Quantcast
Channel: Kalkidan Amharic – Kal Tube
Viewing all articles
Browse latest Browse all 212

የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በኬንያ 28 የኦሮሞ ጥገኝነት ጠያቂዎችን መብት እንዲከበር ጠየቀ-VOA Amharic

$
0
0

ሰሜን ኬንያ ውስጥ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ያሉ ጥገኝነት ፈላጊ ኢትዮጵያዊያን መብታቸው እንዲከበር ኬንያ የሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ቅርንጫፍ ጠየቀ። ሐሙስ ፍርድ ቤት ሊቀርብ የነበረውን 28 ጥገኝነት ጠያቂ ኦሮሞዎችን ጉዳይ የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር – UNHCR የኬንያ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ጣልቃ በመግባት ጉዳያቸው በጥልቀት እንዲታይ እና ለአንድ ሣምንት እንዲራዘም መጠየቁን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ዱክ ምዋንቻ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በኬንያ 25 ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፋ ሰጥታለች የሚለውንም ዜና የኬንያ መንግሥት አስተባብሏል።
UNHCR ባወጣው መግለጫ፣ ቁጥራቸው 28 የሚደርስ የኦሮሞ ተማሪዎች በሰሜን ኬንያ ማርሳቢት አካባቢ ታስረው እንደሚገኙ ገልጿል።
ተማሪዎቹ ወደ ኬንያ ተሰደው ጥገኝነት ለመጠየቅ ሲጠባበቁ የኬንያ ፖሊስ ወደ ኢትዮጵያ መልሶ ለማባረር በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸዉ ታውቋል። በዚህም መሰረት የዓለም አቀፋ የስደተኞች ድርጅት ጣልቃ ገብቶ ጉዳያቸዉን ለፍርድ ቤት ለማቅረብ የሳምንት ጊዜ እንዲሰጠዉ የኬንያን መንግስት መጠየቁን ቃል አቀባዩ ዱክ ምዋንቻ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
“ይህንን ጉዳይ ለሳምንት እንዲቆይ ጠይቀናል። ምክንያቱም ጉዳዩን በጥልቀት እንድናይ፣ የህግ ባለሞያዎቻችንም ለጥገኝነት ፈላጊዎቹ እንድንልክ ግዜ ለማግኘት ነዉ” ብለዋል።
አክለውም፣ “ስደተኞችን በእንደዚህ አይነት ቦታ ተክተው ለመብታቸዉ የሚቆሞም የስደተኞች አካል በኬንያ ወይም እንደ(Refugee Consortium of Kenya) በመባል የሚታወቁ ድርጅቶችን ወደ ቦታው እንልካለን” በማለት መልስ ለቪኦኤ ሰጥተዋል።
ባለፈዉ ሳምንት ኬንያ ስደተኞችን ለኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን አሳልፋ ሰጠች የተባለዉንም ጉዳይ ለኬንያ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ (Department of Refugee Affairs/DRA) ጥያቄ ያቀረበው ቪኦኤ የናይሮቢ ቢሮ ቃል አቀባይ ስታንሊ ኛሌ ስለ ጉዳዩ ለጊዜዉ አስታያየት መስጠት አልችልም ብለዋል። ነገር ግን ቢሮው ናይሮቢ ላለው የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ኬንያ ስደተኞችን አልመለሰችም በማለት አስተባብለዋል ።
“ለመንግስት ባለስልጣናት ስለዚህ ሁኔታ አንስተንላቸዉ ነበር ነገር ግን አስተባብለዋል። እኛ ደግሞ የምንመሰረተው ከመንግስት በምናገኘዉ መረጃ ነዉ በቂ መሳርያ በሁሉም የሃገሪቱ ቦታዎች ስላላቸው። ይህንን ጉዳይ በትክክል ‘ይህ ነው’ ማለት ባንችልም እውነቱ ጋር ለመድረስ በራሳችን በኩል ጥናት እያደረግን ነው። ከመንግስት ያገኘነው መረጃ ግን ይህ ነገር በርግጥ አለመከሰቱን ነው። በአሁኑ ግዜ በእጃችን ያለዉ መረጃ በማርሳቢት አካባቢ ታስረዉ ስላሉት 28 የኦሮሞ ወጣቶች ነው። የእነርሱንም ጉዳይ ለመከታተል የአንድ ሳምንት ጊዜ ጠይቀናል” ብለዋል።
በቁጥጥር ይገኛሉ ስለተባሉ የኦሮሞ ስደተኞች ለናይሮቢዉ ኦሮሞ ማህበረሰብ መሪ ለአቶ ሸጋ አረዶ ጥያቄ ያቀረበው ቪኦኤ እስካሁን የጥገኝነት ጠያቂዎችን ማንነትም ሆነ ያሉበትን ሁኔታ ምንም አናውቅም ብለዋል። በፊት ተያዙ የተባሉት 41 ጥገኝነት ፈላጊዎች አሁን 28 ብቻ ናቸዉ የተገኙት ብለን ስንጠይቃቸው በአካባቢው በቂ ለሰብአዊ መብት የሚቆሙ ድርጅቶች ባለመኖራቸው እንደሌሎቹ ሊመልሷቸዉ ይችላሉ በማለት ለቪኦኤ ተናግረዋል።
በተጨማሪም አቶ ሸጋ በማርሳቢት አካባቢ በተለይ በኦሮሞ ጥገኝነት ፈላጊዎች ላይ እየደረሰ ነዉ ያሉትን የሰባዓዊ መብት ረገጣ የዓለም ዓቀፉ ህብረተሰብና ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች መፍትሔ እንዲፈልጉ ተማጽነዋል።
የአሜርካ ድምጽ ዘጋቢ ገልሞ ዳዊት ከናይሮቢ የላከውን ዘገባ ያዳምጡ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 212

Trending Articles