረምያ ቤቱ ሶስቱን ጦማራውያን አሳድሮ ዛሬ ፈታቸው።
ጦማሪ በፈቃዱ ሐይሉ፤ ከሽብር ክሱ ነፃ የተደረገ ቢሆንም፤ በምርመራ ወቅት ለፖሊስ በሰጠው ቃል፣ ጽሑፎቹ የማነሣሣት ፀባይ እንዳላቸው አምኗል በመባሉ ክሱ ወደ ወንጀል ክስ እንዲዞር ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡በፈቃዱ የዋስትና ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ዋስትና ይሰጠው ወይም አይሰጠው የሚለውን ለመወሰን ለጥቅምት አሥር ቀጥሮታል፡፡
ክሷ በሌለችበት ሲታይ የነበረው 1ኛ ተከሳሽ ሶሊያና ሽመልስ በሌለችበት በነፃ ተሰናብታለች፡፡ ጦማርያኑ በነፃ የተሰናበቱት፣ “የዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎች የቀረበውን ክስ በሚገባ አላስረዱም” በሚል ፍ/ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ሲሆን አራቱም መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ በይኗል፡፡
ከአንድ ዓመት ከአምስት ወራት በፊት በድንገት ተይዘው ከታሰሩት 10 ጋዜጠኞችና ጦማርያን ውስጥ አምስቱ ሐምሌ 1 እና 2፣ 2007 ዓ.ም በድንገት መፈታታቸው ይታወሳል፡፡
በትላንትናው እለት በነፃ ከተባሉት ናትናኤል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላ፣ አጥናፉ ብርሃኔ ፍርድ ቤቱ ነፃ ቢላቸውም ማረምያ ቤቱ ሳይፈታቸው የቀረ ቢሆንም ዛሬ ተፈተዋል።


“ህዝቡ ሲፈልግ ያሳክመኝ፤ ያለበለዚያ ስሞት ይቅበረኝ”- ሳክስፎኒስት ጌታቸው መኩሪያ

$
0
0

4ba2a160e3ae857ca2c59c7cfea33d80_M
• በመላው ዓለም እየዞሩ በመስራት ከ5 ሚ. ብር በላይ አጠራቅመው ነበር
• እሳቸውና ባለቤታቸው በመታመማቸው ገንዘቡ በህክምና አለቀ
• አሁን ገቢያቸው ከቤት ኪራይና ከጡረታ 1500 ብር ገደማ ነው
• “ህዝቡ ሲፈልግ ያሳክመኝ፤ ያለበለዚያ ስሞት ይቅበረኝ”

ጌታቸው መኩሪያ በሳክስፎን ተጫዋችነቱ አንቱ የተባለ አንጋፋ ባለሙያ ነው፡፡ በማዘጋጃ ቤት፣ በብሄራዊ ቴአትርና በፖሊስ ሰራዊት የሙዚቃ ክፍል ከሙዚቃ ተጫዋችነት እስከ ዋና መምህርነት አገልግሏል፡፡በ1986 ዓ.ም ጡረታ ከወጣ በኋላ በሸራተን አዲስ ሆቴል ለስምንት አመታት የሰራው አንጋፋው ሙዚቀኛ፤ ከመቶ በላይ አገራትን በሥራ አጋጣሚ ዞሯል፡፡ አልቶ ክላርኔት እና ሳክስፎን አሳምሮ የሚጫወተው አርቲስቱ፤ ከሦስት አመታት ወዲህ በህመም ምክንያት ከሚወደው ስራው ርቆ የበርካታ ሆስፒታሎችን ደጃፍ ለመርገጥ ተገድዷል፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ ከ81 ዓመቱ የእድሜ ባለፀጋ ከጌታቸው መኩሪያ ጋር በጤናው፣ በሙያውና በአጠቃላይ ህይወቱ ዙሪያ ሰፊ ቃለምልልስ አድርጋለች፡፡

የጤና እክል እንዳጋጠመህ ሰምቻለሁ፤ ህመምህ ምንድን ነው?
የልብ ችግር ቀደም ሲል ነበረብኝ፡፡ አሁንም ያው የልቤ ህመም ነው የተባባሰብኝ፡፡ በዚያ ላይ ሁለቱም እግሬ ታፋዬ ላይ አብጦ መራመድ አልቻልኩም፤ ብቻ ተደራርቦብኛል፡፡
ህክምና አላገኘህም እንዴ?
ፖሊስ ሆስፒታል በነፃ መታከም እችላለሁ፤ ግን እዛ ለበሽታዬ መፍትሄ አልተገኘም፤ ላንድማርክም ታክሜያለሁ፤ ውጤት አላገኘሁም፡፡ አሁን ይሄው ኮሪያ ሆስፒታል ዛሬ ሄጄ (ቃለ ምልልሱ ረቡዕ ነው የተደረገው) ውጤት ዘጠኝ ሰዓት ብለውኛል፡፡ እስኪ የሚሆነውን አያለሁ፡፡ እዚህ ካልተቻለ ታይላንድ ባንኮክ ሄደህ ትታከማለህ እያሉኝ ነው፡፡ እግዚአብሄር ያውቃል፡፡
አሁን ሙሉ በሙሉ መራመድ አትችልም?
አልችልም፡፡ በሰው ድጋፍ በምርኩዝ በስንት ችግር ነው የምንቀሳቀሰው፡፡
ስለዚህ ስራ እየሰራህ አይደለማ?
እንዴት አድርጌ… እግሬ አላላውስ ብሎኛል፡፡
በሙዚቃ ህይወት ምን ያህል ጊዜ አሳለፍክ?
ከ60 ዓመታት በላይ ቆይቻለሁ፡፡ በ1940 ዓ.ም ወዳጄነው ፍልፍሉ የሚባል ጓደኛዬና ተፈራ አቡነወልድን አይቼ ነው ወደ ሙዚቃው የገባሁት፡፡ ወዳጄነው ፍልፍሉ ጐበዝ ክላርኔት ተጫዋች ነበር፡፡ ተፈራም ከማዘጋጃ እስከ ብሄራዊ ቴአትርና እስከ ውጭው ዓለም ድረስ ብዙ ታሪክ የሰራ፣ ድንቅ የጥበብ ሰው ነበር፡፡ አሁን ሁለቱም በህይወት የሉም፡፡ መጀመሪያውኑ ዋሽንት መጫወት፣ ሰርግ ላይ መጨፈር እወድ ነበር፡፡ እነተፈራን ሳይ ደግሞ ፍላጐቴ ጨመረና ማዘጋጀ ቤት ገባሁ፡፡ ከዚያ ትንሽ ሰልጥኜ የመንገድ ላይ ታምቡር (ድራም) አስያዙኝ፤ በኋላ እራሴን እያሻሻልኩ ወደ ክላርኔት ተሸጋገርኩ፡፡ ከክላርኔት ወደ ሳክስፎን አሻሻልኩ ማለት ነው፡፡
እዚያው ማዘጋጃ ቤት ተቀጠርክ ማለት ነው?
አዎ! ማዘጋጃ ቤት ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻልኩ ስመጣ፣ ደሞዝ የሁለት የሁለት ብር ጭማሪ ሲደረግ፣ ስንወዳደር ሁሉንም በልጬ ተቀጠርኩኝ፡፡ እነዚያ የበለጥኳቸው ልጆች ተናደው መንገድ ላይ ጠብቀው ደበደቡኝ (ረጅም ሳቅ…)
በጣም ተጐዳህ?
ድብደባው እንኳን እስከዚህም ነው፤ እንደው ነገሩ ነው እንጂ፡፡
የመጀመሪያው ቅጥር ደሞዙ ስንት ቢሆን ነው የሁለት ብር ጭማሪ የተደረገው?
(በጣም እየሳቀ)… ደሞዙማ አስር ብር ነበር፤ መጀመሪያ ስቀጠር፡፡ በውድድሩ እነሱን በልጬ 18 ብር ስለገባሁ አይደለም እንዴ ባልደረቦቼ ደበደቡኝ ያልኩሽ፡፡
ከዚያስ?
ከዚያማ እንዲህ እንዲህ እያልን… በሶስተኛው ዓመት በ1943 ዓ.ም መሆኑ ነው፡፡ ኮሪያ ዝመቱ ተባልን፡፡ በወቅቱ መንግስቱ ነዋይ ኮሎኔል ነበር፤ መጣና፤ “ይህችን ልጅ ተዋት፤ ጥይት አታባክኑ” ብሎ ነገራቸው፡፡ ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) ሲዘምት፣ እኔ ቀርቼ በሙዚቃው ቀጠልኩ፡፡ ከተስፋዬ ጋር ሌሎችም ዘምተዋል፡፡ ምክንያቱም እኔ ያን ጊዜ ቀልጣፋና ጐበዝ ነበርኩ፡፡ እነሱ ሰነፍ ስለሆኑ ዘመቱ ማለቴ ግን አይደለም፡፡
ለመሆኑ የሙዚቃ መሳሪያዎቹን ማን አሰለጠነህ?
እኔ ቀደም ብዬ ስትተዋወቂኝ እንዳጫወትኩሽ፣ ሳልማር ያስተማርኩ ነኝ ብዬሻለሁ፡፡ በቀለም ትምህርት እስከ ዘጠነኛ ክፍል ነው የተማርኩት፣ ከዚያ በላይ አልገፋሁም፡፡ የሙዚቃ መሳሪያዎቹን ያስተማሩኝ ግን ነርሲስ ናልቫንዲያን እና ዘልቤከር የተባሉ ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚያ እራሴን እያሻሻልኩ በመሄዴ፣ የነርሲስ ረዳት ሆኜ በመምህርነት በርካታ ሰዎችን አስተምሬያለሁ፡፡
በወቅቱ ደራራ ባይሳ የተባለ በኋላ ስሙን ቀይሮ ተድላ ተብሏል፤ እሱ ጐበዝ ሳክስ ተጫዋች ነበር፤ ሁለተኛ እኔ ነበርኩኝ፤ በጥረቴ አንደኛ ሆኜ ረዳት መምህር ሆንኩኝ፡፡
ከማዘጋጃ ቤት በ1948 ወደ ብሄራዊ ቴአትር ቤት ተዛወርክና በርከት ላሉ አመታት እዚያ ሰራህ፣ ከዚያም ወደ ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል ገባህ፡፡ እስኪ ሂደቱን አስታውሰኝ?
ልክ ነው በ1948 ብሄራዊ ቴአትር ከገባሁ በኋላ ለ17 አመታት ሰርቻለሁ፡፡ ጥሩ ጊዜ ነው ያሳለፍኩት፡፡ ከዚያ ወደ ፖሊስ የተዛወርኩት የነርሲስ ረዳት መምህር ሆኜ ነው፤ መቼም ፖሊስ ውስጥ እኔና ሂሩት በቀለ ከሌለን ቤቱ አይደምቅም ነበር፡፡ እኔና እሷ ፖሊስን ፖሊስ አሰኝተነው ነው ያለፍነው፡፡ ለበርካታ አመታት አስተማሪም ተጫዋችም ሆኜ ጡረታ እስከወጣሁበት ጊዜ ድረስ አገልግያለሁ፡፡
በ1986 ዓ.ም ነው ጡረታ የወጣኸው አይደለም?
ልክ ነው ከመንግስት ለውጥ ከሦስት አመት በኋላ ነው ጡረታ የወጣሁት፡፡
ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል ምክትል መምህር ሆነህ ስትሰራ ዋናው መምህር ነርሲስ ናልቫንዲያን በመሞታቸው፣ ዋና መምህር ሆነህ ነበር፡፡ ለመሆኑ የ18 ብር ደሞዝህ ስንት ደረሰ?
ነርሲስ ሲሞት እኔ ዋና መምህር ሆንኩኝ፡፡ ደሞዙ 800 ብር ነበር፡፡ የእሱ ደሞዝ እንዲከፈለኝ ከተደረገ በኋላ ተስፋዬ አበበ አብሮ ለፍቷል፤ በጀት ውስጥ ይግባ ተባለና የኔ ደሞዝ ለሁለት ተከፍሎ፣ እኔ 600 ብር ሆነ ደሞዜ፡፡
ዶ/ር አርቲስት ተስፋዬ አበበ ናቸው?
አዎ፡፡ እሱንም እንደኔ ረስተውት ነበር፡፡ አሁን አስታውሰው ዶ/ር አድርገውታል፤ እውነት ለመናገር ይገባዋል፡፡ ዘግይተውም ቢሆን ይህን ክብር ስለሰጡት ደስ ብሎኛል፡፡
ጡረታ ከወጣህ በኋላ ሸራተን መስራት እንደጀመርክ ይታወቃል፡፡ ከዚያም ከመቶ በላይ የዓለም አገራትን በስራ መዞርህንም አውቃለሁ፡፡ እስኪ ስለሱ አጫውተኝ?
ልክ ነው ሸራተን ገብቼ ስጫወት የፈረንጅ መአት ይመጣ ነበር፡፡ እኔ እንደነገርኩሽ ብዙ ቋንቋ አልችልም፤ በማህሙድ አህሙድ አስተርጓሚነት ከፈረንጆቹ ጋር ተነጋገርኩና ውጭ መሄድ ጀመርኩ፡፡ ብቻ ምን አለፋሽ… ወደ 104 አገራትን አይቻለሁ፡፡ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ሆላንድ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ… ከመላኩ በላይ ጋር እየዞርን፣ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ አሰኝተናታል፡፡ አሜሪካ እንኳን ሰባት ስቴት ውስጥ ስራዬን አቅርቤያለሁ፡፡ እስራኤልም እንዲሁ… ብቻ አሁን የማስታወስ ችሎታዬ ቀንሷል… ድፍን አለምን ዞሬያለሁ፡፡
የማስታወስ ችሎታዬ ቀንሷል ስትል… ለእርጅና እጅ ልትሰጥ ነው እንዴ?
ኧረ የለም አልሰጥም፤ ገና የ81 አመት አፍላ ጐረምሳ እኮ ነኝ፡፡ በ1927 እኮ ነው የተወለድኩት፡፡
ክፍለሀገር ነው የተወለድከው?
አዎ፡፡ ይፋትና ጥሙጋ ነው፡፡ ልጅ ሆኜ ነው አዲስ አበባ የመጣሁት፤ እስከ ዘጠኝ ተምሬ እንደነገርኩሽ ወደ ሙዚቃው ገባሁ፡፡
ከ100 በላይ የአለም አገራትን ስትዞር መቼም ጥሪት መቋጠርህ አይቀርም ብዬ አስባለሁ፡፡ አሁን ያገኘሁህ ግን በሰዎች እርዳታ ስትታከም ነው፡፡ አሁን ምንም ንብረት የለህም ማለት ነው?
እንዳልሽው ጥሪት ቋጥሬ ነበር፡፡ ለልጆቼም ለጥቂቶቹ ላዳም ገዝቼ ሰጥቼ ነበር፡፡ መለስተኛ ቤትም አለኝ፡፡ ነገር ግን ባለቤቴም እኔም ታመን ያልሄድንበት ሆስፒታል፣ ያልታከምንበት ሀኪም ቤት የለም፡፡ ግን ገንዘቤን አሟጥጬ ከመጨረስ በቀር መፍትሄ አላገኘሁም፤ በመጨረሻ ከስድስት ወር በፊት ባለቤቴ አረፈች፡፡ (በጣም ትካዜ ውስጥ ገባ) ገንዘቤ ሲያልቅ መልሼ ፖሊስ ሆስፒታል አስገብቻት ነበር፡፡ የልብ ህመም ነበረባት፤ አልዳነችም፡፡ ምን አለፋሽ… ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ አጠራቅሜ ነበር፤ አሁን ይሄው መላኩ ነው እየደገፈኝ ያለው፡፡
ብዙ ልጆች እንዳሉህ ሰምቻለሁ፤ አይረዱህም?
ዘጠኝ አካባቢ ልጆች አሉኝ፤ የቁጥራቸው መብዛት ፋይዳ የለውም፡፡ በአጭሩ ለራሳቸውም በቂ ኑሮ እየኖሩ አይደለም፡፡
ከሸራተን ስራ ያቆምከው ለምን ነበር?
ሸራተን እየሰራሁ እንዳልኩሽ ለስራ ብዙ ጊዜ ወደ ውጭ እወጣ ነበር፡፡ “እዚህ እየሰራህ እንዴት ውጭ ሄደህ አንድና ሁለት ወር እየቆየህ ትመጣለህ?” አሉኝ፡፡ ታዲያ ስራ ላልሰራ ነው፤ ከፈለጋችሁ ተውት እንጂ ውጭ መሄዴን አላቆምም ስል፣ ለሼህ አላሙዲን ነገሩት እና አቀያየሙን፡፡ እንደውም እሱ የገዛልኝን ሳክስፎን እንመልስልሃለን ብለው ወስደው ሸጡት፡፡
እነማን ናቸው የሸጡት?
የኔ ልጅ ተይው እከሌ ነው እከሌ ነው ማለቱ ጥቅም የለውም፡፡ ስም ለመጥራትም ያስቸግራል፡፡ ብቻ ያልኩሽ ሆኗል፡፡ እኔም በጣም ተቀየምኩኝ፡፡
እና አሁን ሳክስፎን የለህም?
ኧረ ደንበኛው ሳክስፎን ነው ያለኝ፡፡ ክላርኔትም አልቶም አለኝ ሶስትና አራት መሳሪያ ነው የምጫወተው፡፡ ይሄው ሶስት አመት ስታመም ተረስቼ ቀረሁ፤ ጤናው ቸገረኝ እንጂ መሳሪያው አለኝ፡፡ አሁን ለብሄራዊ ቴአትር 60ኛ አመት በዓል እኔና መርአዊ ስጦት በተቻለን መጠን አንድ ሙዚቃ ለመጫወት አስበናል፤ ከተሻለኝ ማለቴ ነው፡፡ ያው እሱም ልቡን ያመዋል እንደሚታወቀው፡፡
አሁን ከማን ጋር ነው የምትኖረው? ማንስ ነው የሚጦርህ?
አንድ ሴት ልጅ አለችኝ፡፡ እሷ ብቅ እያለች ታየኛለች፤ በቃ ከሰራተኛ ጋር ነው የምኖረው፡፡
የገቢ ምንጭህ ምንድነው?
ቤት አለኝ ብየሽ የለም፤ ሁለት ትንንሽ ክፍሎች አከራያለሁ፤ ከእነሱ ወደ አንድ ሺህ ብር አካባቢ አገኛለሁ፡፡ ጡረታዬ አሁን በጭማሪው ሁለት መቶ ብር ተጨምሮልኝ ወደ አምስት መቶ ከፍ ብሏል፤ እሷን እሷን እያደረግሁ ነው የምኖረው፡፡
ለህክምና ባንኮክ ያልከውስ…?
እንኳን ባንኮክ ሄጄ የምታከምበት አሁን ሃኪም ቤት የምመላለስበትንና የምታከምበትን እንኳን የሚከፍልልኝ ይሄው መላኩ በላይ ነው፡፡ እንግዲህ ፈጣሪ ያውቃል፡፡
ብዙዎቹ የአገር ባለውለታዎች በህመምና በገንዘብ ማጣት ሲቸገሩ ብዙ አያገኙም፤ “ሲሞቱ ግን ቀብራቸው ይደምቃል” ይባላል፡፡
ልክ ነው፡፡ እኔ አንድ የምወደው አባባል አለኝ፤ “ከሞተ ጀነራል የቆመ ወታደር ይሻላል” የሞተን ሰው ጀነራል ከማድረግ፣ ለቆመው ወታደር እንክብካቤ መስጠት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ጀነራል፣ ሚኒስትር፣ ደጃዝማች እያሉ ማሞካሸትና መካብ የወሬ ጋጋታ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ ያን ያህል ክብር ከሰጡት በቁም የሚያስፈልገውን እንክብካቤ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ እኔም አሁን ታምሜ ብረሳም ሲሻለኝ ብቅ ብዬ ህዝቡን አለሁ እለዋለሁ፡፡ ህዝቡ ራሱ እንደሚያሳክመኝ አምናለሁ፡፡ እዚያ ከመድረሴ በፊት ግን ሁሉም በየእምነቱ እሱ እንዲምረኝ ይፀልይልኝ፡፡
እስኪ ማዘጋጃም ብሄራዊ ቴአትርም ፖሊስ ክበብም ስትሰራ ያጋጠመህና የማትረሳቸው ፈገግ የሚያሰኙ፣ የሚያሳዝኑ ገጠመኞች ካሉህ አጫውተኝ…
አንዱ ቀደም ብዬ የነገርኩሽ ነው፡፡ ማዘጋጃ ቤት ተወዳድረን ሳሸንፋቸውና ደሞዜ 18 ብር ሲገባ ባልደረቦቼ የደበደቡኝን አልረሳውም፡፡ እንደውም ሳስታውሰው ያስቀኛል፡፡ ሌላው ፖሊስ ሙዚቃ ክፍል ውስጥ እያለሁ የሚሊታሪ ልብስ እለብስ ነበር፤ ቅጥሬ ግን በሲቪል ነው፡፡ የሚሊታሪውን ልብስ ስለብስ ግን ከጀነራሉ የበለጠ ያምርብኛል፡፡ ሲያዩ የማእረግ ምልክት የለውም፤ ምንድነው ማእረግህ፤ “ኮሌኔል ባሻ” እላለሁ፡፡ ሌላውም ሲጠይቀኝ፤ “ኮሎኔል ባሻ” እላለሁ፡፡ ይሄ በሰራዊቱ ውስጥ የሌለ ማእረግ ነው፤ ግን እነሱ ይኑር አይኑር አያውቁትም፡፡
ይሄን የምለው ናቅፋ አልጌና እና አውራሮ ስሄድ ነው፡፡ ሌላ ጊዜ ሲጠይቁኝ፤ “አሁንማ ጀነራል ባሻ ሆኛለሁ” ስል አንድ ችኩል የሆነ ኮሎኔል አያሌው አበበ የሚባል አለቃ ነበረኝ፤ “ዝም በሉት፤ እንዲህ የሚባል ማእረግ የለም፤ እሱ ሲቪል ነው” ብሎ አዋረደኝ እልሻለሁ (ረጅም ሳቅ…)
ታዲያ ያኔ ጦር ሰራዊቱ አዲስ ማእረግ የመጣ እየመሰለው፤ “ጀነራል ባሻ” እያለ ወታደራዊ ሰላምታ ገጭ ያደርግልኛል፡፡ እኔም ምላሹን እሰጥ ነበር፡፡
አንዴ ደግሞ ሱዳን ሄጄ ሙቀቱ ሲያስቸግረኝ ሻወር ለመውሰድ ገንዳውን ውሃ ከፍቼ እየሞላሁ፣ እዚያው ባለሁበት እንቅልፍ ጭልጥ አድርጐ ወሰደኝ፡፡ ውሃው ከገንዳው አልፎ እስከ ውጭ ድረስ ይፈሳል ለካ፡፡ ሰራተኞቹ እንደምንም በመስታወት ተንጠራርተው ሲመለከቱ፣ ውሃው ውስጥ ተኝቻለሁ፡፡ “ወፍራም ሰው ገንዳ ውስጥ ሞቷል” ብለው መጮህ ጀመሩ፡፡ ከዚያ በሩን በሃይል ክፍት ሲያደርጉት፣ ብንን ብዬ ተነሳሁ፡፡ “አስደነገጥከን እኮ” ብለው ጮሁ፤ ይሄ ብሄራዊ ቴአትር ስሰራ ሱዳን ሄጄ ነው የተከሰተው፡፡
አሁን ከድሮ ጓደኞችህ ጋር ትገግኛለህ… ትጠያየቃለህ?
አዎ ከድሮ ጓደኞቼ ጋር አልፎ አልፎ እንጠያየቃለን፤ በተለይ ከመርአዊ ስጦት ጋር፡፡ ከግርማ፣ ከተስፋዬ አበበ፣ ከአፈወርቅ ጋር እንገናኛለን፡፡ ማህበርም አለን፤ በብሄራዊ ቴአትር በኩል፡፡ በግልም የሽማግሌዎች ማህበር አለን፡፡ እኔ ስላመመኝ ነው እንጂ በየወሩ ቅዳሜ ቅዳሜ እንገናኝ ነበር፡፡
በወጣትነትህ ምን አይነት ባህሪ ነበረህ? ለመጀመሪያ ጊዜ ትዳር የመሰረትከው በቅርብ ካረፉት ባለቤትህ ነው ወይስ?
እኔ በወጣትነቴ ሌላ ሚስት ነበረችኝ፡፡ የመጀመሪያው ትዳሬ ጥሩ አልነበረም፡፡ አሁን በቅርብ ካረፈችው ባለቤቴ ጋር ከተጋባን 55 አመታችን ነው፡፡ ከመጀመሪያው ትዳሬ ሦስቱ ልጆች ቢወለዱም አብዛኛዎቹ ከዚህችኛዋ የተወለዱ ናቸው፡፡ የጨዋ ቤተሰብ ልጅና መልካም ሴት ነበረች፤ መልክና ቁመናዋም ሌላ የሚያሳይ አልነበረም፡፡ ከሷ በኋላ ወደዚህም ወደዚያም ሳልል፣ በሰላምና በፍቅር ነው የኖርነው፤ ሞት ለያየን እንጂ፡፡ ብቻ ነፍሷን ይማረው፡፡በኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት፣ በደርግ አሁንም በኢህአዴግ … በሦስት መንግሥታት ኖረሃል፡፡ በእነዚህ ሦስት መንግስታት የሙዚቃ ሁኔታ… አጠቃላይ የስርአቶቹ ሂደት በአንተ አስተያየት ምን ይመስላል?
እኔ እንግዲህ ሽማግሌ እንደመሆኔ የአድርባይነት ወሬ አላወራሽም፡፡
ይህችን አገር በስልጣኔውም ሆነ በሁሉ ነገር መሰረት ያስያዟት አፄ ምኒልክ እና ኃይለስላሴ ናቸው፡፡ በኋላ መንግስቱ ኃይለማሪያም የሚባል አገር አጥፊ መጥቶ፣ አገሪቱን እንዳልነበረች አደረጋት፡፡ አሁን ብዙ ሰው “መንግስቱ የሀገር ፍቅር አለው” ብሎ ይከራከራል፤ አገሩን የሚወድ ሰው ያንን ሁሉ የአገሪቱን ምሁራን ሰብስቦ ይጨርሳል እንዴ? እሱ የሚወደው ራሱንና ስልጣኑን ነበር፡፡ ከዚያ አገር አጥፊ መቼም አንደኛውን ኢህአዴግ ይሻላል፡፡ እንግዲህ ኢህአዴግንም ሆነ ደርግን ብወድም ባልወድም መብቴ ነው ግን ኢህአዴግንም የምነቅፍበት ብዙ ጐኖች አሉኝ፡፡
ለምሳሌ?
ለምሳሌ ኤርትራን አስገንጥሎ አገሪቱን የባህር በር በማሳጣቱ፣ አንቀፅ 39ን አምጥቶ ህዝብ በመከፋፈሉ ቅር እሰኛለሁ፡፡ ከተማዋም ብትሆን በእቅድ ብትገነባ ጥሩ ነው፤ ህዝቡ አሁን በመቶ ብር አንድ ፌስታል እቃ አይሸምትም፤ ነፃ ገበያ እየተባለ ማንም የሚፈነጭባት አገር ሆናለች፡፡ ይሄ ይሄ ቢስተካከል ኢህአዴግ ጥሩ ይሆን ነበር፡፡
ምህረቱን ይስጥህ… ጋሽ ጌታቸው፡፡
አመሰግናለሁ፡፡ እናንተም አስታውሳችሁኝ ስለመጣችሁ አመሰግናለሁ፡፡ አሁን አሞኛል እኔ ያቅሜን ያህል አገሬንና ህዝቤን አገልግያለሁ፤ ህዝቡ ቢፈልግ ያሳክመኝ፤ አለበለዚያ ስሞት ይቅበረኝ፡፡ ይሄው ነው አመሰግናለሁ፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ

በጦማሪያኑ ላይ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ ማለቱን ሪፖርተር ገለፀ

$
0
0

12107780_1512167905763406_2572413332814840742_n
ከሚያዝያ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 18 ወራት በእስር ላይ የነበሩት ጦማሪያን፣ ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ.ም. የተመሠረተባቸውን የሽብር ድርጊት ወንጀል ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ተወሰነ፡፡

ከታሰሩ ጀምሮ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸውን ክስ ሲመረምር የከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ በነፃ እንዲሰናበቱና በዕለቱ እንዲፈቱ ትዕዛዝ የሰጠው ጦማሪያን አቤል ዋበላ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔና በሌለችበት የተከሰሰችው ሶሊያና ሽመልስ ናቸው፡፡ ጦማሪ በፈቃዱ ኃይሉ የተከሰሰበት የወንጀል ሕግ ተቀይሮ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን እንደገለጸው፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ያቀረባቸው የሰውም ሆኑ የሰነድ፣ የኦዲዮና ቪዲዮ ማስረጃዎች እንደ ክሱ የሚያስረዱ ሆነው አልተገኙም፡፡ ወይም ምንም ዓይነት ቅርርብ የላቸውም፡፡ በመሆኑም መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ብይን ሰጥቷል፡፡

ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ግን ለፖሊስ በሰጠው የተከሳሽነት ቃል፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት (ኢሕአዴግ) በምርጫ ወይም በሰላማዊ ትግል የሚወገድ ስላልሆነ፣ በሁከትና በሕዝባዊ አመፅ መወገድ አለበት፡፡ አምኜ እንደ ግብፅ ሁከትና ብጥብጥ በኢትዮጵያም እንዲከሰት ቀስቃሽ ጽሑፎችን ጽፌያለሁ፤›› ብሎ የእምነት ቃል መስጠቱን ፍርድ ቤቱ በንባብ አሰምቷል፡፡ ዓቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የሚያስረዱ ከኢንተርኔት ያቀረባቸው ጽሑፎችም፣ ተከሳሹ ለፖሊስ ከሰጠው ቃል ጋር ተያያዥነት እንዳላቸውና የሚደግፉ መሆናቸውን በመግለጽ እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ብይን ከሰማ በኋላ የተከሳሾች ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ፣ ተከላከል የተባለው ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ይከላከል የተባለበት የሕግ አንቀጽ ዋስትና ስለማይከለክለው፣ አቅሙን ያገናዘበ ዋስ እንዲፈቀድለት ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም በዋስትና ጉዳይ ላይ ተወያይቶ ለማሳወቅ ለጥቅምት 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በብይኑ ላይ ይግባኝ ስለማለቱ ተጠይቆ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ብይን እርስ በርሱ እንደሚጋጭ በመጠቆምና የተሰጠው ብይን የቀረበውን ማስረጃ ያላገናዘበና በአግባቡ ያልተመዘነ መሆኑን በመግለጽ፣ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለቱን አስታውቋል፡፡

ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ብይን በሚመለከት አስተያየታቸውን የሰጡት ጠበቃ አመሐ መኮንን ‹‹ብይኑ ከግለሰብ ችሎታ አንፃር ከታየ በበለጠ በተሻለ ሁኔታ መተንተን ይቻል ነበር፡፡ ከፍርድ ቤቱ አቅም አንፃር ግን ብይኑ ሚዛናዊ ነው፡፡ መረጃዎቹን ከሕጉ ጋር በደንብ አገናዝበው ሠርተውታል፡፡ በአጠቃላይ ጥሩ ብይን ነው፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ሥጋት እንዳላቸው የተናገሩት አቶ አመሐ፣ ሥጋታቸው ደግሞ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲሰናበቱ የሰጠውን ትዕዛዝ፣ ቀደም ብሎ በሌሎች ደንበኞቻቸው (እነ ሀብታሙ አያሌው) ላይ የተፈጸመው ዓይነት ድርጊት ይፈጸማል የሚለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ በዕለቱ እንዲፈቱ ካዘዘ በኋላ፣ የማረሚያ ቤት ኦፊሰር የማስፈቻ ትዕዛዝ ወስዶ ለሚመለከታት የማረሚያ ቤቱ ሠራተኛ መስጠቱን መረጃ እንዳላቸው የተናገሩት አቶ አመሐ፣ የማረሚያ ቤቱ ሠራተኛ በተደጋጋሚ ስትጠየቅ ‹‹አልደረሰኝም›› ማለቷንም መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም በፍርድ ቤት የተገኘውን መብት እንደገና የሚነፈግበት ወይም ሊነጠቅ የሚችልበት ዕድል ሊኖር እንደማይገባም አቶ አመሐ አስረድተዋል፡፡ ከአራትና ከአምስት ለማይበልጡ ጉዳዮች የፍትሕ ሥርዓቱን በጠረባ እየመቱ መጣል ለማንም እንደማይጠቅምም አክለዋል፡፡ ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ጥቅምት 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ሌሊት ድረስ ጦማሪያኑ አለመፈታታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ምንጭ ሪፖርተር

ጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ በ20 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቅ ተወሰነ

$
0
0

12170404_1031991300165872_317411867_n
ጥቅምት 5/2008 አራቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን በነፃ እንዲለቀቁ ሲወሰን በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 257/ሀ እንዲከላከል የተባለው በፍቃዱ ሀይሉ የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ጠይቆ በነበረው መሰረት ለዛሬ ጥቅምት 10/2008 ዓ.ም የዋስትናውን ጉዳይ ለማየት ቀጠሮ የሰጠው የልደታ ፍርድ ቤት በ20 ሺህ ብር ዋስ ወጥቶ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል ወስኗል፡፡
ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት በፍቃዱ ሀይሉ ከእስር ቤት አልወጣም።

ፍትሕን በብሔር ግንኙነት የሚሸጡና ለወሲብ ድርድር የሚያቀርቡ ሙያተኞች እንዳሉ ተነገረ

$
0
0

ከፖሊስና ከማረሚያ ቤት በበለጠ ፍርድ ቤት ለሙስና የተጋለጠ መሆኑ ተጠቆመ

በኢትዮጵያ የፍትሕ ተቋማት ውስጥ ሙያዊ ሥነ ምግባራቸውን ጠብቀው ሕዝባዊ ኃላፊነታቸውን የሚወጡ ታማኝ የፍትሕ ባለሙያዎች ያሉትን ያህል፣ ፍትሕን በገንዘብ የሚቸበችቡ፣ የተሰጣቸውን የሙያ ሥነ ምግባር ዘንግተው ዳኝነትና

ፍትሕን በአገር ልጅነት ወይም በብሔር ግንኙነት የሚሸጡና ለወሲብ ድርድር የሚያቀርቡ እንዳሉ ተነገረ፡፡
d11be8ab966081bf919d3439c92cfca1_L
የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ ጥቅምት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ‹‹በኢትዮጵያ ፍትሕ ዘርፍ ሙስናን ለመከላከል የሚያስችሉ፣ የፍትሕ ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥና አፈጻጸም አመላካቾች›› በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፣ የተወሰኑ በፍትሕ ተቋማት ውስጥ ያሉ ሙያተኞች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ የሚገኙና ሙስና የሚፈጽሙ ናቸው፡፡ ሙስና በተንሰራፋበት በፍትሕ መድረክ ላይ ዜጐች በእኩልነት አይስተናገዱም፡፡ በተለይም ለነፃ ገበያ ዋነኛ መሠረት የሆነው የኮንትራት አስተዳደር ከቅጥፈት፣ ከአድልዎና ከአላስፈላጊ ባህሪዎች ነፃ ሆኖ ዳኝነት መስጠት በማይቻለበት ሁኔታ፣ አገሪቱ የምትመኘውን የኢኮኖሚ ዕድገትና የሚታሰበውን ያህል ኢንቨስተሮችን መሳብ እንደማይቻል ኮሚሽነሩ አብራርተዋል፡፡ ይኼንን እውነታም ሕዝቡ ጠንቅቆ እንደሚያውቀው አክለዋል፡፡

ሙስናን የመታገያው የመጨረሻው መተማመኛ ተቋም የፍትሕ ሥርዓቱ በሙስና ከተፍረከረከ፣ አጠቃላይ የፀረ ሙስና ትግሉ አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር መሆኑን አቶ ዓሊ አስረድተዋል፡፡ የፍትሕ ተቋማት ከዘርፈ ብዙ የሙስና ዓይነቶች ካልፀዱ፣ አሠራራቸው ለሕዝብ ግልጽ ካልሆነ፣ በሕግ ከተቀመጠው የአሠራር ሥርዓት ያፈነገጡ በሕግ ተጠያቂ ካልሆኑ፣ ችግሩ በፍትሕ ተቋማት ብቻ እንደማይፈታና ወደ አገራዊ አደጋ እንደሚሸጋገር ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽነሩ እንዳሉት፣ ሕግ መተርጐም ለዳኞች የተሰጠ ኃላፊነት ነው፡፡ ነገር ግን ዳኞች ሕግን በነፃነት እንዳይተረጉሙ ለሕዝብ ተቆርቋሪ በመምሰል የግል ፍላጐትን ለማሟላት በዳኝነት ሥራ ላይ የሚደረገው ጣልቃ ገብነት ሊወገድ ይገባል፡፡ የኮሚሽነር ዓሊን ንግግር ተከትሎ በፍትሕና ሕግ ሥርዓት ምርምር ኢንስቲትዩት ባልደረቦች ከላይ በተገለጸው ርዕስ ያዘጋጁትን ጥናት አቅርበዋል፡፡

ወ/ሪት ማዕረግ ገብረ እግዚአብሔር፣ አቶ አሮን ደጐልና ዶ/ር ደጀኔ ግርማ የተባሉት የጥናቱ አቅራቢዎች፣ ጥናታቸውን ያደረጉት ለሙስና ዋና ተጋላጭ ናቸው ባሏቸው ፍርድ ቤት፣ ዓቃቤ ሕግ፣ ፖሊስና ማረሚያ ቤቶች ላይ ነው፡፡ ጥናቱ ከድሬዳዋ ውጪ በቆዳ ስፋታቸውና በሕዝብ ብዛታቸው ቀዳሚ ናቸው ያሏቸውን ኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ ክልሎች፣ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና የፍትሕ አካላትን ማካተታቸውን አስረድተዋል፡፡

ዋና ዋና ያሉዋቸው አራቱ የፍትሕ አካላት ሊፈጽሟቸው የሚችሉ የሙስና ድርጊቶች ጉቦ፣ ሥራን መበደል፣ ምዝበራ፣ በሥልጣን መነገድና የማይገባ ሀብት ማካበት መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የፍትሕ አካላቱ ለሙስና ተጋላጭ የሚያደርጓቸው ምክንያቶች ዕውቀትና ክህሎት ማነስ፣ የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ማነስ፣ ነፃና ገለልተኛ አለመሆን፣ ሰፊ ሥልጣን መኖር፣ ግልጽ የሆነ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት አለመኖር በዋናነት የገለጿቸው ናቸው፡፡

ከወንጀለኞች ጋር በቅርበት መሥራት፣ ለኃላፊዎች ያላቸው መታየት ዝቅተኛ መሆን፣ ወንድማማችነት (ጥፋትን መሸፋፈን)፣ ተግባራቸው ለሕዝብ ግልጽ አለመሆን፣ ፖሊሶችን ለሙስና ከሚያጋልጡ ምክንያቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የማረሚያ ቤቶች ጥበት፣ በታራሚዎች አያያዝ ላይ የሠራተኞቹ ግንዛቤ አናሳ መሆን፣ የማረሚያ ቤት ሠራተኞች ለሕግ ተገዢ አለመሆን፣ የጥበቃ ሠራተኞች ከታራሚዎች ጋር የሚፈጥሩት ከሙያ ውጪ የሆነ ቅርበትና ወዳጅነት ደግሞ ማረሚያ ቤትን ለሙስና ተጋላጭ ከሚያደርጉት ምክንያቶች ጥቂቶቹ መሆናቸውን ጥናት አቅራቢዎቹ ገልጸዋል፡፡

የፍርድ ቤትን አሠራር ቀልጣፋ ማድረግ፣ የፍርድ ቤት ሠራተኞችን ሥነ ምግባር ማሻሻል፣ ተጠያቂነትን ማረጋገጥ፣ ግልጽ አሠራር ማጐልበት፣ የዳኝነትን ነፃነት ማረጋገጥ፣ ከገቢ ጋር ተያያዢነት ያላቸውን ለሙስና የሚያጋልጡ ምክንያቶችን ማስወገድ፣ ተቋማትን ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ማደራጀት፣ የመረጃና የሰነድ አያያዝ ሥርዓት ማጠናከር፣ የክትትል ሥርዓት መዘርጋት፣ የጥቅም ግጭት ማስወገድና ሌሎችንም ለሙስና በር የሚከፍቱ ምክንያቶች በጥናቱ መለየታቸውን አቅራቢዎቹ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር፣ የፌደራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የዓቃቤ ሕግና የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች የቀረበውን ጥናት አድንቀው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ምንጭ ሪፖርተር ተጻፈ በ ታምሩ ጽጌ

“ከቤት ኪራይ ባሻገ…” (ተወልደ “ተቦርነ” በየነ)

$
0
0

804639_1514132968900777_437236521_n
ሰሞኑን ጋዜጠኛ አርአያ ተ/ማርያም አንዲት አጭር ማስታወሻ በገጹ ላይ ከትቦ ተመለከትኩ። ጋዜጠኛ አርአያ በዲሲና እና አከባቢዋ በሚገኙ ጉራንጉሮች እየቃረመ የሚያስነብበን የተለያዩ ገጠመኞች ናቸው። እርግጥ አብዛኞቹ በግለሰብ ማንነትና ስብእና ያተኮሩ ቢሆንም በሀገረ አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጲያውያን ሌላኛውን ገጽታ ለማሳየት ይጠቅማሉ ። በተለይ ሀገራችንን በወያኔ ተቀምተን ስደትን እንደአማራጭ የወሰድን ኢትዮጲያውያን “ትልቁን – ስዕል” እንዳንረሳ ከእነዚህ ውድቅዳቂ ገጠመኞች ማወቅ እንደሚጠቅመን አስባለሁ። ጋዜጠኛ አርአያም በአደገኛ ቦታዎች እየተሹለከለከ የሚያቀርበውን “ግለሰባዊ” ታሪኮች ቢገፋበት የሚያስከፋ አይደለም። እርግጥ አብዛኛው ሰው “የመንደር ወሬ” እያለ ቢያጣጥለውም እኔ ግን ከምንም ይሻላል የሚል አስተያየት አለኝ። አንዳንዶች ደግሞ “አርአያ አልቆበታል” ሲሉ ይደመጣሉ። ይህም ቢሆን ምላሹ ያለው ራሱ ጋዜጠኛው ጋር ስለሆነ ገፍቼ ልከራከር አልችልም።
በሌላ በኩል ሀገሩን በጥቂት የወያኔ ጉጅሌውች የተቀማው አብዛኛው ኢትዮጲያዊ ጋዜጠኛው ከቃረማቸው አከባቢዎች ውሎ የሚያድር አለመሆኑን መገንዘብ ያሻል። በሀገራቸው የመስራት እድል የተነፈጋቸው ኢትዮጲያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ኑሮን ለማሸነፍ የሚተጉ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። በሀገር አሜሪካን የኢትዮጲያውያን አንዱ መታወቂያም የስራ ትጋታቸው እና ፍላጎታቸው መሆኑ ምስክር የሚያሻው አይደለም። በመሆኑም የዋሽንግተን ዲሲ ደቡባዊ ምስራቅ የሚገኙ አደገኛ ቦታዎች የሚውሉና የሚያዘወትሩ ጥቂት ኢትዮጲያውያን በመሆናቸው ብዙሃንን እንደማይወክሉ መገንዘብ ያሻል።
ይህ እውነት እንደተጠበቀ ሆኖ አንዳንዶች በአቋራጭ መንገድ ኑሮአቸውን ለመግፋት የሚፈልጉ ኢትዮጲያውያን አልታጡም። አቋራጭ መንገድ በራሱ መጥፎ አይደለም። ቢሆንም የምቆምበትን “ኢትዮጲያዊ ምሶሶ” በሚንዱ ተግባራት ላይ የሚመሰረት ከሆነ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም።
እንደሚታወቀው አገዛዙ ኢትዮጲያዊነትን ለማጥፋት “ህወሀታዊ ፓሊሲ” ነድፎ ቀን ከሌት እየተጋ ነው። በምንወዳት ሀገራችን ውስጥ ኢትዮጲያዊ ምልክት የሆኑ እሴቶች እየተሸረሸሩ የግለሰቦች መጫወቻና መወደሻ እየሆኑ መሄዳቸው በግልጽ እየታየ ነው። ትላንትና አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ኢትዮጲያዊ በዓል በዓል እንዲሸት የሚያደርጉት እነ ብሔራዊ እና ሀገር ፍቅር ቲአትር ቤቶች እንዲደበዝዙ ተደርገው የበአሉ ድምቀት ወሳኞቹ ግለሰቦችና ሆቴላቸው ሆኗል። ኢትዮጲያዊ አንጋፋ አርቲስቶች ወደጎን ተገፍተው (አሊያም ለባለጊዜው እንዲያድሩ ተደርገው) በደጋፊነት የሚታዩበት በዋናነት ደግሞ ከምዕራቡ አለም በዶላር ተገዝተው የሚመጡ ባህላችንን በቅጡ የማያውቁ የሚጨፍሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጲያዊ ኩራታችን እና ክብራችን ማሳያ የሆኑት ገድሎች እየቀሩ በሌላ ማንነታችን በማይገልጹ ታሪኮች እየተተካ ነው። ዛሬ በኢትዮጲያ ምድር ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እየተደረገ የሚከበረው የካቲት 11 እንጂ የካቲት 23 አይደለም። ደደቢት አድዋን ተክቶታል። ዛሬ በኢትዮጲያ ምድር ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ እየወጣ እንዲከበር የሚደረገው ሚያዚያ 27 ሳይሆን ህዳር 11 ሆኗል። ድላችንን የወያኔ የበኩር ልጅ የሆነው ብአዴን ተክቶታል። እውነተኛ ታሪክ እየተፋቀ አዲስ ታሪክ እየተዳፈነ ነው። ኢትዮጲያዊነት የሚታይባቸው ተቋማት እየተሸረሸሩ የቡድኖችና የዘመናችን ባለ ገንዘቦች መጨፈሪያ ሆነዋል።
ሆኖም ግን ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጪ ባሉ ቦታዎች እንዲህ አይነት ሁኔታ እንዳይፈጠር ኢትዮጲያውያን በእልህና ቁጣ እየተንቀሳቀሱ ነው። ከዚህ አንጻር ኢትዮጲያውያን “በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጲያውያን የባህልና ስፖርት ፌስቲቫል” የሚባለው ቅርስ በጠላቶች እጅ እንዳይወድቅ የሚያደርጉት የሞት ሽረት ትግል በምሳሌ የሚታይ ነው። ይህ የአንድነታችን እና ነጻነታችን አርማ የሆነ ፌስቲቫል በባለገንዘቦች እንዳይከፋፈል ኢትዮጲያውያን ጥረት በሚያደርጉበት ሰዓት ከከፋፋዮች ጋር መሠለፍ ወይም መሳተፍ ከዘመናዊ ባንዳነት የማይተናነስ ሀቅ ነው። “የቤት ክራይ እና የኑሮ ወጪዎች” እንደ አመክንዮ በማቅረብ አሊያም በእነሱ ድግስ ብገኝም “ባለገንዘቡን እና ባለራዕዩን አላወደስኩም” የሚል ወንዝ የማይሻገሩ ምክንያቶች የሚያስኬድ አይደለም። በእንደዚህ አይነት ፀረ- ኢትዮጲያዊ ተግባራት ከጊዜያዊ ድለላዎችና ጥቅማ ጥቅሞች በመነሳት የሚሳተፉ ኢትዮጲያውያን ሊያፍሩ ይገባል። ሊፀፀቱ ይገባል። እውነትም ሊሸማቀቁ ይገባል። እነዚህ ግለሰቦች ማህበረሠቡ ያገለላቸው የነፃነት አርማውን፣ ከትውልድ ትውልድ ሊያስተላልፍ የሚፈልገውን ቅርስ እና የኢትዮጲያዊነት ህልውናውን ሊነጥቁ ቀን ከሌት ከሚተጉ ቡድኖችና ባለ-ገንዘቦች ጋር በመተባበራቸው ምክንያት ብቻና ብቻ ነው።
ጋዜጠኛ አርአያም ትልቁን ስዕል ትቶ ማሞና መታወቂያውን ለማዛመድ የሄደበት አካሄድ ትክክል የማይሆነው በዚህ ምክንያት ነው። እንደ ግለሰብ በሸራተን መዝፈንም ሆነ በባለ ገንዘቦች ክርን ስር መውደቅ የምደግፈው አይደለም። ነገር ግን “ኢ. ኤስ. ኤፍ. ኤን. ኤ.“ እና ሸራተን አንድ አይደሉም። ለምክንያት እና መንስኤ ማነጻጸሪያ ሊሆኑ አይችሉም። ሸራተን የዘፈነ ሁሉ አልተወገዘም። ይወገዝም አልተባለም።
በተረፈ ጋዜጠኛ አርአያ “ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው” እንዲሉ በእኔና በሰይፉ ፋንታሁን መካከል ያለውን ግኑኝነት በድፍረት መግለጽ መሞከሩ ሳያስገርመኝ አልቀረም። ያቀረባቸው መረጃዎች የጋዜጠኛውን የዛሬ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ትላንትና እና ነገን እንድጠራጠር አድርጎኛል። ፈጣሪ ለአሉባልታ እሩቅ፣ ለመረጃ ቅርብ ያድርገን እንዲሉ:

ቴዲ አፍሮና ጎሳዬ ተስፋዬ ለምስጋና ቀን ይዘፍናሉ!

$
0
0

12178226_1032887753409560_1643712093_n
በሰሜን አሜሪካው የኢትዮጵያዊያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ላይ ከተዘጋጅት የሙዚቃ ዝግጅቶች መካከል በጉጉት ተጠብቆ በቪዛ ምክንያት ሳይደረግ የቀረው የቴዲ አፎሮና የጎሳዬ ተስፋዬ የሙዚቃ ኮንሰርት በምስጋና ቀን ለመጀመርያ ግዜ ሊደረግ ነው።
አሜሪካኖቹ Thanksgiving በሚሉት (የምስጋና ቀን ) አመት በዓላቸው ዋዜማ Nov.25.2015 በአትላንታ የተዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ዝግጅት መጀመሩን የኮንሰርቱ አዘጋጆች ለቃልኪዳን ትዩብ የገለጹ ሲሆን፤ቴዲና ጎሳዬን ለመጀመርያ ግዜ በአንድ መድረክ ሲዘፍኑ ለመመልከት በርካቶች ይገኛሉ ተብሎ ተገምቷል።

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንደሌሉ ገለፀ

$
0
0

kalkidantube.com38
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ -5ኛ መዝገብ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሱት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንደሌሉ ማረሚያ ቤቱ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛው ወንጀል ችሎት በላከው ደብዳቤ ገልፆአል፡፡ 19ኛ ወንጀል ችሎት ሀምሌ 29/2007 ዓ.ም የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸውን ለምን እንዳላቀረበ እንዲያብራራ፣ እንዲሁም ለምስክርነት እንዲያቀርብ ለዛሬ ለጥቅምት 12/2008 ዓ.ም ለአራተኛ ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ቃሊቲ እንደሌሉ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡
ተከሳሾቹ ማረሚያ ቤቱ ሲያጉላላቸው ቆይቶ አሁን የለም ማለቱ ትክክል እንዳልሆነ የገለፁ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ አቶ አሸናፊ አካሉ ማረሚያ ቤቱ ምላሽ የሰጠው በአራተኛው ትዕዛዝ መሆኑን ጠቅሶ የፍርድ ሂደታቸውን ከሚገባው በላይ እያጓተተ እንደሆነ ለፍርድ ቤቱ ገልፆአል፡፡ ‹‹መከላከል ከጀመርን አንድ አመት ከስድስት ወር ሆነ፡፡ በግዞት ነው ያለነው፡፡ የሚቀርብልን ምግብ ለእንሰሳትም መቅረብ የማይገባው ነው›› ያለው አቶ አሸናፊ የማረሚያ ቤቱን ምላሽ ‹‹ፌዝ ነው›› ብሎታል፡፡
3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛ በበኩሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በመከላከያ ምስክርነት ሲጠቅሱ አቃቤ ህግ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኛ እንደሆኑ በመጠቆም ተቃውሞ አሰምቶ እንደነበር፣ የእድሜ ልክና የሞት ፍርደኛ ቃሊቲ እንደሚታሰር ገልፆ ማረሚያ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው እንደሌሉ መግለፁ ‹‹የስርዓቱን ሽፍትነት ያመላክታል›› ብሏል፡፡ ‹‹የእድሜ ልክ ወይንም የሞት ፍርደኛ የት ነው የሚታሰረው?›› ሲልም ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡
3ቱ ተከሳሾች የፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉና ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ አንዳርጋቸውን እንደያዙ በቴሊቪዥን መግለፃቸውን አስታውሰው አሁንም ለሁለቱ አካላት ደብዳቤ እንደሚፅፉ ለፍርድ ቤቱ አሳውቀው የነበር ቢሆንም ከ6ኛ-9ኛ ያሉት ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ በፈጠረው ችግር የአቶ አንዳርጋቸውን ምስክርነት ለመስማት የፍርድ ሂደታቸው እየተጓተተባቸው በመሆኑ የአቶ አንዳርጋቸው ምስክርነት ቀርቶ ብይን እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
ሆኖም ግን 4ኛ ተከሳሽ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተህ መመሪያ ተቀብለሃል ስለተባልኩ አቶ አንዳርጋቸው መጥቶ መመስከር አለበት›› ሲል አሁንም አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡለት ጥያቄውን አቅርቧል፡፡ ፍርድ ቤቱም 4ኛ ተከሳሽ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲቀርቡለት የሚያቀርበውን አቤቱታ ተመልክቶ ይገኙበታል ተብሎ ለታሰበው ተቋም ትዕዛዝ ለመስጠት ለጥቅምት 23/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ምንጭ በነገረ ኢትዮጵያ


ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ”ክሱ የሕትመት ውጤቶቹን ለመዝጋት ታስቦ የነበረና ያለአግባብ የተመሠረተ ነው”ቃለምልልስ-VOA Amharic

$
0
0

የሎሚ” መፅሔት አሳታሚ የሆነው ዳዲሞስ ኢንተርቴይመንት እና የፕሬስ ሥራዎች ድርጅትና ሥራ አስኪያጁ በጋዜጠኛ ግዛው ታዬ ላይ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የገንዘብና የእሥራት ፍርድ ካስተላለፈ በኃላ ቪኦኤ ግዛውን አነጋግሮታል፤

ፍርዱ በሌለበት የተላለፈበት ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ “ሲጀመርም ሆን ተብሎ የሕትመት ውጤቶቹን ለመዝጋት ታስቦ የነበረና ያለአግባብ የተመሠረተ ክሥ ነበር እራሳቸው የዘጉትን ድርጅት ከአመት በኃላ ሁለት መቶ ሺህ ብር ቀጥተነዋል ማለት ፌዝ ነው ብሏል።ሙሉ ቃለምልልሱን ያዳምጡ።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቤተሰብ እንዳይጎበኝና ስንቅ እንዳይገባለት ተከለከለ- VOA Amharic

$
0
0

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቤተሰብ እንዳይጎበኝና ስንቅ እንዳይገባለት ተከለከለ..በእሥር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቤተሰብ እንዳይጎበኝና ስንቅ እንዳይገባለት መከልከሉን ወንድሙና ጠበቃው ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገለጹ።ሙሉ መረጃውን ያድምጡ።..ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቤተሰብ እንዳይጎበኝና ስንቅ እንዳይገባለት ተከለከለ

የተባበሩት መንግስታት በኤርትራ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለአንድ ዓመት አራዘመ-VOA Amharic

$
0
0

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ከዚህ በፊት በኤርትራ ላይ የቆየውን ማዕቀብ የሚያጠብቅ ውሳኔ መውሰዱ ይታወሳል። በትናንትናው ምሽት ማዕቀቡ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም የጸጥታው ምክር ቤቱ መወሰኑ ታውቋል።

የውሳኔው መዝገብ ከዚህ በፊት በቀረቡት ክሶች ላይ ተመርኩዞ ሲሆን፣ ኤርትራ አል-ሸባብን ትደግፋለች፣ ከጅቡቲ ጋር ያልቋጨችው የድንበር ጉዳይ አለ፣ ማለትም በእአአ 2008 ያሰረቻቸውን ወታደሮች የመፍታት ክሶችን ያጠቃልላል።

የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ እንግሊዛዊው አምባሳደር ማትው ራይክፍርት (Mathew Rycroft) ውሳኔውን እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል።

“የኤርትራና የሶማልያን ጉዳይ በተመለከተ ለየጸጥታ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት እንደተገለጸው፣ ከዚህ በፊት ተጽፎ ለውሳኔ በቀረበው የሃሳብ ሰነድ S/2015/810 ድምጽ ለመስጠት የምትፈልጉ እጃቹን አንሱ። የድምጽ አሰጣጡ ውሳኔ ይህንን ይመስላል፣ 14ቱ በመደገፍ ድምጻቸውን ሲሰጡ፣ የተቃወመ የለም። 1 ድምጸ ተአቅቦ አድርጓል። ረቂቅ ሰነዱ 22/44በመባል አልፏል” ብለው ገልጸዋል።

የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ውሳኔውን ህግ የጣሰነ ነው በማለት አጣጥሎታል። ዝርዝሩን ከቪኦኤ ያዳምጡ።

“ ታዳጊዋ የኖቤል ተሸላሚ ማላላ ወደ አደባባይ እንድወጣ አድርጋኛለች” የወሲብ ተጠቂዋ አበራሽ በቀለ( ከ አውሮፓ)-ታምሩ ገዳ

$
0
0

ስለሴቶች መብት መከበር ፋና ወጊ የሆነው “ድፍረት” ሲኒማ ከአሜሪካ ሲኔማ ቤቶች ገባ
12188831_1514914768822597_1961748752_n
ከሁለት አስር አመት በፊት ትምህርት ቀሰማ ቤተሰቧን አና ማህበረሰቧን ለመረዳት ህልም የነበራት ፣ ነገር ግን ሕልሞቿ ሁሉ በጉልበተኞች ሰለተ ጨናገፉባት አንዲት ኢትዮጵያዊት ልጃገረድ አበራሽ በቀለ ( የሲኒማዋ ሂሩት) ላይ ሰለ ደረሰ የጠለፋ ጋብቻ ፣ወጣቷም በጠላፊዋ ላይ ሰለ ወሰደችው እርምጃ፣ በወቅቱ ሰልነበረው የባህል የማሕበረሰብ አመለካከት እና የህግ አግባብ እና የወጣቷዋን ሕይወት ከሕግ ክፈተተ እና ከኋላቀር አሰተሳሰብ ሰለባነት ለመታደግ የተከፈለውን አስቸጋሪ ውጣ ውረድ እና ነጻነቷን እንዲት አንዳገኘች እና መሰል ጉዳዮች ዙሪያ የሚያውጠነጥነው እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘው “ድፍረት” የተሰኘው ሲኒማ ከኢትዮጵያዊያን ተመልካቾች አና ሲኒማ ቤቶች አልፎ ከአርብ ጥቅምት 23 2015 አኤአ ጀምሮ በ አሜሪካ ሲኒማ ቤቶች (ኔዮርክ ላይ )መታየት ጀምሯል። በቅርቡም በተለያዩ ከተሞችም የታያል ተብሎ ይጠበቃል።
እውቋ የ ሆሊውድ ሲኒማ ተዋኒት ፣ዳይሬክተር ፣ጸሀፊት እና የስብእና አምባሳደር አንጀሊና ጁሌ አሻራዎች ያለበት ፣በኢትዮጵያዊው ደራሲ እና ዳይሬክተር እና ተሸላሚው ዘረሰናይ ብርሃኔ መሃሪ ተደረሶ ፣እነ ሜሮን ጌትነት ፣ሞገስ ዮሃንስ ፡ትዘታ ሃገሬ ፣ሽታዮ አብረሃ፣ ግርማ ተሾመ የመሳሰሉት ሰመ ጥር አርቲስቶች የተካተቱበት “ ድፈርት “ ሲኒማ 1 ሰእት ከ 39 ደቂቃዎች የሚፈጅ ሲሆን ሲኒማውን በተመለከተ በረካታ የምእራባዊያን ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን እየሰጡት ይገኛሉ።
የሲኒማው ዋንኛ ባለ ታሪክ የሆነችው አበራሽ በቀለ አኤአ በ 1996 የደረሰባት አስገድዶ መጠልፍ ፣ጥጠላፊዋን በገዛ ጠምንጃው በመግደል ወንጀል ለእስራት መዳረጉዋ ፣ የሲቶች የህግ ባለሙያዋች ማህበር ሊቀመንበር መሰራች የሆኑት ወ/ሮ መአዛ አሽናፊ በግላቸው አና በደረጅታቸው ባደረጉት ጣልቃ ገብነት የሞት ቅጣት ይጠብቃት የነበርቸው ወጣቷ አበራሽ ከሁለት አመት ውጣውረድ በሁዋላ የግድያ እርምጃውን የወሰደችው እራሷን ለመከላከል በሚል ውሳኔ በነጻ መሰናበቷ አንዳንድ የወንድ የበላይነት አቀንቃኞችን ያስቆጣ ቢሆንም በተቃራኒው ለወትሮው ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ህጻናትን ጠልፎ ካገባ “አበጅህ” የሚያስብለውን በኢትዮጵያ ውስጥ የቆየውን ኋላ ቀር ጎጂ ባህል እና የሕግ ክፍተትን እንዲፈተሽ እና በአሁኑ ወቅት የድርጊቲ ፈጻሚዎች እሰከ 15 አመት የሚደረስ እሰራት እንዲ በየንባቸው የሚያስችል መንገድ ከፍቷል።
የሕግ ባለሙያዋ ወ/ሮ መአዛም በበኩላቸው በአንድ ወቅት ስለ አበራሽ ሲናገሩ”አበራሽ በኢትዮጵያ ውስጥ በ አንዳንድ ሕገወጥ ወንዶች የሚደርሰው ጾታዊ ትንኮሳን በመጋፈጥ እና ድል በማድረግ የመጀመሪያዋ ሴት አብዮተኛ ነች ።”ሲሉ ለአበራሽ ያላቸውን ልዩ አክብሮት ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የጋብቻ ሕግ መሰረት አንድ ሴት ልጅ ከ 18 አመት በፊት ማግባት እንደማይፈቀደላት የሚደነግግ ሲሆን ችግሩ ሙሉ በሙሉ እንዳለተወገደ መረጃዎች ይገልጻሉ ።ከ 2002 እስከ 2012 ባሉት ጊዜያት 16%ልጃገረዶች እድሜያቸው ከ 15 በታች ሳለ እንደሚያገቡ እና 40% ደግሞ 10 አመታቸውን ሳይጨርሱ ትዳር ይይዛሉ ተብሏል። በአሁኑ ወቅት በደቡብ ኢትዮጵያ ከ6 ልጃገረዶች መካከል አንዷ ሰትጠልፍ በ ሰሜን ኢትዮጵያ ደግሞ ከ 20 ልጃገረዶች መካከል አንዷ እነደምትጠለፍ ኦፊሴላዊ መረጃዎች ይገልጻሉ።
ከጠላፊዎቿ ቤተሰቦች ብቀላ እንዳይ ደረሰባት በመሰጋት እና ከህግ በላይ ተሰሚነት እንዳለቸው በሚታመኑት የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች ግፊት ሳቢያ አዲስ አበባ ውስጥ ለመደበቅ የተገደደችው አበራሽ በሁዋላም ወደ ምእራብ አውሮፓ ( ደብሊን አይር ላንድ) ተሰዳ ኑሮዋን እየገፋች ሲሆን ስለ ደረስባት አሳዛኝ ገጠመኝ በተመለከተ ለዜና ሮይተርስ በ ኢሜል በሰጠችው ምላሽ”ከዚህ ቀደም እራሴን ደብቄ መኖርን መርጪ ነበር።አሁን ግን በዚህ ሲኒማ (ድፍረት)አማካኝነት እና በፓኪስታናዊቷ የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዋ ማላላ ዮሳፊዝ (እንዳትማር ማእቀብ የጣሉባት አክራሪ ታሊባኖችን አሻፈረኝ በማለቷ በ2012 አኤ አ የ 14 አመት ወጣት ሳለች የግድያ ሙከራ የተደረገባት እና በተአምር የዳነች ታዳጊ ነች)የእኔንም ብሶት ወደ አደባባይ ወጥቼ አንዳስተምር አነቃቅቶኛል።” ብላለች። ሲኒማው “ደፈርት” ከከተማዎች አልፎ ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ቢዘልቅ የብዙ ሴቶች ህይወትን ይታደጋል ፣ትልቅ ሰኬት ኣንደሚሆን ምኞቱዋንም ገልጻለች። አበራሽ ሪፋይነሪ 29 ለተባለው ደሀረገጽ በኣስተርጓሚ በሰጠችው አስተያየት “አንድ ቀደም ሲል ያልተሞከረ ነገረን መተግበር ቀላል አይደለም። ይሁን እና ያነን መጥፎ ገጠምኝን ወደአስተማሪነት መልክ መለወጥ መቻሉ አስደስቶኛል ።”ብላለች። አበራሽ ሴቶች ለሴቶች (Women to Women) የተሰኘ አገር በቀል ድርጅት በማቋቋም ለወገኖቿ ለማገልገል ጥረት እያደረገች መሆኑዋን አስታውቃለች። በአማሪኛ ቋንቋ (በደምጽ) እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ (በጽሁፍ የታጀበው) “ድፍረት” ሲኒማ በ ኢትዮጵያ ውስጥ በመታየት ላይ ሲሆን “ድፍረት”የሚለው ቃል በአማሪኛ ሁለት ትርጉሞች ያለው ሲሆን አንደኛው የወሲባዊ ጥቃት ሰለባነትን ሲገልጽ ሁለተኛው ደግሞ ቆራጥነትን ያመለክታል።
ከዚህ ቀደም ከ ኢትዮጵያ አንዲት ሴት ልጅን (ዘሃራ) በጉድፊቻ መልክ በመውሰድ ኢትዮጵያዊ ቁርኝት የፈጠረችው ታዋቂዋ የሰኒማ ባለሙያ አንጀሊና ጁሊ በበኩሏ “ሲኔማው ለአኢትዮጵያ ኪነጥበብ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።ኢትዮጵያ የሚያኮራ ታሪክ እንዳላት ሁሉ ከ ኢትዮጵያ ውጪ የጾታ መደፈር ለሚደረሰባቸው ሴቶች የሚከፈሉት ቆራጣነትን ያሳያል፣ ለሴቶች መብት መከበር ተስፋ ይሰጣል ፣ያሰተምራልም።”ብላለች።
በዚህ ታላቅ እና አለማቀፍ እውቅና ባገኘው “ድፍረት” ሲኒማ ላይ እውነተኛ ባለታሪኳ የሆነችው አበርሽ በቀለ ብትካተትበት ኖሮ ፊልሙን የበልጥ ተወዳጅ እና ቀልብ ሳቢ እንደሚያደረገው የሚተቹ የኪነጥበብ ቤተሰቦች አልታጡም። የሲኒማው ዳይሬክተሩ ዘረ ሰናይ ብርሃኔ አበርሽ በቀለን በመግኘት በሲኒማው ውስጥ ለማካተት የደረገው ተደጋጋሚ ሙከራዎች እንዳልተሳኩ እና በእርሷ ፋንታ “ሂሩት “የሚል ዋንኛ የገጸባህሪ ስም ለመሰጠት መገደዱን ይናገራል። “ድፍረት” ሲኒማ በቅርቡ በአሜሪካው ኦታዋ ግዛት በተደረገው አመታዊ የሳንዳንስ ሲኒማ ፊስቲቫል እና በ ጀርመን (በሪሊን )የሲኒማ ፊስቲቫል ላይ ቀርቦ ከ 200 በላይ የተለያዩ ሲኒማዎች በልጦ በመገኘቱ ተሸልሟል።

ጌታቸው ይመር (አሌክስ አብርሀም) እና ያልተገራ “ፈረሱ”ከኢብራሂም ሻፊ አህመድ

$
0
0

የዓለማችን ሁለተኛው ጸረ ፕሬስ መንግስት የሆነው ኢህአዴግ ጋዜጠኞችን እስር ቤት በማጎር የሚረካ አልሆነም። እናም ከጥቂት ተልመጥማጭ የህትመት ውጤቶች በቀር የሰላ ሂስ በማቅረብ የሚታወቁትን ጋዜጣና መጽሄቶች በጉልበት ዘግቶ ጋዜጠኞችንም ለስደት ዳረገ። የረጂዎቹ ምዕራባውያን በትር እስኪያርፍበት።

አምባገነኑ አገዛዝ ከዓመት በኋላ ደግሞ የበቀል በትሩን በመምዘዝ… በተሰደዱ ጋዜጠኞች ላይ 18 ዓመት ለመፍረድ ዓይኑን አላሸም።

የህትመት ውጤቶቹ ተዘግተው… ጋዜጠኞቹ እስኪሰደዱ ለአንዲት ቀን እንኳ ትችት አቅርበው የማያውቁት የገዢው ፓርቲ ሎሌ ጸሀፊዎች “ጋዜጠኞቹ ወደ ሀገር አይመለሱም” ብለው መደምደም ከጀመሩበት ጥቂት ወራት ወዲህ… የ”ጭቃ ጅራፋቸውን” መምዘዝ ጀምረዋል። በፌስቡክ የለቀቁትን ጽሁፍ ለ”ሎሚ” እና ሌሎች መጽሄቶች እያቀበሉ… ገንዘብ በመቀበል ” ሌላ መጽሄት ላይ ስለምሰራ እባካችሁ ስሜን አታውጡ” እያሉ ሲማጸኑ የኖሩት እንደ ጌታቸው ይመር (የአሌክስ አብርሀም እውነተኛ ስም ነው) የቀድሞ ከፋዮቻቸውን ከሀገር መራቅ ተከትለው “የእስር ፍርዱ ያንሳቸዋል” የሚል ዘመቻ እንዲጀምሩ ታዘው “ሥራቸውን” እያጣደፉት ነው።

ጭምብላቸው ወልቆ እስኪወድቅባቸው ድረስ “መንግስት በጋዜጠኛ ላይ 18 ዓመት መፍረዱ ልክ ነው” በማለት የአምባገነኖች “የቁርጥ ቀን ልጅ” መሆናቸውን በማሳየት የደጅ ጥናታቸውን ልክ “እያስመሰከሩ” ነው።

ለመሆኑ ይህን የግፈኛውን አገዛዝ የ18 ዓመት እስራት ፍርድ “ልክ ነው” እያለ በመዘመር… የአገዛዙን ሎሌዎች በፊታውራሪነት በመምራት ላይ የሚገኘው ጌታቸው ይመር (አሌክስ አብርሀም) ማን ነው? ለስደት ከተዳረጉ ጋዜጠኞች አንዱ የሆነው ኢብራሂም ሻፊ አህመድ እንደሚከተለው ገላልጦ… እርቃኑን ያሠጣዋል።
…………… ……………….. ………………. ……………………..
“ሰው ያለቦታው………”
ደርሶ ሁሉም ቦታ አዋቂ……..ሁሉም ቦታ እኔን ስሙኝ……….እኔ ብቻ አውቅላችኋለው…….እኔ…..እኔ…..እኔ…..የሚሉ ሰዎች ብዙም ምቾት አይሰጡኝም፡፡ የእኔ መንገድ ትክክለኛው መንገድ ነው ብለው ከደመደሙም የበለጠ ምቾት ይነሱኛል፡፡ በጉዳዩ ላይ ያላቸው አውቀት ጥራዝ ነጠቅ ሆኖ “እኔን ብቻ ስሙኝ…….” የሚሉ ከሆነ ብልግናቸው ያሳፍረኛል፡፡ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ ከዚህ በፊት የሰበሰብኳቸው አሁን እንደፈለግሁት የምነዳቸው ተከታዮች አሉኝ በሚል ድፍረት ከሆነ ጤንነታቸውም ያጠራጥረኛል፡፡ የዚህ ሁሉ የምሬት መግቢያ መነሻዬ አሌክስ አብረሃ ገፅ ላይ “የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ሩጫ” የተመለከተን ፅሁፍ ማንበቤ ነው፡፡ ፅሁፉ ኢትዮጵያ ቡና ላይ የተነጣጠረ ይመስል እንጂ ሁሉም የኢትዮጵያ ቡድኖችን፣ የስፖርት አመራሮችን፣ ደጋፊዎችን፣ ተጨዋቾችን፣ አሰልጣኞችን፣ አርቢቴሮችን እና የስፖርት ስርዐት ጠባቂዎችን ይመለከታል፡፡ ስለስፖርቱ መረጃን የሚያቀርቡ ሰዎችን በገደምዳሜው ይነካካል፡፡ ስለስፖርት……በተለይ በባለሙያዎች ስለሚደረግ (Professional) እግርኳስ ባህሪ እና በውስጡ ስለሚገኙ እምቅ ስሜቶች ሳይተነትን ወደዘለፋ ይጓዛል፡፡ ፀያፍ ቃላትን ደራርቶ ባደባባይ አፍ ተካፈቱኝ ብሎም ይጋብዛል፡፡ ርካሽ ተወዳጅነት ያስገኙልኛል ያላቸውን ነጥቦች (Elements) ከስድብ ጋር አጅሎ ሰጥቶናል፡፡ ሆኖም ከእርሱ ለስፖርቱ እንቀርባለን ብለን የምናስበው እኛ በዚህ መንገድ ፅሁፉን እንወቅሰዋለን፡፡
አትዋሽ
“ገና ከመጀመሪያው ለቡና የስፖርት ክለብ ገቢ ማሰባሰቢያ መኖሩን ስሰማ ቲሸርቱን ልገዛ ጎራ ብዬ ነበር…….ግን ምን ያደርጋል ከቡድኑ አርማ ይልቅ ፊት ለፊት በትልቁ የቢራ ፋብሪካ ስም የታተመበት ቲሸርት ለብሸ እንደምሮጥ ሲነገረኝ ተውኩት”
ኢትዮጵያ ቡና ለተጨዋቾች የመኖሪያ ካምፕ እና የልምምድ ማዕከል ማስገንቢያ የደጋፊወች ሩጫ እንዳለ ካሳወቀ ሶስት ወራት ሆኖታል፡፡ አንተ (አሌክስ) “ገና ከመጀመሪያው” ከተጓዝክ ሶስት ወራት ተቆጥረዋል ማለት ነው፡፡ ያኔም የመሮጫ ቲሸርቱን አሳይተውኽ ንቀሃቸው እንደተመለስክ እየነገርከን ነው፡፡ ሆኖም እውነታው ይሄ እንዳልሆነ ስለሩጫው በቅርብ የተከታተሉ ሁሉ ያውቁታል፡፡ የሩጫው አዘጋጆች ጋር ፅፌም የተረዳሁት የቲሸርቱ ዲዛይን ሩጫው ሊከወን ሶስት ቀናት እሰኪቀሩት ምስጢር ነበር፡፡ በሶስቱ ወራት ውስጥ ቲሸርቱ ምን መምሰል እንዳለበት፣ የቡድኑ ደጋፊዎች ስታዲየም ሲመጡም እንዲለብሱት እና ጥራቱን በተመለከተ እርማት እና ማስተካከያ ሲሰሩ ነበሩ፡፡ አንተ ግን ቲሸርቱን ቢያንስ ከሶስት ወራት በፊት አይቼዋለሁ ብለህ ትዋሻለህ፡፡ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ቁጥሩ ብዙ ነው ብልህ አስበህም አሁንም “የርካሽ ተወዳጅነት” ስሌትህን ወደዚሁ አምጥተህ “ልሮጥላችሁ ነበር…….ሆኖም ሀበሻ ቢራ ከለከለኝ” ልትል ትፈልጋለህ፡፡ መዋሸት ምንም ኃጢያት እንዳልሆነ ማን እንደመከረኽ……የትኛው መፅሐፍ ላይ እንዳነበብከው እንጃ፡፡ ብቻ ባደባባይ ብዙ ግዜ ትዋሻለህ፤ ጌታቸው ይመር የተባለ፣ ኢትዮጵያን ሊያሰደምም የሚችል ገጣሚ እየመጣ ነው…..አንብቡት አልክ፡፡ እኛም ምን አይነት ጥሩ ገጣሚ እና ቅዕናት የሌለው በጎ አስተዋዋቂ መጣ ብለን ጥቂት ግጥሞች ኮሞኮምን፡፡ ሆኖም ጌታቸውም አንተው………አሌክስም አንተው ሆነህ ራስህን እያሞካሸህ እንደሆነ ተረዳን፡፡ ይሁን ቢያንስ ግጥም አስነበበን እንጂ አልጎዳንም ብለን ተውነው፡፡ አንድ ሌሊት ላይ በዐሉ ግርማን ሙልጭ አድርገህ በስድብ አጥረገረከው (አሁንም እኔን በዚህ ወይም በሌላ አካውንትህ እንደምትዘልፈኝ እጠብቃለሁ)፡፡ ወዳጅህ አፈንዲ ሙተቂ “አሌክስን ደውዬለት ነበር……መጠጥ ቀማምሶ ስለነበር በቸልተኝነት የፃፈው ነው” አለን፡፡ አንተ ግን አፈንዲንም ባደባባይ ካድከው፡፡ “ሳይለኝ ነው ያልኩት” እንዲል በሚያስገድድ ቃና አስተባባዬ ጓደኛህን “እኔ ነኝ ውሸታሙ” አስባልከው፡፡ ግን ሆድህ ያባውን እና ብቅል ያወጣውን ፅሁፍህን አጠፋሃው፡፡ ሳትቀማምስ የፃፍከው ፅሁፍ ቢሆን አስከመጨረሻው በፃፍከው በፀናህ እና ፅሁፉም ባልጠፋ ነበር፡፡ ያኔም ከመታዘብ ውጪ ምንም አላልንም፡፡ ብቻ ባደባባይ ሌላ በጓዳ ሌላ ሰው መሆንህን በግልፅ ተረዳንበት፡፡ ውሸትህ እንዲህ እየተጎተተ እዚህ አድርሶኃል……….ያላየኸውን አየሁ…………ያልነበርክበትን ነበርኩ እስከሚያስብልህ፡፡ በዚህን ያህል መጠን ባደባባይ የሚዋሽን ሰው “ሰክረው የሚወላገዱና አላፊ አግዳሚው ላይ ቢራ የሚረጩ ነበሩ!” የሚል ምስክርነትን ሲሰጥ ማን ይቀበለዋል? የፎቶ ማስረጃዎችን ጠቅሼ በሩጫው ላይ ብዙ ስርዐት አስከባሪዎች አይቻለሁ የምለው እኔ አፍራለሁ፡፡ ምክንያቱም ስደተኛ ነኝ እና በቦታው አልነበርኩም፡፡ ሆኖም የፎቶ ማስረጃዎቹን አምኜ እና የሃገሬን ስርዐት አስከባሪዎች ባህሪ ተንትኜ “ይህን ሲያደርጉ ማንም ዝም አይላቸውም፤ ስለዚህ አላደረጉትም” የሚለውን ባምን ይሻለኛል፤ ያንተ ተደጋጋሚ ውሸት ለዚህ ድምዳሜዬ መድረሻ ዋነኛው ሰበብ መሆኑን ግን አትዘንጋ፡፡
ሁለት ፍትህ ለአንድ ጉዳይ (Double Standard)
“የቢራ ፋብሪካ አርማ ታትሞብኝ በየመንገዱ መጠጥ ከማስተዋውቅ ኢትዮጵያ ቡና የሚባል የስፖርት ክለብ ገቢ አጥቶ ቢበታተን እመርጣለሁ”
ኢትዮጵያ ቡና ተበታትኖ የማየት ፍላጎትህ ጥልቀት ካስቀመጥከው አስቂኝ ምክንያት ጋር ሲደመር “ሰው ያለቦታው…….” ያስብላል፡፡ በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ቡና የቢራ ፋብሪካን ለማስተዋወቁ የመጀመሪያው አይደለም፤ የመጨረሻውም አይሆንም፡፡ ከሃገራችን እንጀምር፡፡ ከተመሰረተ 80 ዓመታትን ያስቆጠረው ቅዱስ ጊዮርጊስ በየዓመቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፋብሪካ የሚደረግለት የገንዘብ ድጋፍ አለ………ዳሽን ቢራ………ሀረር ቢራ………..(አሁን ስያሜው ተቀይሯል) ተብለው የተቋቋሙ ቡድኖችም አሉ፡፡ ፋብሪካዎቹ የኢትዮጵያ እግርኳስ እንዲያድግ ለሚያደርጉት አስተዋፅዖ ይመሰገናሉ እንጂ ምነው በእነርሱ ከምንረዳ “ተበታትነው በቀሩ” አያስብልም፡፡ ለትርፍ የተቋቋሙ ድርጅቶች በማህበራዊ ዘርፍ ተሳትፎን ያድርጉ ስንል ትምህርት ቤት፣ ጤና ጣቢያ እና መንገድ ሲገነቡ የምንሰጣቸውን ያህል አክብሮት የእግርኳስ ቡድኖችንም ሲረዱ እንሰጣቸዋለን፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውጤት አስመዝግቦ ከበደሌ-ሄይኒከን ቢራ የ24 ሚሊዮን ብር ስፖንሰር ሲያገኝ ዝም ያልክ ልጅ ዛሬ “ኢትዮጵያ ቡና ለምን በሀበሻ ቢራ ስፖንስር ተደረገ?” ማለትህ ሁለት ፍትህ ለአንድ ጉዳይ (Double Standard) ይሆንብኃል፡፡
ክልከላ መፍትሄ አይደለም
“ስታዲየሙ ቀስ በቀስ ትልቅ የቢራ ገበያ እየሆነ ነው”
ለእኔ ቀላሉ ነገር “ቢራን አትጠጡ…..ሃራም ነው!!!” ማለትን ነው፡፡ ቢያንስ ሀይማኖቴ የሚያዘኝ እና ከሀይማኖቴ ቀኖናዎች አንዱ ይሄ ነው፡፡ ሆኖም ነገሩን በሌላ መንገድም ማየት አለብን፡፡ ነብያችን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በመጀመሪያ ስለ መጠጥ ክልከላ ዱዐ (ፀሎት) አደረጉ እንጂ “አትጠጡ” ብለው አልከለከሉም፡፡ በጊዜ ሂደት ዱዐቸው ተቀባይ ሆኖ የቁርዐን አያ (አንቀፅ) ወረደላቸው፡፡ መጠጥም ክልክል ሆነ፡፡ አየኽ አሌክስ ሀይማኖቴ ያስተማረኝ ይሄንን ነው፡፡ አትከልክለው፣ አትጠየፈው፣ አታግልለው፣ አትዝለፈው፣ አታንኳሰው…………አስተምረው!!! ከሁሉም ከሁሉም ግን ዱዐ አድርግለት፡፡ ስለዚህም የስታዲየሙ ዙሪያ “ትልቅ የቢራ ገበያ” የሆነው እነዚያ ሰዎች ከአንተ አይነት አስመሳይ ሲሸሹ ነው፡፡ከውሸታሙ የበለጠ እንደትልቅ ሃጢያተኛ ተቆጥረው ምሳር ስለበዛባቸው ነው፡፡ የተፈጥሮ ባህሪ ነው እና አምሳያቸውን ፈልገው የተቀላቀሉት፡፡ የተሰበሰቡበትን ቦታ ምሽጋቸው ያደረጉት፡፡ ግን እኛ አስመሳዮቹ ብንጠጋቸው፣ ብንመክራቸው እና ፀሎት ብናደርግላቸው ከስህተት መንገድ እንታደጋቸዋለን፡፡ መቼም እነዚህን ሰዎች ማስታወቂያ አታሏቸው የገቡ “አይረቤ” ናቸው ብለህ እንደማትንቃቸው ተስፋን አደርጋለሁ፡፡
“ውበትን ፍለጋ”
“ማንኛውም የስፖርት ክለብ ህይወት አይደለም……..ከትውልዱ ኑሮ ሞራል እና ጤንነት ቀጥሎ የሚመጣ ሁለተኛ ነገር ነው”
ለእግርኳስ የሚሰጠው ትርጓሜ እና ክብር ከዚህም በታች ወርዶ ስለተመለከትኩ ብዙም አልገረምም፡፡ እግርኳስን 22 ተጨዋቾች አንዲት ቅሪላን እንደሚያባሩ………….በዙሪያቸው የከበቧቸው ሰዎች ደግሞ እሱን እየተመለከቱ እንደሚያውካኩ………ተደርጎ ሲሳል አስተውያለሁ፡፡ አሌክስ አብርሃን ጨምሮ እግርኳስን ስለሚዘግቡ ሰዎች “በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኛ ለመሆን መስፈርቱ ምንድን ነው?” ብለው ሲያፌዙም ታዝቤያለሁ፡፡ እግርኳስ ግን በእንደ ቢል ሻንክሌይ አይነቱ ታላቅ አሰልጣኝ እና አሰላሳይ “እግርኳስ የህይወት እና ሞት ጉዳይ አይደለም፤ ከዚያም በላይ እንጂ” ሲባልም አንብቤያለሁ፡፡ ለበርካታ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ቡድናቸውን የቢል ሻንክሌይ ትርጓሜ ይገልፅላቸዋል፡፡ ለቅዱስ ጊዮርጊስም…….ለሁሉም የኢትዮጵያ ቡድኖች ደጋፊዎችም ይህ ገለፃ ይመስጣቸዋል፡፡ ለቡድናቸው ህይወታቸውን የከፈሉ ደጋፊዎች አውቃለሁ፡፡ ጤናቸው ተቃውሶ (አንዳንዶች የአይናቸው ብርሃን ማየት ተስኖት እንኳን) ቡድኔን ልከታተል ብለው ስታዲየም ውሰዱኝ የሚሉ ሰዎችን እኔው ራሴ አይቻለሁ፡፡ አንተም ከፈለግህ ቀጣይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታን ፕሮግራም ልብ ብለህ ስታዲየም መጓዝ ትችላለህ፡፡ እንደኔው በአይንህ አይተህም ተገርመህ ትመለሳለህ፡፡ ስለምን ዓይነት ሞራል እንደምታወራ እንጃ እንጂ ብዙ ግዜ 25000 ደጋፊ እንድላይ ተቀምጦ፣ የተለያየ ቡድን ደግፎ፣ ተቃራኒ ሆኖ ተበሻሽቆ እንዲሁም በቃላት ተቆራቁዞ በስተመጨረሻም በሰላም ወደቤት የሚጓዘው ስታዲየም ውስጥ ነው፡፡ ይሄ ህዝብ የገንዘብ እንጂ የሞራል ድሃ አይደለም፡፡ ከጤንነቱ ቡድኑን………..ከህይወቱ ክለቡን የሚያስቀድምም ብዙ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኛ ለመሆንም የዚህን ህዝብ ስሜት እንዳንተው ሳይዘባርቁ በትክክል ማስቀመጥ የመጀመሪያው መስፈርቱ ነው፡፡
አሁንም “ማስ ሰፖርት?”
“ስፖርት ትውልድን ከዚህ ዓይነት ፀያፍ የመጠጥ ሱስ ትውልድን ለማዳን አንዱ መንገድ ነበር የሚመስለኝ”
ስፖርት ሲባሉ በልጅነታቸው ከሰሙት የተስፋዬ ገብሬ “ስፖርት ለጤንነት……ለምርት……ለወዳጅነት……..ስፖርት…….ለአእምሮ ማንቂያ……ስፖርት ለጤና መጠበቂያ………..” ዘፈን ያልተላቀቁ ብዙ ሰዎች አሉ………አንደኛው አሌክስ ነው፡፡ ተስፋዬ ጥሩ ዘፈንን ዘፍኗል፡፡ በወቅቱ ስፖርት የሁለት ርዕዮተዓለም ትርጓሜዎች ከወዲህወዲያ ያላጉት ስለነበር ትርጓሜውም አብሮ ይንገላታ ነበር፡፡ ተስፋዬ ኢትዮጵያ ከምትከተለው ርዕዮተዓለም (Communism) ተነስቶ ዘፈኑን አቀነቀነው፡፡ ልክም ነበር፡፡ አሁን ግን ስፖርት ከእነዚህ ዋጋዎች አልፎ የመልቲ ቢሊዮን ዶላር ንግድ ሆኗል፡፡ እግርኳስም ያንን መንገድ ተከትሏል፡፡ ተጨዋቾቹም የሙሉ ሰዐት ስራቸው ኳስን መጫወት (Professional) ሆኖ ክፍያቸውም በዚያው መጠን አድጎላቸዋል፡፡ ታላላቅ ኩባንያዎችም የእግርኳስ ጨዋታን ስፖንሰር ያደርጋሉ፡፡ የቢራ ፋብሪካዎች እዚህ ውስጥም ይደመራሉ፡፡ ስታዲየም በመደበኛ ስራቸው ታላላቅ የምንላቸው ሰዎች እንኳን ደስ የሚሉ “ህፃን” የሚሆኑበት ቦታ በመሆኑ ኃላፊነት እንዲሰማቸው ማገዝ እንጂ ክልከላ የለም፡፡ ስለዚህም ቢራ ይሸጣል……….ለሲጋራ ማጨሻ የተከለለ ቦታም አለ፡፡ እዚህ ጋር ሁለት ነገሮች አሉ፡፡ አንዱ መፈለግ ሲሆን ሁለተኛው ኃላፊነት ነው፡፡ የማይፈልግ አይጠጣም እንዲሁም አያጨስም፡፡ ድርጊቱን የሚከውን ደግሞ በኃላፊነት እንዲያደርገው በስፖርት ጠባቂዎች (Stewards) ይታገዛል፡፡ ለዚህም ነው የዓለምዓቀፉ እግርኳስ አስተዳዳሪ ኣካል (ፊፋ) እና የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር (ዩኤኢፋ) ጨምሮ ብዙ ታላላቅ ውድድሮች በቢራ ፋብሪካዎች ስፖንሰርነት የሚደረገው፡፡ ታላቁ የዓለም ዋንጫ ከቡድዋይዘር ሲቀጥልም ከዓምስቴል ቢራ ጋር ወዳጅ ነው፡፡ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ በሄይኒከን ስፖንሰር ይደረጋል፡፡ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ቢያንስ ለስምንት ዓመታት ወጪው ሲሸፈንለት የነበረው በካናዳው ካርሊንግ ቢራ ነው፡፡ ማክኤዋንስ፣ ካራቢስ እና ቻንግ የተባሉ ቢራዎችም የተለያዩ የዓለማችን ጎበዝ ክለቦችን ስፖንሰር ያደርጋሉ፡፡ ያንተ “የሆነው ሆኖ የስፖርት አፈርድሜ አንደበላች እና በአሁኑ ሰዐት የስፖርት ክለቦቻችን ከዓለምዓቀፍ የስፖርት ዓላማ ርቀው የቢራ ፋብሪካዎች የማርኬቲንግ አንድ ክፍል ከመሆን” ትንታኔ የመረጃ እና እውቀት እጥረት መሆኑንን እታዘባለሁ፡፡ ቡድኖቻችን ዓለምዓቀፉን መንገድ ተከተሉ እንጂ በተቃራኒው አልተጓዙም፡፡ አሁንም እነዚሁ ቡድኖቻችንን የስፖንሰሮችን ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም……ኢትዮጵያ ቡናም…….ብሔራዊ ቡድኖቻችንም…..ሁሉም ቡድኖቻችን የስፖንሰሮችን ድጋፍ ይሻሉ፡፡ በወልጋዳ ብዕር ተሸብረው ስፖንሰር አድራጊዎች የኢትዮጵያን እግርኳስ ከመርዳት መታቀብም የለባቸውም፡፡ ባለፈው ግማሽ ምዕተዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ያለምንም ልዩነት በደስታ የፈነጠዘው እና ፊቱ ላይ ፈገግታ የታየው ብሔራዊ ቡድኑ ደቡብ አፍሪካ ላይ ለተዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ሲበቃ መሆኑን ማን ይዘነጋል?

ሰውዲ አረቢያ በገንዘብ እጦት ችግር ክፉኛ ልትመታ ነው ተባለ (ታምሩ ገዳ)

$
0
0

ነገሩ ቀልድ እና ሟርት ይመሰላል፣ ነገር ግን እውነት ነው ።ለብዙዎች እርጥባን እና ምጽዋት በመቸር እንደ ጣኦት የምተመለከው ስውዲ አረቢያ እንደ አለማቀፍፉ የገንዘብ ማእከል (አይ ኤም ኤፍ) ሰሞነኛ ማሰጠንቀቂያ ከሆነ (ይህቺው የአለማችን ቁጥር አንድ የተፈጥሮ ነዳጅ አመራች እና ሻጭ አገር) በቀጣዮቹ ጥቂት አመታት ውስጥ ክፉኛ የገንዘብ እጦት ችግር ሊገጥማት አንደሚችል አስጠንቅቋል።
12187784_10154397605034298_5413447188516908346_n
የአሜሪካው ኬብል ኔውስ ኔት ዎርክ(CNN ) በሰኞ ጥቅምት 25 2015 ዘገባው እንደ ገለጸው ከሆነ በአሁኑ ወቅት በአለም ገበያ ላይ ያለው የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በአማካኝ በበርሚል $50( ሃምሳ ዶላር) ሆኖ ከዘለቀ የዋጋ ማሽቆልቆሉ በ አምራቾቹ ላይ የ 360 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ሰለሚፈጠር ዋንኛ ነዳጅ አቅራቢያዋ እና ነዳጅም ስትንፋሷ የሆነው ሰውዲ አረቢያን ጨምሮ በቀጣዩ 5 ወይም ከዚያ ባነሰ አመት ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ እጦት የገጥማቸዋል ሲል አለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት አስጠንቅቋል።ሪፖርቱ ጎረቤት ኦማን እና ባህሪንም ተመሳሳይ እጣ እንደሚገጥማቸው ተንብዮዋል።ከ አመት በፊት በበርሚል$ 100( አንድ መቶ ዶላር) የነበረው ነዳጅ ዘይት በቅርቡ እሰከ $45 ዶላር መወረዱ እና ሰወዲ አረቢያ የመሳሰሉት አገሮች ከመጠባበቂያ ፉንዳቸው እስከ መቆንጠር ተገደዋል ተበሏል።”ነዳጅ ሻጮች አገሮች ገቢያቸውን እና ወጪያቸወን ማሰተካከል የጠበቅባቸዋል” ሲል IMF ምክሩን ለእነ ስውዲ አረቢያ ሰጥቷል።
12065652_10154397606274298_6809108321173359753_n
የእነ ስውዲ አረቢያ የኢኮኖሚ መንገዳገድ የመጣው በአካባቢው በተቀሰቀሰው የእርሰ በርስ ጦርነት እና የገበያው መናጋት በተፈጠረ ማግስት መሆኑ ሁኔታውን አባብሶታል ተብሏል።ስወዲ አረቢያ ከችግሯ ለማገገም ነዳጅ በበርሜል በያንስ $106 መሸጥ የግድ ይላታል ያለው ሪፖርቱ ስውዲ አረቢያ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ቦንድ በመሽጥ ችግሯን ለመቅረፍ ጥረት ብታደርግም በጎረቤት የመን የሚገኙ የሺያት አማጺያኖችን ለመዋጋት በሚል ሽፋን እና ደንበሯን ለማሰከበር ስትል እኤአ 2014 ብቻ የመከላከያ ባጀቷን ወደ 80.8 ቢሊዮን ዶላር(17% ጭማሪ አና በ አለማችን 4ኛዋ ለመከላከያ ወጪ አድራጊ አገር አደርጓታል። አሜሪካ 610 ቢሊዮን ፣ቻይና 216 ቢሊዮን ዶላር ፣ሩሲያ 81 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት ከ 1 እስከ 3 ይከታተላሉ) የመደበች፣ በ 2011 አካባቢውን ያመሰቃቀለው የአረብ ስፕሪንግ (የአረብ አብዮት)ከደጃፏ ጎራ አንዳይል ጥረት የምታደረገው ሪያድ የዜጎቿን ቁጣ ለማብረድ ስትል የማሕባራዊ (social) እና የመከላክያ ወጪዋን በቀላሉ የምትቀነስ አይመስልም ተብሏል
የሰውዲ ነገር ሲነሳ ከሁለት አመት በፊት ኑሮን ለማሸነፍ እና አንጀራ ፍለጋ ወደ ግዛቷ የገቡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምስኪን አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኛ እህቶቻችን እና የጉልበት ሰራተኞች ወንድሞቻችንን ጨረቄን እና ማቄን ሳይሉ እጅግ ኢ-ሰብ እዊነት በተሞላው መንገድ ከግዛቷ ጠራርጋ ማባረሯን በርካታ አትዮጵያዊያኖችን ማሳዘኑ እና ማስቆጣቱ አይዘነጋም። ያንንም መጥፎ አጋጣሚ ብዙዎች “ብ ሔራዊ ውርደት” ሲሉት ተደምጠዋል።
ማን ያውቃል የዛሬ 50 እና 60 አመትታት የግመሎች እና የፍየሎች መፈንጪያ የነበረችው ያቺ ከበረሃው ከረሰ ምድር ውስጥ በሚቀዳ የነዳጅ ሃብቷ ብቻ የአለም ጡነቸኞችን ሳይቀር የመታሰገዳቸው ስውዲ አረቢያ የነበረው እንዳልነበረ ሆኖ ኪሳራው ሲበረታባት እና ደግነታችንን ከቅደመ አያቶቿ ሰለመታውቅ ወደ ሃበሽ ምድር(ኢትዮጵያ) ለመሸሸግ ዜጎቿን ትልክ ይሆናል፣ሰደቱ ወደ አረቡ አለሙ መሆኑ ቀርቶ ወደሰው ልጆች መፍለቂያ (ኢትዮጵያ) የማይሆንበት ምክንያት አይኖርም ። ኋለኞች ፊተኞች ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ የሚባለው ስለዚህ አይደል?።

የአሌክስ አብርሀም ጸረ ፕሬስ “ሳዲስታዊ”ጩኸት…ከኢብራሂም ሻፊ አህመድ

$
0
0

ሳድዝም መራር ተግባር ነው፤ ቃሉ ራሱ አፍ ላይ የሚመር ይመስላል፡፡ ስጠራው ቅፍፍ ይለኛል፡፡ የሌሎችን ሰዎች ውድቀት፣ ህመም፣ ምቾት አለመሰማት እና ስቃይን እያዩ ከልብ መደሰት፣ ጥርስን ማፍነክነክ፣ “ቪቫ” ብሎ በድል ስሜት እጅን እንደመቀሰር እና መፈንደቅ የሚል ትርጓሜ የሚሰጥ ነገር ምኑ ይወደዳል? ለአንዳንዶች ግን ቃሉ ብቻ አይጥማቸውም፤ ግብሩም ይዋጣላቸዋል………. ልክ ለእንደ አሌክስ አብረሃ ……..ጌታቸው ይመር…… (ኧረ በየትኛ ስሙ ልጥራው)አይነቱ!!!
ኢትዮጵያዊያን በሊቢያ በረሃ በአይኤስ ጭካኔ ታርደው ህዘብ ሲያነባ፣ ሲያለቅስ እና መከራ ከፈነቀለው ብሶት አደባባይ ሰልፍ ሲወጣ በዝምታ አድብቶ፤ መንግስት በጠራው የሁለተኛ ቀን ሰልፍ ላይ ገና በጠዋቱ “ፌዴራል ፖሊስ እና ህዝብ ተቃቅፈው እየተላቀሱ ነው፤ በዐይኔ በብረቱ ዐይቻለሁ” ብሎ የፌስቡክ ግድግዳው ላይ ውሸት የፃፈ እና ያስደበደበ ነውረኛ ነው፡፡ ህዝብ ሲራወጥ፣ በፖሊስ ቆመጥ ሲንገላታ፣ ህይወቱን ለማትረፍ ሲባትት እና የእስርቤት ደጃፎችን ላለመርገጥ ሲሸመጥጥ አሌክስ የኮምፒዩተር ኪቦርዱን እየጠቀጠቀ እና ፌስቡኩን እየተመለከተ ሲያፌዝ የነበረ የሳድስቶች አውራ ነው፡፡
ይህ ሳድስታዊ ባህሪ የተፀናወተው እና የማይለቀው በመሆኑ ከእርሱ ከፍ ያሉ የመሰሉትን በመሉ በመዝለፍ፣ በማንጓጠጥ እና በማሰቃየት ለመርካት ጥረትን አድርጎ ነበር፡፡ ዮሴፍ ገብሬ (ጆሲ)፣ ሰይፉ ፋንታሁን፣ ግሩም ኤርሚያስ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) እና በዐሉ ግርማ ላይ ጀምሮት የነበረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ከብዙ በጥቂቱ ማንሳት እንችላለን፡፡ እነዚህን ሰዎች እና ቤተሰቦቻቸውን ስቃይ ላይ ጥሎ እርሱ “ፈገግ” ሊል ቢፈልግም ህዝብ አልፈቀደለትም እና ውጥኑ መና ሆኖ ቀርቶበታል፡፡ የሰዎቹ እና ቤተሰቦቻቸው ስብዕና እጅግ ጠንካራ ነበር እና ከዘበትም ሳይቆጥሩት አልፈውታል፡፡ ለሳድስቶች ግን በፀብ ተጠምዶ “እኝ” ማለት፣ ሌሎችን ለማስፈራራት መሞከር እና የተለያዩ የስቃይ ዘዴዎችን መሻት ስራቸው ነው እና ለእነዚህ ሰዎች ውድቀት የተለያዩ ጉድጓድ በተደጋጋሚ ለመማስ ሞክሮ ነበር፤ በሁሉም ዘንድ ፊት ተነስቶ አዳፈነው እንጂ!!!
በሰዎች ሁሉ ስቃይ፣ ውድቀት እና መከራ ከሚረኩት ሳድስቶች አንዱ የሆነው አሌክስ በቅርብ ደግሞ ” የሎሚ ጋዜጠኛ/ባለቤት (ግዛው ታዬ) እንኳን 18 ዓመታት እስር እና 300ሺህ ብር ቅጣት ተጣለበት” በማለት እውነተኛ ማንነቱን አሳይቶናል፡፡ የሰው ልጆች ውድቀት እና ስቃያቸው ነበር እና የሚያረካው አንድ የሚበልጠው የመሰለው ሰው እጅግ ዘግናኝ የእስር ቅጣት ሲተላለፍበት ጮቤ ረግጧል፡፡ ግዛው በሌለበት የተፈጠረ ክስ፣ ባልዋለበት የተሰማ ጭብጥ እና የቀረቡ ማስረጃዎች ለእንደ አሌክስ አይነቱ ጨካኝ ገልቱዎች ምንም አይደሉም እና ውሳኔውን “እንኳን” ብለው በደስታ እየፈነጠዙ ተቀብለውታል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ “ፅሁፌን ሳያስፈቅደኝ መጽሔቱ ላይ አውጥቷል” የሚል ማስረጃ ያልቀረበበት እና እጅግ ተልካሻ ሰበብ ነበር፡፡
አሌክስ ከሳድስታዊ ባህሪው በተጨማሪ ማቋረጥ የማይችል ውሸታም ሆኖ እንጂ ግዛው ታዬ፣ የሎሚ ቅጥር ሰራተኞች እና ጋዜጠኞችን ብትጠይቋቸው መጽሔቱ ላይ ለወጡት እያንዳንዱ ጽሑፉ ክፍያን ተቀብሏል፡፡ “አዲስ ጉዳይ ስለምስራ እና ስሜ እዛ ላይ ስለሚወጣ እባካችሁ ስሜን አታውጡብኝ” የሚል ተማፅኖን እያቀረበ እንጂ ስግብግብ ነፍሱ አካሉን ረስታው እንደማታውቅ ይነግሯችኋል፡፡ ይሄንን ዘዴንም በብዙ መጽሔቶች ላይ ተጠቅሞ ስሙ ሳይወጣ (ከአዲስ ጉዳይ በስተቀር) ገንዘብ እንደሰበሰበበት ይመሰክሩበታል፡፡ ብሩን ለመቀበሉም በርካታ ጋዜጠኞችን እማኝ አድርጎ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ሆኖም እንደ ጥሩ ማስረጃ እነዚህ መጽሔቶች ህትመት ላይ በነበሩበት ሰዐት ከመለማመጥ ውጪ ዘልፎ እና ወደፊት ገፍቶ አለመሄዱን ልብ ማለቱ በቂ ነው፡፡ ልምምጡም ስሙ ሳይጠቀስ ስራው ከሚወጣባቸው መጽሔቶች ጋር በሽርክና የሚደረግ (ለእነርሱም እንደማስታወቂያ ቢጤ መሆኑ ነው) በመሆኑ በፍፁም ወደ ክስ አምርቶ የማያውቅ እና ሊያመራ የማይችል መሆኑን ለመረዳት ቀላል ነበር፡፡
ሎሚ በመንግስት ክስ የተፈጠረበት አሌክስ እንደሚለው “የሰው አዕምሯዊ ንብረት ስለወሰደ” አይደለም፡፡ ክሱ “ያለ ታክስ ለአምስት ዓመታት ሰርተሃል” የሚል ነው፡፡ በአሁኒቷ ኢትዮጵያ መንግስት ዐይኑን ጥሎብህ፣ በአደባባይ የሚታተም እና የሚሰራጭ የህትመት ውጤት ሆነህ፣ ጋዜጦች እና መጽሔቶች በየጊዜው ከሚደረግባቸው ምርመራ አንፃር ለበርካታ ዓመታት ያለ ታክስ መስራትን የመሰለ የፈጠራ ክስን እናንተው አስቡት፡፡ መልዕክቱ መንግስትን ሚዛናዊ ሆነው ለፈተኑት ለኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኝነት እና ጋዜጠኞች እንጂ ለግዛው ታዬ አለመሆኑን ተረዱት፡፡ ኢትዮጰያ ተመልሳችሁ ብትመጡ “ዋ!” የሚል መልክት እንደያዘም ማሰብ ትችላላችሁ፡፡ እንደ አሌክስ አይነቱ ሳድስት ግን ዐይኑ የሚያነበው ሌላ ነው እና የበላበትን ወጪት ሰብሮ ግዛው ታዬ 18 ዓመታት ሲፈረድበት ፈንጥዟል፡፡ እንደው ግዛው ታክስ ሳይከፍል ቢሰራ እንኳን “የኢትዮ ቻናሉ ሳምሶን ማሞ በተመሳሳይ ጥፋት ስንት ጊዜ ታሰረ? እንዴትስ ተፈታ? የሚል ንፅፅራዊ ነጥቦችን አንስቶ አንደመፃፍ ” እንኳንም ታሰረ……ያንሳል” ብሎ ተሳልቋል፡፡ ጊዜ የሁሉም ነገር መፍቻ ነው፡፡ ጊዜ አሌክስንም ሳድስታዊ ባህሪው ሳይታወቅ፣ የቅድሚያ ክፍያ እና ብድር ሳይቀር እየወሰደ ከሎሚ እና ሌሎች መጽሔቶች ጋር አሰርቶት ነበር፡፡ ጊዜ ደግሞ መንግስት የፈጠራ ክስን ይዞ ቀርቦ አጅግ ዘግናኝ ውሳኔን ሲያሳልፍ አሌክስን ማልያ አስቀይሮ እና ሳድስታዊ ባህሪውን አጋልጦ አሳይቶናል፡፡ ፍትህ፣ርትዕ፣ ዲሞክራሲ እና መልካም አስተዳደር በተደፈጠጡበት፣ ሙስና የህዝቡን አጥንት ሳይቀር እየጋጠ ባለበት፣የሀገር ፍቅር እንደ ጉም ተኖ ከጠፋበት እና ራስን የመቻል ብልሃት ፍፁም እንቆቅልሽ ከሆነበት የኢትዮጵያ ችግር የግዛው ታዬ 18 ዓመታት መታሰር በልጦበት “እንኳን…..ደግ አደረጉልህ” አስብሎታል፡፡ እኛ ግን እትርሳ እንለዋለን…….የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም!!!


የተቦርነ የፈራረሱ ቅኝቶች (ከአርአያ ተስፋማርያም)

$
0
0

804639_1514132968900777_437236521_n
ወዳጄ ተቦርነ በተመለከተ ግልፅ ያልሆኑልኝ ነገሮችን አንስቼ በጥያቄ መልክ አቅርቤ ነበር። አንተም ለኔ ጥያቄ የሚሆን የመልስ ፅሑፍ ለጥፈህ አነበብኩት። የመለስክልኝ መልስ በጣም አስገርሞኛል፣ ግራም አጋብቶኛል። ያንተኑ ተረት በመዋስ “ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ” ብየዋለሁ። ምክንያቱም ጥያቄዬን መመለስ ስላልቻልክ ወይም ስላልፈለክ እኔን በመሳደብ ጥያቄውን ለማድበስበስ ስትሞክር ነበር። ሃሳብን በሃሳብ መርታት ሲቃትህ ሃሳቡን ያቀረበውን ግለሰብ የማጥቃት የተባለ የክርክር ግድፈት ወይም ሎጂካል ፋለሲ ነው። ምን አልባት ጥያቄዬን ካልተረዳኸው ደጋሜ ላንሳው።
ዘረኛ፣ ኣምባገነንና ሙሰኛ የሆነው የኢህአዴግ መንግስት ህዝባችንን ከፍላጐቱ ውጭ በሀይል፣ በማስፈራራትና በዘር በመከፋፈል እየገዛ 24 አመታት አለፈ። ይህ መንግስት የስልጣን ዘመኑ እንዲቀጥል ህዝቡን በዘር መከፋፈል፣ በሀይል ማፈንና አዲሱ ትውልድ በተለያዩ የማይረቡ ጉዳዮች ማደንዘዝ ዋና አላማዬ ነው ብሎ እየሰራ ይገኛል። ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ሞት፣ እስራት፣ ግርፋት፣ ድህነትና ስደት ተጠያቂ ከሆነው ከዚህ መንግስት ጋር የጥቅም ተካፋይ ሆነው ስልጣኑ እንዲረዝም በገንዘባቸውና በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከሚረዱት ሰዎች አንዱ ሼኽ አልሙዲ ናቸው። ሼኹ በኢትዮጵያ ፖለቲካ በፈፀሙት ደባ፣ የሀገሪቱን ሃብት በመበዝበዝ የሃገራችንን ባህልና ወግ የሚያናጋ የማህበራዊ ቀውስ በህብርተሰቡ ውስጥ በማምጣት የሚጠየቁ ሰው ናቸው።
ከላይ እንደጠቀስኩት የዚህ መንግስት ዋና አላማው ህዝቡን ከፋፍለህ መግዛት ብቻ ሳይሆን ትውልዱን ስለሃገሩ ታሪክ፣ ስለማንነቱ፣ ስለሰብዓዊና ዴሞክራሲ መብቶቹ እንዳያውቃና እንዳይጠይቅ ማደንዘዝ ነው። ለዚህ አላማ መሳካት የፖለቲካ፣ የታሪክ፣ የፍትህ፣ ፍልስፍናና የማንነት ጥያቄ የማያነሱትን እንዲሁም ህዝብ እንዲነቃ የሚያደርጉትን የመገናኛ ብዙሃን እየዘጋ፣ ሽብርተኛ እያለ ጋዜጠኞችንም እያሰረ፣ እያሸማቀቀ፣ ከሀገር ያሰድዳል። በተቃራኒው ደግሞ ህዝቡ ከሀገሩ ጉዳይ ጋር እንዲፋታ የፖለቲካም ሆነ የመብት ጥያቄ ሲያነሳ የተባለውን አድራጊ፣ የተጠየቀውን ፈፃሚ ይሆን ዘንድ እንደ ሰይፉ ፋንታሁን አይነት ትውልዱን የሚያደነዝዙ ዝግጅቶችንና መገናኛ ብዙሃንን “የመዝናኛ ፕሮግራም” በሚል ስም ይለፈልፋል።
አነተ ገለልተኛ እያልክ የምታወድሰው ጓደኛህ ሰይፉ ፋንታሁን ይህንን የኢህአዴግን አላማ ግንባር ቀደም አስፈፃሚ ከመሆኑ በተጨማሪ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን አምባገነን መንግስት የሚደግፍ ካድሬ መሆኑን አገር ያውቃል። ከዚህ በተጨማሪ ሰይፉ የኢሃዴግ መንግስትን እድሜ ለማርዘም ሌት ተቀን የሚለፉትና የአገርን ሃብት ያለአግባብ የሚዘርፉት የሼኹ ሎሌ ነው። በቅርቡ በሸራተን ሆቴል ሲያገባ የሰርጉን ወጪ ሙሉ በሙሉ በሼኹ የተሸፈነለትም በዚሁ የኢህአዴግ ካድሬነቱና ታማኝነቱ የውለታ ምላሽ ነው። ከሼኹና ከገዢው ፓርቲ ጋር አልተባበርም ያሉና ከተፅዕኖ ውጭ የሆኑ አርቲስቶች ፈተና ሲገጥማቸው አይተናል። ህዝብ የጀግንነት ክብር ከሰጣቸው ታማኝ በየነና ቴዲ አፍሮ ይጠቀሳሉ።
ኢ.ሴ.ኤፍ.ኤን ከኢህአዴግና ከሼኽ አልሙዲ ተፅዕኖ ራሱን አላቆ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመስራቱ ምን ያክል የህዝብ ድጋፍ እንደነበረውና ውጤታማ እንደነበረ አይተናል። እኔ ለአንተ የማቀርበው ጥያቄ የሚነሳው እዚህ ላይ ነው። እዚህ አሜሪካ አላሙዲ ከፈጠሩት የስፖርት ፌዴሬሽን ጋር የተባበሩትን አርቲስቶች እያወገዝክና ሌላ ስራ እንዳይሰሩ እያሳደምክ፣ በአንፃሩ ቀንደኛ የገዥው ፓርቲ ካድሬና የሼኹ ወዳጅ በመሆን ከኢትዮጵያ ህዝብ ከተዘርፈው ገንዘብ ተካፋይ የሆነው ሰይፉ ፋንታሁንን የአንተ ጋዷኛ በመሆኑ ብቻ አላሙዲ በሸራተን ደግሰው ሲድሩት ለምን ለማውገዝ ተሳነህ?..ማውገዝ እንኳ ቢቀር የሼኹ ሎሌ የሆነው ሰይፉን በምን መለኪያ ገለልተኛና በእመነቱ የሚፀና ለማለት ደፈርክ?.. ወይም ገለልተኛነትና በእምነት መፅናት ምን እንደሆኑ አታውቅም! አለበለዚያ ለአንተ ገለልተኛነትና በእምነት መፅናት ማለት ከአንተ ጋር የሚመሰረት ጓደኝነት ነው ማለት ነው። ሌላው ጥያቄ እዚህ አሜሪካ አገር ከአልሙዲ ጋር የተባበሩትን አርቲስቶች ከተቃወምክ አዲስ አበባ ላይ ከዚያው ግለሰብ (ሼኹ) ጋር የሚተባበሩትንና የቅርብ ወዳጅ የሆኑትን ሰዎች ማንቆለጳጰስ እንዴት ትችላለህ?..በተጨማሪ በአላሙዲ የሚረዳውን ፌዴሬሽንና ሸራተን ለየብቻ እንደሆኑ አድርገህ ለመግለፅ ሞክረሃል። እጅግ አስቂኝ ነው።ሁለቱም በሼኹ የሚዘወሩ ናቸው!
ከአምባገነኑ መንግስት ኢህአዴግና መንግስትን ከሚደግፉት እነሼኽ አላሙዲ ጋር መተባበር አይገባም ካልክ አቋምህ ወጥ ሊሆን ይገባል። አዲስ አበባም ሆነ አሜሪካ፣ ሰርግም ሆነ ስፖርት ጓደኝነት ኖረም አልኖረ፣ የግል ጥቅም ተገኘም አልተገኘ፣ አቋምህ ወጥ መሆን ይገባዋል። ስትቃወም፣ ስትደግፍ፣ ወጥ የሆነ አቋም ይኑርህ!
በእነኚህ ጉዳዮች ላይ የምታንፅባርቀው ወጥ ያለሆነ አቋም ሳስብ አንድ ጥንታዊ የቻይና ተረትን አስታወሰኝ። ሰውዬው በመንደሩ ውስጥ ሱቅ ከፍቶ ጦርና ጋሻ አንድ ላይ ይሸጣል። የሚገርመው ግን ጦሩን ሲያሻሽጥ “ሁሉንም ነገር ይበሳል” እያለ ሲሆን ጋሻውንም ሲያሻሽጥ “ምንም ነገር አይበሳውም” እያለ ነበር። አንተም፣ ያንተም ጓደኛም ሰይፉ ፋንታሁን ከአልሙዲ ተሻርኰ እየሰራና ሸራተን ሰርግ ሲደገስለት እያየህ ገለልተኛና በእመነቱ የሚፀና ብለህ ታወድሰዋለህ! አሜሪካ አገር ያሉ አርቲስቶች ከአልሙዲንና አላሙዲ ከፈጠሩት ፌዴሬሽን ዝግጅት ላይ ሲዘፍኑ ደግሞ “ባንዳና ከሃዲ” ብለህ ታወግዛለህ፤ እንዴት ነው ነገሩ?..የባንዳነትና የኢትዮጵያዊነት መለኪያው የአንተ ፍቃድና ጓደኝነት ሆነ እንዴ?..ለነገሩ የአንተን የአቋም መዘባረቅ በተመለከተ ግራ የሚያጋቡኝን አንድ ሁለት ነገሮች ልጠቃቅስልህና ወደ ዋናው ሃሳቤ ልመለስ። ድምፃዊ ቴዴ አፍሮ ከአልሙዲ ጋር ላለመስራት ወስኖ የኢትዮጵያ ህዝብ ጀግና እያለ ሲወድሰው ኢህአዴግ ደግሞ እንደጠላት ሲያዋክበው በነበረት ጊዜ አንተም ከሰይፉ ጋር ሆነህ ቴዲ አፍሮን በማዋከቡና የድምፃዊውን መልካም ስም በማጠልሸት ዘመቻ ላይ ከሰይፉ ጋር ተሳታፊ ነበርክ። ሁለተኛ የሰይፉን በመዝናኛ ስም ህዝብ የማደንዘዝ ተግባር ላይ አካልና አጋር ነበርክ። አንተ የእኔን የትላንት፣ የዛሬና የነገ አቋም ለመጠየቅ አንዳችም ማስረጃ ባይኖርህም እኔ ግን እነዚህንና ሌሎች ለጊዜው የማልገልፃቸውን ስህተቶችህን እያወቅኩ ኢትዮጵያዊነትህን አልተጠራጠርኩም።
ስለጋዜጠኝነቴ ደረጃ ለመስጠት መሞከርህ አስቆኛል። ስለፖለቲካ፣ ማህበራዊና ሌሎች ጉዳዮች ለመፃፍ ስፈልግ – የምፅፈውን ነገር አንተ ልትመርጥልኝና ልትወስንልኝ አትችልም! ለነገሩ በሁሉም ነገር ደረጃ የመስጠትና ታፔላ የመለጠፍ ችግር ስለራስህ ካለህ የተዛባና የተጋነነ ግምት የመጣ ነው። በምን የጋዜጠኝነት እውቀትህ፤ ልምድህና ብቃትህ ለእኔ የጋዜጠኝነት ደረጃ ልትሰጥ እንደፈለግክ አልገባኝም። ለመሆኑ ኢትዮጵያ በነበርንበት ጊዜ ለእውነት ቆመን መንግስትን ስናጋልጥና ፊት ለፊት ስንጋፈጥ፣ የአገዛዙን ደባ ስናጋልጥ አንተ የት ነበርክ? ..አንተ የት እንደነበርክ ትዝ ካላለህ እኔ ላስታውስህ፤ በወቅቱ አንተ የመንግስትን ትውልድ የማደንዘዝ አላማ ከሚያስፈፅመው ከሰይፉ ጋር ተሰልፈህ ህዝብን ግራ በማጋባት ትሰራ ነበር። በወቅቱ ድምፃዊ ቴዴ አፍሮ ከመንግስትና ከነአላሙዲ ጋር አልተባበርም፣ ሃገሬ ትበልጣለች ብሎ ራሱን ሲያገል፣ አንተ ከሰይፉ ጐን ቆመህ የድምፃዊውን መልካም ስም በራዲዬ ታጠፋ ነበር። ለመሆኑ አንተ ጋዜጠኛ ሆነህ በፍትህና በዲሞክራሲ ድምፅህን አሰምተህ ወይም ፅሁፍ ፅፈህ የምታወቅው መቼ ነው?..እኛ በጋዜጠኝነት ስንታሰር፣ ስንደበደብና ዋጋ ስንክፈል አንተ ግን በዛኛው ወገን ቆመህ ትውልዱን ታደነዝዝ ነበር። ሆኖም ሰው ሊለወጥ ይችላል። እዚህ መጥተህ «አርበኛ ነኝ» ስትለን በበጐ ስሜት ተቀበልነሃል። በመጨረሻ ሁሌ በአዕምሮህ ልታኖረው የሚገባውን አንድ እውነት ልነገርህ። አገራችን የብዙ ሚሊየኖች አገር ናት። ትግሉም ህዝባዊና ሁሉን አሳታፊ ነው! በመሆኑም አንተ በማንኛውም መለኪያ የጋዜጠኝነት ደረጃ አውጪ፣ የፖለቲካ አቋሞች አጣሪና የኢትዮጵያዊነት ፈቃድ ሰጪ ልትሆን አትችልም!

የሲቪክ ማህበራትና ነፃ ሚዲያ አስፈላጊ መሆንን ኢትዮጵያን የጎበኙት የስዊዘርላንድ ፕሬዚደንት ገለጹ።

$
0
0

ኢትዮጵያን የጎበኙት የስዊዘርላንድ ፕሬዚደንት ሲሞኒታ ሲማሩገ ለተወካዮች ምክር ቤት በቀጥታ በተላለፈ ንግግራቸው የሲቪክ ማህበራትና ነፃ ሚዲያ አስፈላጊ መሆኑን ገለጹ።ዝርዝር ዘገባውን ከቪኦኤ ያዳምጡ።

የኃይለማሪያም ደሳለኝ የትጥቅ ትግል አቁሙ ጥሪና የቡድኖቹ ምላሽ-VOA Amharic

$
0
0

በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በትጥቅ ትግል መንግስት ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ መንገድ ቢመጡ ይሻላቸዋል ሲሉ ያቀረቡትን ጥሪ ተቃዋሚዎች አጣጣሉት።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ቃል አቀባይ አቶ ዳውድ ኢብሳ ለቪኦኤ በሰጡት ምላሽ “የትጥቅ ትግል ውስጥ የገባነው ፈልገን ሳይሆን መብታችንን ለማስከበር ነው አቶ ኃይለማርያም እኛን የማስተማር አቅም የላቸውም” ብለዋል ። በቅርብ አዲስ አበባ ለድርድር ሄደው ተባረው የተመለሱት አቶ ሌንጮ ባቲ ጥሪውን ደግፈዋል።ዝርዝር ቃለምልልስ ያድምጡ።

ጤፍ በአሜሪካ እየተለመደ ነው

$
0
0

የኢትዮጵያና የኤርትራው ጤፍ፣ የደቡብ አሜሪካው ኪንዋ እና ማዕከላዊ አሜሪካ ውስጥ አዝቴክ የሚባል ሕዝብ የለት ማዕድ የሆነው አማራንዝ ከጥንት አንስቶ ሃገሮቻቸውን፣ ሕዝቦቻቸውን ለቅቀው ብዙ ርቀው አያውቁም፡፡

አሁን አሁን ግን የሰሜን አሜሪካ የገበያዎች መደርደሪያዎች ላይ እነርሱን ማየት እየተዘወተረ የመጣ ይመስላል፡፡

የቪኦኤው ሪፖርተር ታም ባንስ እንደዘገበው እንግዲህ ጤፍም የኢትዮጵዊያንና የኤርትራዊያን ብቻ ምግብ መሆኑ ታሪክ ሊሆን ነው፡

አይኔ አያየ እዚህ ዉስጥ አልገባም – መሠረት ሙሌ (ኤፍሬም ማዴቦ ከአርበኞች መንደር)

$
0
0

oo
መብራቱን አጥፍቼዉ አልጋዬ ላይ የወጣሁት በግዜ ነዉ። አለወትሮዬ እንቅልፍ የሚባል ነገር በአይኔ አልዞር ብሎኝ ከጨለማዉ ጋር ፊት ለፊት ተፋጥጠናል። የነፋስ ሸዉታ እንኳን የማይሰማበት ደረቅ ሌሊት ነዉ። ጨላማዉ አይን ይበሳል። እቤቱ ዉስጥ ያለዉ ሰዉ ሁሉ ተኝቷል። ቀኑን በሠላም ላዋለኝ አምላክ ምስጋና ሰጥቼ ሌሊቱንም አደራ ብዬዉ ፀሎቴን ጨረስኩ። ያ ምቀኛ እንቅልፍ ግን አሁንም እንደከዳኝ ነዉ። ትንሿ አልጋዬ ላይ ግራ ቀኝ እያልኩ ተገለባበጥኩ። እንቅልፍ ተጎትቶ የሚመጣ ይመስል አሁንም አሁንም ላይ ታች እያልኩ አልጋዉ ላይ እራሴን ጎተትኩት . . . እንኳን እንቅልፍ ሊወስደኝ ጭራሽ አይኖቼ መርገብገባቸዉን ያቆሙ ይመስል ቀጥ ብለዉ ቀሩ። ከተጋደምኩበት ብድግ ብዬ መብራቱን አበራሁና ለመንገድ ከያዝኳቸዉ ሁለት መጻህፍት አንዱን አዉጥቼ ማንበብ ጀመርኩ። እኔ ላንብበዉ ወይ መጽሀፉ ያንብበኝ አላዉቅም። ጧት ስነሳ ግን “The Architecture of Democracy” የሚል መጽሐፍ ደረቴ ላይ ተለጥፎ ነበር። ሰዐቴን ሳየዉ ከሌሊቱ ስምንት ሰዐት ተኩል ይላል። ከአልጋዬ ላይ ዘልዬ ወረድኩና ሰዉነቴን ታጥቤ ልብሴን ከለበስኩ በኋላ መኪናዉ ዉስጥ ገብቼ “I’m ready” አልኩ። የመኪናችን መብራት ጨለማዉን እየገላለጠዉ የአስመራ ከረንን መንገድ ተያያዝነዉ። መኪናዉ ዉስጥ ከገባሁ በኋላ እንደገና አፌን የከፈትኩት ባሬንቱ ደርሰን ቁርስ ሳዝ ነዉ። ባሬንቱ በግዜ መድረሳችን ደስ ቢለኝም የቀረን መንገድ ርዝመት ታየኝና ቁርስ መብላቴን ትቼ . . . በሰዐት ይህን ያክል ብንጓዝ እያልኩ ዋናዉ ጉዳያችን ቦታ የምንደርስበትን ሰዐት ማስላት ጀመርኩ። የስሌቱ ዉጤት ከሦስት ሰዐት ሲበልጥብኝ ተናደድኩ። ቀሪዉ መንገድ ገና ሳልጀምረዉ ሰለቸኝ። በተፈጥሮዬ መንገድና መኃላ ሲረዝም አልወድም።
ተሰነይ ስንደርስ መኪናዉ ዉስጥ የነበረዉ ሰዉ ሁሉ ቡና ካልጠጣሁ አለ። መኪናችንን አቁመን በቁማችን ቡናችንን ፉት አድርገን መንገዳችንን ተያያዝነዉ። እሁድ ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓም አርበኞች ግንቦት ሰባትን የፈጠሩት ሁለት ድርጅቶች ከተዋሃዱ በኋላ ለሁለተኛ ግዜ የሰለጠኑ ታጋይ አርበኞች የሚመረቁበት ቀን ነበር። ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነቱን የምርቃት ዜና የምሰማዉ በኢሳት ሬዲዮና ቴሌቭዥን ብቻ ስለነበር እቦታዉ ደርሼ የምረቃዉን ስነስርዐት ለማየት የነበረኝ ጉጉት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነበር። የምሳ ሰዐት ከመድረሱ በፊት በቀኝ በኩል ዋናዉን መንገድ ለቅቀን ዉስጥ ዉስጡን ወደ ምርቃቱ ቦታ የሚወስደዉን ኮረኮንች መንገድ ተያያዝነዉ።

ግቢዉ ዉስጥ ያለዉ ጥድፊያና ግርግር አንድ ትልቅ ዝግጅት መኖሩን በግልጽ ይናገራል። የተለያየ ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱና መሳሪያ የተሸከሙ አርበኞች ግቢዉን ሞልተዉታል። ያነገቱትን ጠመንጃ ስመለከት ቆራጥነታቸዉ ታየኝ። በቀጭኑ ተጎንጉኖ ማጅራታቸዉ ላይ የወደቀዉን ፀጉራቸዉን ሳይ ቴዎድሮስና ዮሐንስ ትዝ አሉኝ። ፈገግታ በፈገግታ የሆነዉን ፊታቸዉን ስመለከት ደግሞ የእናት አገሬ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ደጃፍ ላይ መሆኑ ታየኝና የኔም ፊት እንደነሱ በፈገግታ ተሞላ። ተራ በተራ እየመጡ “ጋሼ አፍሬም” እንደኳን ደህና መጣህ ብለዉ ሲጠመጠሙብኝ በአንዱ ትከሻዬ ፍቅራቸዉ በሌላዉ ጀግንነታቸዉ ዘልቆ ሰዉነቴ ዉስጥ ገባ። ጥንካሬያቸዉ በጅማቴ ፍቅራቸዉ በደም ስሬ ዘለቀ። እኔነቴ ሲታደስና በአገሬ ላይ ያለኝ ተስፋ ሲለመልም ተሰማኝና ደስ አለኝ። አዎ ደስ አለኝ . . . እየመጣ የሚሄድ ግዜያዊ ደስታ ሳይሆን የዉስጥ አካላቴን የዳሰሰ ዘላቂ የመንፈስ ደስታ ተሰማኝ። በጣም ደስ የሚልና በአሁኖቹ ቋንቋ “የሚመች” ቀን ነበር። የዕለቱን ዝግጅት ለማየት መቸኮሌን ያወቁት እግሮቼ የምረቃዉ በዐል ወደሚከበርበት ዳስ- ፍትህ፤ ነጻነትና እኩልነት የናፈቀዉ ልቤ ደግሞ ወደ ወደፊቷ ኢትዮጵያ ይዘዉኝ ጭልጥ አሉ፡ . . . ለካስ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ሩቅ አይደለችም።

“ማነዉ ሚለየዉ . . .ሚለየዉ፤ ይህም ትዉልድ ፍም እሳት ነዉ” የሚለዉን የጃሉድ ዘፈን በርቀት ሲሰማ በቀኑና በዘፈኑ መግጠም ተገረምኩ። “እዉነትም ይህ ትዉልድ ፍም እሳት ነዉ” እያልኩ በለሆሳስ ለራሴ እየነገርኩት ዳሱ ዉስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ። እርግጠኛ ነኝ ይህንን ጽሁፍ የሚያነብ ሰዉ ዳሱ ዉስጥ የነበረዉን ፍጹም ኢትዮጵያዊ የሆነ የጀግንነት፤ የቆራጥነት፤ የእልህና የመተማመን ልዩ ስሜት መረዳት የሚችለዉ እኔ በዚህ ባልተባ ብዕሬ ስገልጸዉ ሳይሆን እንዳዉ በደፈናዉ ዳሱ እራሱ ኢትዮጵያዊ ነበር ብዬ ባልፈዉ ነዉ።

አገራችን ኢትዮጵያ ከራሱ ምቾትና የተደላደለ ኑሮ ይልቅ የወገኖቹ መብትና ነጻነት የሚያንገበግበዉና እራሱን ለፍትህ፤ ለአንድነትና ለነጻነት ለመሰዋት ዝግጁ የሆነ የየዘመኑ ምርጥ ትዉልድ አላት። ይህንን የኛን ዘመን ምርጥ ትዉልድ ነዉ አርቲስት ጃሉድ “ይህም ትዉልድ ፍም እሳት ነዉ” ብሎ በጣፋጭ ዜማዉ ያወደሰዉ። እኔ ጥርጥርም የለኝ ይህ ትዉልድ አንድና ሁለት ብቻ ሳይሆን ለቁጥር የሚታክቱ ብዙ ፍም እሳቶች አሉት። ችግሩ የእሳት ነገር አዚህ ቤት ነደዳ እዚያም ቤት ነደደ ስራዉ ማቃጠል ነዉና አንዱን እሳት ከሌላዉ እሳት መለየት አስቸጋሪ ነዉ። እኔም ችግሬ እዚህ ላይ ነዉ። ፊት ለፊቴ ላይ ቁጭ ብለዉ ስለማያቸዉ ፍም እሳቶች (ጀግኖች) ላወራችሁ እየፈለኩ ምርጫዉ አዋጅ ሆነብኝ. . . የራሱ ጉዳይ ብዬ አንዱን ጀግና መረጥኩ። ይህንን ዛሬ የምተርክላችሁን ጀግና ስመርጥ ግን እንዳዉ በደፈና አልነበረም። ጉዳይ አለኝ . . . . ጉዳዩ አንዲህ ነዉ።

በዕለቱ በተመራቂ አርበኞች ተዘጋጅተዉ ከቀሩቡት የተለያዩ የኪነት ስራዎች ዉስጥ አንዱ የድራማ ዝግጅት ነበር። ሦስት የተለያዩ ድራማዎች መታየታቸዉ ትዝ ይለኛል። ዳሱ ዉስጥ የተሰበሰበዉን በብዙ መቶዎች የሚቆጠር ሰዉ ስሜት የኮረኮረዉና የእያንዳንዱን ሰዉ የልብ ትርታ ሰቅዞ የያዘዉ ግን በእዉነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተከወነዉ የመጨረሻዉ ድራማ ነበር። ድራማዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለይ ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ናችሁ እየተባለ በየቀኑ በህወሃት የደህንነት ሠራተኞች እጃቸዉ እየታሰረ በየወንዙና በየፈፋዉ በግፍ እየተገደሉ ስለሚጣሉ ኢትዮጵያዉያን የሚተርክ ድራማ ነበር።

ድራማዉ “ኮሜዲ” የሚባል ክፍል የለዉም። ተጀምሮ እስኪያልቅ “ትራጄዲ” ብቻ ነዉ። ያሳዝናል፤ ያስቆጣል፤ ያስቆጫል፤ያንገበግባል፤ አንጀት ያቆስላል፤ ልብ ያነድዳል . . . ወይ ነዶ ያሰኛል ። እኔማ እንኳን ትራጄዲ አይቼ በተፈጥሮዬ ሆደ ቡቡ ነኝና በደል ስመለከት ማዘን ልማዴ ሆኖ አምባዬ መፍሰስ የጀመረዉ ገና ድራማዉ ሲጀምር ነበር። በተለይ አናታቸዉ እየተደበደበ የሚቀበሩበትን ጉድጓድ በግድ እንዲቆፍሩ የተደረጉትን ሁለት ወጣት ወገኖቼን ሳይ ሆዴ ባባ፤ አንጀቴም ቆሰለ። ልቤ ዉሰጥ የነደደዉ እሳት ትንታጉ እየተንቦገቦገ ወጥቶ የዉጭ ሰዉነቴን ጭምር ለበለበዉ። ለወትሮዉ ነገር ማመዛዘን የሚቀድመዉ አዕምሮዬ በቀል በቀል አሰኘዉ። የነደደዉ ልቤም ለበቀል አደባ። ጉድጓዱ ተቆፍሮ ካለቀ በኋላ የደህንነት ሠራተኛዉ AK ጠመንጃዉን አንደኛዉ ወጣት አገጭ ላይ ቀስሮ በአፈሙዙ አንገቱን ቀና እንዲያደርግ እያስገደደዉ . . . “አየኸዉ የምትገባበትን ጉድጓድ” እያለ ወጣቱ ወገኔ ላይ ሲሳልቅበት ሰማሁና በሀይወቴ ለመጀመሪያ ግዜ ኢትዮጵያዊነቴን ጠላሁት። አጠገቡ የቆመዉና በቁሙ ሞቱን የሚጠባበቀዉ ሌላዉ ወጣት ወገኔ ደግሞ . . . ግደለኝ . . . ግደለኝ. . . ግደለኝ እንጂ! . . . ምን ትጠብቃለህ እያለ የጓደኛዉን ሞት በአይኑ ከሚያይ የራሱን ሞት የሚለምነዉን ቆራጥ ኢትዮጵያዊ ድምጽ ስሰማ ደግሞ 360 ዲግሪ ተገለበጥኩና ከደቂቃዎች በፊት የጠላሁትን ኢትዮጵያዊነት መልሼ ወድድ አደረኩት። የወያኔዉ ጨካኝ ነብሰ ገዳይ ፉከራና ቆራጡ ኢትዮጵያዊ ያደረጉት የቃላት ምልልስ እምባዬን ጎትቶ አመጣዉና ፊቴ እምባ በእምባ ሆነ። ያ ከግማሽ ሰዐት በፊት ሲጨፈርበትና ሲደነስበት የነበረዉ ዳስ ሰዉ የሌለበት ባዶ ቤት ይመስል ጭጭ አለ። እኔ ኤፍሬም ሰዉ አልገድልም፤ በእኔ እጅ የሰዉ ህይወት ይጠፋል ብዬ አስቤም አልሜም አላዉቅም። ያንን የህወሃት ቅጥረኛ በዚያች ሰዐት ባገኘዉ ኖሮ ግን ለመበቀል ሳይሆን ለሰዉ ልጅ ህይወት ክብር ስል እገድለዉ ነበር።

ድራማዉ እንዳለቀ ወደ ዉጭ ወጣሁና ድቅድቅ ጨለማ ዉስጥ ብቻዬን ቁጭ አልኩ። ሀሳብ. . . የትናንት ሀሳብ፤ የዛሬ ሃሳብ፤ የነገ ሀሳብ፤ የከረመ ሀሳብና ሁሉም ሀሳብ አንድ ላይ ተሰባስበዉ ወረሩኝ። ግራ ሲገባኝና መላቅጡ ሲጠፋኝ ግዜ ትንፋሼን ዋጥ አደረኩና አንቺ እማማ ብዬ አገሬን ተጣራሁ . . . አሁንም አሁንም ደግሜ ተጣራሁ። ህመሟ ብርቱ ነበርና አልሰማችኝም። አይዞሽ ይህ ቀን ያልፍና አንቺም ከህመምሽ እኔም ከማያባራዉ የሀሳብ በሽታ ድነን አዲስ ታሪክ እንጽፋለን ብዬ ከአገሬ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁና ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ዳሱ ዉስጥ ከነበሩት አርበኞች ጋር ተቀላቀልኩ። እለቱን ሲያስጨፍረን የዋለዉ አደራ ባንድ “ነይ ደኑን ጥሰሺ” የሚለዉን ቆየት ያለ የመሀሙድ አህመድ ዘፈን ሲጫወት ልጅነቴ ትዝ አለኝና ከፍም እሳቶች ጋር መደነስ ጀመርኩ።

ጭልጋን ይዞ፤ጋይንትን ይዞ፤ የጎበዞቹን ጎራ ጃናሞራን ይዞ፤ ደምቢያን ይዞ፤ ወልቃይት ጠገዴን ይዞ፤ ላይ አርማጭሆንና ታች አርማጭሆን ይዞ ወዘተ . . .ድፍን ጎንደር የጀግኖች አገር ነዉ። አዎ! ወልቃይት ጠገዴ ከጀግናም የጀግና አገር ነዉ።ወልቃይት ጠገዴ ጎንደሬ አይደለህም ተብሎ ከተነገረዉ ከሃያ አራት አመታት በኋላ ዛሬም ህልዉናዉን ለወያኔ ፋሺስቶች አላስረክብም ብሎ ጎንደሬነቱን ለማረጋገጥ ሽንጡን ገትሮ የሚዋጋ የጀግኖች አገር ነዉ። ጎንደር የአፄ ቴዎድሮስ፤ የእቴጌ ምንትዋብ፤ የፊትአዉራሪ ገብርዬ፤ የአየለ አባ ጓዴና የጄኔራል ነጋ ተገኝ አገር ናት። ጎንደር ኢትዮጵያ ከሌለች እኛ የለንም ብለዉ ሙሉ ህይወታቸዉን ለትግል የሰጡ እነ ታማኝ በየነንና እነ አርቲስት ሻምበል በላይነህን ያበቀለች አገር ናት። ወላድ በድባብ ትሂድ. . . የጎንደር ማህፀን ዛሬም አልነጠፈም።

ዛሬ ይዤላችሁ የመጣሁት ጀግና ተወልዶ ያደገዉ አማራ ክልል ጭልጋ ወረዳ ልዩ ስሟ ጫኮ በምትባል ቦታ ነዉ። የገበሬ ልጅ ነዉ፤ እሱም ምኞቱ ገበሬ መሆን ነዉ። የሚኖረዉ መተማ ከተማ ዉስጥ ነዉ። ስሙ መሠረት ሙሌ ይባላል። ፈገግታ የማይለየዉ ፊቱ የዋህነቱንና ገራገርነቱን አፍ አዉጥቶ ይናገራል። ሲናገር ረጋ ብሎ ነዉ። አተኩሮ ላየዉ ሰዉ አይነ አፋር ይመስላል፤ የቁርጥ ቀን ሲመጣ ግን እንደ መሠረት ሙሌ ደፋር ሰዉ የለም። አይኑ እፊቱ ላይ ቆሞ ከሚያናግረዉ ሰዉ አይን ጋር ሲጋጭ አንገቱን ይሰብራል። እቺ የሰዉ አይን የመሸሽ በሽታ ደግሞ አበሾች ስንባል የሁላችንም በሽታ ናት። ጠይም ፊቱ ላይ እንደ ችቦ የተተከሉት የመሠረት ሙሌ አይኖች የሰዉን ዉስጥ ዘልቀዉ የሚያዩ ይመስላሉ። ሰዉነቱ ደንዳና ቁመቱ መካከለኛ ነዉ። ልቡ ግን ትልቅ ነዉ። አዎ መሠረት ሙሌ ልቡ ትልቅ ነዉ።

ዕለቱ ሰኞ ነዉ – ሰኞ ሚያዝያ 26 ቀን 2007 ዓም። የህወሃት የደህንነት ሰዎች አንድ ኮሎኔልና ሌሎች አራት ሰዎች ተገድለዋል በሚል ድፍን መተማን እያመሷት ነዉ። እያንዳንዱ የመተማ ነዋሪ በግድያዉ የተሳተፈ ይመስል በአጠገባቸዉ ያለፈዉን ሁሉ ወንድ፤ ሴት፤ ወጣትና ሽማግሌ ሳይለዩ ሁሉንም እያስቆሙ አጥንት ዉስጥ ዘልቆ የሚገባ ስድብ ይሰድባሉ፤ ይደበድባሉ ያስራሉ። በሠላም አዉለኝ ብሎ በጧት የተነሳዉ መሠረት ሙሌ የእህል ወፍጮዉን አስነስቶ የዕለት ስራዉን ለመጀመር ጉድ ጉድ ማለት ጀምሯል። ሴቶች እህላቸዉን ያስመዝናሉ። ሸክም የተራገፈለት አህያ ያናፋል። ነጋዴዉ፤ ደላላዉ፤ ገበሬዉና ሸማቹ ዋጋ ቀንስ ዋጋ ጨምር እያሉ ይንጫጫሉ። መተማ መደበኛ ስራዋ ላይ ናት።

“ቁም . . . እጅ ወደ ላይ . . . እንዳትነቃነቅ” የሚል ድምጽ የደራዉን የመተማ ገበያ በአንድ ግዜ ጭጭ አሰኘዉ። መሳሪያ ያነገቡ ፖሊሶችና ሲቪል የለበሱ የደህንነት ሰራተኞች ከመኪና እየዘለሉ ወርደዉ መሠረትን የፊጥኝ አስረዉ መኪናዉ ላይ ወረወሩት። ምነዉ? ምን አጠፋሁ . . . ዬት ነዉ የምትወስዱኝ? አለ መሠረት በሁኔታዉ እጅግ በጣም ተደናግጦ። አንድ አጠገቡ የነበረዉ የህወሃት ነብሰ ገዳይ . . . ዝም በል ብሎ በጥፊ አጮለዉና ለአርበኞች ግንቦት 7 የመለመልካቸዉን ሰዎች አድራሻና ስም ዝርዝር ካላመጣህ ዕድሜህ ከአንድ ጀምበር አያልፍም አለዉ።

መኪናዉ ዉስጥ ከተቀመጡት ሁለት ሰዎች አንደኛዉ አንሂድ ብሎ በእጁ ምልክት ሲያሳይ መሬት ላይ የነበሩት ፖሊሶች እየዘለሉ መኪናዉ ላይ ወጡና መሠረትንና ሌሎች ሦስት እስረኞችን የያዘችዉ ቶዮታ ሂሉክስ መኪና ፍጥነት እየጨመረች የመተማ ሁመራን መንገድ ተያያዘቸዉ። በሚቀጥለዉ ቀን ጧት ሲነጋጋ ሁመራ ደረሱና አራቱ እስረኞች እጃቸዉ እንደታሰረ ፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ተደረገ። ከምሽቱ ሦስት ሰዐት ሲሆን መሠረትና ጓደኞቹ እጅ ለእጅ እንደተሳሰሩ ጉዞ ወደ ተከዜ ወንዝ ሆነ። የዚህች ከንቱ አለም የመጨረሻ ጉዟቸዉ ነበር።

ዶማና አካፋ ያዙ እንጂ . . . ደግሞም ፈጠን በሉ ግዜ የለንም. . . አለ የነብሰ ገዳዮቹ አለቃ። ከሁመራ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ተከዜ ወንዝ የሚያደርገዉ ጉዞ በህይወቱ የመጨረሻዉ ጉዞ እንደሆነ የተረዳዉ መሠረት . . . አንተዬ ልትገድሉን ነዉ እንዴ ብሎ ጠየቀ። ፊት ለፊቱ የነበረዉ ፖሊስ ከተቀመጠበት ዘልሎ ተነሳና . . .ዝም በል . . . አንተ የሴት ልጅ . . . ምን አስቸኮለህ ይልቅ የተጠየከዉን ጥያቄ መልስ አለዉና የያዘዉን የእጅ መከርቸሚያ ካቴና ፊቱ ላይ ወረወረበት። ካቴናዉ ሳይሆን ከዚያ ባለጌ አፍ የወጡት ቃላት ጅማቶቹ ድረስ ዘልቀዉ ገብተዉ መንፈሱን ጎዱትና መሠረት ለመጀመሪያ ግዜ ተስፋ ቆረጦ . . . ምንም የምሰጥህ መልስ የለኝም አለና አንገቱን ደፋ። . . . አንቺ ወላዲት አምላክ ምነዉ . . . ምን አደረኩሽ ብሎ ቀና ሲል እሱንና ሦስት ጓደኞቹን ለመዋጥ አፋቸዉን ከፍተዉ የሚጠባበቁትን አራት ጉድጓዶች ተመለከተ። አይኔ እያየ እዚህ ወስጥ አልገባም ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ተከታታይ የጥይት ድምጽ ሰማ። ዞር ሲል ፖሊሶች አብረዉት ከታሰሩት ሦስት እስረኞች ዉስጥ አንዱን በእግራቸዉ እየገፉ የተቆፈረዉ ጉድጓድ ዉስጥ ሲጨምሩት አየ። ደቂቃዎች የቀሩት የሱ የራሱ ህይወት ሳይሆን በህወሃት ነብሰ ገዳዮች በግፍ የተገደለዉ የጓደኛዉ ህይወት አንገበገበዉ። አዘነ – በአይኑም በሆደም አነባ። “አይኔ እያየ እዚህ ወስጥ አልገባም” ብሎ የተናገረዉ የራሱ ድምጽ ጆሮዉ ላይ አቃጨለበት። መሠረት ሞት ፈርቶ አያዉቅም፤ ግን ህይወቱ የህይወትን ክቡርነት በማይረዱ ባለጌዎች እጅ እንድታልፍ አልፈለገም። ያ የንጹሃን ኢትዮጵያዉያንን ሰዉነት ማፍረስ የለመደዉ የህወሃት ጠመንጃ ወደሱ ከመዞሩ በፊት አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ብሎ ወሰነ። እጁ ከጓደኛዉ ጋር የታሰረበትን ገመድ በጥርሱ በጣጠሰዉና ከቀለሁ እንደተላቀቀ ጥይት ተወርዉሮ እግሬ አዉጭኝ ብሎ ጫካ ዉስጥ ዘልሎ ገባ። የህወሃት ነብሰ ገዳዮች የጥይት ናዳ ለቀቁበት፤ እሱ ግን ጫካ ጫካዉን ይዞ ወደማያዉቀዉ ቦታ ሩጫዉን ተያያዘዉ።

መሠረት- ቆራጥነቱና የልቡ ትልቅነት ጉልበት እየሆኑት ነዉ እንጂ ያ የሚጠላዉ የህወሃት ጥይት አካሉን በሳስቶ ወንፊት አድርጎታል። ሰዉነቱ ቁስል በቁስል ሆኗል። ከራሱ ሰዉነት እንደ ጎርፍ የሚፈስሰዉ ደም ጠልፎ የሚጥለዉ እስኪመስለዉ ድረስ አካሉ ደምቷል። ሩጫዉን ግን አላቆመም። ደም እንዳይፈሰዉ ጥይት የበሳዉን ቦታ ሁሉ በሁለት እጆቹ ሸፈነ። እንደኛዉ ቁስል ጋብ ሲልለት እጁን ከሱ ላይ እያነሳ ሌላዉን ቁስል ሸፈነ። ደሙ መፍሰሱን ግን አላቆመም። መሠረትም ሩጫዉን አላቆመም። መሠረት ሙሌ ህይወቱን ለማዳን ወደ ፊት የህወሃት ነብሰ ገዳዮች ደግሞ ወንጀላቸዉን ለመደበቅ ወደኋላ በተለያየ አቅጣጫ ሩጫቸዉን ተያያዙት። ሁለቱም አግሬ አዉጭኝ አሉ።

መሠረት ሞትን እየሸሸ መሆኑን ነዉ እንጂ ከሞት ለመራቁ ምንም ዋስትና አልነበረዉም። ደግሞም መሮጡን ብቻ ነዉ እንጂ ወዴት እንደሚሮጥ አያዉቅም ነበር። ከኋላዉ የሚከተለዉ ማንም ሰዉ እንደሌለ ቢረዳም ከፊት ለፊቱ ህይወቱን የሚታደግለት ሰዉ እስኪያገኝ ድረስ ሩጫዉን ቀጠለ። ጧት ጎህ ከመቅደዱ በፊት “ጠጠዉ በል” የሚል ድምጽ ሲሰማ ያ ሁሉ ሩጫዉ መልሶ ሞት ዉስጥ የከተተዉ መሰለዉና ደነገጠ። ሩጫዉን እንዳይቀጥል ቁም ያሉት ሰዎች ከበዉታል። እሺ ብሎ እንዳይቆም ሞትን አልቀበልም ያለዉ ልቡ አሁንም እንደደነደነ ነዉ። ትንፋሹን ሰበሰበና. . . ማናችሁ እናንተ ብሎ ያቆሙትን ሰዎች ጥያቄ ጠይቆ መልሱን ሳይሰማ ተዝልፍለፎ መሬቱ ላይ በግንባሩ ተደፋ።

የኤርትራ ድንበር ጠባቂ ወታደሮች መሠረትን አንድ ወር ሙሉ በህክምና ሲንከባከቡት ቆዩና እሱ እራሱ በጠየቃቸዉ መሠረት ሃሬና ወስደዉ ለአርበኞች ግንቦት 7 አስረከቡት። መሠረት ሙሌ ጥቅምት 7 ቀን ከተመረቁት አርበኞች ዉስጥ አንዱ ነዉ። ለዚህ ጀግና ያቀረብኩለት የመጨረሻ ጥያቄ . . . ሊገድሉህ የነበሩትን የህወሃት ሰዎች አሁን ብታገኛቸዉ ምን ታደርጋቸዋለህ የሚል ጥያቄ ነበር። ነጻ አወጣቸዋለኋ! አለኝና ጭፈራዉ ዉስጥ ዘልሎ ገባ። አርግጠኛ ነኝ መሠረት ሙሌ አንድ ቀን ሁላችንንም ሸገር ላይ ያስጨፍረናል። ቸር ይግጠመን።

ኤፍሬም ነኝ ከአርበኞች መንደር
ebini23@yahoo.com

Viewing all 212 articles
Browse latest View live