Quantcast
Channel: Kalkidan Amharic – Kal Tube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 212

አቶ አባይ ፀሐዬ በኦሮሚያ የተከሰተውን ሕዝባዊ ተቃውሞ የኦህዴድ ባለስልጣናት የቀሰቀሱት ነው አሉ

$
0
0

በሚንስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ ፀሐዬ ባለፉት ሦስት ወራት በኦሮሚያ የተከሰተውን ሕዝባዊ ተቃውሞ የኦህዴድ ባለስልጣናት የቀሰቀሱት ነው አሉ።
የመንግስት ደጋፊ ለሆነው ድህረ ገጽ ለሆርን አፌይርስ በሰጡት ቃለምልልስ ለሁለተኛ ግዜ “ልክ እናስገባቸዋለን ” ያሉበትን ድምጻቸውን የኔ አይደለም በማለት ያስተባበሉ ሲሆን የዘረፉት ያስዘረፉት ጥቂት ነጋዴዎችና የኦሮሚያ ባለስልጣናት ናቸው ያፈናቀሉት ህዝቡን ካሣ ስጡት ተበለው ካሣውን የበሉት እነሱ ናቸው፡፡ እነሱ እንዳይጠየቁ ባንድ በኩል ማስተር ፕላን ነው ይባላል፡፡ በሌላ በኩል ህወሓት ነው ፌዴራል መንግስት ነው፡፡ የማይመለከተው እጁ የሌለበት አካል እዚህ ጉዳይ ላይ ተጠያቂ ሊያደርጉ፡፡ ተጠያቂዎቹ ሌላ ሰው ተጠያቂ እያደረጉ ነው ያሉት፡፡ ሲሉ እጃቸውን ወደኦህዴድ ባለስልጣናት ቀስረዋል።
በቃለምልልሱ ላይ የኦሮሚያ ባለስልጣናት ናቸው የህዝቡ በዳዮች ያሉ ሲሆን የተበደለው ህዝብ ላይ ጦር ለምን እንዳዘመቱበት፣ከ150 በላይ ሰለመገደሉ፣ብዙ ሺህዎች ስለመታሰራቸውና ስለመቁሰላቸው ጋዜጠኛውም አልጠየቅም እሳቸውም አላነሱም።ቃለምልልሱን ሊንኩን ተጭነው ይመልከቱ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 212